Al-Afia Schools‘ Community @alafiaschoolscomunity Channel on Telegram

Al-Afia Schools‘ Community

@alafiaschoolscomunity


We promote quality education that shapes generations

Al-Afia Schools‘ Community (English)

Welcome to the Al-Afia Schools' Community! Our Telegram channel, @alafiaschoolscomunity, is dedicated to promoting quality education that shapes generations. Who are we? Al-Afia Schools is a renowned educational institution that focuses on providing students with a well-rounded education that prepares them for success in the modern world. With a team of dedicated teachers and staff, we strive to create a supportive and nurturing environment for our students to learn and grow. What do we do? Our community channel serves as a platform for sharing educational resources, tips, and updates with our students, parents, and anyone passionate about quality education. Whether you're looking for study tips, information on upcoming events, or simply want to engage in discussions about education, our channel has something for everyone. Join us in our mission to promote quality education that shapes generations. Together, we can make a difference in the lives of students and inspire a love for learning that will last a lifetime. Stay connected with us on @alafiaschoolscomunity and be a part of our growing community of learners and educators. Experience the Al-Afia Schools' difference today and see how we are transforming education one student at a time. Join our community channel now and be a part of our journey towards excellence in education. We look forward to having you with us!

Al-Afia Schools‘ Community

11 Jan, 18:51


7 BEST WAYS TO RAISE DISCIPLINED CHILDREN

Parenting is a journey filled with both joys and challenges. One of the most significant challenges parents face is disciplining their children. Traditional methods of punishment often lead to negative outcomes, such as resentment, fear, and a damaged parent-child relationship. Sarah’s Gentle Discipline offers a refreshing approach to parenting, emphasizing emotional connection and positive reinforcement over punishment

Dear parents:
Today, for our weekly message, we have chosen the following seven key lessons and insights from the book, "Gentle Discipline," Enjoy reading the seven points and try them in disciplining your children:

1. The Power of Connection
At the heart of gentle discipline is a strong emotional connection between parent and child. By building a bond of trust and understanding, parents can guide their children's behavior effectively. This connection fosters a sense of security and belonging, making children more receptive to guidance and less likely to misbehave.

2. Understanding Child Development
To effectively discipline children, it's essential to understand their developmental stages. By recognizing the cognitive, emotional, and social milestones of each age group, parents can tailor their approach to meet their child's specific needs. This understanding helps parents respond to challenging behaviors with empathy and patience.

3. The Importance of Positive Reinforcement
Positive reinforcement is a powerful tool for shaping children's behavior. By acknowledging and rewarding positive actions, parents can encourage desired behaviors and strengthen the parent-child bond. This approach is more effective than punishment, as it motivates children to repeat positive behaviors.

4. The Art of Effective Communication
Effective communication is crucial for gentle discipline. Parents should use clear, concise language to explain expectations and the consequences of negative behavior. Active listening is also essential, as it allows parents to understand their child's perspective and address their needs.

5. Setting Limits and Boundaries
While gentle discipline emphasizes positive reinforcement, it's still important to set clear limits and boundaries. Children need structure and consistency to feel safe and secure. By establishing clear expectations, parents can help children develop self-discipline and responsibility.

6. The Role of Empathy
Empathy is the ability to understand and share the feelings of another person. By empathizing with their child's emotions, parents can respond to challenging behaviors with compassion and understanding. This approach helps children feel heard and validated, reducing the likelihood of future misbehavior.

7. The Power of Self-Reflection
Gentle discipline is not just about changing our children's behavior; it's also about transforming ourselves as parents. By reflecting on our own emotions, triggers, and parenting style, we can become more mindful and responsive parents. Self-reflection allows us to grow and evolve as individuals and as parents.

Gentle Discipline is a valuable resource for parents seeking to raise confident, capable, and kind children. By embracing the principles of emotional connection, positive reinforcement, and empathy, parents can create a nurturing and supportive environment for their children to thrive.

Al-Afia Schools‘ Community

06 Jan, 05:00


#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

@tikvahethiopia

Al-Afia Schools‘ Community

05 Jan, 04:56


እናመሰግናለን!!!
ሹክረን!!!

ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡-
“ሪድ አል-አፊያ” በሚል መሪ ቃል ለወራት በተሻለ እንቅስቃሴ ሲካሄድ የቆየው የ 2017 የንባብ ዘመቻ በሁሉም ካንፓሶቻችን በተለያዩ ንባብ ተኮር መርሃግብሮች በከፍተኛ ድምቀት በዚህ ሳምንት ተጠናቋል፡፡ እኛም የዚህ ሳምንት መልዕክታችን ስለንባብ እንዲሆን መርጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

በኣረብኛ አል-ኢልሙ ፊ ሲገር ከነቅሹ አለል ሃጀር ማለትም በልጅነት የሚቀሰም ዕውቀት እንደ ድንጋይ ላይ ፅሁፍ ነው ይባላል ፡፡ ንባብ ደግሞ ሁላችንም እንደምናውቀው የዕውቀት መግቢያ በር ነው፡፡ ልጆቻችን በንባብ ሲጠነክሩ የተሻለ ዕውቀት ይሰንቃሉ፤በዚህም የአስተሳሰብ አድማሳቸው እየሰፋ ይሄዳል፡፡ በዚያው መጠንም የሚኖራቸው ተቀባይነት እንዲሁም ተፅእኖ ፈጣሪነት እያደገ ይሄዳል፡፡ ለዚህም ነው ብዙውን ጊዜ አንባቢዎች መሪዎች ናቸው የሚባለው፡፡

ዓመታዊ የንባብ ዘመቻ በአል-ዓፊያ ት/ቤቶች የትምህርት ፅ/ቤት ስር በሚገኘው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት አማካኝነት በ2016 በይፋ የተጀመረ ሲሆን ለ2ተኛ ጊዜ በ2017ም በተሻለ ሁኔታ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለማካሄድ ተሞክሯል፡፡

በተለይ በዚህ ዓመት  በመንግስት ትምህርት ቢሮ በቅድመ-መደበኛ (ኬጂ) ጭምር የንባብ እንቅስቃሴው እንዲጀመር በሰርኩላር ደረጃ መውረዱ የንባብ ክህሎት ከስር ከመሰረቱ መጀመር እንደሚገባው ያረጋገጠ እንዲሁም ተቋማችን በዚህ ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት ቀድሞ መሄዱን ያመላከተ ልዩ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡

ሁላችንም ተማሪዎቻችን ማንበብ እንዲወዱ የመርዳት ፍላጎት አለን። ስለዚህ  ሁላችንም ይህንን ግብ ማሳካትይኖርብናል። ይህን ከባድ ሥራ ትምህርት ቤት በአመታዊ የንባብ ዘመቻ ብቻውን ሊወጣው አይችልም። ተማሪዎች ማንበብ ለመማር የሚያደርጉትን ጥረት ማህበረሰቡ እንዲደግፍ እንፈልጋለን። ወላጆች ልጆችን እንዲያበረታቱና እንዲያግዙ እንፈልጋለን። ወላጆች ለማንበብ፣ ሞዴል ንባቦችን ለማቅረብ የሚያግዙ ተግባራትንና ቦታዎችን በማመቻቸት እንዲተባበሩ እንፈልጋለን።ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎች ጥሩ አንባቢ እንዲሆኑ እንዲያግዙና አቅጣጫ እንዲያመላክቱ እንፈልጋለን።

በዚህ መሰረት ወላጆች/አሳዳጊዎች  ልጆቻችንን ዛሬ ባሉበት ዕድሜ ክልል ይህንን መሰረታዊ የስኬት ቁልፍ የሆነ ክህሎት( ንባብ)  ፍላጎት እንዲኖራቸው በማበረታት እና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ልጆች አንባቢ ሆነው እንዲታነፁ የድርሻችንን ኃላፊነት መወጣት ከቻልን በዕርግጥም የላቀ ውለታ ውለናቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከላይ ቀደም ብሎ እንደተጠቆመው ልጆች ብዙ ባነበቡ ቁጥር የዕውቀት አድማሳቸው እየሰፋ ይሄዳል ፡፡ ይህም በትምህርታቸው ጎበዝ ፤በስነ-ምግባራቸውም እየተመሰገኑ ሆነው እንዲታነፁ ብሎም ወደፊት ኃላፊነት የመሸከም ብቃታቸው ክፍ እንዲል በእጅጉ ያግዛቸዋል፡፡

ከናንተ ጋር በአንድ ላይ ሆነን ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ልጆቻችን ስኬታማ አንባቢዎች እንዲሆኑ ማብቃት እንችላለን።  በመሆኑም ልጆች ገና ናቸው ብለን ሳንዘናጋ ከወዲሁ በዕድሜያቸው ልክ የንባብ ፍላጎት ማስረፅ ይቻል ዘንድ የተጀመረው የጋራ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥል!! እንዲሁም በዚህ ሳምንት የተጠናቀቀው በት/ቤቱ ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊ የንባብ  ዘመቻ እንጂ ንባብ አለመሆኑን ሳንታክት ለልጆቻችን እናስታውስ!! እንምከር!! እናስረዳ!!

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፣አንባቢዎች አሸናፊዎች ናቸው፤አሸናፊዎችም አንባቢዎች  ናቸው፣የማያነብ ሰው መስኮት እንደሌለው ቤት ነው ይባላል እና እኛ እያነበብን ለልጆቻችን አርአያ በመሆን አንባቢ ትውልድ በማፍራት ልጆቻችን  የዕውቀት ጉዞዋቸው የተሳካ ይሆን ዘነድ የድርሻችንን እንወጣ!!  

ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች
እናንተም “ስለልጄ የንባብ ክህሎት መዳበር የድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል ለልጆቻችሁ የተለያዩ መፅሀፍት በመግዛት፣ሰዓት መድባችሁም በማገዝና በማበረታታት እንዲሁም  ንባብን የሚያግዙ ሁኔታዎችንም በማመቻቸት ብሎም ንባብን ለማጎልበት ስንልክላችሁ የነበሩ መልዕክቶችን በሚገባ ተግባራዊ  በማድረግ ከት/ቤቶቻችን እንዲሁም ከመምህራኑ ጋር በመወያየት ጭምር የንባብ አርአያ በመሆን፤ ከዚህ ባሻገር በት/ቤቶቻችን ንባብ ማጠቃለያ ፕሮግራም መድረኮች እንድትገኙ የቀረበላችሁን ጥሪ አክብራችሁ በመገኘትና ስለንባብ አስፈላጊነት ገንቢ እና አነቃቂ መልዕክቶች በማቅረብ ለንባብ ዘመቻው ስኬታማነት ላሳያችሁት ቁርጠኝነትና ቀና ትብብር  ሁሉ በመላው የትቤታችን ማህበረሰብ ስም እጅግ አድርገን ከልብ እናመሰግናለን!!! ሹክረን!! በማለት የዛሬውን ሳምንታዊ መልዕክታችንን እንቋጫለን፡፡

Al-Afia Schools‘ Community

05 Jan, 04:48


ልጃችን ኢብቲሳም ዳግም ዛሬም ድል አደረገች !!!
በኮልፊ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በተካሄደው ከ11 ወረዳ አሸናፊ ሁነው በመጡ ተማሪዎች መካከል በዛሬው እለት በተካሄደው የጥያቂና መልስ ውድድር ላይ ተማሪ ኢብቲሳም አብዱልበር 3ኛ ወጣች፡፡ ውድድሩ ከፍተኛ ፎክክር የነበረበት የተወዳዳሪ ተማሪዎች አቅም የታየበት እንደመሆኑ መጠን ተማሪ ኢብቲሳም ያላትን አቅም ለተወዳዳሪዎ ያሳየችበት ነበር፡፡
ለመላው የአል-ዓፊያ ት/ቤት ማህበረስብ እንኳን ደስ አላችሁ!!! አለን!!!

Al-Afia Schools‘ Community

04 Jan, 05:01


#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና የ " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ " ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ላሰቡ ጥሩ እድል መመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናዎቹን ለመውሰድ ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ የመንግስትና የግል ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ ስልጠናዎችን መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠና ቀናት
#ቅዳሜ እና #እሁድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30 እንደሆነ ተመላክቷል።

የስልጠና ቦታው አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ ሲሆን ለመመዝገብ ይህን ሊንክ 
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia

Al-Afia Schools‘ Community

28 Dec, 19:47


እንግሊዝኛ ቋንቋን መልመድ የሚቻለው እንዴት ነው?

ውድ ወላጆች፡-

የምርምር ጥናት እንደሚያሳየው: በልጅነት እድሜ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋዎችን መማር፤ለአእምሮ መዳበር ይረዳል፡፡ ከአንድ ቋንቋ በላይ መናገር የልጆችን አእምሮ ያዳብራል። እንዲሁም በበለጠ የፈጠራ አስተሳሰብ እንዲኖራቸውና ለችግሮች በቀላሉ መፍትሄ ማግኘት እንዲችሉ ይረዳል። ብሎም ልጆች የተሻሉ አንባቢዎች፣ አድማጮችና በቀላሉ ተግባቢዎች እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። የማስታወስ፣ የማስተዋል ትኩረትና የቁጥር ትምህርት ችሎታንም ያዳብራል፡፡

በዚህም መሰረት የዛሬው ሳምነታዊ መልዕክታችን ከቋንቋ በተለይ አለማቀፍ በሆነው እንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ መረጃውን ያጋራን EM ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡

እንግሊዝኛንም ሆነ ማንኛውንም ቋንቋ ለመልመድ፣ በመጀመሪያ ደፍረን መናገር መቻል አለብን። ትንሽም ትሁን የምናውቃትን ቃል እየደጋገምን መናገር አለብን! መናገር ስንጀምር ነው ሁ ሉ ም ነገር ፈር እየያዘ የሚሄደው!

አብዛኞቻችንኮ በርካታ የእንግሊዝኛ ቃላትንና ሀረጋትን እናውቃለን፤ እንዲሁም ሙሉ ዓረፍተ ነገሮችን መመስረት እንችላለን፤ ነገር ግን የመናገር ልምድ ስለሌለን መናገር ይከብደናል። የምናውቀውን ቃላትና ህግጋት እንዴት አሰካክተንና ቅደም ተከተል አሲዘን መናገር እንደምንችል አናውቅም። ለመናገር አንደፍርም፤ እንፈራለን። ሰው ምን ይለኝ ይሆን የሚል ይሉኝታ ያሸማቅቀናል።

ምን መሠላችሁ፣ ችግሩ ያለው አመለካከታችን ላይ ነው። እንግሊዝኛ ለመናገር መፍራት የለብንም;; ፈረጆቹኮ አማርኛ ሲናገሩ በፍፁም አይፈሩም ወይም ደግሞ አያፍሩም። የፈለገ ቢሰባብሩትም ዘና ብለው ነው የሚናገሩት። ትንሽ አማርኛ ካወቁ "አማርኛ እንችላለን!" ብለው ያስባሉ። እኛ ሁልጊዜ በመማርና በማጥናት ላይ ነው ትኩረታችን። ቲዮሪ ብቻ ፋይዳ የለውም ተግባር ነው ዋናው።

የፈለገ Vocabulary ብናውቅ የፈለግ Grammar ብናጠና፣ የተማርነውን ነገር ካልተለማመድነው ወይም ባገኘነው አጋጣሚ ውስጥ ጣልቃ እያስገባን ካልተጠቀምነው፣ እንረሳዋለን። ትርጉሙ፣ ህጉና አገባቡም ይጠፋብናል፥ እውቀታችን አይዳብርም! ልምዳችን አይጨምርም። ልጆቻችን በእንግሊዝኛ የመናገር ልምድ ሲያዳብሩ ፣ በራስ መተማመናቸውም ይጨምራል። በዚህ ሰአት ያለ ምንም ጭንቀት መናገር ይጀምራሉ።

እንደዚህ ሲባል ግን ቃላትን፣ ግራመርን ወይም ስፖክን ኢንግሊሽን ማጥናት የለባቸውም  ማለት አይደለም። እነዚህን ነገሮች ማጥናት በጣም አስፈላጊ ነው። ገቢ ከሌለ ወጭ አይኖርም። ከየት አምጥተው ያወጡታል? If there is no input, there is no output. ይላሉ ፈረንጆቹ። ገቢ ሲኖር ነው ወጪም የሚኖረው። ስለዚህ ማጥናት የግድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ያጠናነውን ነገር በደንብ እየደጋገምን መለማመድ አለብን። አንድ ጊዜ ብቻ አንብቦ ወይም አድምጦ ዘወር ማለት በቂ አይደለም።


የምንፈራው ለተወሰነች ጊዜ ብቻ ነው፤ ከዛ ፍርሃታችን እኛኑ እስከሚደንቀን ድረስ ለቆን ይጠፋል። አንድ ማወቅ ያለብን ነገር አለ፣ ማንኛውንም ነገር በትክክል መሥራት የምንችለው ብዙ ጊዜ ካጠፋንና ከተሳሳትን በኋል ነው። ይህን ማወቅ አለብን። ካልተሳሳትን ደግሞ እየሞከርን አይደለም፤ ካልሞከርን፣ ምንም ነገር ማሳካት ወይም ከእቅዳችን መድረስ አንችልም ማለት ነው። አስታውሱ፣ ትንሽም ትሁን የምናውቃትን ቃል እየደጋገምን መናገር አለብን! መናገር ስንጀምር ሁ ሉ ም ነገር ፈር እየያዘልን ይመጣል!ሲል የመረጃ ምንጫችንን የቀረበውን መልእክት ከጥቂት ማስተካከያ ጋር እንዲህ አጋራናችሁ፡፡

በትምህርት ቤታችንም  የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትምህርት ዓይነትና በማስተማሪያ ብሎም በመግባቢያ ቋንቋነት እየተሰጠ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ተማሪዎች በድፍረት ቋንቋውን እንዲጠቅሙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያግዙ ሪዲንግ ካምፔይን ፣ ስፔሊንግ ቢ፣ዲቤት ፣ ስቶሪ ዴይ ፣ሞቲቬሽናል ስፒች እና ግራንድ ኢንግሊሽ ዴይ የመሳሰሉ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ወላጆች፡-
ከላይ እንግሊዝኛ ቋንቋን ለመልመድ የቀረበውን ጠቃሚ መልዕክት ከልጆች ጋር በመወያያት እና ለተግባራዊነቱ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎቻችን የሚማሩትን ትምህርት በአግባቡ እንዲረዱና ውጤታማ እንዲሆኑ እንግሊዝኛ ቋንቋን የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የማዳመጥ ክህሎታቸውን በሚገባ በማሳደግ አለም አቀፍ ተወዳደሪ ይሆኑ ዘንድ እየተደረገው ያለውን ጥረት በማገዝ የጋራ ሓላፊነታችንን ዕንወጣ ስንል የዛሬውን መልዕክታችንን አጠናቀቅን፡፡

Al-Afia Schools‘ Community

22 Dec, 17:14


How Children Succeed

In his book entitled "How Children Succeed," Tough explores the factors that contribute to children's success beyond traditional measures of intelligence and academic achievement. Through research and real-life examples, he argues that character traits such as perseverance, curiosity, and resilience play a crucial role in helping children thrive.

