Последние посты ኢስላማዊ ግጥም (@abdul_fettah) в Telegram

Посты канала ኢስላማዊ ግጥም

ኢስላማዊ ግጥም
gram.me/abdul_fettah
በአቡ ያሲር የተገጠሙ - የተለያዩ ኢስላማዊ ግጥሞች ወደ እናንተ የሚደርስበት ቻናል ነው"Join"አድርጋችሁ ተቀላቀሉኝ ማስተካከልን እንጂ ሌላን አልሻም !!
@abdulfettahjemal
3,811 подписчиков
157 фото
15 видео
Последнее обновление 11.03.2025 07:46

Последний контент, опубликованный в ኢስላማዊ ግጥም на Telegram

ኢስላማዊ ግጥም

09 Feb, 05:10

1,514

🎤 ይህን ታላቅ ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን ኢንሻ አሏህ

በኢብን ሙዘይን ቻናል👇👇
https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy

ታላቅ የምስራች በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ ታላቅ የሙሓደራ ድግስ በአዳማ ከተማ


    እነሆ የፊታችን እሁድ የካቲት 2/2017 በአዳማ ከተማ 03 ቀበሌ በመደረሰቱል ፈትህ ወነስር ልዩ የሙሐደራ እና ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።

     የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች : –

①ታላቁ እና ተወዳጁ ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን ብን ሙሐመድ አስልጢይ (ሀፊዘሁሏህ)

②ተወዳጁ ዳዒ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁሏህ)
  
በአሏህ ፍቃድ ሌሎችም ይኖራሉ

     ፕሮግራሙ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2 : 30 የጀመራል ። 

https://t.me/adama_ahlusuna_weljemea
ኢስላማዊ ግጥም

08 Feb, 05:22

1,411

🖲ውርደት በአኼራ🖲

የሰው ስጋን መብላት አፍሽ ካላቆመ
አካልሽ ጠቅላላ   ከሀራም ካልፆመ
ወንድን ለመፈተን   ልብሽ  ከዳዳው
መኳኳል መዋዋብ ብሎም ከቃጣው
በሀራሙ ፍቅር ወንድን ለማስገባት
ድምፅሽን ማቅጠኑን ልብሽ ካማራት
ይህንን ከ ፈፀምሽ  በትልቁ  ወራት
እንደው ምን ይባል ያንቺ ተግባር ስሌት
የረመዳን ስራሽ ጥቅም አልባው ልፋት
ትርጉሙ አልገባኝም የፆምሽ ውጤት
አሁን አይደገም ይሄ መጥፎ ስራ
ያስከትልብሻል  ውርደት በአኼራ


✍️አቡ ያሲር አብዱል ፈታህ

የረመዳን ፆም ከሚለው ግጥም ለእህቶች ከተሰጠው ምክር የተወሰደ።
             👇👇
t.me/abdul_fettah
t.me/abdul_fettah
ኢስላማዊ ግጥም

06 Feb, 04:05

1,913

🗞ምርጡን ወር በላግጣ🗞

📱
ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም ወንድም
ምሽቱ እንዳይረፍድ አንተ ስታይ ፊልም
ማታ በተራዊህ  ቀን ክፍል በፆም
ቢያንስ 4 ግዜ ቁርዓን
ለማኽተም
ኢኽላስን ሰንቀህ  አሁኑን አልም


በአሉባልታ ነገር ማታ አታርፍድ
ሱብሂን በጀመዓ ሁል ግዜ ስገድ

ሱብሂማ በጀምዓ ወንድም የሚሳካው
Data መጠቀሙን ስትቀንስ ብቻ ነው

እስኪ በfb  አፍጥጠህ ካደርክ
በኢሞ በቫይበር  ሴት እያናገርክ
እስከ 8 ሰዓት ጫትህን ከቃምክ
የቀኑንም ክፍል  ተኝተህ ከዋልክ

ግዴታ ሰላትን መስጅድ ካልሰገድክ
ጥያቄ አለኝ ለኔ እስኪ ልጠይቅክ
በራህመቱ ወር  ምኑን ተጠቀምክ

እንዲህ ስትሳነፍ ሊያውም በረመዷን
እንዴት ዘነጋሀው እንዳለው እርግማን
ጊዜ'ኮ ሰይፍ ነው አንተ ካልቆረጥከው
ቆርጦ ይጥልሃል ቆመህ ከጠበቅከው

