Neueste Beiträge von ኤዞፕ መጻሕፍት (@azop78) auf Telegram

ኤዞፕ መጻሕፍት Telegram-Beiträge

ኤዞፕ መጻሕፍት
ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
8,884 Abonnenten
9,064 Fotos
26 Videos
Zuletzt aktualisiert 06.03.2025 09:30

Ähnliche Kanäle

Asfaw abreha
9,876 Abonnenten
Ethiopian Law
6,578 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von ኤዞፕ መጻሕፍት auf Telegram geteilt wurde.

ኤዞፕ መጻሕፍት

28 Jan, 07:18

919

#ከጣምራ ጦር የተወሠደ

በጠላት ጥይት የቆሰለ ጓደኛው “ግደለኝ ' ጨርሰኝ…”
እያለ የሚያስቸግረው ሰው ፣ ዙሪያው በጠላት ተከቦ ማምለጫ መንገድ ያጣ ወታደር ምን ያደርጋል ?

በጠላት መድፍ እተደበደበች ከተማ ውስጥ የነበሩት
ቤተሰቦቹ በሕይወት መኖራቸውን ፡ ካሉም የደረሱበትን
የማያውቅ ሰው ምን ይሰማዋል ?

በብዙ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ካለው የወገን ጦር ጋር
ለመገናኘት ሳይችል ቀርቶ ፡ ውሃ ጥሙና ርሃቡ እያሰቃየው
በጠላት እየታደነ በረሃ ለበረሃ የሚንከራተት ወታደርስ ?

መጽሐፍዋ ቆራጥነትን ፡ ብልሃትን ፡ ትዕግስትን ' ጀግ
ንነትን ... በሚጠይቀው በዚህ አስቸጋሪ ስፍራ ፡ ሁኔታና
ጊዜ ውስጥ የነበሩት ገፀባህሪያት የተጫወቱትን ሚናና የደረሱበትን ግብ ታሳያለች ።

📖ጣምራ ጦር
📖ስደተኛው
📖ዕንባና ሳቅ

ገበየሁ አየለ
ኤዞፕ መጻሕፍት

28 Jan, 07:14

892

አዲስ ግጥም በገበያ ላይ

#የባካኙ_ምልጃ

እግዚኦ ለሰው ልጅ - አቤት ለፍጥረቱ
ሥራውን ሳይጨርስ....
እንዴት ዳናው ጠፋ? - ጠቢብ መለኮቱ
ይኽ ኹሉ ምስቅልቅል - ይኽ ኹሉ ዝብርቅርቅ
አይታይም እንዴ? - ለመለኮት ከሩቅ?
ሰማይ ቤት የለውም? - ለማየት አሻግሮ
መስኮት አላበጀም? - እልፍኙን ሸንቁሮ

ምንድን ነው ማምታታት - የአዳኝ ገዳይ በዛ
ከጊዜ ሰንበሌጥ...
ዘለዕለት ይረግፋል - ዘለዕለት ይጠላል - ፍጥረት እንደ ጤዛ።
ከገዳይ አድኖ - ያዳኑትን መግደል
የሰው ልጅ ባሕሪ...
ከዓርብ እስከ ዓርብ ድፍርስ - አይጠራም ቢጠጠል።
ለወንዝ ጊዜ አለው - ለመንጻት ደፍርሶ
በሰው ልጆች እልፍኝ...
ተቃቅፈው ያድራሉ - ዕልልታና ለቅሶ።
የሰው ልጅ ግራ ቀኝ - ሕጉ ጉራማይሌ
በእሱ የጠላውን - ያውጃል በሎሌ።

ሥራውን ሳይጨርስ - አምላክ ከየት ጠፋ?
ጀምሮ የተወው...
የሰው ልጅ ባሕሪ - ለራሱ ሲከፋ።

አምላክ ወደየት ነህ...
"ና" ጅምርህ ይቋጭ - ይፈፀም የሰው ልጅ
አውሬና መለኮት....
አያድሩም በአንድ ልብ - አይኖሩም በአንድ ደጅ።