Dear parents:

Today, for our weekly message, we have chosen the following ten key lessons and insights from the book, "How Children Succeed,"  Enjoy reading the ten points and try your best to help your child succeed. 

1. The Importance of Character:

The author, Tough emphasizes that character traits, often referred to as "non-cognitive skills," are critical for success in life. Qualities such as determination, resilience, and emotional intelligence are just as important, if not more so, than IQ in determining a child's long-term outcomes.

2. Understanding Determination and Resilience:

The author highlights the concepts of determination and resilience as key components of success. Determination refers to the passion and perseverance needed to achieve long-term goals, while resilience is the ability to bounce back from setbacks. Both traits are essential for navigating challenges.

3. The Role of Adversity:

Tough discusses how experiencing adversity can actually foster resilience in children. He notes that overcoming obstacles can teach valuable life lessons and develop coping strategies, ultimately leading to greater success in the future.

4. The Impact of Environment:

The book explores how a child's environment influences their development of character traits. Supportive environments, whether at home or in school, encourage the growth of resilience and determination, while toxic environments can hinder these qualities.

5. The Importance of Relationships:

Tough emphasizes the significance of strong relationships in a child's life, particularly with adults. Positive mentorship and supportive adult interactions can help children develop the skills and confidence needed to succeed.

6. Teaching Self-Regulation:

The author discusses the concept of self-regulation, which involves managing emotions, thoughts, and behaviors. Teaching children how to self-regulate can improve their academic performance and social interactions, contributing to their overall success.

7. The Role of Failure:

Tough argues that experiencing failure is an essential part of personal growth. Allowing children to face challenges and learn from their mistakes fosters resilience and helps them understand the value of perseverance.

8. Educational Approaches:

The book examines various educational models that prioritize character development alongside academic achievement. Schools that focus on social and emotional learning create environments where children can develop the necessary skills for success.

9. Mindset Matters:

Tough explores the concept of a growth mindset, popularized by psychologist Carol Dweck. Encouraging children to view challenges as opportunities for growth rather than as threats can significantly impact their motivation and willingness to take risks.

10. Long-Term Strategies for Success:

Finally, the author advocates for long-term strategies that prioritize character development from an early age. Programs that focus on social-emotional learning, mentorship, and building resilience can set children on a path toward lifelong success.

In his book "How Children Succeed," Paul Tough presents a compelling argument for the importance of character and resilience in children's success. By highlighting these ten key lessons, he encourages parents, educators, and policymakers to prioritize the development of non-cognitive skills alongside traditional academic measures, ultimately fostering a generation of capable, resilient individuals.

Al-Afia Schools‘ Community

21 Dec, 13:54


ለአል-ዓፊያ ማኀበረሰብ በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ትምህርታዊ ውድድር የአል-ዓፊያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቤተል ቅርንጫፍ ተማሪዎች በ8ኛ ክፍል 1ኛ፣ በ6ኛ ክፍል ደግሞ 2ኛ በመሆን አስደናቂ ውጤት ማስመዝገባቸው በጣም ያስደስታል!
እንኳን ደስ አላችሁ‼️‼️

Al-Afia Schools‘ Community

17 Dec, 14:28


ክፍል 2

5. የልጆችዎን የትምህርት አቀባበል የሚመዝኑባቸው ቀላል ዘዴዎች ይኑርዎት

ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ለመርዳት በየዕለቱ ምን ተምረው እንደመጡ መፈተሸና መከታተል እንዲሁም ቀለል ባለ ዘዴ የምዘና ጥያቄ አዘጋጅተው መመዘን ይችላሉ፡፡ በተወሰነ የጊዜ ርቀት ይህን ተግባር በማከናወን ልጆችዎን ከተማሩት ምን ይህል በሚገባ እንደተረዱት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ግን ልጅዎን በሚያሳስብና በሚያስጨንቅ መልኩ መካሄድ የለበትም፡፡ ልጆችዎ እተዝናኑና እየተጫወቱ ሊሰሩ የሚችሉበትን ድባብ መፍጠር ይገባል፡፡ ልጆችን በዚህ መልኩ የተማሩትን በተለያየ ዘዴ እየገመገሙ ማነፅ በልጆቻችን ትምህርት በስፋት ተሳታፊ እንድንሆን፤ ልጆችንም የተማሩትን ትምህርት በጊዜ በሚገባ እንዲከልሱና በጥልቀት እንዲረዱ እንዲሁም በቀላሉ የተማሩትን አስታውሰው በምዘና መለኪያዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እና በክፍል ውስጥም በንቃት እንዲሳተፉ ጭምር ያበረታታቸዋል፡፡

6. ልጆችዎን በትምህርታዊ ጉዞ ያዝናኑዋቸዋል

“ካሉበት ቦታ መቀየር ከድካም ዕረፍት የመውሰድ ያህል አስደሳች ነው” ይባላል፡፡ እንግዲያው እርስዎ ልጆችዎን ቀኑን ሙሉ ከሚውሉበት ት/ቤት እንዲሁም ከቤትዎ በተወሰነ ጊዜም ቢሆን በማላቀቅ ለምን በሽርሽር አያዝናኗቸውም? ከተለመደ ቦታ መቀየር ለሁሉም ቢሆን ያዝናናል፡፡ በተለይ ደግሞ ትምህርት በመማር ከፍተኛ ውጣ ውረድ በት/ቤትም ሆነ በቤት ለሚጋፈጡ ልጆችዎ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ጋር ግን አንዴ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን አለ እሱም ልጆቻችን በሽርሽር/በጉብኝት ለማዝናናት ከመነሳታችን በፊት የምናዝናናበት/የምናስጎበኝበት ቦታ ለልጆቻችን የአካልም ሆነ የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የሥነ ልቦና ደህንነታቸው ብሎም ሞራልና ግብረ-ገብነታቸው ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያስከትል (ዋጋ የማያስከፍለን) ስለመሆኑ ቅድሚያ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ አለያ ግን አተርፍ ባይ . . . ነው የምንሆነው፡፡

7. ልጆችዎ የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ዕውቅና ሰጥተው ያበረታቱ፤ ይሸልሙ

ልጆችዎን ለሚያስመዘግቧቸው የትምህርት ስኬቶች ዕውቅና ሰጥቶ ማበረታታትና መሸለም የተሻለ እንዲሰሩ በጣም ያግዛቸዋል፡፡ እርስዎ ታዲያ ልጆችዎ የላቀ ውጤት ይዘው ወደ ቤት ሲመጡ በማበረታታትና በሽልማት ሊቀበሏቸው ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን የግድ ከፍተኛ የሆነ ወጪ ማውጣት አይጠበቅም፡፡ አቅም በፈቀደ ከወላጅ ለልጆች የሚደረግ ሽልማት ልጆች ደክመው ያመጡት ውጤት በወላጅ የላቀ ዋጋ እንደሚሰጠው መልዕክት ለማስተላለፍ መሆን ነው የሚገባው፡፡

8.ልጆችዎ እረፍት እንዲኖራቸው ያድርጉ! ለልጆችዎ ሰዓት ይኑርዎት! 

ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከጥናት ዕረፍት መውሰድ ለልጆች ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም ልጆችዎን በትምህርት ለማገዝ የሚረዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡ በቤት ውስጥም ቢሆን አንዳንዴ ልጆች ከትምህርት ተለይተው (አቋርጠው) ሊዝናኑ የሚችሉበት ጊዜ ያመቻቹላቸው፡፡ እርስዎም ካለዎት ሰዓት ምርጡን ከልጅዎ ጋር በመሆን ያሳልፉ፡፡ ግን ግን ስንቶቻችን ነን ካለን ሰዓት ምርጡን ነገ እኛን ይተኩናል ብለን ብዙ ከምንደክምላቸው ውድ ልጆቻችን ጋር የምናሳልፈው? ምን ያህል እርስዎ ለልጆችዎ ቅርብ ነዎት? ለልጅዎት ምርጡን ሰዓት ሰጥተው ያገኟቸዋል ወይስ . . . ? እኛ ለልጆቻችን ቅርብ ልንሆን ይገባል፡፡ ይህን የማናደርግ ከሆነ ግን ልጆቻችንን እኛ ሳንሆን የሚያንፃቸው ሌላ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክ፣ ቲቪ፣ እና የመሳሰሉት፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ የምንመኘውን አይነት ትውልድ ማፍራት ባዶ ተስፋ ሆኖ ይቀራልና ለልጆቻችን ሰዓት መስጠታችን በሚገባ መፈተሽ ለነገ የማይባል ነው፡፡

9.ልጆችዎ በአግባቡ መመገባቸውንና በተገቢው ሰዓት ወደ መኝታቸው መሄዳቸውን ያረጋግጡ!

ት/ቤት እንደ ስያሜው እውቀት የሚቀሰምበት ቦታ ነው፡፡  ትምህርት ለመማር ደግሞ ተማሪ በአካልም ሆነ በአዕምሮ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የምግብ ስርዓትና የመኝታ ሰዓት የተስተካከለ ሊሆን ይገባል፡፡ እንደ ወላጅ ለልጆች አሸክመን ለምንልከው ምግብ ምን ያህል ተገቢውን ጥንቃቄ እናደርጋለን? አንዳንዴ ልጆች እንደማይመቻቸው እየታወቀ የሚታሰርላቸውን ምግብ እንዲጨርሱ በት/ቤት የሚፈጠረው ግብ ግብ  ለጉድ ነው፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ምግብ በዕርግጥ እየተመለከቱት ነውን? የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ በተመሳሳይ የልጆች የእንቅልፍ ሰዓትም ከፍተኛ ክትትል ያሻዋል፡፡ ልጆች መተኛት በሚገባቸው ሰዓት ስለመተኛታቸው እንደ ወላጅ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ልጆች ማረፍ በሚገባቸው የመኝታ ሰዓት ተገቢ ባልሆኑ ተግባራት የሚጠመዱ ከሆነ በአካልም ሆነ በአዕምሯቸው ላይ የሚፈጠረው ጫና በትምህርታቸው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡

ውድ ወላጅ እንግዲህ ልጆቻችንን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚቻልባቸው ቀላል ዘዴዎች 9ኙን የጠቆምንበት  መልዕክት በዚሁ ተጠናቋል፡፡

እንደ ወላጅ ከጽሑፉ ልጅዎን በትምህርቱ/ቷ ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ነጥቦች እንዳገኙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እባክዎ ልጆችዎን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ለመርዳት እንደወላጅ ሃላፊነትዎን በአግባቡ ይወጡ የዛሬው መልዕክታችን ነው፡፡ ሰላም!

Al-Afia Schools‘ Community

16 Dec, 18:31


ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ስኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው 9 ቀላል ዘዴዎች

Easy ways for parents to support their children's studies


ክፍል 1

ባለንበት ዘመን ልጆች ማሳደግ እጅግ ፈታኝ ከሆኑት ሃላፊነቶች አንዱ ነው፡፡ “ልጄ ምርጥ ትምህርት አግኝቶ ስኬታማ መሆን እንዲችል እኔ ምን ማድረግ አለብኝ?” የሚለውም እንደወላጅ በጣም አሳሳቢና ዕረፍት የማይሰጥ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ አፋጣኝና ተገቢ ምላሽ የሚሻ:: የልጅዎትን የትምህርት ሁኔታ ሲያስቡም ልጆችን በትምህርታቸው ለመርዳት ይህ ነው የሚባል አስተዋፅኦ ማበርከት የማይችሉ ሊመስልዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጥናቶች እንደሚነግሩን ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው መርዳት ወይም ሥኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው በርካታ ዘዴዎች መኖራቸውን እንገነዘባለን፡፡

እኛም ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚችሉባቸው ቀላል ዘዴዎች መካከል 9ኙን ለዛሬው ሳምንታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በርዕሰ ጉዳይነት መርጠናል፡፡ በጽሑፉ ልጆችዎትን በትምህርታቸው ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ዕውቀቶችን እንደሚቀስሙበት እምነታችን ነው፡፡ መልካም ንባብ

1. ልጆችዎ ሲማሩ የሚቸገሩበት ስለመኖሩ ጊዜ ሰጥተው ይጠይቋቸው፡፡ ቀረብ ብለው ያወያዩዋቸው፤ የሚችሉትን ዕገዛም ያድርጉላቸው!!

ልጆችዎን በትምህርታቸው ከሚረዱበት ዘዴዎች እጅግ ቀላል የሚባለው የልጆችዎን የትምህርት እንቅስቃሴ እርስዎም ጉዳዬ ብለው እንደሚከታተሉዋቸው ማሳየት፤ የሚከብዳቸው ትምህርት ካለም እነርሱን መጠየቅ ነው፡፡ “ትምህርት እንዴት ነው? ምን ችግር ገጠመህ/ሽ? የምረዳህ/ሽ ነገር አለ?” እና መሰል ጥያቄዎችን ልጆችን ቀርቦ መጠየቅ ቀላል ግን የላቀ ፋይዳ የሚገኝበት ነው፡፡ ግን ስንቶቻችን ነን ሥራዬ ብለን ይህን የምናደርገው? ስንቶቻችን ነን ልጆቻችንን ት/ቤት ከመላክ በዘለለ እንዲህ በትምህርታቸው ተጨንቀን የምንጠይቅ? እራሳችንን እንጠይቅ! ልጆችዎ የርስዎን ዕርዳታ ሲፈልጉ ለዚህ ዝግጁ መሆንዎን ማወቃቸው በራሱ እርስዎ ለእነርሱ ትምህርት ዋጋ እንደሚሰጡ ብሎም ከጎናቸው መሆንዎን ለማሳየት ጭምር ይጠቅማል፡፡ ልጀችዎ የሚቸገሩበትን የትምህርት ርዕስ (topic) ለእርስዎ መጥተው ካሰረዱዎት በቻሉት መጠን ሳይዘገዩ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባዎታል፡፡ ልጅዎን የገጠመው/ማት የትምህርት ችግር ከአቅም በላይ ከሆነም በጉዳዩ ዙሪያ የተሻለ መርዳት የሚችሉ ባለሙያዎችን በማማከር አለያም በትምህርቱ ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍትን ገዝተው ማቅረብን እንደ መፍትሔ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ልጆችዎ ላይ የሚያስተውሉት የትምህርት ችግር እየከፋ ከሄደና ለመስተካከል ረጅም ጊዜ የሚፈልግ አይነት ከሆነ ልጅዎን በትምህርት አይነቱ (subject) ዙሪያ የግል አስጠኚ መቅጠርዎ ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ልጅዎ ከትምህርት ገበታ የቀረ ወይም ታሞ ከነበረ አለያም ሌላ የጤና ችግር ገጥሞት የትምህርት አቀባበሉ ላይ ጉልህ ችግር ከተፈጠረ ከት/ቤት ባሻገር ቤት መጥቶ በግል የሚረዳው የትምህርት ባለሙያ (አስጠኚ) ቀጥሮ ልጅዎ እንዲረዳ ማድረግ ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡

2. ልጆችዎ ማንበብን የደስታ ምንጫቸው እንዲያደርጉ ያበረታቱ

ማንበብ የብዙ ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎች አይነተኛ ባህሪ ነው፡፡ ወላጆች ይህን ተግባር ልጆች ይተገብሩት ዘንድ ማበረታታት አለባቸው፡ ይህን ማድረግ ምን ይከብዳል? ወደ ቤተ-መጻሕፍት ሲሄዱ ልጆችዎንም ይጋብዟቸው ፣ በቤትዎ በቂ መጽሐፍ እንዲኖር ያድርጉ ከተቻለም የቤት ውስጥ ቤተ-መጻሕፍት (ላይብረሪ) ይኑርዎት፤ ልጆችዎ የተሻለ የትምህርት ውጤት ካመጡም መጽሐፍ ይሸልሟቸው፤ ስጦታም ያበርክቱላቸው፡፡ እነዚህ ተግባራት በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች የንባብ ፍቅርን ለማስረፅ የሚያስችሉ ቀላል ዘዴዎች ሆነው ማገልገል ይችላሉ፡፡