ቲክቶክን በተለይ ከስልክህ ላይ አውጣ
እንዳታሳልፈው ምርጡን ወር በላግጣ
____💧
🕳የተለያዪ አፕልኬሽኖች የረመዷንን ውድ ግዜዎችን የሚገድሉብን ስለሆኑ መጠንቀቅ አለብን ካለፈው ስህተታችን ታርመን በዘንድሮው ረመዷን በአግባቡ ዒባዳ ለመስራት መዘጋጀት ይኖርብናል።


አቡ ያሲር_አብዱልፈታህ

ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ሼር አድርጉት


➡️ የቴሌ-ግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
                 👇👇
https://t.me/abdul_fettah
https://t.me/abdul_fettah
ኢስላማዊ ግጥም

05 Feb, 15:09

1,240

👉ትናንትና ባስጠነቀቁት ነገር ላይ
ዛሬ የወደቁ ጉዶች

        ክፍል ስድስት
ይደመጥ

አቡ ሙስሊም እንዲህ ይላል፦
⚠️ ጄላን ለኢብኑ ሙነወር ምን አለው?

👉 በሰላሳ ኪኒኖች ውስጥ  ያለው ስህተት ብዙ የመንሃጅ ስህተት ነው
ዝም ብለን አይደለም
ዛሬ ችግር አለባቸው የምንለው በአንዴ አይደለም

⚠️ ጄላን ይላል :-
እነ ኢልያስ ተመልሰዋል ከኛጋ ሆኖዋል
ይላል አስለን በድምፅ አለኝ  ከአስር አመት በፊት ሲያደርግ የነበረውን ደዕዋ ቀይሮዋል ይላል በድምፅ ነው የሚለው
ከፈለጋቹህ ሰላሳ ምክሮችን አላደማጠቹም እሳጣቹሃለው ይላል።

ጄላን ማለት :- 
ኢትዮ ላይ እያለ ሱዑዲን ሚረግም  
ሀጅ ሲመጣ በሱዑዲ ወጪ ሚሄድ ሰው ነው........

እኛ እነዚህን አካላት አቋም ቀይረዋል ስንል በመረጃ ነው።
👌 አሁንም ቢሆን ሰከን ብላችሁ ወደ ጤናችሁ ብትመለሱ ይበጃል።

  አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን!

https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy
ኢስላማዊ ግጥም

03 Feb, 15:04

1,564

https://t.me/abdul_fettah
ኢስላማዊ ግጥም

03 Feb, 15:04

1,665

⚠️ትናንትና ባስጠነቀቁት ነገር
ላይ ዛሬ የወደቁ ጉዶች

        ክፍል አምስት

👉 ኸድር ከሚሴው ድሮ ስለሙመይዓዎች ይህን ይል ነበር ዛሬ በዚሁ ባስጠነቀቀው የተመዩዕ አደጋ ውስጥ ገብቷል

⤵️ የከድር ከሚሴ የበፊቱ አቋሙ ይሄ ነበር  አሁን ላይ ቢሟሟም

⚠️ አልሙመዪዓህ የተሰኙት አካላቶች ወይም ጉሩፖች ተምዪዕ እና ነገራቶችን ያለ አግባብ በመለጠጥ እና በማግራረት የሚታወቁ አካላቶች አሉ ግልፅ የሆነ ነገር ነው።

⚠️ የሙመዪዓ መንገድ አዲስ መንገድ ነው ዑለማዎች የኮነኑት መንገድ ነው ብዙ አኢማዎች  ኮንነውታል ይህንን መንገድ እኛ አንቀበልም።

👉 ከቢዳዓ ባልተቤቶች ጋር መተጋገዝ ይቻላል የሚል ቃዒዳ ይዘው የተነሱ አካሎች ሆነው ተስተውለዋል።

ድሮ ሱናን ያንፀባርቁ ነበር  በኋላ በኋላ ላይ ግን ከቢደዓ ባልተቤቶች ጋር አብሮ መስራት ችግር የለውም የሚል ቃዒዳ ይዘው መጥተዋል በመልካም ነገር እስከሆነ ድረስ ይላሉ !  ይህ ባጢል ነው።

