Últimas publicaciones de Advanced Educational Consulting Ethiopia (@aec_ethiopia) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Advanced Educational Consulting Ethiopia

Advanced Educational Consulting Ethiopia
Certified Educational Consultants
4,191 Suscriptores
229 Fotos
6 Videos
Última Actualización 06.03.2025 13:31

El contenido más reciente compartido por Advanced Educational Consulting Ethiopia en Telegram

Advanced Educational Consulting Ethiopia

30 May, 18:13

2,788

#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
Advanced Educational Consulting Ethiopia

21 May, 13:16

8,438

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።

2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
Advanced Educational Consulting Ethiopia

20 Apr, 16:20

3,507

የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

Via @tikvahuniversity
Advanced Educational Consulting Ethiopia

08 Apr, 08:35

3,952

👉 የዚህ ዙር ትምህር ሚያዚያ 15, 2016
ይጀመራል!
👉 ቦታ ሲሞላ ወደ ቀጣይ ዙር እስኪሞላ
ይጠብቃሉ!
👉 ምጁሎችንና ሞዴል ጥያቄዎችን ያገኛሉ!
👉 ለኦንላየን መለማመጃ ፈተናዎች 50%
ቅናሽ ያገኛሉ!
Advanced Educational Consulting Ethiopia

24 Jan, 17:51

4,946

" የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ መራዘሙን አስታወቀ።

በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመፈተን የምዝገባ ጊዜው ጥር 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 15/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ መጠቀሱ የሚታወሰ ነው።

ይሁን እንጂ ትምህርት ሚኒስቴር በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት የምዝገባ ጊዜው እስከ ጥር 20/2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ሌሎች ሁኔታዎች ግን ቀደም ሲል በተገለጸው አግባብ የሚከናወኑ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል ፦ https://t.me/tikvahethiopia/84290?single

@tikvahethiopia
Advanced Educational Consulting Ethiopia

10 Jan, 12:10

4,749

የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በጥር ወር መጨረሻ ይሰጣል።

ፈተናውን ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም ለመስጠት መታቀዱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

በዚህም ሁሉም ፈተናውን የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከነገ ጥር 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቁልፍ ብቃት መለኪያ (Core Competency) ቲቶሪያል፣ የኮምፒውተር ስልጠና እና የሙከራ ፈተና (Mock Exam) መስጠት እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
Advanced Educational Consulting Ethiopia

07 Dec, 12:56

11,076

#ExitExam

📌ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች
📌ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የመውጫ ፈተናን ድጋሚ የሚወስዱ ተፈታኞችን ይመለከታል፤

በ2015 የትምህርት ዘመን በሁሉም የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል፡፡በተሰጡት ፈተናዎች የማለፊያ ነጥብ #ያላገኙ ተፈታኞች በጥር ወር መጨረሻ ላይ ለዳግም ፈተና እንዲቀመጡ ታቅዷል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ተፈታኞች በተቋማት እየኖሩ ስላልሆነ ተገቢውን ዝግጅት ለማድረግ እየተቸገሩ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይገልፃሉ፡፡

በመሆኑም ተቋሞቻችሁ በሚችሉት መንገድ ተፈታኞቹ #ቤተመጽሐፍት መጠቀም እንዲችሉ አስፈላጊው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉላቸው እንጠይቃለን፡፡ [ትምህርት ሚኒስቴር]


➡️ https://t.me/aec_ethiopia
Advanced Educational Consulting Ethiopia

13 Nov, 16:01

5,683

🌟 የምስራች ለመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች 🌟

🔔 ለመውጫ ፈተና በብቃት የሚያዘጋጅዎ Mock እና Model  Exam በ Online ይለማመዱ!

አድቫንስድ የትምህርት ማማከር አገልግሎት ማዕከል ከአተርቴክ የቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ጋር በመተባበር ፦

➭ በዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና መምህራን የተዘጋጀ፣
➭ የትምህርት ሚኒስቴርን የብቃት መስፈርት መሰረት ያደረገ፣
➭ ተገቢውን ሳይንሳዊ  የምዘና ሥርዓት የተከተለ፣
➭ ለአንድ ፕሮግራም ከ1,000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን የያዘ፣
➭ ሁሉንም የፈተና ኮርሶች ያካተተ፣
➭ ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስና ማብራሪያ የያዘ፣
➭ በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ሰዓት የሚያገኙት የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) መለማመጃ አቀረበልዎ!

ለሙሉ መረጃው፡-

➧ www.http://elts.com.et ይጎብኙ፣
➧ https://t.me/aec_ethiopia ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

#AdvancedEducationalConsultingCenter
Advanced Educational Consulting Ethiopia

07 Nov, 18:01

4,235

elts.com.et የአጠቃቀም መመሪያ
Advanced Educational Consulting Ethiopia

25 Oct, 20:00

5,796

የመጀመሪያውን የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚዘጋጀው ሌላ ፈተና መፈተን የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር  ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ስርዓት እንደሚዘረጋ መግለፁ አይዘነጋም (በዚህ ጉዳይ ወደፊት የሚወጣ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን)።