3. በቤት ውስጥ የፀጥታ ጊዜ እንዲኖር ያድርጉ

በቤት ውስጥ ያሉ ህጻናትም ሆኑ ዐዋቂዎች እየተንጫጩና እየረበሹ ሌሎች ልጆች ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው በአንድ ልብ ማንበብ፣የቤት ስራቸውንም ሆነ ሌሎች በትምርት ቤት የታዘዙትን መስራት ይቸግራቸዋል፤ ሀሳባቸው ይበታተንባቸዋል፡፡ የተሰበሰበ ትኩረት ማድረግ ይሳናቸዋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ታዲያ በቀን ውስጥ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምንም አይነት የልጅዎትን ትኩረት የሚነሳ ጫጫታና ረብሻ የማይኖርበት የጸጥታ ጊዜ ስርዓት በቤትዎ ውስጥ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህም ልጆች በቤት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ተግባራት በተረጋጋና ፀጥታ የሰፈነበት (distraction-free) በሆነ ሁኔታ እንዲሰሩ ያመቻቻል፡፡


4. ከልጆችዎ ት/ቤትና መምህራን ጋር ቅርብ ይሁኑ

ት/ቤት የነገ የልጅዎ ማንነት የሚቀረፅበት ስፍራ ነውና እንደ ወላጅ የልጆችዎን ት/ቤት ጉዳዬ ብለው ሊከታተሉ ይገባል፡፡ አሁን እያነበቡ ያሉት ሳምንታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክትን  ጨምሮ ሌሎች በት/ቤቱ የሚዘጋጁ መልዕክቶችን (ዕለታዊ፣ወርሃዊ … ) በሚገባ ማንበብና ቦታ ሰጥተው መረዳት እንዲሁም ከልጆችዎ መምህራን ጋር በቅርብ መነጋገር ይጠበቅቦታል፡፡ ከዚህ ባሻገር በየጊዜው ስለ ልጆችዎ የትምህርት ጉዳይ ሳይታክቱ ከመምህራን ጋር በመወያየት (በመጠየቅ) ልጅዎ ምን አይነት ድጋፍ ከእርስዎ እንደሚያስፈልገው መረዳት ይጠበቅብዎታል፡፡ ከልጅዎ መምህራን ጋር ቅርርብ በመፍጠር በሚኖርም ውይይት ልጆችዎ ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉባቸው ክፍተቶችንም ይገነዘባሉ፡፡

ክፍል 2 ይቀጥላል

Al-Afia Schools‘ Community

13 Dec, 16:42


በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሸያ (Remedial) ትምህርት ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፣

👉ለመደበኛ Remedial ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

⚡️በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

👉በግል ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

💥ለምዝገባ ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ፣ 3*4 የሆነ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፤

• የካምፓስ ምደባ በሚመለከት ከዚህ በታች በተገለጸዉ መሠረት ይሆናል።

Natural Science

ስማቹህ A to G የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
ስማቹህ H to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

Social Science

ስማቹህ A to J የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
ስማቹህ K to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

#WachamoUniversity #Remedial

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Al-Afia Schools‘ Community

07 Dec, 14:36


ልጆችን ማበረታታት

ትምህርት ለልጆቻችን የወደፊት ስኬት ዋንኛው መሰረት መሆኑን ሁላችንም እንገነዘባለን፡፡በመሆኑም ወላጆች ልጆቻችን  በትምህርታቸው ስኬታማ መሆን ይችሉ ዘንድ ተገቢውን ትኩረት አድርገን መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ልጆችን ማበረታታት ደግሞ  የልጆቻችንን ስኬት ዕውን ማድረግ ከምንችልባቸው ቁልፍ ዘዴዎች  መካከል ነው፡፡

በወላጅዎች የሚበረታቱ ልጆች ከሌሎቹ የበለጠ ውጤታማ የመሆን ዕድል እንዳላቸው በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ በርካታ ሙሁራን ይናገራሉ፡፡ በወላጆቻቸው ተገቢውን ማበረታታት የሚደረግላቸው ልጆች ለትምህርት የሚኖራቸው አመለካከትም እየተስተካከለ እንደሚሄድ ጭምር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የዛሬው መልዕክታችን ርዕሰ-ጉዳይ  ልጆችን ማበረታታት ላይ እንዲያተኩር መርጠናል፡፡ ልጆች በምን መልኩ ብናበረታታቸው ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተወሰኑ መንገዶችን እንዲካተት አድርገን ከዚህ በሚከተለው መልኩ አሰናድተን ለማቅረብ ሞክረናል፤ መልካም ንባብ፡፡

1.ከልጅዎ ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግልፅ እና አዎንታዊ ግንኙነት ተግባራዊ በማድረግ ልጅዎን ያበረታቱ

ይህን ማድረግ በልጅዎ ላይ እጅግ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉበት ታላቅ መሳሪያ ነው፡፡ ለልጅዎ  በዚህ ርቀት ቅርብ መሆን ከቻሉ በእርግጥም በሚገባ እያበረታቱት መሆኖን ልብ ይበሉ፡፡

2. በልጅ አስተዳደጎ ሩህሩህ በመሆን ልጅዎን ያበረታቱ

ከሀይልና ከልክ በላይ ቁጥጥር እንዲሁም ቁጣና ቅጣት ታቅበው ለልጅዎ  ሩህሩህ ፣ ተባባሪ አና ጽኑ  ወላጅ ለመሆን  የድርሻዎትን ይወጡ፡፡ከልጅዎ ጋር በሚኖርዎት ቅርርብ ለምትፈጠር እያንዳንዷ  አሉታዊ ግንኙነት ብዙ እጥፍ አዎንታዊ አብሮነት በመፍጠር በጊዜ ያብሱት፡፡ልጆችዎን በሆነ ባልሆነ  ከመጨቅጨቅና ከማስጨነቅ ይልቅ እነሱን ርህራሄ በተሞላበት ሁኔታ በማገዝና ማበረታታት ላይ ትኩረትዎ እንዲሆን ያድርጉ፡፡

3.ከልጅዎ ጋር የመነጋገር ባህል  በማዳበር ልጅዎን ያበረታቱ

ልጆች በትምህርታቸው ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ስለትምህርት ፈላጎታቸው እና ችሎታቸው ማውራት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ወላጆች ልጆቻቸውን ሊያደምጧቸው፣ ጠንካራ ጎኖቻቸውንም  እውቅና ሰጥተው ሊያበረታቷቸው ይገባል፡፡ ለምሳሌ  “በጣም የምትወደው የትምህርት አይነት ምንድን ነው?”  “ እንዴት ይሄ ሊሆን ቻለ?” እያሉ መጠየቅና መወያየት  ፋይዳው የላቀ ነው፡፡

 4.የልጅዎን የትምህርት ዝንባሌ ዝቅ አድርጎ ባለመመልከት ያበረታቱ

የልጅዎ የትምህርት ምርጫ(ፍላጎት)  እርሶ ከሚያስቡትና ከሚጠብቁት የሚቃረን ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን  የልጅዎን ፍላጎት ማክበርና በመረጠው ፊልድ ስኬታማ ይሆን ዘንድ ማበረታታት የላቀ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ልጅዎ የስነ ፅሁፍ ፍላጎት እና ዝንባሌ ያለው ሆኖ እርሶ ግን ንባብ  ላይ እምብዛም ስለሆኑ ብቻ ስነ ጽሁፍን ፋይዳቢሰ  የትምህርት ዘርፍ (ፊልድ) አድርገው የልጅዎን የአስተሳሰብ ነፃነት መጫን አይገባም፡፡ ባይሆን ልጆዎን በዝንባሌው መሰረት ውጤታማ ይሆን ዘንድ በተለያየ መልኩ ግብዓቶችን በማቅረብ እንዲሁም ወደ ቤተ-መጽሀፍት ይዘው መሄድ  ከሁሉም ወላጅ የሚጠበቅ ልጆችን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ የማበረታታት አይነተኛ ዘዴ  ነው፡፡

5. ለልጅዎችዎ ጥረት ተገቢውን ዕውቅና በመስጠት ያበረታቱ

ልጆች ከውጤታማነት በላይ ጥረቶቻቸው በወላጅዎቻቸው ተገቢውን እውቅና ተሰጥቷቸው መመልከት ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤  የበለጠም ያበረታታቸዋል፡፡ለልጆቻቸን ጥረቶች ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተን የምናበረታታ ከሆነ ልጆች ከውጤት ባሻገር ትምህርትን ጠንክሮ መማር የበለጠ ዋጋ እንዳለው መረዳት ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ልጅዎ ፈተና የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ ከውጤቱ በላይ ጠንክሮ ማጥናቱ ላይ ትኩረት አድርገው አስተያየት ይስጡ፡፡ “አየህ ለፈተና ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ ከንቱ አልቀሩም፤ በእርገጥም በውጤትህ ተንፀባርቋል፡፡ ” በማለት የልጅዎን ብርቱ የጥናት ሂደት ማበረታታት በልጅዎ የትምህርት ስኬት የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡

6.ልጅዎችዎ ውጤት ባያስመዘግቡምኳ የበረታቷቸው

ልጅዎችዎ እንደጠበቁት ውጤታማ ሆነው ሳይገኙ ሲቀሩ ወደፊት እንዴት ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገንቢ ምክሮትን በመለገስ ያበረታቷቸው፡፡ ውጤት ስላልተመዘገበ ብቻ የልጅዎን ጥረትና ድካም በፍጹም ዝቅ አድርገው አይመልከቱ፡፡እነዲህ የሚያደርጉ ከሆነ ልጅዎ ወደፊት ስህተቱን አርሞ፤ ክፍተቱንም ሞልቶ ወደ ውጤታማነት ከመገስገስ ይልቅ ጠንክሮ ማጥናትና ጥረት ማድረጉ ፋይዳ እንደሌለው በማሰብ ፊቱን ከትምህርት ይልቅ ወደ ሌላ በማዞር ቀጣይ የትምህርት ህይወቱ ላይ አደጋ ሊደቀን ፤ስኬታማነነታቸውንም ሊያጨናግፍ ይችላል፡፡ ልጆች ውጤታቸው ምንም ያህል ዝቅ ቢልኳ “   አንተ ሰነፍ፤የማይገባህ፣  ” እና  መሰል እጅግ ጸያፍ እና አፍራሽ የፍረጃ ቃላትና ውንጀላዎች  ወላጅዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ለልጅዎ ካስመዘገበው  ውጤት በላይ እነደሚጠብቁና ለዚህም ተባብሮ ለመስራት እስከመጨረሻው
ዝግጁነትን ከማንጸባረቅ  ውጭ ልጆችን በወቀሳ ናዳ ማስበርገግ ፤ በዛቻ ማዕበል ማጥለቅለቅ  የማበረታታት ተቃራኒ የስኬታማነትም ፀር ነው፡፡

7.በልጅዎችዎ ላይ የሚተገብሯቸው የቅጣት ዕርምጃዎች ሁሉ ልጆችዎ የተሻሉ ሆነው ይቀረጹ ዘንድ ለማበረታተት እንጂ ለሌላ አለመሆኑን በተግባሮትና በቃልዎ ይረጋግጡላቸው፡፡

ለምሳሌ “አበዛኛውን ሰዓት ለቲቪ ሰጥተህ ከጥናትህ በመዘናጋትህ ውጤትህ ምን ያህል መበላሸቱን ተመልከት?!” ብሎ መገሰጥም  ልጆችን ከአገጓጉል ተግባራት እንዲታቀቡ በመርዳት ማበረታታት ሊሆን የችላል፡፡

8..ለልጅዎ ውጤታማነት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ያበረታቱ፤የአጠናን ዘዴዎቻቸውንም ይፈትሹ

የተለያዩ የመማር ወይም የጥናት ዘዴዎችን ለልጆችዎ በማመላክትም ማበረታታት ይችላሉ፡፡ ልጆች መጽሀፍና ደብተሮቻቸው ላይ አፍጥጠው እንዲታዩ ብቻ ማስገደድ ልጆችን ከማሸማቀቅና ከማሰልቸት የዘለለ ሚና ላይኖረው ይችላል፡፡ ልጆች ጥናታቸውን በተገቢ መልኩ እንዲያካሂዱ የሚመቻቸወን የጥናት ዘዴ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከነሱ ጋር በጋራ መወያየት እና መመካከር ያስፈልጋል፡፡ የልጅዎችዎን መምህርም በዚህ ዙሪያ እያወያዩ ፤ ጥናት ፕሮግራም በማዘጋጀት ክትትልና ድጋፎችን በማድረግ   ማበረታታት ልጅዎን የላቀ ውጤት ባለቤት እንዲሆን  ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ስለዚህ ሁላችንም ልጆቻችንን በተገቢው ሁኔታ ሳንታክት በማበረታታት  ስኬታቸው ዕውን ይሆን ዘንድ ሁሌም ከጎናቸው ልንሆን ይገባል፡፡

Al-Afia Schools‘ Community

07 Dec, 07:17


እናመሰግናለን
ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡-
ህዳር 27 ቀን 2017 በሁሉም ካንፓሶቻችን ተካሂዶ በነበረው የት/ዘመኑ የመጀመሪያው የወላጅ-መምህር ኮንፍረንስ “ስለልጄ ለመወያየት ከጥሪ በላይ አያስፈልገኝም” በሚል የጥዋት ብርድ ተቋቁማችሁ፤ የስራ ሰዓታችሁም ሳይበግራችሁ ጭምር በነቂስ በመውጣት በሩብ ዓመቱ በት/ቤቶቻችን ልጆቻችሁ ስለነበራቸው አጠቃላይ የትምህርት አቀባበል እና የስነ-ምግባር ሁኔታ ከመምህራን ጋር በመወያየት ላሳያችሁት ቁርጠኝነት እጅግ አድርገን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

በዚህ ልክ ተግባብተን እና ተጋግዘን በጋራ ከሰራን በእርግጥም የልጆቻችን ሁለንተናዊ ከፍታ ዕውን ይሆናል፡፡

አል-ዓፊያ ት/ቤቶች ፅ/ቤት

Al-Afia Schools‘ Community

04 Dec, 09:16


የወላጅ-መምህር ግንኙነት
የወላጅ - መምህር ግንኙነት ልጆች በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡የወላጅ-መምህር ግንኙነት የተማሪን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሁለት ወሳኝ ባለድርሻ አካላት መካከል የሚኖረውን ትብብር ለማጠናከር ከሚረዱ እስትራቴጂዎች አንዱ ወሳኙ ነው፡፡ 

ወላጆች ከልጆቻቸው መምህራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ስለሚኖረው ፋይዳ በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል፡፡ ከጥናቶቹ መረዳት እንደሚቻለው በልጆቻቸው ትምህርት ዙሪያ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉ ወላጆች በዚያው መጠን የልጆቻቸው ውጤትም በከፍተኛ  ደረጃ እንደሚሻሻል ነው፡፡

ውጤታማ የወላጅ - መምህርን ግንኙነት እንዲኖር መጀመሪያ መሆን ያለበት ከልጅዎ መምህር ጋር የሚኖርዎት ውይይት መረጃ መሰብሰብ ላይ ብቻ የሚገደብ አለመሆኑን ጠንቅቆ መረዳት ነው፡፡ የወላጅ-መምህር ግንኙነት ፋይዳው ልጅዎን በትምህርት ቤት ዙሪያ ሳለ የሚታይበትን የባህሪ ሁኔታ በሚመለከት መረጃ ከመሰብሰብም በላይ ነው፡፡

የወላጅ መምህር ግንኙነት ወላጆችና መምህራን አንድን ተማሪ አስመልክተው በት/ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ ምን ዓይነት የትምህርት ብቃት(capacity) እንዲሁም ባህሪ(behavior) እንዳለው ጠቅላላ መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው፡፡ አንድ ተማሪ በትምህርት  ቤትም ሆነ በቤት ውስጥ ያለውን ጠንካራ ጎን እንዲሁም መስተካከል ያለበትን ድክመት በግልጽ ተወያይተው የጋራ መፍትሄ የሚያበጁበት ነው፡፡የወላጅ -መምህር ግንኙነት (parent-teacher communication):: ወላጆች ልጆቻቸው ቤት ውስጥ እንዴት ለትምህርታቸው ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ተገቢውን ምክርና ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የወላጅ-መምህር ግንኙነት የሚያበረክተው አስተዋፆም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡

ሆኖም ግን በርካታ ወላጆች ይህን ሁሉ በሚገባ የተረዱት አይመስልም፡፡ እነሱ መስራት የሚገባቸውን ተግባራት ሁሉ የትምህርት ቤት መምህራን ብቻቸውን እንዲወጧቸው ሲጠብቁ በተደጋጋሚ ይስተዋላል፡፡ ልጆች ቤት ውስጥ የሚደረግላቸው የቤተሰብ ድጋፍ እና ክትትል እጅግ ከፍ ያለ ሚና ሲዘነጉ ይስተዋላል፡፡