༺❀༻


ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ የከተማችን ፈርጥ ቤተ መጽሐፍት። በምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው የአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ/ን ህንፃ አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው !!
ስልክ:- 09 11 72 36 56

ለማዘዝ
@Mesay21
@Mesay21
ኤዞፕ መጻሕፍት

26 Jan, 13:19

395

የዶ/ር መስከረም ለቺሣ ሁለት ድንቅ መፅሐፎችን

#የፀሐይ_ከተማ

በመጽሓፉ ውስጥ የተብራሩ ጉዳዮች፡

~ ጣልያናዋው ቶማሶ ካምፓኔላ፦ “የፀሓይ ከተማ” የሚላት ማንን ነው?

~ አክሱማውያን ምን ዓይነት ሕዝቦች ነበሩ?

~ የ16ኛው ክፍለ ዘመን የጣልያን ኅዳሴ ምስቅልቅሎች፤

~ የአክሱም ሥልጣኔ፦ በጣልያን ኅዳሴ ያበረከተው አስተዋጽኦ፤

~ ሴትነት፣ ድንግልና፣ ወንድነት፣ ጀግንነት... በአክሱማውያን አይታ፤

~የባቢሎንና የጽዮን ፍጥጫ፦ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፤

~ ደቀቀ አስጠፋኖስ አነማን ናቸው?

~ “ሪፐብለክ” ምንድን ነው?

