AVT - aviewtainment

@aviewtainment


AVT - aviewtainment

27 Jun, 21:55


አፍሪካውያን የቀድሞ ኮከቦች አዲስ አበባ ገብተዋል
******
ናይጄሪያዊውን የቀድሞ እግርኳስ ኮከብ ንዋንኮ ካኑን ጨምሮ ሄንሪ ካማራ፣ ዳንኤል አሞካቺና ሌሎች በርካታ የቀድሞ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቾች ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቀጣይ ቀናት በሚካሄደው የሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል ላይ ይሳተፋሉም ተብሏል። በፌስቲቫሉ የውጭ ሀገራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ተዋናዮች፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ዲፕሎማቶችና በሌሎች የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦች እንደሚሳተፉ የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

AVT - aviewtainment

27 Jun, 14:54


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቻምፒዮና 10 ሜዳሊያ ወስዳለች
*********
ኢትዮጵያ በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቅቃለች። ላለፋት ስድስት ቀናት በካሜሩን ዱአላ ከ50 ሺ ሰው በላይ የመያዝ አቅም ባለው የጃፑማ ሁለገብ ስታዲየም ከ27 ሀገራት በላይ የተውጣጡ 2 ሺህ 500 አትሌቶችን በሁሉም የአትሌቲክስ ተግባራት ሲያፎካክር የቆየው ቻምፒዮና ትናንት ምሽት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል።

ኢትዮጵያም በ32 ሴት እና በ36 ወንድ አትሌቶች በ19 የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት ተሳትፋ በ5 ወርቅ፣ በ4 ብር እና በ1 ነሐስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳሊያዎች ውድድሩን አጠናቅቃለች።

AVT - aviewtainment

27 Jun, 14:27


የቀድሞው የዩናይትድ ኮከብ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል
June 27, 2024
Amen

የመቻል እግር ኳስ ክለብ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ ሙግለጫ የቀድሞ ማንችስተር ዩናይትድ እና ፖርቹጋላዊ ኮከብ ሉዊስ ናኒ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ አረጋግጦልናል ብሏል። ከሃምሌ ስድስት ጀምሮ ኢትዮጵያ ይደርሳል የተባለ ሲሆን በአስደናቂ አብዶዎቹ የሚታወቀው የቀድሞ የመስመር አጥቂ ናኒ በቀጥታ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት “ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያን ለማየት ጓጉቻለሁ” ብሏል።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64381

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

27 Jun, 12:53


ህልሙን እውን ያደረገው ጆርጅያዊ
June 27, 2024
Amen

የያኔው የዳይናሞ ቲቢሊሲ አካዳሚ ታዳጊ እንደ ብዙ ታዳጊ ተጫዋቾች ሮናልዶን እያየና እሱን መሆን እየተመኘ ነው ያደገው። ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ፈርጥ ኳስ ሳያቆም አንድ ቀን አብሬው ብጫወት እያለ ሲመኝና ሲያልምም አድጓል። ይህ ህልምና ምኞቱ ቅዠት ሆኖ አልቀረም።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64376

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

26 Jun, 16:37


የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የአመቱ ኮከብ እጩዎች
******
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች፤ ግብ ጠባቂ እና የዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሲደረጉ፣ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ባሲሩ ኡመር፣ ሽመልስ በቀለ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ቸርነት ጉግሳ፣ አሊ ሱሌይማን፣ ከነዓን ማርክነ እና ቢንያም ፍቅሬ ሆነዋል።
የዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ እጩዎች አቡበክር ኑራ፣ ሰዒድ ሀብታሙ እና ፍሬው ጌታሁን ሆነው ተመርጠዋል። የዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ወገኔ ገዛኸኝ፣ ተመስገን ብርሃኑ፣ ዮሐንስ መንግሥቱ፣ በፍቃዱ አለማየሁ እና መድን ተክሉ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ተመልካቾች እስከ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ብቻ በተቋሙ የቴሌግራም ቻናል በመግባት ድምፅ መስጠት እንደሚችሉ አስታውቋል።

AVT - aviewtainment

26 Jun, 14:47


የአቡበከር ናስር ወደ አንጋፋው የጋና ክለብ?
June 26, 2024
Amen

አቡበከር የሙከራ ጊዜውን አጠናቆ ከተሳካለት 88 አመት የሆነውን አንጋፋ የጋና ክለብ ይቀላቀላል። 1935 የተመሰረተው አሳንቴ ኮቶኮ በጋና አሳንቲ ግዛት ኩማሲ መቀመጫውን ያደረገ ክለብ ሲሆን፣ በአማኮም ኩማሲ የሚገኘው ባባያራ ስቴድየምን ይጠቀማል።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64368

