የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ስልጠና ሰጠ
የአ.ሳ.ቴ.ዩ የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ከየኮሌጁ ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ት/ት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሶፍትዌር (HEMIS, Higher Education Management Information System ) አጠቃቀም ዙሪያ ከት/ት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያ አቶ ሐብታሙ ገበየው ስለጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር ያደሳ መለኩ እንዳሉት በትምህርት መስክ ላይ ያሉ የመረጃ ምንጮች ተአማኒነት እንዲኖራቸውና ለሚፈለጉበት ዓላማ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በቴክኖሎጂ ማዘመንና ታአማኒነታቸውን ማረጋገጥ አንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ት/ት ሚኒስቴር የከፍተኛ ት/ት ተቋማት አስፈላጊ መረጃዎች በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በማድረግ በስራ ላይ ያሉ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን አፈጻጸም ለመገምገምና ወደ ፊት ለሚወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃችን ከአንድ የመረጃዎች ቋት ለማግኘት እንዲቻል ‘’HEMIS’’ ሶፍትዌር በማበልጸግ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እያደረገ መገኘቱን በመግለፅ የአ.ሳ.ቴ.ዩ ይሄንኑ መረጃ በማደራጀት ለት/ት ሚኒስቴር እየላከ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ፕሮፌሰር ያደሳ መላኩ በዩንቨርስቲያችን ተጨባጭ ሁኔታ የሚፈለጉትን መረጃዎች በጥራና በጊዜው ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በኩል ውስንነቶች ስላሉ ስልጠና ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ት/ት ሚኒስቴር የመጡ ባለሙያ አቶ ሐብታሙ ገበየሁ በበኩላቸው ስለስለልጠናው አስፈላጊነት በሰጡት ማንብራሪያ መሰረት የሚመለከታቸው የዪኒቨርስቲው ባለድርሻ አካለት ስልጠናውን መውሰዳቸው ለተቋማቸውና ለሀገራቸው ትከክለኛና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ በመስጠት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራችው አስረድተዋል፡፡