~ የኢየሱሳውያን (Jesuits) ተልዕኮ፦ በዘመናዋው ዓለም፤ አና ሌሎችም 
``````````
(ኢ)ዩቶፕያ

ከመጽሓፉ የተወሰደ

...ባላባቶቹና ባለሥልጣናቱ፡ ብፁዓን የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ፡ ቀድሞ መሬቱ የሚያስገኝላቸው የኪራይ ክፍያ አላረካ እያላቸው፡ የማይኾን ውሳኔ በሕዝቡ ላይ ወስነው ሕዝቡን ይጎዳሉ። እነርሱ ያለችግር ስለሚኖሩ ለሕዝቡ
ደኅና ነገር መሥራት እንደሚገባቸው እንኳ አያስቡም። የእርሻን ሂደት ያስቆማሉ፤ አብያተ ክርስቲያናትን ብቻ እያስቀሩ፡ ቤቶችንና ትናንሽ ከተሞችን ያፈርሳሉ...

**

ለዚህም እንደሽፋን የተጠቀሙት ማሞኛ፡ _ ይኽን ባዕድ አምልኮ፡ “Secularism” ወይም “ዓለማዊነት” የሚል ስም ሰጥተው፡ “ከሃይማኖት ነጻ ነው” በሚል እንዲታይ ማድረግን ነው። በዚያ ረገድም ተሳክቶላቸዋል።

***

ኢትዮጵያውያን ግን፡ እንደአገርና እንደሕዝብ፡ ላለፉት በርካታ ክፍለ-ዘመናትና አኹንም እየደረሰብን ያለው ፈተና፡...ከዚሁ፡ ከ“ቄሱ ንጉሥ” ዘመን ጀምሮ፡ እስካኹን ድረስ የቀጠለው የመልካም ሕይወት (ዩቶፕያን
የመጠበቅና የመመከት፥ አልያም፡ የመነጠቅና በከሓዲነትም የማስነጠቅ ውጥረት ጋራ በቀጥታ የተያያዘ መኾኑን፡ በበቂ ኹኔታ አልተገነዘብነውም።
ኤዞፕ መጻሕፍት

26 Jan, 12:27

422

የለበሰችው ጃኬትና ሱሪ ወንድ ቢያስመስላትም ረጂም ፀጉሯ ሴትነቷን ይናገራል፡፡ በድንገት ትከሻዋን ሰው ነካት፣ በፍጥነት ዞር አለች፡፡

“መፋቂያሽ ከየት ተላከልሽ? አላት እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ፡፡ ደንገጥ ብላ እጇን ከኪሳ አወጣችና፣

       ከጃማይካ ብላ ጨበጠችው፡፡

                  ***

አልጋዋ ላይ ተጋደመች፡ ደግሞ በደረቷ ተኝታ ትራሱን ጭንቅላታ ላይ ጫነች። መረጋጋት ግን አቃታት፡ የሆነው ሁሉ ሊሆን የሚችል መሆኑን ብትቀበልም፣
መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ብትሆንም ለእንዲህ ዓይነት የሃዘን ስሜት ግን ዝግጁ አልነበረችም፡፡ የሚመጣውን ሁሉ በቀላሉ የምትቀበል ይመስላት ነበር፣ ልትቀበለው ግን አልቻለችም። በላይሁን ከአይኖቿ አልሰወር አላት፡ አስቻለውን አስታወሰችው እናቱንም አሰበቻቸው፡፡ ቅዱስ አብሯት እንዲሆን ፈለገች፡ አጠገቧ ሆኖ አይዞሽ እንዲላት ያለመስዋዕትነት ድል የለም!” ብሎ እንዲያበረታታት ተመኘች፡፡ አንተነህ ግጥሞቹን እንዲያነብላት፡ የትግል ታሪኮችን እንዲነግራት… ሀሳቧ ትርምስምስ አለባት። ጋዲሳና ዘርዓይ ከሀሳቧ አልጠፋ አሏት፡ ይህን ጊዜ የት ይሆኑ? ምንስ እያደረጉ ይሆን? ጥያቄዎቹ ሰላም አልሰጥ አሏት። ትራሱን ወረወረችና ተነሳች፡ ፊቷን ጠራረገችና ሰዓቷን ተመለከተች፡፡ ወደነበላይሁን ቤት ለመሄድ ራመድ ስትል
           ምን ብላ እንደምታጽናናቸው ጨነቃት፡፡

             ****

"ለአገር መሥራት በፖለቲካ ብቻ ነው ያለው ማነው? በሕይወታችን እያንዳንዱ ቀን
አንድ በጎ ነገር ማበርከት መቻል ላገር መሥራት ነው!"
             * *
ቢያንስ በሙያችን ለዓላማ የምንኖር መሆን አለብን። ለሕዝብ አስቦ ሕይወቱን የሰዋ ትውልድ አካል በመሆናችን ፖለቲካው ባይሳካልንም በሙያችን የጓዶቻችንን ዓላማ ተከትለን ለህዝብ አገልጋይ መሆን ከቻልን ባለዕዳነታችንን ከሕይወት መስዋእትነት በመመለስ ለመክፈል እንችላለን

    📖📖 ምርኮኛ
    ቅንጅት ብርሃኑ
ወደው የሚያኑቡት ድንቅ መፅሐፍ
ኤዞፕ መጻሕፍት

26 Jan, 06:39