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

26 Jun, 13:49


እድለ ቢሱ ጀርመናዊ!
June 26, 2024
Amen

ባላክ በሁለት የተለያዩ አመታት በትልልቅ ውድድሮች ላይ ስምንት ዋንጫዎችን ለማንሳት አንድ ጨዋታ እየቀረው ሳያነሳ የቀረበት አጋጣሚ አስገራሚ ነው። ይህም በ2002 በባየርሊቨርኩሰንና በብሔራዊ ቡድኑ ሲሆን ሌላው በ2008 ከቼልሲ ጋር ነበር።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64362

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

23 Jun, 15:10


“አብቅቶልኛል!” – ፖል ፖግባ
June 23, 2024
Amen

ፖግባ ስለቀጣይ የእግር ኳስ ህይወቱ በሰጠው አስተያየት ” ከዚህ በፊት የነበሩኝ ነገሮች ሁሉ አብቅተዋል ፣ አሁን አብቅቶልኛል የቀድሞው ፖግባ በድጋሚ መመለስ አይችልም ” ሲል ተደምጧል።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64356

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

23 Jun, 14:32


ዩኤፋ ሜዳ የሚገቡ ደጋፊዎች ላይ ጠንካራ ርምጃ ይወስዳል
June 23, 2024
Amen

ፖርቹጋል ትናንት ቱርክን 3ለ0 በረታችበት ጨዋታ ወቅት ከጨዋታው ውጤት ይልቅ በተለያየ ደቂቃ ወደ ሜዳ ዘለው ገብተው ከአል ነስሩ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ፎቶ ለመነሳት ጨዋታውን ያወኩ ሰባት ደጋፊዎች ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል። በዚህም የተነሳ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንደነዚህ አይነት ደጋፊዎችን ለማስቆም ጥበቃውን ለማጠናከር እንደሚገደድ አስታውቋል።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64351

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

22 Jun, 15:43


በአውሮፓ ዋንጫ የተሸፈነው ኮፓ አሜሪካ
June 22, 2024
Amen

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64346

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

22 Jun, 14:53


ህይወት አድኗ ‘አርም ባንድ’
June 22, 2024
Amen

ሮናልዶ በተለያዩ የሰብአዊ ድጋፎቹና የረድኤት ስራዎቹ የተመሰገነ ስም አለው። የወርቅ ጫማውን ሸጦ ሳይቀር ለተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎች ሲያውልም አለም ያውቀዋል። ይህን የሚያደርገውም አውቆና አስቦበበት ነው። በንዴት አውልቆ የወረወረው አርም ባንድ ግን በአንድ ሰው ተነስቶ የሌላ ሰው ህይወትን እታደጋለሁ ብሎ ባላሰበበት መንገድ ሌላ ታሪክ ሰርቷል።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64341

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

20 Jun, 12:16


ሰርቢያ የአውሮፓ ዋንጫውን ልታቋርጥ ትችላለች
June 20, 2024
Amen

ትናንት ምሽት ክሮሺያና አልባኒያ በምድብ ሁለት 2ለ2 በተለያዩበት ጨዋታ ወቅት የሁለቱ አገራት ደጋፊዎች “ሰርቢያዎችን ግደሏቸው” የሚል ድምፅ ማሰማታቸውን ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በነዚህ ደጋፊዎች ላይ እርምጃ ካልወሰደ ሰርቢያ ውድድሩን አቋርጣ እንደምትወጣ አስጠንቅቃለች።

👇ሊንክ በመጫን ሙሉውን ያንብቡ
https://aviewtainment.com/?p=64336

ቤተሰብ ለመሆን👇ይጫኑ
https://aviewtainment.com/?page_id=59503

AVT - aviewtainment

20 Jun, 10:52


ቀበሮዎቹ አዲስ አለቃ አግኝተዋል
....................................
ከአንድ አመት የቻምፒዮንሺፕ ተፋላሚነት በኋላ ወደ ፕሪሚየርሊጉ ያደጉት ሌስተር ሲቲዎች አዲሱን የውድድር አመት በአዲስ አሰልጣኝ ይጀምራሉ። ስቲቭ ኩፐርም የቀበሮዎቹ አዲሱ አለቃ በመሆን ተሹመዋል።
የ44 አመቱ ጎልማሳ አዲስ አዳጊውን ክለብ ለሶስት አመታት ለማሰልጠን መስማማታቸው ይፋ ሆኗል። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የታህሳስ ወር ከውጤት መጥፋት ጋር ተያይዞ ከኖቲንሀም ፎረስት ሀላፊነቱ የተሰናበቱት ኩፐር ከ2021-2023 በአሰልጣኝነት መምራት መቻላቸው አይዘነጋም። ኩፐር አዲሱን የኪንግ ፓወር ሀላፊነት በሀምሌ ወር አጋማሽ ከቀበሮዎቹ ጋር በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ጨዋታዎች ይጀምራሉ ተብሏል።
ሌስተር ሲቲ በኢንዞ ማሬስካ እየተመራ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ቢያድግም አሠልጣኙ የቼልሲ አሠልጣኝ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።