አፍሪካውያን የቀድሞ ኮከቦች አዲስ አበባ ገብተዋል
******
ናይጄሪያዊውን የቀድሞ እግርኳስ ኮከብ ንዋንኮ ካኑን ጨምሮ ሄንሪ ካማራ፣ ዳንኤል አሞካቺና ሌሎች በርካታ የቀድሞ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቾች ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቀጣይ ቀናት በሚካሄደው የሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል ላይ ይሳተፋሉም ተብሏል። በፌስቲቫሉ የውጭ ሀገራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ተዋናዮች፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ዲፕሎማቶችና በሌሎች የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦች እንደሚሳተፉ የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።