634

ድብ አንበሳ
ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህል እና የተፈጥሮ መስህብ

በኃይለማርያም ኤፍሬም

***
የአንድ ማህበረሰብ ማንነት መገለጫዎችና የቱሪስት መስህቦች ከሚባሉት ዋናዋና ጉዳዮች ውስጥ የተፈጥሮ መልክዓ ምድርና በውስጡ አቅፎ የያዛቸው ፍጥረታት ዓይነትና ስብጥር፣ የባህል መገለጫ የሆኑት የምግብና የመጠጥ አይነቶች እስከ መሉ ስርዓቱ፣አልባሳትና መጊያጊያጫዎች፣ የቤትና የመስክ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የወራት የቀናትና የወቅቶች ስያሚዎችና የዘመን አቆጣጠር፣የተለያዩ በዓላትና ስያሚ እስከ ስርዓታቸው፣ የሰርግና የሐዘን ስርዓት፣ መንፈሳዊ ቅርሶችና ሥነ ስርዓቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች የሙዚቃ ስራዎችን ያካትታል፡፡ ለትውልድ ማንነትን ለማውረስ እነዚህን ሁሉ በአግባቡ ሰንዶ ማቅረብና ማስተማር የግድ ይሆናል፡፡በተለምዶ በቃልና በክዋኔ እንጂ በሰነድ አስደግፎ ትውልድን ማስተማር በሀገራችን ብዙ አልተለመደም፡፡ የቱሪስት መስህብ ብለን የምናቀርበው ከብዙ በጥቂቱ ወይም በከፊል ብቻ በመሆኑ ጥልቅ ዕሴትና መስህብ ያለን ብንሆንም የአቅማችንን ያህል አልተጠቀምንም፡፡ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ አንደ ተቀናበረው ከላይ የተጠቀሱትን አንኳር ጉዳዩች ለቅሞና ሰንዶ ለማቅረብ ሲሞከር እኔ እስከማውቀው ድረስ ኃይለማርያም ፋና ወጊ ሊባል ይችላል፡፡ ለልጆችና ወጣቶች ማስተማሪያ ሊሆን ከመቻሉም በላይ ከአማርኛ ወደ ውጭ ቋንቋዎች ቢተረጎም የቱሪስትን ቆይታ ለማራዘምና እኛነታችንን የበለጠ ለማሳወቅ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስራ ጥቃቅን ለሚመስሉ ጉዳዮች ትኩረት መስጠትን፣ በራስ መተማመንና መኩራትን ብሎም በትጋት ለሌሎች ለማጋራት መፍቀድን ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም ወጣት ኃይለማርያምን አለማመስገንና አለማድነቅ አይቻልም፡፡

መልካም ንባብ

ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)

***
ኢትዮጵያዊነት ከድል አድራጊነት እና ጀብደኝነት ታሪካችን ሌላ ያለውን ገጽታ እና ከእያንዳንዱ ባህላዊ ድርጊቶቻችን፣ንግግራችን እና አለባበሳችን ጀርባ ያለውን የራሳችን የሆነውን ስልጣኔያችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህም ጥለናት የሄድናትን አገራችንን ዞር ብለን እንድናውቃት እና እንድንሻት ይረዳናል፡፡አገራችንን ላወቅናትም ላላወቅናትም ለራሳችንም ለልጆቻችንም እንዲሆን አድርጎ ታሪክን ቀለል ባለ ዘዴ ለመንገር ይህንን መጽሐፍ ላዘጋጀልን ልምዱን፣እውቀቱን፣ጊዜውንም ላጋራን ለኃ/ማርያም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

ዶ/ር ፅጌማርያም አበበ ቢሆነኝ

***
የሀገራችንን የቱሪዝም መስህቦች በዝርዝር ያቀረበ፣በባለቀለም ምስሎችና ማስረጃ የተደገፈ፣በዓይነቱ ልዩ የሆነ ለቱሪስቶች፣ቱርኦፕሬተሮች እና የቱሪዝም ቤተሰቦች አጋዥ የሆነ በቀላል እና ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተዘጋጀ የቱሪዝም ማስተማሪያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ትኩረት ያልተሰጣቸው ተደብቀው የነበሩ ብርቅ እና ድንቅ የቱሪዝም መስህቦቻችንን ለማስተዋወቀ ግሩም ፍሬ ያለው ለቱሪዝም ሊህቃን ታላቅ ግብዓት የሚሰጥ ለታሪካችን፣ ለባህላችን፣ መዳበር የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው፡፡በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ቢተረጎም ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል፡፡

