💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

@zmare_dawit


#እነሆ_ድንቅ መዝሙሮች፣ ወረቦች፣ አስተማሪ ፅሁፎች እና ሌሎችንም የሚያገኙበት ቻናል ጌታችን በዓለት መሠረት የመሠረታት፤ አባቶቻችን ሐዋርያት ያስተማሩላት፣ነቅዕ የሌለባት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት ያደረጉ ትምህርቶች የሚያገኙበት channel.
ተቀላቀሉን!
👇 👇
https://t.me/joinchat/vRKyRbcLVO1iYjVk
👆👆
Creater @Te_best ←

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

19 Oct, 08:44


ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት የተገነባው  ዘመናዊ ስቱዲዮ   በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ እውቅና የተሰጠው "ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር "ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት'  ቡራኬ ተመረቀ።
በመዝግጅቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ከመላው ዓለም ለ43ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የተሰባሰቡ ልዑካን ተገኝተዋል ።
ስቱዲዮው አንድ ዘመናዊ ስቱዲዮ ማሟላት የሚገባው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ግዙፍ 8k ስክሪን የተገጠመለት ሲሆን በተጨማሪም በስቱዲዮው የተለያዩ ቀረጻዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ገጽታዎች እና የግንኙነት ካሜራ ተሟልቶለታል። የስቱዲዮ መቆጣጠሪያ ክፍል ያለው ሲሆን ግንባታው ባለፉት ከ2 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ዘመናዊ መሣሪያዎች ከውጪ ሀገራት ተገዝተው ተገጥመውለታል።
በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መስራች መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ሙሉ ወጪ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ ድርጅቱ በሚያሠራጫቸው ይዘቶች የፕሮዳክሽን ጥራት ለመጨመር ከፍተኛ አስተውጽኦ እንደሚያመጣ ተገልጿል።

#ድምፀ_ተዋህዶ

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

15 Oct, 06:01


እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

14 Oct, 08:50


“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

09 Oct, 12:49


"በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ፤ እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ፡ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው'' መዝ. 122:1-3

#ድምፀ_ተዋህዶ

▫️https://t.me/dmtse_tewaedo

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

05 Oct, 15:21


#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ

✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት   አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡ 
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ  የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
  ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
      እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
( የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት #ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን #ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም
የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ  ተጠቀሙ፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

    #ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

04 Oct, 18:27


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

26 Sep, 05:58


መስቀል ሃይላችን ነው ፣መስቀል መፅናኛችን ነው ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው ።
አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን ድነንማል።
የተወደዳቹ የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለታላቁ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo

💜 ዝማሬ ዳዊት 💜

25 Sep, 12:05


# ልዩ የመሰቀል ደመራ ፕሮግራም !!
     ✝️✝️✝️
#የሶዶ_ወረዳ_ቤተክህነት_ልዩ_የደመራ_ዝግጅት
በምሥራቅ ጉራጌ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት የሶዶ ወረዳ ቤተክህነት አስተባባሪነት በተዘጋጀው የደመራ በዓል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ልዩ ፕሮግራም በቡኢ ከተማ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
✝️✝️✝️
እርስዎም የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እናሳስባለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
✝️✝️✝️
የምስራቅ ጉራጌና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ሰብከት !
መስከረም 11/01/2017 ዓ.ም
             ቡኢ
          ኢትዮጵያ
         ✝️✝️✝️

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo

12,517

subscribers

300

photos

5

videos