Abay Media

@abaymedia


Abay Media

Abay Media

21 Nov, 06:18


Can you do me a favor? Just accept this invitation, up to $50 for each of us!!
https://temu.com/s/6cx5rq9Exlntrj

Abay Media

26 Dec, 22:00


"አሜሪካ የህክምና ክትትል እያደረግኩ፣ እዛ በሚገኘው ቢሯችን እየተገኘሁም ስራዬን እየሰራሁ እገኛለሁ"--- አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለኢትዮጵያ ቼክ

ከሰሞኑ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች፣ አካውንቶች እና ቻናሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከስራቸው እንደለቀቁ፣ በውጪ ሀገር ጥገኝነት እንደጠየቁ እንዲሁም ከስራ ታግደው አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚገኙ የተለያዩ ፅሁፎችን ሲያጋሩ ተመልክተናል።

በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ኢትዮጵያ ቼክ አቶ ተወልደን እንዲሁም አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የስራ ባልደረባቸውን መረጃ ጠይቋል።

አቶ ተወልደ "አሜሪካ የህክምና ክትትል እያደረግኩ፣ እዛው በሚገኘው ቢሯችን እየተገኘሁም ስራ እየሰራሁ እገኛለሁ" የሚል አጠር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። የስራ ባልደረባቸው የሆኑት ግለሰብም ይህንን አረጋግጠው "ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚፃፈውን እኔም እያየሁ ነበር፣ ፍፁም ውሸት ነው" ብለው መልስ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በተጨማሪ አየር መንገዱ እስከ ቅርብ ቀናት ድረስ ያወጣቸውን ጋዜጣዊ መግለጫዎች የተመለከተ ሲሆን ከትናንት በስቲያ አርብ (ታህሳስ 15/2014) የወጣ መግለጫ ላይ እርሳቸው እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚ የተጠቀሱበት እና አስተያየት የሰጡበት መግለጫን ተመልክቷል።

ስለዚህ በዚህ ዙርያ ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎች ከሶስት አቅጣጫ ሲታዩ ሀሰተኛ እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል።

ያልተረጋገጡ፣ ማስረጃ ያልቀረበባቸውን እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይቀንሱ።

Via #EthiopiaCheck Exclusive

Abay Media

26 Nov, 12:55


Message from PM Dr Abiy

Abay Media

26 Nov, 00:40


Breaking!!!!!

Today's War

Abay Media

14 Nov, 11:39


ኅዳር 5/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሕወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደርና ሰሜን ወሎ ዞኖች 184 ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ ማረጋገጡንና የአማጺዎቹ ወንጀሎች የጦር ወንጀሎች ስለመሆናቸው አመላካች ሁኔታዎችን እንዳገኘ አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። አማጺዎቹ በሰላማዊ ሰዎች ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እንዳደረሱ፣ ሆን ብለው ሲቪል መሠረተ ልማቶችና እና እምነት ተቋማትን እንዳወደሙና እንደዘረፉ ሪፖርቱ ገልጧል። አማጺዎቹ ሰላማዊ ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መድፍ እንደተኮሱ እና ከሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ውስጥ ምሽግ ቆፍረው ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ነዋሪዎች ለመንግሥት አጸፋዊ ጥቃት እንዲጋለጡ ማድረጋቸውን ሪፖርቱ ገልጧል። ከሰኔ 21፣ 2013 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 22 ምርመራ የተደረገው፣ በደብረታቦር፣ ሐራ፣ ወልድያ፣ ቆቦ፣ ራያ ቆቦ፣ ራያ አላማጣ እና ማይጨው ከተሞች ሲሆን፣ በወቅቱ የግጭት ቀጠና የነበሩት ዋግኽምራ ዞን፣ ሰሜን ጎንደር ዞን እና የሰሜን ወሎ አንዳንድ ከተሞች በምርመራው አልተካተቱም።

2፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አሜሪካ ትናንት በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታነሳ መጠየቁን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። አሜሪካ ማዕቀቡን ስትጥል፣ ሕወሃት በኤርትራ ላይ ሚሳይሎችን መተኮሱን፣ ኤርትራ የግዛት አንድነቷና ሉዓላዊነቷ ላይ ከጥቃት መከላከል መብቷ መሆኑን፣ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ስለመኖራቸው ኢትዮጵያ ለዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ቅሬታ አለማቅረቧን እና ኤርትራ ወታደሮቿን ከሰኔ ጀምሮ ከትግራይ ማስወጣቷን ከግምት ውስጥ አላስገባም በማለት ማዕቀቡን አውግዟል። ኤርትራ ለኢትዮጵያ ሰላም እንቅፋት አይደለችም ያለው መግለጫው፣ በኢትዮጵያና አፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ አሜሪካ እና ቀሪው ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች ርምጃዎችን መውሰድ ያለባቸው በሕወሃት ላይ መሆን አለበት ብሏል።

3፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞችን እና ቀሳውስትን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ተወላጆች በጅምላ እየታሰሩ ነው ሲል አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። መንግሥት ያወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጸጥታ ኃይሎች አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚጠረጥሯቸውን ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር እንዲያውሉ እና አስረው እንዲያቆዩ መፍቀዱ ከዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎች ጋር ይጻረራል- ብሏል አምነስቲ።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፣ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት በብሄር ማንነታቸው ምክንያት እንዳልሆነ እና የተያዙትም መረጃዎች እየተጣሩ እንደሚለቀቁ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

4፤ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ትናንት በሰጡት መግለጫ ትግራይ ክልል በተቀናጀ እቀባ ስር በመውደቋ ሰዎች በመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረት እየሞቱ ነው በማለት ተናግረዋል። በትግራይ ክልል ላይ ተጥሏል ያሉትን እቀባ ማን እንደጣለው ወይም ተጠያቂው ማን እንደሆነ ግን ዶ/ር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው አለብራሩም። የተመድ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሐሙስ'ለት ባወጣው መረጃ፣ በትግራይ 400 የዕርዳታ ሠራተኞች ቢኖሩትም የነዳጅ እጥረት የዕርዳታ ሥራዎቹን እንዳስተጓጎለበት ገልጧል። በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ ደሞ ዕርዳታ የጫኑ 364 የተመድ ካሚዮኖች ወደ ትግራይ ለመግባት ገና ፍቃድ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ቢሮው አመልክቷል።

5፤ አሜሪካ በኤርትራ መንግሥታዊ ተቋማት፣ ንግድ ኩባንያዎች እና ግለሰቦች ላይ ትናንት የጣለችው የተናጠል ማዕቀብ ጥፋተኛውን ትቶ በተጎጅው ላይ የተጣለ ኢሞራላዊ ማዕቀብ ነው ሲል የኤርትራ መንግሥት በሸባይት ድረገጹ ባወጣው መግለጫ አውግዞታል። አሜሪካ የጣለችው የተናጥል ማዕቀብ፣ ዓለማቀፍ ሕጎችን እና የሀገራትን ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚጻረር እንደሆነ የጠቀሰው መግለጫው፣ የማዕቀቡ ዓላማ በኤርትራ ውስጥ ርሃብ እና እርዛትን በማስፋፋት ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለመፍጠር እና በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ ሰላም እንዳይሰፍን ለማድረግ ነው ብሏል። ኤርትራ የነጻነት አፍቃሪ የሆኑ ሀገራት ሁሉ የአሜሪከን የተናጥል ማዐቀብ በመቃወም ከጎኗ እንዲቆሙ ጠይቃለች።

6፤ የኬንያ መንግሥት ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ ሕገወጥ ስደተኞች እና ሽግግር መንግሥት አካል የነበሩ ሲቪሎችን ግን በአዲሱ ሉዓላዊ ምክር ቤት አላካተቱም።

Abay Media

26 Oct, 14:58


ለቸኮለ! ሰኞ ጥቅምት 15/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

ማምሻውን በወጣ ዜና፤

አሜሪካ ዛሬ በጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ ሥልጣን የተደረገበት የሱዳን ሲቪል መንግሥት ባስቸኳይ ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ማምሻውን ማሳሰቧን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። አሜሪካ ጦር ሠራዊቱ ሥልጣኑን ለብቻው መጠቅለሉን በመቃወም ለሀገሪቱ ልትሰጠው የነበረውን 700 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታም ማገዷን አስታውቃለች። ⁩

1፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የሽግግር ሰነድ የተቀመጠው የዲሞክራሲያዊ ሽግግር ጊዜ እንዲጠናቀቅና የሽግግሩ ሰነድ እንዲከበር እንደሚፈልግ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ በኩል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ዛሬ በሱዳን የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በማስመልከት በወጣው ይኼው መግለጫ፣ ሁሉም ወገኖች ውጥረቱን እንዲያረግቡ እና ለቀውሱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ መንግሥት ጥሪ አድርጓል። ኢትዮጵያ በሱዳን ቀውስ ውስጥ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር እንደምትፈልግም መግለጫው አክሎ ገልጧል።

2፤ ፌስቡክ ኩባንያ የፌስቡክ ማኅበራዊ ትስስር ዘዴው በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሰ እንደሆነ እያወቀ አንደችም ርምጃ እንዳልወሰደ ለአሜሪካ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ከቀርቡት ሚስጢራዊ የኩባንያው ሰነዶች ተመልክቻለሁ ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል። ኩባንያው ኢትዮጵያን "ለግጭት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት" በሚለው ምድብ ቢያስቀምጣትም፣ የኩባንያው ሠራተኞች ፌስቡክ በኢትዮጵያ ለግጭት አባባሽነት እየዋለ ስለመሆኑ ላቀረቧቸው ጥቆማዎች ግን ኩባንያው ምላሽ እንዳልሰጠ ከሰነዶች መረዳት መቻሉሉን ዘገባው ገልጧል። ሰነዶቹ የውጭ መንግሥታትና ድርጅቶች በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና ግጭትን ለመስበክና ለማሰራጨት ፌስቡክን እንደተጠቀሙበት ያሳያሉ ተብሏል።

3፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ አዘጋጀዋለሁ ባለው ብሄራዊ የፖለቲካ ውይይት ቢሳተፍ ተሳትፎው ዋጋ አይኖረውም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኦፌኮ የብሄራዊ ውይይቱ አካል የሚሆነው፣ በትጥቅ የታገዙ ግጭቶች ቆመው ሁሉም ታጣቂ ኃይሎች በድርድሩ ከተካተቱ፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ከተፈቱና ውይይቱ የዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ ባለው የውጭ ገለልተኛ አካል የሚመራ ከሆነ ብቻ እንደሆነ መግለጫው አብራርቷል። የፓርቲው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ አካታች ባልሆነ ውይይት መሳተፍ ፍሬ የለውም- ብሏል ፓርቲው።

4፤ የአማጺው ሕወሃት ወታደራዊ ዕዝ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከምቦልቻ ከተማ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ሲቪል አውሮፕላኖች እንዳያርፉ ማሳሰቡን የሕወሃት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ተዋጊዎቹ በደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ ደሴ በቅርብ ርቀት ያሉ ቦታዎችን እንደተቆጣጠሩ መግለጣቸውን እና ኮምቦልቻ ከተማን በመድፍ ርቀት ውስጥ አስገብተናል ማለታቸውን ዘገባዎቹ ጠቁመዋል።

5፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ትናንት በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ የደበደበው አልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን እንደሆነ የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ አረጋግጠውልኛል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ፋብሪካው የጥቃት ዒለማ የሆነው፣ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ከኤርትራ ሠራዊት ደንብ ልብሶች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ወታደራዊ አልባሳትን ለሕወሃት ታጣቂዎች በማምረቱ እንደሆነ ለገሠ ተናግረዋል። ሌሎቹ ዒላማዎች በምዕራብ ትግራይ ማይጸብሪ አካባቢ የሚገኝ የነዳጅ ዲፖ እና ወታደራዊ ማሰልጠኛ እንደሆኑ የተገለጠ ሲሆን፣ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ግን ጥቃቱ የተፈጸመው በሆስፒታል ላይ ነው ብለዋል።

6፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ለቤት ሠሪዎች ብድር ለመስጠት የተቋቋመው ሞርጌጅ ባንክ ዛሬ በአዲስ አበባ በይፋ ሥራ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። ጎህ ቤቶች ባንክ የተባለው የግል ባንክ በቤት ግንባታ ለተሠማሩ ደንበኞች ብድር የማቅረብ ዓላማ ያለው ሲሆን፣ በሀገሪቱ ታሪክም በዋናነት ለቤት ሠሪዎች ብድር አቅራቢ የሆነ የግል ባንክ ሲቋቋም ያሁኑ የመጀመሪያ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።

7፤ ዛሬ በሱዳን ሽግግር መንግሥት ላይ መፈንቅለ ሥልጣን ያካሄዱት የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳወጁ የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ጀኔራል ቡርሃን ራሳቸው የሚመሩትን ከፍተኛውን የሱዳን ሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት፣ ሲቪሉን ካቢኔ እና የክፍለ ሀገር ገዥዎችን በሙሉ የበተኑ ሲሆን፣ ከዓመት በኋላ ጠቅላላ ምርጫ እንደሚደረግ አስታውቀዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ ያስፈለገው፣ የሽግግር መንግሥቱ ባለሥልጣናት የሥልጣን ፍትጊየ በሀገሪቱ ሰላም እና ብሄራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ በመደቀኑ እንደሆነ ቡርሃን ተናግረዋል።

8፤ ዛሬ ጧት መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው የሱዳን ጦር ኃይል ጠቅላይ ሚንስትር ሐምዶክን፣ አራት ሲቪል ሚንስትሮችን እና የክፍለ ሀገር ገዥዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ዓለማቀፍ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ በመካሄድ ላይ እያለ የጠቅላይ ሚንስትር ሐምዶክ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ መላ ሱዳናዊያን የመንግሥት ግልበጣውን አደባባይ ወጥተው እንዲቃወሙት ጥሪ አድርጓል፤ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተዋል ተብሏል። የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ጄኔራል ሞሐመድ ዴጋሎ (ሐሚቲ) የሚመሩት ኢመደበኛው ፈጥኖ ደራሽ ታጣቂ ኃይል በመንግሥት ግልበጣው ከሠራዊቱ ጋር አብሯል። አሜሪካ፣ አውሮፓ ኅብረት፣ ተመድ እና አፍሪካ ኅብረት በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ መደረጉ እንዳሳሰባቸው ገልጠዋል። [ራዲዮ]

Abay Media

22 Sep, 01:03


አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ዴቪድ ቤስሊ ጋር ተወያዩ
*************************

በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል መንግሥት በሃላፊነት ስሜት የሚያካሂደው የሰብዓዊ ድጋፍ ጥረት እውነቱ ሊሸፈን እንደማይገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በ76ኛ የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባኤ ለመሳተፍ ኒው ዮርክ፣ አሜሪካ የገቡ ሲሆን፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ዴቪድ ቤስሊ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል መንግሥት በሃላፊነት ስሜት የሚያካሂደው የሰብዓዊ ድጋፍ ጥረት መሬት ላይ ያለው እውነት ሊሸፈን እንደማይገባም አሳስበዋል።