ስለ ልጆች አጠቃላይ ሁኔታ ከሌላው ሰው ቀድመው የሚረዱት ወላጆቻቸው ናቸው፡፡የልጆችን ባህሪ፣ የትምህርት አቀባበላቸውን እንዲሁም ያላቸውን ዝንባሌ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን ጭምር ከመምህራን በፊት የሚያውቁት ወላጆች ናቸው፡፡ መምህራን የዚህን ያህል ርቀት ተጉዘው የተማሪውን የልብ ትርታ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

አንድ መምህር የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች ሁሉ በሚገባ ተረድቶ ተገቢ መፍትሄ ማበጀት እንዲህ ቀላል ስለማይሆን ወላጆች የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን (means of communication) በማመቻቸት የልጆቻቸውን ባህሪ፣ጠንካራ እና ደካማ ጎን ከልጆቻቸው መምህራን ጋር በመወያየት መምህሩ/ሯ ተማሪውን በሚገባ ተረድቶ የተሻለ ድጋፍ ያደርግለት ዘንድ ከነሱ የሚጠበቀውን ካደረጉ በርግጥም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ጥረት አድርገዋል ማለት ይቻላል፡፡

የወላጅ-መምህር የቅርብ ግንኙነት ልጆች በትምህርት ቤትም ሆነ ከዚያ ውጭ ባለ ህይወታቸው ስኬታማነትን ይጎናፀፉ ዘንድ በጣም እስፈላጊ ግብዓት መሆን ይችላል፡፡በወላጅ እና መምህራን መካከል በተማሪው ዙሪያ የሚመክር የግንኙነት መስመር ሲኖር ተማሪውም እሱን የላቀ ደረጃ ለማድረስ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ የሚንቀሳቀስ ጠንካራ የትብብር መድረክ መኖሩን እንዲረዳ ያስችለዋል፡፡

በተመሳሳይ ወላጆችና መምህራን በቅርብ እነደሚገናኙና እነደሚወያዩ የተረዱ ልጆች ብዙውን ጊዜ ከሌሎቹ የተሻለ ከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ይሰማቸዋል፤ በውጤታቸውም ብልጫ ይኖራቸዋል፡፡ከዚህም ባሻገር በትምርት ቤት ውስጥም በባህሪያቸው የተመሰገኑ ጎበዝ ተማሪዎች ይሆናሉ፡፡

የወላጅ- መምህር ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ የተወሰኑትን እንመልከት፡-

1. በወላጆችና መምህራን መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች ዓላማቸው የልጅዎን የትምህርት ውጤት ማሻሻል መሆኑኑን ይረዱ፡፡ልጅዎ ነገ የተሻለ ዜጋ ሆኖ ይቀረጽ ዘንድ ዛሬ እየተደረገ ያለ ጥረት መሆኑን ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባም፡፡

2. ስለ ልጅዎ የትምህርት ውጤት ሲነሳ ጠንካራ ጎን ላይ ብቻ ትኩረቶን ከማድረግ ተቆጥበው መሻሻል የሚገባውንም በመለየት መወያየት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

3. ስለ ልጅዎ ለመወያየት ሁል ጊዜ ኮንፍረንስ ብቻ አይጠብቁ፡፡ከልጅዎ መምህር ጋር መገናኘትና መወያየት መደበኛ(regular) ተግባርዎ ያድርጉ፡፡ በዚህም ልጅዎ ላይ ጤናማ ያልሆነ ክስተት ቢፈጠርኳ በጊዜ ተረድተው አፋጣኝ የመፍትሄ  እርምጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡

እነዚህን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ ከልጅዎ መምህር ጋር ያልዎት ግንኙነት እየተጠናከረ ይመጣል፤ሁሌም የሚያልሙት የልጅዎ ስነምግባርም ሆነ የትምህርት ውጤት ከፍታም እውን መሆን ይችላል፡፡
ጠንካራ የወላጅ መመምህር ግንኙነት ለተማሪዎች ውጤታማነት

Al-Afia Schools‘ Community

03 Dec, 11:55


ክፍል 3 (የመጨረሻ ክፍል)

11. ሚዲያ በልጆች የስሜት እና በጤናማ ማህበራዊ ግንኙነት መዳበር ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል/IMPACT on SOCIAL-EMOTIONAL DEVELOPMENT/

የስሜት መዳበር እንደሌሎች የመዳበር ዘርፎች በሂደት የሚያድግ ሲሆን እደገቱ ስኬታማ እንዲሆን የቤተሰብ፣ መምህራን እና የሊሎችም ሚና በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የስሜት መዳበር በአእምሮ መዳበር አማካኝነት የሚከሰት ለውጥ ሲሆን የራስን ስሜት መረዳትና መቆጣጠር መቻልን እንዲሁም ለሌሎች ርህራሄ እና ፍቅር እንዲኖረን የሚዳርግ ነው፡፡ ይህ እድሜ ሲጨምር የበለጠ እየዳበረ የሚሄድ የመዳበር ዘርፍ ነው፡፡ ነገር ግን ለእደገቱ ወሳኝ የሆነ ሁኔታ እስካልተፈጠ ድረስ ለውጡ የሚታሳብ አይደለም ይሉቁንም የራሳቸውን ስሜት ብቻ የሚያስቀድሙ እና ለሌሎች ደንታ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህ ረገድ ሚዲያ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን ይህም የሚሆን ለረዥም ሰዓታት በትዕንት መስኮት ጊዜን ማሳለፍ በእውነተኛው ህይወት የሰዎችን ስሜትና ሁኔታ ለመመልከት ጊዜ እንዳይኖራቸው ስለሚያደርግ ነው፡፡

የልጆች ስሜት አወንታዊ በሆነ መንገድ እንዲደብር ከሰዎች ጋር መገናኘትና መስተጋብር መፍጠር አስፈላጊ ነው። ሚዲያ በልጆች ስሜታዊና ማህበራዊ መዳበር ላይ የሚዳርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ በተመለከተ በስድሰተኛ ክፍል ተማሪዎች የሰዎችን በፎቶና ቪዲዮ ስሜታቸውን የመረዳት ችሎታ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ ከነዚህ ተማሪዎች የተወሰኑት ለአምስት ቀናት ትዕይንቶችን በሚዲያ መስኮት እንዲመለከቱና የተቀሩት ደግሞ ምንም አይነት ትዕይንት በሚዲያ እንዳይከታተሉ በማደረግ ያላቸወን የሰዎች ስሜት የመረዳት ችሎታ ለመለካት የተቻለ ሲሆን ውጤቱ እንደሚያሳየው ለአምስት ቀናት ሚዲያ ያልተከታተሉ ልጆች ከጥናቱ በፊት ከነበራቸው የሰዎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ የበለጠ መሻሻል ሲያሱ ለአምስት  ቀናት ሚዲያ የተከታተሉት ግን በተቃራኒው በፊት ከነበራቸው ስሜትን የመረዳት ችሎታ ያነሰ ሁኖ ተመዝግቦል፡፡  ከሚዲያ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከሰዎች ጋር የሚኖርን የርስበርስ ግንኙነት እንዲቀንስ በማድረግ በሰዎች ላይ የስሜት ምልክቶችን መከታተል እንዳይችሉ እና የሰዎችን ስሜት የመረዳት ችሎታም እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን ወጤቱም የስሜት መዳበርን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳ የጥናቱ ተመራማሪዎች አስተውቀዋል፡፡


ሚዲያ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ለማስቀረት ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ነገሮች

ሚዲያ በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና ያለውን አወንታዊ አስተዋፅኦ ለመጨመር ወላጆች ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ያደረጉ ሙህራኖች ያሳስባሉ፡፡ ነገር ግን የሚዲያን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና አወንታዊ አስተዋፅኦ የማሳደግ ተግባር በወላጆች ብቻ የሚሳካ ተግባር ሳይሆን የመምህራን፣ የሚዲያው ባለቤቶች፣ የመንግስት ፖሊሲ አውጭዎችና አስፈፃሚዎችን ቁርጠኝነት የሚፈልግ ነው፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን ምክሮች ወላጆች በመተግበር  ሚዲያ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመቀነስ አወንታዊ አስተዋፅኦውን ለመጨመር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡

1. ልጆች በተለይ እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚመለከቱበትን ጊዜ መቀነስ

2. የኤሌክትሮኒክስ መጫወቻዎችን መቀነስና በምትኩ ሌሎች መጫወቻዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ

3. የተለያዩ የፈጠራ ችሎታን የሚያሳድጉ መጫወቻዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት ለምሳሌ የሚገጣጠሙ፣ የሚደረደሩ እና በተግባር ልጆች እያዩና እየነካኩ ሊጫወቱባቸው የሚያስችሉ መጫወቻዎች

4. በምግብ ሰዓት ቴሌቭዥን መዝጋት እንዲሁም ሌሎች ሚዲያዎችንም እንዳይጠቀሙ ማድረግ መረሳት የለበትም

5. በመተኛ ክፍሎቻቸው ልጆች ቴሌቭዥን ፣ኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙና እንዳይጠቀሙ ማድረግ።

6. ልጆችን ከኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ውጭ የሆኑ የመዝናኛ ተግባራትን ማለትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚጫወቱባቸው፣ የአእምሮ ተግባራትን የሚፈልጉ ጨዋታዎች እና ተግባራት በመስራት እንዲያዘወትሩ ማበረታታት

7. ለልጆች እድገት አስፈላጊ የሆኑ እና ትምህርት ሰጭ የሆኑ የቴሌቪዝን ፕሮግራሞች በመምረጥ አንድላይ ከልጆች ጋር ሁነው መመልከት የሚገባ ሲሆን በሚመለከቱበት ጊዜም ልጆች የተመለከቱትን ነገር ምን ያህል እንደተረዱት መጠየቅ፣ ማብራሪያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

8. በሚዲያ አጠቃቀማቸው ወላጆች ለልጆች ጥሩ አርዓያ እና ምሳሌ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ልጆችን በቤት ውስጥ አስቀምጦ የአዋቂ ይዘት ያላቸው ፊልሞች፣ፕሮግራሞች የመመልከት ሁኔታ በየቤቱ ይስተዋላል ፡፡ ይህን በማስወገድ ተገቢ ወደሆኑ ተግባራት ማምራትና ማከናወን ይገባል ፡፡ ለምሳሌ ማንበብ፣ የተለያዩ የወረቀት ስራዎችን መስራት ወዘተ ይህን ልጆች በሚመለከቱበት ጊዜ እነሱም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ ፡፡

9. ወላጆች የራሳቸውን የሚዲያ አጠቃቀም መገደብ በምትኩ ለልጆችም ጊዜን በመመደብ የተለያዩ ታሪኮችን፣ ተረቶችን ማውራትና የልጆችን አዕምሮ የሚያሳድጉ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና ተግባራትን መስጠት ይገባል፡፡

10. ወላጆች ከጎረቤቶቻቸው እና ከአካባቢ ሰዎች ጋር ስለልጆቻቸው የሚዲያ አጠቃቀም፣ የሚዲያ ተፅዕኖ በማንሳት መወያየትና የጋራ የሆነ መግባባት ላይ መድረስ ይገባቸዋል፡፡ ምክኒያቱም ልጆች በቤታቸው የሚያዩት ፊልሞች ቢከለከሉ ሌላኛው ቤት ውስጥ በመሄድ የማየት ሁኔታ ስለሚኖር ተመሳሳይ የሆነ መግባባት ላይ መድረስ ይገባቸዋል፡፡

11. ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ስለተለያዩ የቤተሰብ፣ አገራዊ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮች በማንሳት የመወያየት ልማድ ሊያዳብሩ ይገባል፡፡

T.A (MA in Developmental       Psychology)

Sources
Heather L. Kirkorian, Ellen A. Wartella, (2008) Media and Young Children’s Learning: 18 / NO. 1 / Retrived in http://
www.futureofchildren.org

Children, Adolescents, and the Media, October 2005 Revised February 2014 by Jane Anderson, MD Revised July 2016 by Jane Anderson, MD

The Impact of Media Use and Screen Time on Children, Adolescents, and Families American College of Pediatricians – November 2016

Al-Afia Schools‘ Community

02 Dec, 10:27


ክፍል 2…

3. በልጆች ባህሪይና ትኩረት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ/IMPACT on BEHAVIOR and ATTENTION/

ልጆች በቀን ውስጥ ለረዥትም ሰዓታት የተለያዩ ትዕይንቶችን በሚዲያ የሚመለከቱ ከሆነ በባህሪያቸውና በነገሮች ላይ ትኩረት የማድረግ ብቃታቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር ለእንቅልፍ መዛባትን በማስከተል የአእምሮ እድገታቸው ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል፡፡  እ.አ.አ በ2016 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በስክሪን ነገሮችን የመመልከት ጊዜ እና ዝቅተኛ የመኝታ ሁኔታ እና የባህሪ ችግሮች እንደሚያያዙ አረጋግጧል፡፡ በታዳጊ እድሜያቸው ቴሌቪዥንን የሚመለከቱበት የሰዓት ብዛትና ለወደፊት ከሚኖር የትኩረት ችግር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለ ሲሆን በተለይ እድሜያቸው አንድ እና ሶስት አመት የሆናቸው ልጆች በቀን ውስጥ ለሰዓታት ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ከሆነ እነዚሁ ልጆች ሰባት አመት ሲሞላቸው ለትኩረት ችግር እንደሚገጥማቸው በዚህ ጥናት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

4. ለወሲብ ተጋላጭ የሆኑ ባህሪያቶችን እንዲላመዱ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፡፡ IMPACT of MEDIA on SEXUAL RISK BEHAVIORS

በፊልሞች፣ በቴሌቪዥን፣ እና በሙዚቃ ክሊፖች በአብዛኛው ወሲባዊ መልዕክቶች በግልፅ የሚሰራጩ ቢሆነንም አነዚህ መልዕክቶች የተሳሳቱና ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመሩ ናቸው፡፡ እንዳለመታደል ሁኖ እነዚህ መልዕክቶች በታዳጊዎች እውነተኛ እንደሆኑ ተድሮጎ ተቀባይነት ማግኘታቸው ነው፡፡ በሚዲያ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች እና የማስታወቂያ ይዘቶች በብዛት ወሲብ ነክ ናቸው፡፡ ወጣቶችም ሚዲያን እንደ ዋነኛ የወሲባዊ ባህሪያት የመረጃ ምንጭ አድርገውታል፡፡  በዚህም ምክንያት ታዳጊዎች ባገኙት የተሳሳተ የወሲብ መረጃ በራሳቸው ህይወት ያለጊዜያቸው በመሞከር ለተለያዩ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወሲባዊ ይዘት የተቀላቀለባቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን አብዝተው የሚያዩ ወጣቶች ከማያዩ ወጣቶች የበለጠ ያለጊዜያቸው የተለያዩ ወሲባዊ ተግባሮችን ለመጀመር ይነሳሳሉ፡፡ታዳጊ ወጣቶች ከፍተኛ ደረጃ የወሲብ ይዘት ላለው ነገር የተጋለጡ ከሆነ ከሌሎች ካልተጋለጡ ወጣቶች  ጋር ሲነፃፀሩ ሁለት እጥፍ በቀጣዮች ሦስት አመታት የማርገዝ እድል አላቸው፡፡ አነዚህ ጥናቶች በተጨማሪ እንደሚያሳዩት ወሲብ ነክ የንግግር ልውውጥ በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከቱትም ልክ ወሲባዊ ተግባራትንም እንደሚመለከቱ ወጣቶች ተመሳሳይ ችግር ይጋለጣሉ፡፡

5. አልኮልና ሲጃራ ተጠቃሚነት ያስከትላል፡፡ /IMPACT on TOBACCO and ALCOHOL USE/

ከመጠን ያለፈ የቴሌቪዠን፣ ፊልሞችን እንዲሁም የኮምቢውተርና የቪዲዮ ጌሞችን መመልከት ለአልኮልና ሲጃራ ሱሰኝነትን ያስከትላል፡፡ በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደዘገበው ወላጆች ልቅ የሆነ ፊልሞችን ልጆቻቸው እንዳይመለከቱ በማገዳቸው ምክንያት ሲጃራ ለመጨስ የመመከር ሂደት መቀነሱ ተረጋግጦል፡፡

6.በእንቅልፍና አመጋገብ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል/ IMPACT on SLEEP and NUTRITION/

ሚዲያን መጠቀም በቂ እንቅልፍ እና ጥሩ እንቅልፍ እንዳይኖር ማለትም በእንቅልፍ ልብ መንቃት፣ ቅዠት፣ የተዛባ የእንቅልፍ ልማድ እንዲከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም በልጆች በሽታን የመቋቋም ችሎታን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የምግብ የመፈጨት ሂደትን በማስተጓጎል ልጆችን ከመጠን ላለፈ ውፍረት ይዳርጋቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆች በሽታን የመቋቋም ብቃታቸውን እንዲቀንስ እና ለተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ እንዲል የሚያደርግ ሲሆን የትምህርታቸው ውጤታቸውም  እንዲቀንስ አሉታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፡፡
በአንድ ጥናት ልጆቻቸው በመዋለ ህፃናት የሚማሩ 495 ወላጆች ስለልጆቻቸው ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድና እና የመኝታ ሁኔታ ተጠይቀው ነበር፡፡ ከነዚህ  ውስጥ 25 ፐርሰንት የሚሆኑት ወላጆች የተገኘው መረጃ በልጆች መኝታ ክፍል ቴሌቪዥን እንዳለ አሳይቶል፡፡ ይህም ልጆች ለረዥም ሰዓታት ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድ እንዲኖራቸውና በቂ የእንቅልፍ ጊዜ እንዳይኖራቸው በማድረጉ ነው፡፡ የእንቅልፍ መዛባት ችግር የሚያያዝ የበለጠ የበዛበት ምክንያት የቴሌቪዥን ምልከታው የጨመረው በልጆቹ መኝታ ቤት በመገኘቱ ምክንያት እንደሆነ የጥናቱ ተመራማሪዎች  ተናግረዋል፡፡
የእንቅልፍ ማጣት ችግር ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት፣ ከስኮር በሽታ፣ ከትምህርት ችግር፣ እና ከተለያዩ የባህሪ ችግሮች ጋር እንደሚያያዝ ጥናቶች በተደጋጋሚ ይዘግባሉ፡፡