⚠️ ተምዪዕ ውስጥ የገቡ አካላቶችን ሌሎች ሙብተዲዓዎች መጠቀሚያ ድልድይ እንደደረጓቸው ተመልክተናል።

<><><><><><><><><><>
👉 እኛ እነዚህን አካላት አቋም ቀይረዋል ስንል በመረጃ ነው።
👌 አሁንም ቢሆን ሰከን ብላችሁ ወደ ጤናችሁ ብትመለሱ ይበጃል።

  አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን!

https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy
ኢስላማዊ ግጥም

31 Jan, 04:21

2,712

🗞ወሩን የነሺዳ🗞
አስማእ ወሲፋትን ማያፀድቅ ጠማማ
የአህባሽ የተብሊግን የሽርክ መንዙማ
ወንድም አደራህን በጭራሽ አትስማ
ሚሰራው ነሺዳ በ እስልምና ስም
አያውቀውም ዲኑ ነቃ በል ወንድም
የነغም ቅላፄ  የሸይጧን መሳሪያ
ከገባበት ተወው አንተ የአላህ ባሪያ
የረሱልን ﷺ ስም አድርጎ መሸቀያ
ቁርዓን እንዳትቀራ አንተን ማዘናጊያ
ረመዷን ጠብቆ ሞቅ እንዲል ገበያ
መንዙማ ሚለቀው ሁሌ በየ አመቱ
አትስማው በጭራሽ ራቀው የትአባቱ
አሳልፈው እንጂ በዚክር በዒባዳ
እንዳታስመስለው ወሩን የነሺዳ


አቡ ያሲር_አብዱልፈታህ

➡️ የቴሌ-ግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
                 👇👇
https://t.me/abdul_fettah
https://t.me/abdul_fettah
ኢስላማዊ ግጥም

31 Jan, 04:20

1,494

የረመዷን ትልቁ ዝግጅት‼️

❝ ለመልካም ነገራቶች'ን አዝመራ ከሚደረጉ መሰናዶዎች ሁሉ የተሻለው ኢስቲግፋር ማብዛት ነው። አንድ ሰው ወንጀሎቹ ለመልካም ነገር ከመገጠም ሊያሰናክሉት ይችላሉና።❞

[© አሽ_ሺንቂጢ]

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
ኢስላማዊ ግጥም

31 Jan, 03:17

1,352

🔈 #ስለ ቡርዳ ምን ያውቃሉ

📚 ከሸይኽ ሙሐመድ ጀሚል ዘይኑ (ሱፊያ በቁርኣንና በሐዲስ ሚዛን) ኪታብ ደርስ የተወሰደ

🎤 ከሸይኽ ፈውዛን ፈትዋ ጋር

ቀጣዩን ትምህርት (ነገ ጁምዓ ከመጝሪብ በኋላ ይቀጥላል) ለመከታተል ከፈለጉ ወደ አልበያን መድረሳ ጎራ ብለው ይጎብኙን በርካታ እውቀትን ይቀስማሉ ኢንሻአላህ። ካልሆነም ቴሌግራም ላይ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉን።

🎙ኡስታዝ ኑራዲስ ቢን ሲራጅ (አቡልበያን) ሐፊዘሁላህ


🌐 https://t.me/albeyanbutajiragroup
ኢስላማዊ ግጥም

29 Jan, 16:38

3,502

ስለ ረመዷን በአቡ ያሲር

🗞 አዲስ መፅሀፍ🗞

የረመዷን ፆም ምክር በሚል ርዕስ  የተሰናዳ አማርኛ ግጥም:-

<> በውስጡ እጅግ ብዙ ጠቃሚ ምክሮችን አካቶ ይዟል : ግጥሙ በእነዚህ [ 6 ] ጉዳዮች ላይ የጠነጥናል
🗞የሚዲያ አጠቃቀም
🗞 ምክር ለወንድሜ
🗞 ምክር ለእህቴ
🗞የረመዷን በላጭነት
🗞ለፆመኛ ተወዳጅ ተግባራት
🗞ፆምን የሚያፈርሱ ነገሮች

አዘጋጅ ወንድም አቡ ያሲር ዐብዱልፈታህ ጀማል ሃፊዘሁሏህ

➡️ የቴሌ-ግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
                 👇👇
https://t.me/abdul_fettah
https://t.me/abdul_fettah
   <><><><><><><><><><>
https://t.me/YusufAsselafy