ሰብዓዊ ስጋቶችን ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ የሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን አብራርተዋል።

በሰብዓዊ ዕርዳታ ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ከ~WFP ጋር መንግሥት በቅንጅት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመጠቆም፤ በቀጣይም ውጤታማ በሆነ አግባብ ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥን በማመቻቸት ረገድ በመንግስት ላይ ሚዛናቸውን ያልጠበቁ እና ትክክለኛ ያልሆኑ ክሶች ተደጋግመው እንደሚነሱ በማስታዎስ፤ በመንግስት በኩል የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በችግሩ ተጎጂ ለሆኑ ወገኖች በሙሉ ተደራሽ ያደረገ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

Abay Media

06 Sep, 12:04


ነሐሴ 27፣ 2013

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 2 ቢሊዮን ብር ያወጣበትን የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ ማጠናቀቁን ተናገረ።

4 ዓመት የግንባታ ጊዜ የወሰደውና በምስለ ንብ አና የንብ እንጀራ የተሰራው ህንፃ የፊታቸው ቅዳሜ እንደሚመረቅ ሰምተናል።

ባለ 37 ወለሉ የንብ ባንክ አዲሱ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የተለያዩ ቢሮዎች ፣ሱቆች፣ የህፃናት መዋያ፣ የስፖርት ማዘወተሪያ፣ 500 ሰው የሚይዝ አዳራሽና ለሌሎች አገልገሎት የሚውሉ ክፍሎች አንዳሉት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ገነነ ሩጋ ተናግረዋል።

ህንፃውን የቻይናው ጃንግሱ ህንፃ ተቋራጭ የሰራው ሲሆን ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ እንዳጠናቀቀ ሰምተናል።

የህንፃው ወጪ ሲጀመር በ1.67 ቢሊየን ብር ይጠናቀቃል ተብሎ ታስቦ የነበረ ሲሆን በዋና ምክንያትነት የዲዛይን ለወጥ በመደረጉ ወጪው 2 ቢሊዮን መድረስ መቻሉንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል ።

በአዲስ አበባ ራስ አበበ አረጋይ ጎዳና ንግድ ስራ ት/ቤት ( ኮሜርስ) ፊት ለፊት የተገነባው የባንኩ ህንፃ አብዛኛው ክፍሎቹ ለባንኩ አገልግሎት ሲውሉ ቀሪዎቹ ቢሮዎች ይከራያሉ ተብሏል።

አዲሱ ህንፃ ባንኩ በዓመት ለዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ኪራይ የሚያወጣውን 30 ሚሊዮን ብር እንደሚያስቀርለትም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ንብ ባንክ በመጪው አዲስ ዓመት ስራ የሚያስጀምረው የቴክኖሎጂ ማዕከል ግንባታ እያጠናቀኩ ነው ብሏል፡፡

ከተመሰረተ 22 ዓመት የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የተከፈለ ካፒታሉ 5 ቢሊዮን ብር መሆኑን ከፕሬዚዳንቱ ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ንብ_ኢንተርናሽናል_ባንክ #ህንፃ_ግንባታ

Abay Media

28 Aug, 14:28


ትዕግስት ገዛሀኝ መንግስቱ በሴቶች 1,500 ሜትር በማሸነፍና በፓራሊምፒክ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ለማስገኘት #በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አትሌት በመሆኗ እንኳን ደስ ያለሽ። #ኢትዮጵያ ኮርታብሻለች!

Congratulations to Tigist Gezahagn Menigstu for winning the Women’s 1,500m and becoming #Ethiopia’s first Paralympic Games gold medalist. #Ethiopia is proud of you!

Abay Media

20 Aug, 19:15


አሁናዊ የዋጋ መናር ችግርን ለመከላከል ምን መደረግ አለበት ?

(ክቡር ገና - ለኢፕድ ከሰጡት ቃል)

- አስመጪዎቹ ማን እንደሆኑ ይታወቃሉ ፤ ስለዚህ መጋዘናቸው ውስጥ ምርቱ አለ ወይስ የለም ? የት አደረሱት የሚለውን መንግስት መከታተል አለበት። ኅብረተሰቡም ዋነኛ ተባባሪ በመሆን ሥራውን ሊተባበር ይገባል።

- ህብረተሰቡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሕገወጥነት ሲከሰት ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ይገባዋል።

- መንግሥትም ከመጠን በላይ ያከማቹትን መለየት አለበት ከዚህ ባለፈ ተፈላጊ ምርቶች የሚባሉትን በመለየት በብዛት ወደገበያው እንዲቀርቡ ማድረግ ይኖርበታል። ይህም ፋብሪካዎች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ማድረግ።

- ከውጭ የሚመጣውንና በጣም አስፈላጊ ነው የሚባል ምርትን መንግሥት እራሱ አስገብቶ እንዲከፋፈል በማድረግ ችግሩን መቀነስ ይቻላል።