7. ሚዲያ በትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል /IMPACT on ACADEMIC PERFORMANCE

ከመጠን ያለፈ የሚዲያ መጋለጥ በትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ እንደለው ይታወቃል፡፡ ይህን አስመልክቶ ዘመሪመን እና ክሪስታኪስ የተባሉ ተመራማሪዎች አስከሰባት አመት የሚሆናቸውን ታዳጊ ልጆች የቴሌቪዥን ምልከታ በአስተሳሳብ እና በአእምሮዊ እድገታቸው ላይ የሚሳድረውን ተፅዕኖ ለመገምገም የሚከሩ ሲሆን የግምገማ ውጤቱ እንደሚያሳያው ልጆች ሶስት አመት ከመሆናቸው በፊት ለብዙ ሰዓታት በቀን ውስጥ ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ከሆነ በአእምሮ እድገታቸው ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያደርስና ነገሮችን አንብቦ ለመረዳት እንደሚቸገሩ እና በትምህርታቸውም ዝቅተኛ ውጤት እንደሚያሰመዘግቡ ጠቁመዋል፡፡

8. ሚዲያ ለድብርት ያጋልጣል/ IMPACT on DEPRESSION/

ትዕይንቶችን በሚዲያ መስኮት ለረዥም ጊዜ መጠቀም ከድብርት ጋር እንደሚያያዝ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ በሃገረ ዴንማርክ በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል የሚገኙ 435 ወጣቶች ላይ ለረዥም ጊዜ በተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው በእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰዓት ወይም ቀን ቴሌቪዥን መመልከት በጎልማሳነት የእድገት ወቅት ለከፍተኛ ድብርት እንደተጋለጡ ተጠቁሞል፡፡

9. ሚዲያ ለጠብ አጫሪነትን እና ለሁከት ፈጣሪነት ያጋልጣል/ IMPACT on AGGRESSIVE BEHAVIOR and VIOLENCE/

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በትዕይንት መስኮት ሁከትና ብጥብጥ ያለቸውን ነገሮች መመልከት በእውነተኛው ህይወትም የጠብ አጫሪነት እና ሁከት ፈጣሪነት ባህሪያት እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡ በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ፊልሞችና ድራማዎች በአብዛኛው በይዘታቸው የጠብ አጫሪነት፣ የሁከት፣ የጥፋት፣ የድብድብ፣ ወዘተ ትዕንቶችን የተካተቱበት በመሆኑ የልጆችን አስተሳሰብ ከፍተኛ ተፅዕኖ በማሳደር እውነተኛው አለም የጥፋትና የሁከት እንደሆነ እንዲያምኑ ምክንያት በመሆን ለጠብ አጫሪነትና መሰል ባህሪያትን እንዲያሳዩ ምክያት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ህፃናት እንደዚህ አይነት ባህሪያት ያሳያሉ ማለት ሳይሆን ዝንባሌ እንዲኖራቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ለማለት ነው፡፡ ሌሎች ነገሮች ለምሳሌ በአካባቢያቸው የጠብ አጫሪነትና ሁከትን የሚያበረታቱ ሁኔታዎች ከተጨመሩ ከሌሎች ልጆች አንፃር የጎላ የባህሪ ችግሮችን የማሳየት እድላቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ከቴሌቪዥን በተጨማሪ በስማርት ስልኮችና እና በኮምፒውተር ላይ የሚጫኑ ሁከት እና ብጥብጥን የሚያንፀባርቁ ጌሞች/ጨዋታውች/ በልጆች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን ያሳድራሉ፡፡
.....ክፍል 3 ይቀጥላል

Al-Afia Schools‘ Community

01 Dec, 07:57


ሚዲያ በልጆች አእምሮዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቀነስ ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ምክሮች።

ክፍል 1…

እንደሚታወቀው በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን ሚዲያ በልጆች አስተዳደግ እና ሁለንተናዊ ማንነት ላይ ከባድ አደጋ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡በየቤቱ በርካታ ልጆችን አንዳንዴ አዋቂዎችን ሳይቀር አጉል ጠልፎ እየጣለ አያሌ ቤቶችን እያናጋ፤ ሰላምንም እያደፈረሰ ይገኛል፡፡ታዲያ እኛም ለዛሬ በዚህ ዙሪያ ጠቃሚ ግንዛቤ ያስጨብጣል ያልነውን መረጃ ለናንተ ለወላጆች እነደሚከተለው አቅርበነዋል።

መረጃው ጥናትን መሰረት አድርጎ በዘርፉ በለሙያ የቀረበ በመሆኑ ሁላችንም አንብበን ከልጆቻችን ጋር በመወያየት የመፍትሔ አካል መሆን ይጠበቅብናል።
መልካም ንባብ፡፡

የመገናኛ ሚዲያዎች በሁለት ዋና ክፍሎች የሚመደቡ ሲሆን አንደኛው ኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በመባል የሚጠራ ሲሆን እንደ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር፣ ስማርት ስልኮችን፣ ወዘተ በመጠቀም  ፊልሞችን፣ ድራማዎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ጨዋታዎችን፣ ሙዚቃዎችን እና የሙዚቃ ኪሊፖችን የሚተላለፉበት ነው፡፡ ሌላኛው ፕሪንት ሚዲያ የሚባል ሲሆን በወረቀት ላይ የሰፈሩ ፁህፎች፣ ታሪኮች፣ ዜናዎች፣ ልቦለዶች፣ ወጎች፣ መረጃዎችን፣ ወዘተ የሚያካትት ነው፡፡

ሁለቱም የሚዲያ አይነቶች በልጆች ላይ አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ያሳድራሉ፡፡ አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ለምሳሌ የልጆችን ስነምግባር፣ ስነልቦና፣ የፈጠራና ችግር የመፍታት ችሎታዎች የሚያሳድጉ የተለያዩ ትምህርቶች፣ ምክሮች፣ መረጃዎች በሚዲያ አማካኝነት ሲተላለፉ ነው፡፡

ሚዲያ በዚህ ትውልድ ልጆችና ወጣቶች ዘላቂ ተፅእኖ አለው፡፡ ምክያቱም በሚዲያ የሚተላለፉ ይዘቶች በቀላሉ መደጋገም ስለሚችሉ በቀላሉ በልጆችና በወጣቶች አእምሮ የመቀመጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ የሚቀርቡት ይዘቶች የልጆችን ትኩረት ለመሳብ በማራኪ መልኩ መቅረባቸው ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡
የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በተለይ ቴሌቪዥን በልጆች ላይ  የሚያሳድረው ጉልህ ተፅዕኖ መተቸት የተጀመረው ቆየት  ላለ ጊዜ ነው፡፡ ከነዚህም ትችት ውስጥ አንደኛው በለጋ እድሜያቸው ልጆች ለሚዲያ መጋለጥ የአስተሳሰብ እድገታቸው እና የትምህርት ውጤታቸው ላይ የሚያስድረው ተፅዕኖ ነው፡፡ በአጠቃላይ ከተለያዩ ጥናታዊ ውጤቶች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚዲያ በልጆች ሁለንታዊ መዳበር ላይ የሚከተሉትን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ያሳዳራል፡፡

እነሱም፡-
1. ሚዲያ ታዳጊ ልጆች ጤናማ ተግባራት ለማከናወን የሚኖራቸውን ጊዜ ይቀንሳል/ Media use decreases time spent in more healthful activities/

ጤናማ የሆኑ ተግባራት የምንላቸው ከቤተሰብ ፣ ከጓደኝ ጋር የሚኖረን  መስተጋብር በመስተጋብሩም ውስጥ ልጆች የሚያገኞቸው ጠቃሚ ነገሮች ለምሳሌ የፈጠራ ችሎታ መዳበር፣ ችግሮችን የመፍታት ክህሎት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ፣ የማንበብ፣ በቤት ውስጥ ወላጆችን ማገዝ፣ በቂ እንቅልፍ ማግኝት ናቸው፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ተግባራት አብዛኛውን የልጆች ጊዜ በመውሰድ ቀድመው መዳበር የሚገባቸው ሲሆን ለብዙ ሰዓት ሚዲያዎችን መጠቀም ለነዚህ ተግባራት የሚኖርን ጊዜ እንዲቀንስ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

2. ሚዲያ በልጆች የጨዋታ እና የመዳበር ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ /IMPACT on PLAY and DEVELOPMENT/

ታዳጊ ልጆች የወላጆቻቸውን ስልኮች በመጠቀም ለረዥም ሰዓት በስክሪን ላይ መጋለጣቸው በጣም እየጨመሩ በመምጣቱ ተመራማሪዎች በታዳጊ ህፃናት ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅዕኖ መገምገም ጀምረዋል፡፡ ለምሳሌ በቅረቡ የወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች ተገቢ ክህሎቶችን፣ የሚጠበቁ ተግባራትን ፣ ችሎታወችን ከማከናወን ይልቅ የስክሪን ላይ የተመለከቷቸውን የገፀ-ባህርያት ድርጊቶችን፣ እንቅስቃሴዎችና ንግግሮችን አስመስለው ማሳየት እንደሚቀናቸውና በእድሜያቸው የሚጠበቁ መሰረታዊ ክህሎቶችንና ተግባራትን ለምሳሌ ጫማቸውን እራሳቸውን ችለው ማሰር፣ ብስክሌት መንዳት፣ መዋኘት፣ ፊታቸውና እጃቸው መታጠብ፣  መፀዳዳት ወዘተ ላይ ዝቅተኛ የሆነ ክንውን አሳይተዋል፡፡

የሚገርመው በአንድ መዋለ ህፃናት ላይ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው በጥናቱ ከተሳተፉት ህፃናት 58% የሚሆኑት የኮምፒተር ጨዋታዎችን እንዴት መጫወት እንዳለባቸው ህጎችን ጠንቅቀው የሚያውቁ ቢሆኑም ከነዚህም ውስጥ ጫማቸውን እንዴት ማሰር እንደሚችሉ የሚያውቁት 9% ብቻ ናቸው፡፡ ይህ የሚያሳየው ልጆች ለሚዲያ ያላቸው መጋላጥ በመጨመሩ እና የልጆች ሁለንተናዊ መዳበር አሉታዊ ተፅዕኖ በማሰደሩ ነው፡፡  ምንም እነኳን ልጆች የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎችን እንደ ቴሌቪዥን ጨዋታዎች፣ ስማርት ስልኮች፣ ኮምፒውተርን ላይ በተጫኑ ጨዋታዋችን በመጠቀም የሚጫወቱ ቢሆኑም እነዚህ ጨዋታዎች የልጆችን ከማዝናናት ባሻገር የልጆችን አእምሮ፣ አስተሳሰብና የፈጠራ ችሎታ የሚያሳድጉ አይደሉም፡፡ ይልቁንም በተጨባጭ እውነታና በአካባቢያቸው የሚገኙ ነገሮችን በመጠቀም ልጆች እንዲጫወቱ ማድረግ  የልጆችን ሁለንተናዊ እደገት እንዲጨምር ያደርጋል ምክንያቱም ልጆች በቀጥታ ከመጫወቻዎቹ ጋር ያላቸው መስተጋብር ሰፊ እና ሁሉንም የስሜት ህዋሶቻቸው በንቃት መረጃን መሰብሰብ ስለሚችሉ ነው፡፡ በተቃራኒው በሚዲያዎች አማካኝነት የሚጫወቱ ከሆነ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ስለሚሆን በጨዋታው ብቻ ተወስነው ሌሎች ለእድገታቸው አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ተግባሮችን ማከናወን ስለማይችሉ መረጃ ተቀባይ ብቻ እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በሃገረ እንግሊዝ በመምህራን ማህበር አማካኝነት በቅድመ የልጆነት ወቅት የሚገኙ ታዳጊ ልጆች በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ብዙ ሰዓት መጠቀማቸው መሰረታዊ ክህሎቶችን ማከናወን ላይ ዝቅተኛ ችሎታ እንደሚያሳዩ አበክረው ይመክራሉ፡፡ እነዚህ ልጆች የተለያዩ ነገሮች በመደርደር መጫወትና እንዲሁም ለተለያዩ የትምህርት ቤት ተግባራትን ለመስራት ብዕርና እርስሳስ መጠቀም በደንብ እንደማይችሉ ጥናታቸው አረጋግጧል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁለት ጥናቶችን በአካባቢ በሚገኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም የሚዘጋጁ መጫወቻዎች ለታዳጊ ልጆች የቋንቋ መዳበር ጠቃሚ እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡የመጀመሪያ ጥናት እደሜያቸው ከ18 እስከ 30 ወር የሆናቸው ታዳጊ ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር ነገሮችን በመደርድር የሚጫወቱት የቋንቋ ወጤታቸው የተሻለ ሲሆን በሌላኛው ጥናት የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ የሚጠቀሙ ታዳጊ ልጆች ዝቅተኛ የንግግር የቋንቋ ክህሎት አሳይተዋል፡፡

አዋቂዎች መረጃን ከቴሌቪዥን ላይ በመመልከት የሚፈልጉት መረጃ መርጠው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የወሰደቱን መረጃ እውነተኛ ይሁን ምናባዊ መለየት ይችላሉ፡፡ ልጆች ግን ያዩት ነገር መርጠው መውሰድ አይችሉም፡፡ የሚያዩትን ነገር እውነተኛ በገሃዱ አለም ያለ ይሁን በምናብ የተፈጠረ መሆኑን መለየት ይቸገራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ታዳጊ ህጻናትም በቴሌቨዥን መስኮት ያዩትን ባህሪዎች ትርጉም ባለው መልኩ  አስመስለው ማሳየት ይችላሉ፡፡ ታዳጊ ልጀች በምስል ለሚታዩ ነገሮች ከፍተኛ ትኩረት የሚያደርጉ ሲሆን በአብዛኛውም ከምስሉ ጋር የቀረበውን ታሪክ ወይም ንግግር ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ታዳጊ ልጆች በቴሌቪዥን መስኮት ያዩዋቸው የሚያሰፈሩ ምስሎች በወስጠ አእምሮዋቸው ለረዥም ጊዜ መቀመጥ ስለሚችሉ ለተለያዩ የመኝታ ችግሮችና ለቅዠት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

........ክፍል 2 ይቀጥላል

Al-Afia Schools‘ Community

24 Nov, 15:49


PREPARATION AND EXAM DAY CHECKLIST
All of the points below have been shown to help students do their best in exams. Think of the reasons for each of the statements. Discuss them with your children.
Well before the exams,
•  Students should check the exam timetable to make sure they arrive for exams on the correct day, at the correct time. This is entirely their responsibility.
•  Students should make a revision/study timetable.
•  Students should revise every part of their lessons.
•  Students should make notes and summaries of the important parts.
•  Students should find out about the exam. (Timing, number of questions, choice etc.)
•  Students should have extra pencils or pens etc. 
•  Students should eat regularly and get enough sleep before exams.

The evening before the exam
•  Students should not plan to revise a lot of work. This bulk of their revision should have been completed earlier.
•  Students should read over their summaries
•  Students should try to relax
•  Students should get everything ready for the next day; equipment, clothes, etc.
•  Students should get a good night’s sleep.

The day of the exam
•  Students should get up in plenty of time and try not to be rushed.
•  Students should not do revision other than looking over summaries of important points.
•  Students should eat a good breakfast.

During the exams
•  Students should check that the exam paper they are given is the right one.
•  Students should write their name on their exams / answer sheets.
•  Students should read all the questions.
•  Students should check the time regularly during the exam.
•  Students should check the back page of all exam papers to ensure they have finished all of the questions.
•  Students should leave enough time to read over all of their answers.
WISHING OUR STUDENTS THE BEST OF LUCK ON THEIR EXAMS!

Al-Afia Schools‘ Community

24 Nov, 15:48


Reference!