ፋንቱ ጎላ ስዩም የቱሪዝምና ሆቴሎች ከፍተኛ አማካሪ
ኤዞፕ መጻሕፍት

25 Jan, 14:48

778

ሰማንያ አሀዱ
መጽሐፍ ቅዱስ !!

ከገበያ ላይ እንደልብ የማይገኝ !!
ኤዞፕ መጻሕፍት

10 Jan, 06:42

654

ቀደምት የታሪክ መጻሕፍት እነሆ !!!
ኤዞፕ መጻሕፍት

08 Jan, 16:23

943

እነዚህ በምስሉ የምታዩዋቸው ቀደምት በመጠናቸው ከ65 ገጽ የማይበልጡ ነገርግን በውስጣቸው የያዟቸው እጅግ ውብና ጠቃሚ ሀሳቦች ግን ከዘመናችን 1000 ገጽ መጽሐፍ የበለጡ ሆነው የምናገኝበት አጋጣሚ እጅጉን በጣም ሰፊ ነው።

ብታነቧቸው ጠቃሚነታቸውን ለመጠቆም ያህል ነው።

መጽሐፍቱ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ናቸው።
ኤዞፕ መጻሕፍት

06 Jan, 15:26

1,147

«ኃያላን አንዱት ወደቁ የሠልፉም ዕቃ አንዴት ጠፋ!»


ትንሽ ስለ መጽሐፉ !!

ገናና እና ታላቅ፥ ዝነኛና ታዋቂ፥ የተከበሩና አንቱ የተሰኙ ከዘመናት በኋላ ሳይታሰብ በሚያሳዝን ሁኔታ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ብዙዎችንም «እንዴት ወደቁ?» አሰኝተዋል::

የታላላቆች አወዳደቅ መዝሙረኛውን ዳዊት በእግርሞት ድባብ ውስጥ ነክሮታል:: አዎ! በእግዚአብሔር ፊት ይጋርድ የነበረው ኪሩብ (መላዕክ) እንዴት ወደቀ? አዳም እንዴት ወደቀ? ታላላቅ መንፈሳዊ መሪዎች እንዴት ወደቁ? መልስ የሚሻ ብርቱ ጥያቄ ነው::

በእርግጥ ኃያላንን የሚጥል ለዝንተ ዓለም የሚፈታተንና እስከ ጌታ ኢየሱስ ዳግም ምፅአት ያለመታከት በመታገል ለመውደቃቸው ምክንያት የሆነ ባላጋራ አለ:: በዚህ የሰው ልጆች ቀንደኛ ጠላት ተጠልፎ ላለመዉደቅ እውነትን በማወቅ በእውነትና በጽድቅ መኖር ያስፈልጋል:: እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ስለመንፈሳዊ ውጊያ የሚሰጠውን ትኩረት በማመን ከመፍትሔዉ ጋር አብሮ በመራመድ ለተሳካ የክርስትና ሕይወትና ኣገልግሎት ራስን ማዘጋጀት በተለይ በዚህ ዘመን አስፈላጊ ነው::

ይሁን እንጂ የወንጌል አገልጋዮች የሆኑ ሁሉን በቸልታ እያዩት ትኩረት ያልሰጡት ነገር ለመውደቃቸው ምክንያት ስለሚሆን፤ ይህ ሊጤን ይገባል:: ታላላት የምንላቸው ሰዎች ሲወድቁና ሲስቱ «ኃያላን እንዴት ወደ» በማለት በአግርሞት እንዳንዋጥ የዳዊት ምልከታና ጥያቄ ለእኛ ትምህርት ይሆን ዘንድ ተፅፏል:: ስለዚህ አሁን ባለንበት ሁኔታ ራሳችንን እንይ!

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ከተለያዩ አገልጋዮችና ከደራሲውም የሃያ አምስት ዓመት የነፃ መውጣት አገልግሎት የተገኙ መንፈሳዊ ልምምዶች በአንድ ላይ በመዳበል ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲጠቅም ተደርጎ ተዘጋጅቷልና ያንብቡት::

ኤዞፕ ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መሸጫ
@Mesay21
@Mesay21
ኤዞፕ መጻሕፍት

06 Jan, 13:15

1,095

ለገና ስጦታ የሚሆኑ መፅሐፍቶች