- መንግሥት በእራሱ ድርጅቶች በኩል ዋና ዋና ምርቶችን በማስመጣት የዋጋ መናርን ለማቀዛቀዝ ይችላል።

- መንግሥት ሁሉን ነገር ክፍት አድርጎ ጫናውን ሊቋቋመው ስለማይችል ሁኔታው እስኪረጋጋ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በዋና ዋና ምርቶች ላይ ከዚህ ዋጋ በላይ መሸጥ አይቻልም የሚል እቀባን ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባታል።

- ምርት ያቆሙና የቀነሱ ፋብሪካዎችን በመደገፍ በብዛት እንዲያመርቱ ማድረግ የምርት እጥረትን ሆነ የዋጋ መናርን ይከላከላል። ይህ ምርት የደበቁ አውጥተው እንዲሸጡ እና በገበያ ውድድር ውስጥ እንዲገቡ ያስገድዳቸዋል።

- መንግሥት በሚያምናቸው ነጋዴዎች አማካኝነት በተለየ ሁኔታ ምርቶች ወደአገር ውስጥ የሚገቡበትን መንገድ ማመቻቸት ይችላል። በዚህ ወቅት ምርት ደብቀው እና አሽገው ያስቀመጡ ግለሰቦችም እንዳይከስሩ በማሰብ ወደገበያ የሚያወጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል።

Abay Media

15 Aug, 21:35


ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
በልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙሃንናና ማህበራዊ ሚዲያዎች ከምሸቱ 1፡00 ሰዓት በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ልጫ ቀበሌ (ከእሰቴ 30 ኪሎ ሜትር ወደ አንበሳሜ ከተማ በሚወስደው መንገድ ላይ) የቀይ መስቀል አምቡላንስ ሁለት ኩንታል ብር፣ ስድስት ስናይፐር፣ ክላሽና ጥይት ይዞ ሲንቀሳቀስ እርምጃ መወሰዱን አስመልክቶ ዜና ተዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባደረገው ማጣራት ተግባሩን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንስ ያልፈጸመዉና ድርጊቱን የፈጸመው ሌላ ተሽከርካሪና ድርጊቱን ፈጻሚዎችም በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተረጋግጧል፡፡ ለበለጠ መረጃ የእስቴ ወረዳ የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤትን ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ገለልተኝነቱን ጠብቆ፣ የሁሉንም ወገኖች ዕምነት አግኝቶ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን፣ ሁሉም የሚዲያ ተቋማት እንዲያውቁና ከማህበራዊ ሚዲያ የሚያገኙትን መረጃ ከመዘገባቸው አስቀድሞ ከሚመለከተው አካል እንዲያረጋግጡ እንገልጻለን፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዛሬም እንደትናንቱ፣ ነገም እንደዛሬው በአለቶችና በተግዳሮቶች መካከል በጽናት በመቆም ሰብዓዊ ተግባሩን ያከናውናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት፣ አጋሮቹ፣ በጎፈቃኞቹና አባላቱ፤ እንዲሁም በግጭት አካባቢ የሚገኙ ሃይሎች ሁሉ በገለልተኝነትና ያለአድሎ ለምናከናውነው ሰብዓዊነትንና ሰብዓዊነትን ብቻ ማዕከል ላደረገ ተልዕኮአችን የዘወትር ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡

Abay Media

15 Aug, 19:03


በመታነጽ ላይ ሳለህ የቦዘንክ ቢመስላቸው አትደነቅ!

ድሮ እኛ ሃይ ስኩል ስንማር፣ ከመማር ይልቅ ፋብሪካ መሥራት ይሻላል ብለው ትምህርት አቋርጠው ሥራ የገቡ ጓደኞቻችን ነበሩ።

እነዚህ ጓደኞቻችን ወድያው በወሩ ደመወዝ አገኙ፣ ልብስ ቀየሩ። ሲቆዩ ቤት ተከራዩ፣ አልጋና ፍራሽ፣ ቁምሳጥን ወንበርና ጠረጴዛ ገዙ፣ ጓደኛ ያዙ፣ ኬክ ጋበዙ። ኋላም አንዳንዶቹ አግብተው ሌሎቹም በውጭ ወለዱ።

ያኔ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በኋላ አንዱ ወዳጄ አገኘኝና "አሁንም እየተማርክ ነው?" አለኝ። "አዎ!" ነበር መልሴ። "አይደክምህም? አይሰለችህም?" አለኝ። "አሁን እኮ ልጨርስ ነው" አልኩና ተለየሁት።

ከዓመት በኋላ እኔ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ይዤ ሥራ ስጀምር፣ የወዳጄ ደመወዝ የእኔን ሩብ ያህል ነበር። ከብዙ ዓመታት በኋላ አንድ ምሽት ላይ ወዳጄን አገኘሁት። "ከየት ነው?" ስለው "ከትምህርት" አለኝ። የማታ ትምህርት ጀምሮ ነበር። በቀን "አይሰለችህም?" ያለኝን እሱ በማታ መትጋት ጀምሮበት ኖሯል። "ህምምም..." ብዬ "ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?" ስለው እኔ ቀን የተማርሁትን እጥፍ ጊዜ ጠራልኝ።

አንዳንዱ እንዲህ ነው። መጀመሪያ ሳይታየው፣ ኋላ ከረፈደ እጥፍ ዋጋ ሊከፍል ይገደዳል። ስኬት ቀድሞ በመራ አይደለም። ከእውቀት ሥራን ባስቀደመም አይደለም። ሥራ በዕውቀት ካልሆነ ልፋት ነው።

6ተኛ ፎቅ ላይ በፓምፕ እየተገፋ ኮንክሪት ሲሞላ አይተሃል? ያ በእውቀት የሚሠራ ነው። ያለእውቀት የሚሠራው ግን በባሬላ እያጋዘ ይደክማል።

ትጋት እና ልፋት ይለያያሉ። ትጋት የእውቀት ሥራ፣ ልፋት ደግሞ ተቃራኒው ነው። ትጋ እንጂ አትልፋ!