Al-Afia Schools‘ Community

23 Nov, 14:14


ለፈተና ለመዘጋጀት የሚጠቅሙ 9 ነጥቦች

ውድ እና የተከበራችሁ የት/ቤቶቻችን ወላጆች፡-

ከሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 ጀምሮ ትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት አጋማሽ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።ታዲያ በዚህ ወቀት ለተማሪዎች የፈተና ዝግጅት  ጠቃሚ መሆናቸውን በባለሙያዎች የሚመከሩ 9 ጠቃሚ ነጥቦችን ልንነገራችሁ ወደናል፤መልካም ንባብ፡፡

1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች
ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።

ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።
እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።

2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።

3. ከፋፍሎ ማጥናት
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።

4. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።

5. መምህር መሆን
ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።
ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።

6. ከተንቀሳቃሽ ስልኮች መራቅ
ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።

7. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።

8. እንቅልፍ
ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክለሳ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሰውነታችንና ጭንቅላታችን በደንብ ተግባብተው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። ሌሊቱን በሙሉ ለማጥናት ሙከራ አታድርጉ ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ላይ ጫና እያሳደርን ስለሆነ።

9. መረጋጋትና በጎ በጎውን ማሰብ
ተማሪዎች እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ካደረጉ ምንም የሚያሳስባቸው  ነገር ሊኖር አይገባም። ዘና ብለው ወደ ፈተና መግባት ብቻ ነው የሚቀራቸው፡፡ ምናልባት ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ ቢገጥማቸው እንኳን እሱን ረስተው  ለቀጣዩ በጥሩ መንፈስ ለመዘጋጀት መሞከር ነው ፡፡

ምንጭ፡BBC NEWS አማርኛ
በመጠኑ ተስተካክሎ የተወሰደ

ውድ ወላጆቻችን፡-
በእያንዳንዱ የፈተና ጊዜ ልጆቻችሁን ማገዝ እና ማበራታታት እንዲሁም  ሞራል  መስጠት አትርሱ።


ውድ ተማሪዎቻችን ፡-

መልካም ፈተና!!!

Al-Afia Schools‘ Community

20 Nov, 08:25


ለአል-ዓፊያ ወላጆች በሙሉ

የተማሪዎች ክፍያ የሚከፈለው በዳሽን ባንክ በተማሪዎች መለያ ቁጥር(በተማሪዎች ስም) ብቻ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ክፍያውን ከከፈሉ በሗላ የባንክ ስሊፑን ማምጣት ሳይጠበቅባችሁ ደረሰኙ ከት/ቤት ተማሪዎች መውስድ ይችላሉ::

Al-Afia Schools‘ Community

17 Nov, 19:31


የሁለተኛው ሩብ ዓመት የተማሪዎች የት/ቤት ክፍያን ይመለከታል

ውድ ወላጆች የሁለተኛው ሩብ ዓመት ክፍያ ከኅዳር 15 እስከ ኅዳር 30 ባለው ጊዜ ዉስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል::

በመሆኑም በክፍያው  ቀናት  ከሚከሰት አላስፈላጊ መጨናነቅ  ለመቀነስ ክፍያውን አሁኑኑ መክፈል ይችላሉ::

ክፍያው በተማሪዎች መለያ ቁጥር በባንክ ሲሆን የተማሪው/ዋ መለያ ቁጥር ከት/ቤት በወላጅ መምህር መፅሐፍ የሚላክሎት ይሆናል::

ለበለጠ መረጃ ልጅዎን የሚያስትምሩበትን ቅርንጫፍ ት/ቤት መጠየቅ ይችላሉ::

የአል ዓፊያ ት/ቤ/ጽ/ቤት

Al-Afia Schools‘ Community

13 Nov, 15:48


#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

☞ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
☞ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
☞ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
☞ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ፈፅማቹ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታችሁን ያቋረጣችሁ ተማሪዎች፥ የዊዝድሮዋል ቀሪ ፎርማችሁን በመያዝ ህዳር 23 እና 24/2017 ዓ.ም መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Al-Afia Schools‘ Community

11 Nov, 12:17


የ 2016 ት/ዘመን የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ ካርድ ት/ቤት ስለመጣ ከነገ ማክሰኞ 03/02/2017 ጀምሮ መውስድ የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሰውቃለን::

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


📣 DambiDollo University

ለደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ዓ.ም ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችዉ እና በ2016 ዓ.ም የሪሜዲያል ፕሮግራም (የአቅም መሻሻያ ትምህርት) በመደበኝነት ወስዳቹ ያለፋችዉ (50% ከዚያ በላይ) የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የትምህርት ምዝገባ የሚከናወነዉ ህዳር 11 እና 12/2016 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን ስትመጡ ከዚ በታች የተገለፁትን ማለትም፣

1. የ8-12 ክፍል ትራኒስክርብት ኦርጅናልና ኮፒ፣

2. የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርተፍኬት ኦርጅናልና ኮፒ፣

3. 3 በ 4 የሆነ በቅርብ ጊዜ የተነሳችሁትን አራት(4) ጉርድ ፎቶ፣

4. እንዲሁም ለግል መገልገያ የሚሆኑ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አሉሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡
ከተገለፀዉ ጊዜ ቀድሞም ሆነ ዘግይተዉ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳዉቃለን፡፡

በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ተማሪዎች የመግብያ ቀን ወደፊት የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#Borana_University

የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

በ 2017 አዲስ የተመደባቹ እና በ 2016 የ አቅም ማሻሻያ ስትከታተሉ ቆይታቹ ማለፊያ ነጥብ ያመጣቹ  የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ህዳር 12 እና 13 መሆኑን ዩኒቨርስቲ አሳውቋል::

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#UniversityOfGondar

ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ 2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 12 እና 13/ 2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 16/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


📣 Dirredawa University

በድሬዳው ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐ ግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ቀን ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳስባለን።

ምዝገባ ለማድረግ የሚያስፈልጉ፦

- የ8ኛ ክፍል ስርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


በ2017 ዓ.ም ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አንደኛ አመት (Freshman) ተማሪዎች በሙሉ

በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁና አልፋችሁ ለ2017 የትምህርት ዘመን ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ህዳር 04-05 ቀን 2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደረጉ እናሳውቃለን፡፡

💥ማሳሰቢያ
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ማቴሪያሎች ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

1. የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሰርተፊኬት ዋናውና ከማይመለስ ኮፒ ጋር

2. ከ9-12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቃችሁበት ትራንስክሪብት ዋናውና ከማይመለስ ኮፒ ጋር

3. የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ከማይመለስ ኮፒ ጋር

4. ስድስት ፍሬ ጉርድ ፎቶ ግራፍ 3×4.

5. በ ቁ.4 የተገለጸው የጉርድ ፎቶ ግራፍ ሶፍት ኮፒ

6. በግል የምትጠቀሙባቸው አንሶላ፣ብርድ-ልብስ፣የስፖርት ትጥቅ ልብስ

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#AmboUniversity

በ2017 ዓ.ም ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አንደኛ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችን አዲስ የተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲያችን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ነጥብ (50% እና ከዚያ በላይ) ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነዉ ህዳር 09-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳዉቃለን

በተጠቀሱት ቀናት ብቻ
🪺በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በዋና ካምፓስ፣
🪺በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ (አምቦ ከተማ) በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን።


ማሳሰቢያ፦

📣በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችን አዲስ የተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትመጡ:-

የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት (ዋናዉን እና ፎቶኮፒ)

ከ9-12ተኛ ክፍል ትራንስክሪፕት (ዋናውን እና ፎቶኮፒ)፣

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርቲፊኬት (ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ)

3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡ።

ሁሉም ተማሪ አንሶላ፤ ብርድልብስ፤ ትራስልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዞ መምጣት ይጠበቅበታል።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደፊት የምናሳዉቅ ይሆናል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

👉የ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#WallagaUniversity

በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ውጤት አምጥታችሁ ለ2017 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 4 እና 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ፣ ነቀምት

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና ኮፒው
- ስምንት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

መደበኛ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


የ2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች ቅበላ ተራዘመ

ራያ ዩኒቨርሲቲ ሕዳር 02 እና 03/2017 ዓ.ም የ2017 ዓ/ም 1ኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች እንደሚቀበል ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አሳውቀን የነበረ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው በተፈጠረ ድንገተኛ የውኃ መስመር መበላሸት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#JigjigaUniversity

በ2017 ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባቹህ:-

🛫Freshman ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ህዳር 07-09/2017 ዓ.ም. መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

🛫Remedial ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ታህሳስ 01-03/2017 ዓ.ም. መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል

📄 𝐏𝐥𝐞𝐚𝐬𝐞 𝐛𝐫𝐢𝐧𝐠 𝐭𝐡𝐞𝐬𝐞 𝐞𝐬𝐬𝐞𝐧𝐭𝐢𝐚𝐥 𝐝𝐨𝐜𝐮𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐢𝐭𝐞𝐦𝐬:
* Educational Documents: Original and photocopies of certificates from Grades 8 through 12.
* Photographs: Eight recent passport-sized photos.
* Personal Essentials: Blankets, bed sheets, and sportswear.

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

09 Nov, 21:05


#WoldiaUniversity

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ :-

👉አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ፣ በ 2016 በሬሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ እንዲሁም በ 2016 ከ 1ኛ አመት Withdraw የሞላችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 18 እና 19/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

👉 በሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 19-20/2017 ነው ተብሏል፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Al-Afia Schools‘ Community

04 Nov, 12:53


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም : https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia

Al-Afia Schools‘ Community

03 Nov, 06:29


ክፍል -4
ለልጆቻችን ምን እናብብላቸው?

በተለያዩ ርእሰ-ጉዳዮች ላይ የተጻፉ መጽሐፍትን ለልጆቻችን ብናነብላቸው፣ ልጆቹ ከተለያዩ ቃላት፣ ምስሎችና ባጠቃላይ ከአዲሱ ውጫዊው ዓለም ጋር የመተዋወቅ አጋጣሚው ይፈጠርላቸዋል፡፡ በሚከተሉት ርእሰ-ጉዳዮች ስር የተጻፉትን መጽሕፍት ለልጆቻችን እንድንመርጥላቸው ይመከራል፡፡

የሳይንስ ልቦለዶች – በእውነታው ዓለም ያልተለመዱ እንደሚናገር ውሻ፣ በራሪ ሰው፣ በመሬት ስር ስለሚገኝ በሃሳብ የተፈጠረ ዓለምና በሌሎችም መሰል ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የልጆች መጽሐፍት የልጆቻችንን ያስተሳሰብ አድማስ በማስፋት ረገድ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል፡፡

ታሪካዊ ልቦለዶች – በጥንቃቄና በጥራት የተጻፉ ታሪካዊ ልቦለዶች፣ ያለፉ ክስተቶች ህይወት ዘርተው ለልጆቹ እንዲታዩአቸው ያስችሏቸዋል፡፡

የህይወት ታሪኮች– በህይወት ታሪኮች ላይ የተፃፉ መጽሐፍት ልጆቻችንን በመቀስቀስ ወይንም በመነሸጥ በትምህርት ላይ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያግዛሉ፡፡ ስለታዋቂ የሃገር መሪዎች፣ ስለፈጠራ ሰዎች፣ ስለትምህርት ባለሞያዎችና ሳይንቲስቶች የሚተርኩ መጽሐፍትን ማንበብ ይመከራል፡፡ በንባብ ወቅትም ልጆቻችን ከነዚህ ታላላቅ ሰዎች ጋር የመተዋወቁ ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

መረጃ-ሰጪ መጽሐፍት– እሳተ-ጎሞራ እንዲፈነዳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከዓለም በጣም ረጅሙ ሰው ቁመቱ ምን ያህል ይሆናል? ሀበሻ የሚለው ቃል ከየት ተገኘ? ዝናብ እንዴት ይመጣል?...ልጆች ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይወዳሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ዓይነቶቹ መረጃ ሰጪ መጽሐፍት ለጥያቄዎቻቸው መልሶችን በመስጠት ረገድ ይረዷቸዋል፡፡ መሰል መጽሐፍትን ስንመርጥ በቅርቡ ስለመጻፋቸውና ትክክለኛውን መረጃ ስለመያዛቸው ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

ግጥሞች– መነበብ ያለባቸውን ያህል ግጥሞች በሰፊው አይነበቡም፡፡ በርካታ የልጆች ግጥሞች የተሰባሰቡባቸው መጽሐፍት ልጆቻችንን በሳቅ ያስፈነድቋቸዋል፤ ፍፁም በደስታ ይሞሏቸዋል፡፡ ግጥሞች አብዛኛውን ጊዜ አጫጭሮች ናቸው፡፡ ሲነበቡ የሚሰጡት ድምፅ አስደሳች ነው፡፡ ስለዚህም ግጥሞች ንባብን ለሚርቁና ለሚሰለቹ ልጆቻችን በቀላልነታቸው ተመራጭ ናቸው፡፡

ጥንት በልጅነታችን ያነበብናቸው የአያ ጅቦ፣ የእንኮዬ ጦጢት፣ የላሜቦራ፣ የአያ አንበሴ፣ የቀበሮ፣ የተንኮለኛው ከበደና መሰል ታሪኮች ትዝ እንደሚሏችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አቤት ደስ ሲሉ! የነዚህ ዓይነት ታሪኮችንና ከላይ በተጠቀሱት ርዕሶች የተመለከቱትን መጽሐፍት ገዝተን ለልጆቻችን የምናነብበትና ከፍ ከፍ ያሉትንም በራሳቸው እንዲያነቡ የምንገፋፋበት ጊዜው አሁን ነው፡፡በአጠቃላይ የትኛውንም ንባብ ወይንም መጽሐፍ ለልጆቻችን ብንመርጥም፣ አጠቃቀሙን ወይንም አነባበቡን አስደሳች ልናደርገው ይገባል፡፡ በታሪኩ ውስጥ የተዋወቅነውን ዝነኛው ሰው ጋር መተዋወቅ፣ ለጥያቄዎቻቸው በራሳቸው ጥረት መልስ ማግኘት መቻል፣ አጭር ደስ የሚል ግጥም ማንበብ፣ በቃል አጥንቶ መልሶ ማለት… እነዚህ ሁሉ ልጆቻችንን እንዴት እንደሚያስደስቷቸው አስበን እናውቃለን?
ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ
በጥቂቱ የተሻሻለ
........ መጨረሻ .. .....

Al-Afia Schools‘ Community

02 Nov, 13:21


... ..... ክፍል ~ 3
በዚህም መሰረት ልጆቻችን ገና ት/ቤት ያልገቡ ከሆነ፣ ራሳችን እያነበብንላቸው ልምዱን እያዳበሩ እንዲያድጉ ልናግዛቸው እንችላለን፡ መጽሐፍትን ለልጆቻችን የማንበቡ ልምድ ከሚኖሩት በርካታ ፋይዳዎች መካከል የሚከተሉትን ማየት እንችላለን፡፡

ጠንካራ የወላጅ-ልጆች ግንኙነት – ልጆቻችንን በእቅፋችን ሸጉጠን ስናነብላቸው ከምንሰጣቸው መንፈሳዊ ደስታ በተጨማሪ፣ በእኛና በእነሱ መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከርን መሆኑን ልናውቅ ይገባል፡ልጆቻችን በምናነብላቸው ታሪክ የራሳቸውን ደስ የሚል፣ የማይረሳ ዓለም በአእምሯቸው ይቀርፁ ዘንድ ያስቻልናቸውን ወላጆቻቸውን ያደንቃሉ፤ ይወዳሉ፡፡

የትምህርት ብቃት – ለልጆቻችን የምናነበው ታሪክ ለወደፊቱ የት/ቤት ሕይወታቸው መሰረት ነው፡፡ በርካታ ጥናቶች የሚያሳዩት ይሄንኑ ነው፡፡ በእርግጥም ከመደበኛ ት/ቤት በፊት ልጆች ከንባብ ጋር እንዲተዋወቁ ማድረግ ለወደፊቱ ትምህርታቸው ስምረት የሚኖረው አስተዋፅኦ የጎላ ነው፡፡

መሰረታዊ የንግግር ክህሎት – የቅድመ መደበኛ ትምህርት ንባብ የልጁን መሰረታዊ የቋንቋ ችሎታ በማዳበሩ ረገድ ላቅ ያለ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ልጆቻችን የምናነበውን ተከትለው ድምፆችን ደጋግመው ይጠራሉ፤ አስመስለው ይናገራሉ፤ ወይም ለማንበብ ይሞክራሉ፡፡ በዚህ ዓይነት የልጆቻችን የቋንቋ ችሎታቸው የሚሻሻልበት አጋጣሚው ይፈጠራል፡፡

የንባብ መሰረታዊ ዕውቀት – ልጆች ማንበብን ችለው አይወለዱም፡ ንባብ ከግራ ወደቀኝ ወይም ከቀኝ ወደ ግራ ስለመነበቡም አስቀድመው የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቃላት ከምስል የተለዩ መሆናቸውን አውቀው አይወለዱም፡፡ ስለዚህ ማንበብን ማሳየት ወይንም ማሳወቅ በእጅጉ ለልጆቻችን ይጠቅማቸዋል፡፡

የተሻለ የመግባቢያ ክህሎት –በምናነብላቸው ጊዜ ልጆቻችን ስለራሳቸው የመግለፅና ለሌሎች የማውራት ዝንባሌዎችን ያሳያሉ፡ በታሪኩ ውስጥ ባሉት ገፀ-ባህርያት መካከል የሚያስተውሉት ዝምድናና ትስስር፣እንዲሁም ከእኛ ከምናነብላቸው ወላጆቻቸው ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት፣ የልጆቹን መሰረታዊ የመግባቢያ ክህሎትእንዲያድግ ይረዱታል፡፡

የተሻለ የማስተዋል ክህሎት –ሌላው የቅድመ- ት/ቤት ንባብ አስፈላጊነት የሚመዘነው ልጆቻችን ረቂቅ ፅንሰ-ሐሳቦችን የመያዝና የማገናዘብ ችሎታቸውን በማዳበር ረገድ በሚኖረው ጠቀሜታ ነው፡፡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክንያታዊነትን የማሳየት፣ ሳቢያና ውጤቶችን የማወቅና የፍርድ አደላዳይነትን ምንነት እንዲገነዘቡ ያግዛቸዋል፡፡