በልፋት የትም አትደርስም። ይልቅ ጭንቅላትህን አጎልምስ።

አየህ አንተ ስትታነጽ፣ ስትተጋ ማንም ልብ አይልህም። ያንተ ራስን ማነጽ አርቀው ለማያስቡት ቦዘኔነት ነው። ሲያዩህ መሬት አትቆፍርም፣ እንጨት አትልግም፣ ምስማር አትመታም፣ ልብስ አትሰፋም፣ ዳቦ አትጋግርም፣ መርፌ አትወጋም። ለእነርሱ አንተ እየቦዘንክ ነው።

ከትጋትህ መጨረሻ ተሳክቶልህ፣ በኑሮ ከፍ ብለህ ሲያዩህ ግን "እድለኛ ነህ" ይሉሃል። እውነት ነው እድል ማለት ስትተጋ ሳትታይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል ነው።

ስንዴዋ አፈር ውስጥ ገብታ ስትበሰብስ ውጤቱን ለሚያውቀው ለገበሬው እንጂ ለሌላው ብክነት ነው። ሌሎች ውጤቱን የሚያዩት ስንዴዋ ስታፈራ ነው።

ዘሩን የሚያናንቁ በፍሬው ቢደነቁ አትገረም።

አንተ ግን ለሌሎች ታይታ ሳይሆን በገባህ መንገድ አቅጣጫህን መርጠህ ትጋ!

አንድ ቀን ውጤቱን ሲያዩ "እድለኛ ነህ" ይሉሃል።😆
Thought G.Kebede

Abay Media

30 Jul, 13:10


https://youtu.be/L-rqg2ug7dE

Abay Media

08 Feb, 20:19


የካቲት 2013 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች

1፤ ለመጭው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልል እና የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ ባላስረከቡ የክልል መስተዳድሮች በተቀመጠው የጊዜ መርሃ ግብር የዕጩዎች ምዝገባ እንደማያካሂድ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ አስታውቋል። እስካሁን የክልል እና ዞን የምርጫ ቢሮዎችን ባላሳወቁት አማራ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች፣ የዕጩዎች ምዝገባ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና እና የምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት ማከናወን አልቻልኩም- ብሏል ቦርዱ። በተጠቀሱት ክልሎች ሌላ ጊዜ የዕጩዎች ምዝገባ እንዲደረግ፣ እስከ የካቲት 5 ቢሮዎችን እንዲያሳውቁም አሳስቧል።

2፤ በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያሳስባቸው የአውሮፓ ኅብረት ም/ኮሚሽነር እና ሌሎች ሁለት ከፍተኛ ኮሚሽነሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ትግራይ እንዲሁም ሒጻጽ እና ሽመልባ ስደተኛ ጣቢያዎች ለሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽ እንዳልሆኑ ሃላፊዎቹ ገልጠዋል። የኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰባቸው የገለጹት ሃላፊዎቹ፣ ስደተኞች በግዳጅ ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ እና ኤርትራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽመውንና ግጭቱን እየባባሰ ያለውን ጦሯን ከትግራይ እንድታስወጣ አሳስቧል።

3፤ የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል በትግራይ ክልል ለስደተኞች የገነባኋቸው ሕንጻዎች ወድመውብኛል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ አውግዟል። በሒጻጽ እና ሽመልባ የኤርትራዊያን ስደተኛ ጣቢያዎች፣ በቅርብ ሳምንታት አንድ ትምህርት ቤት እና ክሊኒክም እንደወደሙ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ጃን ኢግላንድ ገልጠዋል። በተቋማቱ እና በዕርዳታ አቅርቦቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት መንግሥት እና ለጋሽ ሀገራት እንዲያጣሩ እና ጥፋተኞችን ተጠያቂ እንዲያደርጉም ድርጅቱ ጠይቋል። ድርጅቱ በምንጭነት የተጠቀመው ግን ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገ ዲ.ኤክስ ኦፕን ኔትወርክ የተባለ ድርጅት ያሰራጫቸውን የሳተላይት ምስሎች ነው። በሌላ በኩል የተመድ ዐለም ምግብ ፕሮግራም በመላው ትግራይ ክልል ለረድዔት ሠራተኞች ተደራሽ እንዲሆን እና የዕርዳታ አቅርቦቱም እንዲያድግ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ዴቪድ ቢዝሊ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥም የዕርዳታ ማጓጓዣዎች በወታደሮች እንዲታጀቡ ስምምነቱ ይፈቅዳል። መንግሥትም ወደ ክልሉ ለመግባት ፍቃድ ለሚጠይቁ የረድዔት ሠራተኞች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ተስማምቷል።

4. ሁለት የመንግሥት ባንኮች እና 16 የግል ባንኮች ለግል ተበዳሪዎች የሰጡት ብድር በድምሩ ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ ሪፖርተር አስነብቧል። የብድር መጠኑ እስካለፈው ሰኔ ወር ብቻ ያለውን ብድር የሚያጠቃልል ነው። ከብድሩ 53 በመቶው ለመንግሥት ተቋማት፣ ቀሪው ደሞ ለግል ተበዳሪዎች የተሰጠ እንደሆነ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ባንኮች ከግል ተበዳሪዎች ያልሰበሰቡት ብድር ከ28 በመቶ በላይ ዐመታዊ ጭማሪ አሳይቷል። ከፍተኛ የብድር ድርሻ የያዙት የማዕድን፣ የሃይል እና የውሃ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።

5፤ የሱማሊያ ተቃዋሚ ሃይሎች ለፕሬዚዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ ዕውቅና እንደማይሰጡ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ተቃዋሚዎችን፣ ክልሎችን እና ሲቪል ማኅበራትን ያቀፈ የሽግግር ምክር ቤት እንዲቋቋምም ተቃዋሚ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎቹ ጠይቀዋል። ተቃዋሚ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ፎርማጆን ዕውቅና የነፈጓቸው የሥልጣን ዘመናቸው ዛሬ አብቅቷል በማለት ነው።

6፤ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ ካቢኔያቸውን እንደበተኑ የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሐምዶክ ዛሬ አዲሱን የሽግግር መንግሥቱን ካቢኔ ያዋቅራሉ ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ መንግሥት ከለውጥ አቀንቃኞች ጥምረት እና የሱዳን አብዮታዊ ግንባር ከተሰኘው ሃይል ይውጣጣል። ካቢኔው የፈረሰው የሰላም ስምምነት የፈረሙ አማጺያን ቡድኖችን በመንግሥቱ ውስጥ ለማካተት ጭምር ነው። [ዋዜማ ራዲዮ]

Abay Media

31 Jan, 12:57


ጥር 22፣2013

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 656 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6,099 የላብራቶሪ ምርመራ 656 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ባለፋት 24 ሰዓታት የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 2,091 አድርሶታል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 601 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 122,588 አድርሶታል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 137,021 ደርሷል፡፡

#COVID19Ethiopia #Ethiopia

Abay Media

29 Jan, 11:52


አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን ተቀላቀሉ።

ከአንድ ወር በፊት ፓርቲያቸው በምርጫ ቦርድ የታገደባቸው አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀላቸው ተገልጿል።

ኢዴፓ፣ ኢሀንና ህብር ኢትዮጵያ ነገ በይፋ ሊዋሀዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ (ኢሀን) እና ህብር ኢትዮጵያ በይፋ ተዋህደው በአንድ ፓርቲ ስር ሊሰሩ ነው።

ኢሀንና ኢዴፓ በምርጫ ቦርድ ከምርጫው የተሰረዙ ሲሆን ህብር ኢትዮጵያ ግን በምርጫው ለመወዳደር ፍቃድ በማግኘቱ ተዋህደው በህብር ኢትዮጵያ ስም ሊሰሩ መሆኑን ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ (ኢሀን ) ሊቀ መንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ይሄንኑ ያረጋገጡ ሲሆን ነገ በዚሁ ውህደት ዙርያና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እንሰጣለን ብለውናል።

ህብር ኢትዮጵያ፣ ኢሀንና ኢዴፓ ኢትዮጵያ ህልውናዋ አደጋ ስለተጋረጠበት ፓርቲዎቻችን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል በሚል አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነትን መስርተው በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።

አሁን ይሄ ስብስብ ከነገ ጀምሮ አንድ ፓርቲ ሆኖ እንደሚቀጥል ኢንጅነር ይልቃል ነገረውናል።

የኢዴፓው አቶ ልደቱ አያሌው እና የኢሀኑ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በተነሳው ረብሻ ተጠርጥረው ለወራት ከታሰሩ በኋላ በዋስ ከእስር መፈታታቸው የሚታወስ ነው።

ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም

Abay Media

28 Jan, 13:36


ጥር 20/2013 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያው ትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጡን አሴሴትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በክልሉ ዝርፊያ እና ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም በስደተኛ ጣቢያዎች ጥቃቶችን እንደሚፈጽሙ ሪፖርቶች ደርሰውኛል፤ የኤርትራ ወታደሮችም ኤርትራዊያን ስደተኞችን አስገድደው መልሰዋል- ብሏል መስሪያ ቤቱ፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩም ጠይቋል፡፡

2፤ መከላከያ ሠራዊት የሕወሃት ታጣቂዎችን ከመቀሌ እስከ ቆላ ተንቤን ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ መንግሥታዊው ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡ በቁጥጥር ስር ውለዋል ከተባሉት መካከል 9 ኮሎኔሎች፣ 7 ሌትናል ኮሎኔሎች እና 2 የፖሊስ ኮማንደሮች እንደሚገኙበት ተገልጧል፡፡ መኮንኖቹ በትክክል የት ቦታ እና መቼ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ዘገባው አላብራራም፡፡