አዳዲስ ልምዶችን መቅሰም – ተገቢ የሆኑ (የተመረጡ) መጽሐፍትን ለልጆቻችን የማንበቡ ልምድ፣ ልጆች ወደፊት ለሚያጋጥማቸው ውስጣዊ ጭንቀት፣ ንባብ ማርከሻ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል እንዲረዱ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ልጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ት/ቤት የመሄድ ጭንቀት ሊኖርበት ይችላል፡፡ት/ቤት ከመግባቱ በፊት የምናነብለት ታሪክ፣ ለልጁ የውጩውን አዲስ ልምድ በማስተዋወቅና ኋላም ላይ ሊከሰት የሚችለውን ጭንቀት በማርገብ ረገድ ጥሩ ሚና ሊጫወት ይችላል፡፡ በዚህ ዓይነት ልጁ ጥሩ ተሞክሮ ስለሚኖረው፣ ት/ቤት የመሄዱ ጉዳይ የተለመደ ክስተት መሆኑን እያወቀ ይመጣል፡፡እንደውም አንዳንድ ጊዜ በንባቡ ውስጥ እንዳሉት ተማሪ ገፀ-ባህርያት፣ ልጆቻችን ወደ ት/ቤት እንዲወሰዱ ሊጠይቁን ይችላሉ፡፡

ትኩረትንና ስነ-ስርዓትን ማዳበር – ምናልባት ገና በጅምሩ ልጆቻችን ትኩረታቸው ወደ ንባቡ ላይሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ፣ በሂደት ቀልባቸውን ወደ እኛ ወይም ወደ ንባቡ መመለሳቸው አይቀርም፡፡ በቅድመ - ት/ቤት ንባብ ሳቢያ የሚዳብሩት ከአንብቦ መረዳት ጋር የሚመጡት ጥብቅ ግለ - ስነ-ስርዓቶች፣ የትኩረት መጠን ከፍ ማለትና የተሻለ የማስታወስ ችሎታ በመደበኛው የትምህርት ቆይታቸው ላይ ይጠቅማቸዋል፡፡

ንባብ አስደሳች መሆኑን ማወቅ – ቅድመ - ት/ቤት የሚዳብረው የንባብ ልምድ፣ ልጆች መጽሐፍት አስደሳች እንጂ አሰልቺ አለመሆናቸውን ለመገንዘብ ይረዳቸዋል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚያድጉ ሕፃናት መጽሐፍትን ከቪዲዮ መጫወቻዎች፣ ከቴሌቪዥንና ከሌሎች መሰል የመዝናኛ ዘዴዎች አስበልጠው የመምረጥ ዝንባሌን ያሳያሉ፡፡
.. ... ክፍል 4 (የመጨረሻ ክፍል) ይቀጥላል

Al-Afia Schools‘ Community

30 Oct, 05:00


.......ክፍል 2
ምርምራቸውን በትምህርት ላይ ያደረጉ ባለሞያዎች እንደሚመሰክሩት፣ በንባብና በቃላት መካከል የጠበቀ ቁርኝት አለ፡፡ ወይንም የአንዱ መኖር ለሌላው መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡በቀላሉ ለመግለፅ፣ ብዙ ቃላትን የሚያውቁ ተማሪዎች፣ አብዛኛውን ጊዜ ጥሩ የንባብ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ ይሄ እሰጥ-አገባ የማያስፈልገው ትክክለኛ መረጃ ነው፡፡ በስፋት በተነበበ ቁጥር የቃላት ዕውቀትም በዚያው መጠን ማደጉ እውነት ነው፡፡

ንባብን ልምዳቸው ያደረጉ ልጆች ላቅ ያለ የፈጠራ ችሎታ አላቸው፡፡ ይሄ የሚሆነው ንባቡ እንዲያሰላስሉ ወይንም ጠልቀው እንዲመራመሩ ስለሚገፋፋቸው ነው፡፡ ንባብ ለልጆች የአእምሮ እድገት ይረዳል፤የዓይን ጡንቻዎቻቸውን ያነቃቃል፡፡ ንባብ ትልቅ ትኩረትን የሚጠይቅ ስራ በመሆኑ፣የሚያነቡትን ልጆች የንግግር ክህሎት ያዳብራል፤ በዕለት-ተዕለት ንግግሮች ላይ የሚደመጡ ቃላትንና ሐረጎችን ለመለየት ይረዳቸዋል፤ ወቅታዊ ክስተቶችን ያሳውቃቸዋል፡፡ እንዲሁም ከዘመኑ ፀሐፍት ጋር ያገናኛቸዋል፡፡

በንባብ ጊዜ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ግንዛቤን የመጨበጡ ዓቢይ ጉዳይ ነው፡፡ ግንዛቤን ሳይዙ ወይም ሳይረዱ ዝም ብሎ ማንበብ፣ ጊዜን በከንቱ እንደማባከን ሊቆጠር ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ንባብ በመጽሐፉ ገፅ ላይ የሰፈሩትን ቃላት ትርጉም አልባ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰዎች የሚያነቡት ጸሐፊው ለማስተላለፍ የፈለገውን ለመረዳትና በሚያገኙት መረጃዎችም ለመጠቀም ነው፡፡ እውነታን ለማግኘት፣ አዳዲስ ክህሎቶችን ለማዳበርና ለመደሰት ወይም ለመዝናናትም ይሁን፣ ማንበብ ጠቃሚ ነው፡፡ ከንባብ የሚገኝ ግንዛቤ፣ ትንታኔና መረጃ ለትምህርት ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡ ይሄንን ደሞ ተግባራዊ ለማድረግ፣ አንብቦ የመረዳት ክህሎት ያስፈልጋል፡፡ያለበለዚያ ከንባባችን የተፈለገውን መረጃ ሳናገኝ እንቀራለን፡፡

ግንዛቤ የጎደለው ንባብ ጉዳት አለው፡፡ የተማሪውን የትምህርት ስኬት ያጨናግፈዋል፡፡ ችግሩ በመድሃኒት ብልቃጥ ላይ የተጻፉ ምክሮችን፣ አደገኛ ኬሚካል በያዙ እሽጎች ላይ የሚለጠፉ የማሳወቂያና የማስጠንቀቂያ ጽሁፎችን አንብቦ አስካለመረዳት የሚደርስ ነው፡፡ በከፋ መልኩም ሲታይ አንብቦ የመረዳት ክህሎትን ማጣት የመጨረሻ ውጤቱ፣ ከድህነትና ወንጀል ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ለምሳሌ በአንድ ወቅት በተደረገ ጥናት፣ በአሜሪካ እስር ቤት ውስጥ ከነበሩት እስረኞች 60 ከመቶው የነበራቸው የንባብ ክህሎት ደረጃ ከ4ኛ ክፍል በታች ነበር፡፡ በዚያው ሃገር በእስር ላይ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ሰማንያ አምስት ከመቶ የሚሆኑት የተማሩ መሃይማን ነበሩ፡፡ የተማሩ መሃይማን የሚባሉት ማንበብ መጻፍ የሚችሉ ቢሆኑም፣ ባለባቸው አንብቦ የመረዳት ከፍተኛ ችግር ምክንያት የየዕለት ህይወታቸውን መምራት ወይም መለወጥ የተሳናቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም ያለበቂ የንባብ ክህሎት 4ኛ ክፍል ከደረሱ ተማሪዎች ውስጥ 2/3 ኛዎቹ መጨረሻቸው እስር ቤትና የማገገሚያ ተቋማት ናቸው፡፡ ከዚህ ለመገንዘብ የምንችለው አንብቦ የመረዳት ክህሎትን ማሳደግ የካበተ እውቀት አንዲኖረን፣ በስራችንና በህይወታችንም የተሳካልንና የተሻልን እንድንሆን ያስችለናል፡፡

ስለዚህም ከዚህና መሰል ችግሮች ለመዳንና በሁሉም ዘርፍ የተሻሉ ዜጎችን ለማፍራት በሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ወላጆች በልጆቻችን ውስጥ የምናሰርፀው የንባብ ልምድ ከፍተኛውን ሚና መጫወት ይችላል፡፡ ከት/ቤት በፊት ቀድመው ንባብ የሚጀምሩ ሕጻናት፣ ጥሩ የቋንቋ ክህሎትና ካላነበቡት ሕፃናት ይልቅ ነገሮችን በተሻለ ሁኔታ የመገንዘብ ችሎታ እንደሚኖራቸው ይነገራል፡፡ በት/ቤት ብቻ ሳይሆን በሌላውም መስክ ውጤታማ ሆኖ ለመገኘት ንባብ አስፈላጊ ነው፡፡ ፎርብስ መጽሔት በአንድ ዕትሙ፣ ‹‹if you want to succeed in business, read more novels,›› ብሎ ነበር፡፡ ‹‹በንግድ ስራህ ውጤታማ መሆን ከፈለግህ፣ ተጨማሪ ልቦለዶችን አንብብ›› ማለቱ ነው፡፡ ልቦለድ ማንበብ የሰዎችን ውስጣዊ ብስለት ያሳድጋል ባይ ነው - መጽሔቱ፡፡ ሰዎች ስለራሳቸውና ስለሌሎች ያላቸውን እውቀት ለማጠናከር፣ አዎንታዊ ዝምድናዎችን ለማሳደግ፣ ከሌሎች ጋር የሚፈጠር የተሻለ ግንኙነትን ለማዳበር እንዲሁም ሌሎችን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ንባብ የሚያስገኛቸውን ፋይዳዎች ጽሑፉ ያትታል፡፡

ስለዚህ ልጆቻችን የንባብን ልምድ ያዳብሩ ዘንድ እንዴት እንርዳቸው የሚለው ዋና እና አስፈላጊ ጥያቄ ይሆናል፡፡በልጆቻችን ውስጥ የንባብ ልምድን የማስረፁ ተግባር በየትኛውም የልጅነት ዕድሜያቸው ላይ እያሉ ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፡፡ ሆኖም፣ቢቻል ልጆቹ ት/ቤት ከመግባታቸው በፊት ስራው ቢጀመር የተሻለ እንደሚሆን በመስኩ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ አካሄድ በርግጥም ከፍ ከፍ ያሉትን ልጆች እንዲያነቡ ከመጎትጎትና ከመጫን ይቀላል፡፡

.....ክፍል 3 ይቀጥላል

Al-Afia Schools‘ Community

28 Oct, 18:00


ልጆቻችን የንባብን ልምድ ያዳብሩ ዘንድ እንዴት እንርዳቸው?

ከዚህ ቀደም ስለ ንባብ ጠቃሚነት ብዙ ተብሏል፡፡ጥሩ ጥሩ መጽሐፍትን ማንበብ ከበሰሉ ሰዎች ጋር ሸንጎ እንደመቀመጥ ይቆጠራል ይባላል፡፡ የአስተሳሰብ አድማስን ስለሚያሰፋ፣ ሁለገብ እውቀት ስለሚያላብስና በራስ መተማመንን ስለሚያጎለብት ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡ ታዋቂው የአሜሪካ ፕሬዝደንት፣ አብርሃም ሊንከን የንባብን ጥቅም አስመልክቶ ሲናገር፣ ‹‹ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች የሚገኙት መጽሐፍት ውስጥ ነው፡፡ ያላነበብኩትን መጽሐፍ የሚሰጠኝ እርሱ ከጓደኞቼ ሁሉ የተሻለው ነው›› ብሎ ነበር፡፡

እውነት ነው፣ ማወቅ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ልናገኝ ከምንችልባቸው መንገዶች አንዱና ዋንኛው ንባብ ነው፡፡ ከውይይትና ጠይቆ ከመረዳት ዕውቀት ሊገኝ ቢችልም፣ የተሻለውና አቋራጩ መንገድ ግን ንባብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ዘመን በተራቀቀበት በአሁኑ ወቅት፣ አለማንበብ ራስን ወደ መሃይምነት እንደመለወጥ ይቆጠራል፡፡

ኮንፊሺየስ እንዲህ ይላል “No matter how busy you may think you are, you must find time for reading, or surrender yourself to self-chosen ignorance.” (የቱንም ያህል በስራ ብትወጠር፣ ለማንበቢያ ጊዜ ሊኖርህ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ በገዛ ፈቃድህ ለመረጥከው መሃይምነት እጅህን ስጥ)

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ንባብን ልምዳቸው ያደረጉ ወጣቶች በተሻለ የስራ መስክ የመሰማራት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1970 ዓ.ም በተወለዱ 17,200 ሰዎች ላይ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በተደረገ የቅርብ ጊዜ ጥናት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወጣቶችን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ በመገፋፋት ረገድ ንባብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡ በጥናቱ መሰረት፣ በንባብና በስራ ስኬት መካከል ያለው ቁርኝት የተሻለ ክፍያ ወይም ገቢ እስከማስገኘት ይደርሳል፡፡

እርግጥ ነው የዛሬ ልጆች በዘመን አመጣሽ የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ ማለትም በቴሌቪዥን፣ በቪዲዮ ጨዋታዎች፣ በኢንተርኔት፣ በአይፖድ፣ በሞባይል ስልክና በመሳሰሉት ላይ ስለሚጠመዱ፣ ትኩረታቸውን ወደንባብ የማድረጉ ስራ ለእኛ ለወላጆች የሚያስቸግር ይመስላል፡፡ ሆኖም በእኛ በኩል ያላሰለሰ ጥረት ከተደረገ፣ የሚፈለገውን የንባብ ልምድ በልጆቻችን ውስጥ ማስረፁ ብዙም አይከብደንም፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እነዚህ የቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔትና የቪዲዮ ጨዋታዎች በአስገራሚ ሁኔታ የዕይታ ችሎታን በማሳደግ ረገድ ውጤታማ ናቸው ተብሏል፡፡ ይሁን እንጂ በቪዲዮ ላይ የተጣደው ወጣት ትውልድ የዕይታ ብቃቱ ቢጨምርም፣ በአንፃሩ የተጻፉ ነገሮችን የመረዳትና የማገናዘብ ችሎታው ይቀንሳል፡፡ እንደዚህ ዓይነቶቹን እውነታዎች የተረዳን የልጆቻችን የወደፊት ዕጣ የሚያሳስበን ወላጆች እንኖር ይሆን?

ልጆቻችን በመልካም ባህርይ እንዲታነፁ የቻልነውን እንደምናደርግ ሁሉ፣ በንባብ ልምድም በልፅገው እንዲያድጉ መርዳት ይጠበቅብናል፡፡ ይሄ እኛ ወላጆች ልንተገብረው የሚገባን አንዱና ዋንኛው ሃላፊነታችን መሆኑን ላፍታም ቢሆን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡ በንባብ ልምድ ተኮትኩቶ ያደገ ልጅ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ተመስክሯል፡፡ በትምህርት ላይ ምርምር ያደረጉ አጥኚዎች እንደሚሉት፣ ንባብና ትምህርት በእጅጉ ተያያዥነት ያላቸው ያንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ በሌላ አባባል፣ አንድ ጥሩ አንባቢ የሆነ ተማሪ ከማያነበው ተማሪ በተሻለ መልኩ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ ብቃት አለው፡፡

ጥሩ አንባቢ የሆኑ ተማሪዎች እያንዳንዱን ዓ. ነገር መረዳትና የአንድን ጽሁፍ ቅርፃዊ አቋም ማወቅ አይቸግራቸውም፡፡ ሃሳቦችን የመጨበጥ፣ ክርክሮችን የመከታተልና የወደፊት ድምዳሜያቸውንም የመተንበይ ችሎታ አላቸው፡፡ እነዚህ በንባብ ልምድ የሚያድጉ ተማሪዎች፣ በንባባቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን የእንግዳ ቃላት ፍቺዎች ለመረዳት ብዙም አይቸገሩም፡፡ይህም ካልሆነ፣ በቀላሉ መዝገበ-ቃላትን በአጋዥነት መጠቀምን ይችሉበታል፡፡ ባጠቃላይ ጥሩ አንባቢ የሆኑ ተማሪዎች የተፈለገውን የአንድ ጽሑፍ ሃሳብ በፍጥነት የመገንዘብ ችሎታ አላቸው፡፡

......ክፍል -2 ይቀጥላል

Al-Afia Schools‘ Community

26 Oct, 19:50


ልጄ አሁን 4 ዓመቱ ነው በጣም ቀዥቃዣ እና አስቸጋሪ ልጅ ሆኖብኛል ምክንያቱ ምን ይሆን❓️😴😔

👦 ወንድ ልጆች ለምንድነው ቀዥቃዣ የሚሆኑት ግን ❓️

✔️ ህፃናት በተለይ ደሞ ወንድ ልጆች አካባቢያቸው ለመቃኘት ለመቆጣጠር ወይም የወላጅን ትክረት አውቀው ለመሳብ ሲሉ በጣም ቀዥቃዣ እና አስቸጋሪ ሊሆኑ ይቺላሉ::

✔️ ከበድ ሲል ደሞ በሕክምናው አጠራር ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (Attention Deficit hyperactivity -ADHD) ሊኖራቸው ይቺላል::

📌 ኤዲኤችዲ(ADHD) ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል ስነ አይምሮ እክል ነው።

📌 ይህ እክል ያለባቸው ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና እጅግ ችኩል እና ቅብጥብጥ ናቸው፡፡