3፤ ፍርድ ቤት የእነ ጀዋር ሞሐመድን የዕምነት ክህደት ቃል የሚቀበልበትን ቀን ለጥር 27 እንዳስተላለፈ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የተከሳሾቹን የእመነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተሰይሞ ነበር፡፡ ሌላ ቀጠሮ የተሰጠው ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻችን በችሎቱ እንዳይገኙ ተደርጓል በማለት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆናቸ ነው፡፡ ዐቃቤ ሕግ ግን ቀጠሮው እንደገና መራዘሙን ተቃውሟል፡፡

4፤ ከሳምንት በፊት በመቀሌ ከተማ የተገደለው የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እንዴት እንደተገደለ እንዲጣራ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ በመስሪያ ቤታቸው ድረ ገጽ በተሰራጨ ማሳሰቢያቸው ጠይቀዋል፡፡ የጋዜጠኛውን ግድያ ያወገዙት ዳይሬክተሩ፣ መንግሥት ገዳዮቹን ለሕግ እንዲያቀርብ አሳስበዋል፡፡ ጋዜጠኞች ሥራቸውን እንዳይሰሩ ሃይል የሚጠቀሙ ወገኖች ያለቅጣት መቅረት እና ድርጊታቸው መበረታታት የለበትም- ብለዋል ሃላፊው፡፡

5፤ ወደ ትግራይ መቀሌ ከተማ ላንድ ቀን ተቋርጦ የኘበረው የስልክ አገልግሎት እንደገና እንደተጀመ ኢትዮ ቴሌኮም ለሸገር ተናግሯል፡፡ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው በአዲስ አበባ እና መቀሌ መካከል የተዘረጋው ፋይበር ብልሽት ሳቢያ ነው፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ያስጀመረው ለአጣዳፊ ጊዜ በሚጠቀምበት መሳሪያ ሲሆን፣ በተጓዳኝ የፋይበር ጥገናውን እያካሄደ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

6፤ በኢትዮጵያ ያገለገሉ 4 የቀድሞ የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደሮች ሰሞኑን ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ እንደደረሰው ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ በትግራይ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የኤርትራ ወታደሮች ጣልቃ ገብተዋል መባሉ አሳስቦናል- ብለዋል አምባሳደሮቹ፡፡ መንግሥት ተመድ እና የረድዔት ድርጅቶች ወደ ተረጅዎች መድረስ እንዲችሉ ይፈቅዳል፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም በገለልተኛ አካል ያጣራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

7፤ የኬንያ እና ሱማሊያን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ያጣራው አጣሪ ቡድን ኬንያን ከተጠያቂነት ነጻ እንዳደረገ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጹን የሀገሪቱ ሲትዝን ቲቪ ዘግቧል፡፡ ጅቡቲ ያቋቋመችው አጣሪ ቡድን ባወጣው ሪፖርት ሱማሊያ በኬንያ ላይ የምታሰማው ክስ መሠረተ ቢስ መሆኑን አረጋግጧል ተብሏል፡፡ ሱማሊያ ባለፈው ታኅሳስ በተናጥል ከኬንያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧ ስህተት እንደነበር ቡድኑ ጠቅሷል፡፡ ኬንያ ሕገወጥ ታጣቂዎችን እያስታጠቀች ጥቃት ትፈጽምብኛለች የምትለው ሱማሊያ ግን፣ የቡድኑን ሪፖርት ባንድ ወገን መረጃ ላይ የተንጠለጠለ በማለት አጣጥለዋለች፡፡

8. በኢጋድ ማዕቀፍ ስር የጅቡቲ አጣሪ ቡድን ስለ ሱማሊያ እና ኬንያ እሰጣገባ ዛሬ ያወጣውን ሪፖርት በመቃወም ሱማሊያ ከኢጋድ ልትወጣ እንደምትችል አስጠንቅቃለች። ኢጋድ ገለልተኛ ሊሆን አልቻለም በማለት ወቅሳለች ሱማሊያ። ወደ ኬንያ እና ሱማሊያ ተጉዞ መረጃዎችን ያሰባሰበው ቡድኑ በሪፖርቱ፣ ኬንያ በድንበር አካባቢ በምታደርገው ትንኮሳ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብታለች በማለት ሱማሊያ የምታሰማው ክስ ተጨባጭ እንዳልሆነ አስታውቋል። ኢጋድ ይቅርታ ጠይቆ ሪፖርቱን ካላነሳ፣ ከኢጋድ አባልነቴ እለቃለሁ ብላለች ሱማሊያ።

8፤ ባለ ጸጋ ሀገራት ከሚያስፈልጋቸው በላይ የኮሮና ወረርሽኝ ክትባትን ከማጠራቀም እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎዛ መጠየቃቸውን ዐለማቀፍ ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡ ድሃ ሀገራት ለሕዝባቸው በቂ ክትባት ማግኘት አለመቻላቸው አደገኛ መሆኑን ራማፎዛ አውስተዋል፡፡