📌 አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡

📌 እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው ብቻ ሳይሆኑ ለመቆጣጠር በጣም አዳጋች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ለ አደጋ ሊጋለጡ ይቺላሉ:: 🏄🏂 🤸

📌 ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው::

📌 ይህ ADHD የሚባለው የስነ አይምሮ ቺግር 3 አይነት አለው እነሱም

1. ትኩረት የሌላቸው ( inattentive type)

2.  እረፍት የሌላቸው (hyperactive- impulsive)

3. የሁለቱም አይነት ምልክት ያለው (ከላይ የተጠቀሱን ሁለቱንም ምልክቶች ያለበት

❤️ እስኪ በዝርዝር እንያቸው❗️

1.   ትኩረት የሌላቸው (Inattentive type)

🔷 ብዙውን ጊዜ ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት አለመስጠት

🔷  ከእኮዮቻቸው ጋር ሲነፃፀሩ በግዴለሽነት ስህተት መስራት

🔷 ከፍተኛ ትኩረትን የሚይጠይቁ ተግባራቶች ላይ ለመሳተፍ ወይም ለመሞከር አለመፈለግ ወይም አለመውደድ

🔷 ብዙውን ጊዜ ለስራ ወይም ለጨዋታ የሚያስፈልጉ አስፈላጊ ነገሮችን መርሳት ለምሳሌ የትምህረት መሳሪያዎችን ትምህርት ቤት በተደጋጋሚ ረሰተው መምጣት

🔷 በቀጥታ አንድ ሰው ሲያናግራቸው የሚሰማ ወይም የሚያዳምጥ አለመምሰል - አእምሮን ሌላ ቦታ መውሰድ

🔷 ብዙውን ጊዜ ትዕዛዞችን ለመተግበር ይቸገራሉ እንዲሁም የቤት ስራዎችን በትክክል ለመጨረስ ይቸገራሉ (often has difficulty in following instruction)

🔷 ቀላሉ መረበሽ(often easily distrusted by external stimuli)

2. እረፍት አልባ (በጣም ቀዥቃዣነት)
Hyper Active type

🔺 በእጅ ወይም በእግር ጣቶች መሬት ወይም ሌላ ነገርን መምታት ፣መቆንጠጥ

🔺 መቀመጥ በሚገባቸው ቦታ ወይም ሁኔታ ውስጥ እያሉ ለመሮጥ ወይም ለመንቀሳቀስ መሞከር

🔺 ብዙውን ጊዜ በቦታው ላይ መቀመጥ ሲገባ ለመሮጥ ወይም ለመዝለል መሞከር፤መንቀⶵቀⶵ ወይም በአንድ ቦታ ተረጋግቶ ለመቆየት መቸገር

🔺 ብዙ ጊዜ ተረጋግተው ጨዋታ መጫወት አለመቻል

🔺 ከመጠን በላይ ያወራሉ

🔺 በሌሎች መሃል ብዙን ጊዜ ጣልቃ ይገባሉ ለምሳሌ ትልልቅ ሰዎች በሚያወሩ ሰአት ጣልቃ መግባትእና አላስፍላጊ ንግግር ማድረግ

🔺 አንድ ጥያቄ ሲጠይቅ ጥያቄው ከማለቁ በፊት ለመመለስ መጣደፍ
🔺 ተራቸውን ጠብቀው መናገር ወይም ድርጊቶች መፈፀም ይቸገራሉ

3. የሁለቱም አይነት ምልክት ያለው( Combined type) ከላይ የተጠቀሱት የሁለቱም ምልክት አይነት ይታዩባቸዋል ::


🔷 ምክንያቱ ምን ይሆን ⁉️

📌 ምክንያቱ በትክክል አይታወቅም

📌 በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡

📌 ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 % የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡

👨‍⚕️ ሕክምና አለው ግን ⁉️

አዎ ሕክምናው የሚከተሉት ናቸው

✔️ ስነ ልቦና ህክምና(psychotherapy)

✔️ በአማራጭ ትምህርት(Special Education)


ከላይ ባሉት አማራጭዎች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡

👉 ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ::

📞 ለበለጠ መረጃ 0965314807 መደወል እና ማማከር ይችላሉ

❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለ ሌሎችም እንዲደርስ share ያድርጉ

https://t.me/+4aq2xDAQFUQ3YjZk

Al-Afia Schools‘ Community

24 Oct, 13:25


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahuniversity

Al-Afia Schools‘ Community

23 Oct, 11:00


ውድ የአል ዓፊያ ወላጆች ይህ ዶክመንት ከከፈተላቹህ ከፍታችሁ ካልሆነ በምስል ያለው ተመሳሳይ ስለሆነ አንብባችሁ ከልጆቻቹ ተወያዩበት፡፡

Al-Afia Schools‘ Community

21 Oct, 16:21


#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል።

ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia

Al-Afia Schools‘ Community

19 Oct, 12:06


የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ በአዲስ አበባ የምትኖሩ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አራት ጉርድ ፎቶግራፎች መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ስለምዝገባ ሒደቶች በተመለከተና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Al-Afia Schools‘ Community

16 Oct, 17:44


እንኳን ደስ አላችሁ!!

ዛሬ በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ት/ቤቶች መካከል ተማሪ አማር ዘይኑ ከተፈጥሮ ሳይንስ እና ተማሪ ሩመይሳ ባቂል ከማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍል በ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል::

እንዲሁም የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ኢናያ አብዱልማሊክ እና ራህመት አደም በ 2016 ት/ዘመን በስሩት የፈጠራ ስራ ከክፍለ ከተማው የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::

በተጨማሪም በ2016 ት/ዘመን በተደረገ Uገር አቀፍ የሂሳብ ትምህርት ውድድር ተማሪ ነባት ፋሪስ ከ9ኛ ክፍል 1ኛ እና ተማሪ አማር ዘይኑ ከ12ኛ ክፍል 2ኛ በመውጣታቸው ክፍለከተማው የሜዳሊያ ሽልማት አበርክቶላቸዋል::

ይህንን ውጤት እንዲመጣ የበኩላችሁ የተወጣችሁ የት/ቤታችን መምህራን እና ቤተሰቦች እንዲሁም ተማሪዎች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ‼️‼️

Al-Afia Schools‘ Community

15 Oct, 06:32


HELPING YOUR CHILD WITH TEST-TAKING
 Talk to your child about testing and explain why schools give tests. Explain that tests are yardsticks that teachers and schools use to measure how well students are learning.
These tests are associated with the grades on report cards. The results tell the teacher,students and parents whether students are keeping up with the class, need extra help or are ahead of other students.
 Encourage your child. Praise him/her for the things that he/she does well. If your child feels good about herself, she will do her best on a test. Children who are afraid of failing are more likely to become anxious and more likely to make mistakes.
 Don’t place too much emphasis on test scores. This is elementary school. Emphasize learning, not scores. Demand effort and focus, not perfect results.
Celebrate good test scores, but don’t get upset because of a poor one. Many things can influence how your child does on a test. Use mistakes as a guideline for subject areas that need to be revisited. Consider repeating the test at home later. Celebrate effort and improvements.
 Meet with your child’s teacher to discuss his progress. Ask the teacher to suggest activities for you and your child to do at home to improve your child’s understanding of schoolwork.
 Make sure that your child attends school regularly. Remember, tests reflect children’s overall achievement. The more effort and energy your child puts into learning, the more likely it is that he will do well on tests.
 Provide a quiet, comfortable place for studying at home and make sure that your child is well rested on school days. Children who are tired are less able to pay attention in class or handle the demands of a test.
 Help your child avoid test anxiety. It’s good for your child to be concerned about taking a test. It’s not good for him/her to develop “test anxiety.” Students with test anxiety can become very self-critical and lose  confidence in their abilities. Instead of feeling challenged by the prospect of success, they become afraid of failure. Emphasize the learning process, not the results to your child.
 After the test, review the graded test paper with your child to discuss where he had difficulty and why. Often a child simply misread a question. Reviewing test results is especially important for classes in which the material builds from one section to the next, as in math
A PUBLICATION OF KS LEARNING
CONT.
BY: AL-AFIA SCHOOLS ENGLISH LANGUAGE DEPARTMENT

Al-Afia Schools‘ Community

15 Oct, 06:16


12ኛ ክፍል ለተፈተናችሁ ተማሪዎች

የዩኒቨርሲቲ ምርጫ የሞላችሁት በexcel file በ 12 ኛ ክፍል ቻናል ላይ ተለጥፏል::

የሚስተካከል ካለው ለት/ቤቱ ር/መ/ር ወይም ለIT መምህርት እስከ 9፡00 ማሳወቅ ይኖርባችኋል::

Al-Afia Schools‘ Community

13 Oct, 07:17


#AAU

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የማደሪያ አገልግሎት ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በመርካቶ፣ በላምበረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Al-Afia Schools‘ Community

13 Oct, 04:46


12ኛ ክፍል ለተፈተናችሁ

የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫን ይመላከታል::

የትምህርት መስክ እና ዩኒቨርሲቲ ስትመርጡ ያልተካተቱት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ አ/አ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፣ አክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲ ምርጫ መሙያ  Website ላይ የተካተተ በመሆኑ እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች በማካተት አስተካከላችሁ  መሙላት የምትፈልጉ ተማሪዎች ሰኞ  ቀን 04/2017 ት/ቤት መጥታችሁ እንድታስተካክሉ እያሳስበን ሳትሞሉ ከቀራችሁ ከላይ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሰረት ባለፈዉ ከሞላችሁት ምርጫ በመቀጠል የመጨረሻ ምርጫችሁ እንደሆነ የሚወሰድ ይሆናል፡:

Al-Afia Schools‘ Community

10 Oct, 19:17


ምን ፊልዶችን እናጥና⁉️
================
✍️ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋና አላማዬ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቢሆንም እየተማራችሁ ላላችሁና ለተመረቃችሁ ጭምርም ሊጠቅም ስለሚችል አንብቡት፤ ለሌሎችም አሰራጩት። የረጅም ጽሑፍ phobia ስላለባችሁ ቀጥታ ወደ ነጥቡ እገባለሁ።

*
①) ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦
ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስና ከርሱ ጋር ተያያዥ ወደሆኑ መስኮች የሚያስኬዷችሁን ፊልዶች ደጥኑ።
የዘንድሮውን የ2024 የፊዚክስ የኖቬል ሽልማት ትናንትና የወሰዱት ሳይንቲስቶች ለሽልማት ያበቃቸው ቀጥታ ንጹህ የሆነ የፊዚክስ ሥራ እንዳይመስላችሁ። ማሽን ለርኒንግን ተጠቅመው በANN የሠሩት የፊዚክስ ሃሳብ ነው። ሳይንቲስቶቹ Geoffrey E. Hinton ከUniversity of Toronto, Canada እና John J. Hopfield
ከPrinceton University, NJ, USA ናቸው። ለሽልማት የበቁት “for foundational discoveries and inventions that enable machine learning with artificial neural networks” በሚል ምክንያት ነው።

ስለዚህ በቀጣይ ኤአይ የማይነካው መስክ አለ ማለት ከባድ እየሆነ ነው። በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ … ያልገባበት የለም ማለት ይቻላል።

ስለሆነም የሚጠቆሙ መስኮች፦

1. Artificial Intelligence (AI) and Machine Learning (ML)
2. Biotechnology and Genetics
3. Climate Science and Environmental Studies
4. Quantum Computing and Physics
5. Neuroscience and Cognitive Science
6. Materials Science and Nanotechnology
7. Data Science and Bioinformatics

♠️
②) ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፦
ቴክኖሎጂው በናንተም ፊልድ መጥቷል። ስለዚህ ቴክኖሎጂውን ከፊልዳችሁ ጋር ለማዛመድ የሚያስችሉ መስኮች ላይ አተኩሩ። እኛ ሃገር ላይ ቶሎ ላይተኩ ቢችሉም ወደፊት በቴክኖሎጂው ሊተኩና ሊፈናቀሉ ከሚችሉና ስጋት ካለባቸው መስኮች ራቁ።

ስለሆነም በናንተ ዘርፍ የሚጠቆሙ መስኮች፦

1. Digital Sociology and Internet Studies
2. Public Policy and Global Governance
3. Behavioral Economics and Decision Sciences
4. Psychology and Mental Health Studies
5. Sustainability and Development Studies
6. Criminology and Cybersecurity
7. Cultural Anthropology and Diversity Studies

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት በቀጥታ እንድትመርጡ ከሚቀርቡላችሁ አማራጮች ጋር በስም ላይገናኙ ይችላሉ። ምረጡ የተባላችሁት ዝርዝሩ ቢኖረኝ በራንክ ለማስቀመጥ ይመቸኝ ነበር። ግን ስለሌለኝ እነዚህን ዝርዝሮች ከያዛችሁ በኋላ እንድትመርጡ ከቀረቡላችሁ ጋር አዛምዱ።

♠️
③) ውጤት ላልመጣላችሁ፦
ናቹራልና ሶሻል የሚለው ስለማይገድባችሁ መክሊታችሁንና የውስጥ ፍላጎታችሁን አዳምጡና ከላይ ከተዘረዘሩት መስኮች በአንዱ በግላችሁ ራሳችሁን አስተምሩ። በቂ ማቴሪያል ኢንተርኔት ላይ አለ። ጉዟችሁን ማፋጠን ከፈለጋችሁ ለዓይን መክፈቻ ያክል አጫጭር ስልጠናዎችን በብቃትና ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ የሚሰጡ የቴክኒክና የግል ተቋማትን አፈላልጋችሁ እነርሱ ጋር ተማሩ። አንደዜ በመስመሩ ከገባችሁ ቀሪውን ትቆሰቁሱታላችሁ።

ለሃሳቤ ማጠናከሪያ ኔክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ቀን በፊት ኦክቶበር 7 "The Future of Jobs Report 2024" በሚል ያወጣውን ጽሑፍና WEF (World Economic Forum) ባለፈ አመት ያወጣውን
The Future of Jobs Report 2023 ተጠቅሚያለሁ።

አላህ ያግዛችሁ። ሳትጨናነቁ ሰበቡን አድርሱ። በአላህ ተመኩ። ቁም ነገሩ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ሥራው ዓለም የሚፈለግ ተግባር ተኮር ዕውቀት መጨበጡም ላይ ነውና ሳትዘናጉ ሥሩ። ያላለፋችሁ የህይዎታችሁ ፍፃሜ ነው ማለት አይደለምና ከበረታችሁና በቁጭት የአላማ ሰው ከሆናችሁ ካለፉት በላይ ሁላ የምትሆኑበት አጋጣሚ ይኖራልና ተስፋ ሳትቆርጡ በርቱ።

ከወደዳችሁትና ይጠቅማል ካላችሁ ለሌሎችም አጋሯቸው።

♠️
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
ኦክቶበር 09, 2024

Al-Afia Schools‘ Community

10 Oct, 13:39


#MoE

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopia

Al-Afia Schools‘ Community

09 Oct, 15:04


12ኛ ክፍል የጨረሳችሁ ተማሪዎች

የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ የቀረው አንድ ቀን ነገ መስከረም 30 ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ዛሬ ያልሞላቹህ ተማሪዎች ነገ እስከ 3፡00 ት/ቤት በመምጣት እንድትሞሉ በድጋሚ እናሳውቃለን::

ምርጫው Remedial ለምትገቡ ተማሪዎችም ያካትታል::
ት/ቤቱ

Al-Afia Schools‘ Community

08 Oct, 18:03


በ 2016 ትዘመን 12ኛ ክፍል ለተፈተኑ  ተማሪዎች በሙሉ

ከላይ በተገለፀው መሰረት የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ እስከ መስከረም 30 መሙላት ይጠበቅባቸዋል::
በመሆኑም ተማሪዎች ነገ ትምህርት ቤት ከ 2: 30 ጀምሮ በመገኘት  ምርጫቸውን እንዲምሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን::

Al-Afia Schools‘ Community

08 Oct, 17:58


የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።


2. ማስታወቂያ

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር

ለዘንድሮ ሬሜዲያል ተማሪዎች 👇
Social Natural

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Al-Afia Schools‘ Community

08 Oct, 17:58


#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

★ በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahuniversity

Al-Afia Schools‘ Community

08 Oct, 17:58


የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️

በያዝነው አመት በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመማር የ12ኛ ክፍል ውጤት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የትምህርት ሚኒስትር ለተማሪኮም እንዳስታወቀው የ2016 የሪሚዲያል መግቢያ ነጥብ ለወንዶች 204 ለሴቶች ደግሞ 192 ሆኗል


[ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል]

ለዘንድሮ ሬሜዲያል ተማሪዎች 👇
Natural Social

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Al-Afia Schools‘ Community

01 Oct, 14:39


የመግቢያ ፈተና ውጤታችሁ ተለቋል

በ2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተፈተናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ውጤታችሁ ተለቋል፡፡ ፈተናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀምና አድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

👉ውጤት: https://stu.ethernet.edu.et #AASTU

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Al-Afia Schools‘ Community

26 Sep, 15:11


ቤቴል ቁጥር 2 አፀደ ህጻናት አዲሱ ግቢ ከፊል ገፅታ::

በአማረ እና ምቹ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል::

ትምህርት የፊታችን ሰኞ በደማቅ ሁኔታ ይጀመራል::

4,200

subscribers

358

photos

33

videos