ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

@ortodokstewahido


ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
ይሁዳ 1÷3
ስለ ሃይማኖታችን ማንኛውንም ጥያቄ እናስተናግዳለን
ተጫኑት
@Thomas_Mekonnen
ወጣቶች ሆይ እናንተ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ናችሁ። 🙏
ወጣትነታችን ለሃይማኖታችን

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

22 Oct, 12:14


“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ …

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
    https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

13 Oct, 05:36


ወዳጄ ሆይ! ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ጻድቅም ከኾንህ ከጽድቅ (ጎዳና) እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና፡፡

ኃጢአተኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡

እስኪ ንገረኝ! “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ ምን ውጣ ውረድ፣ ምን ዓይነት የሕይወት መርሕ፣ ምንስ መከራ አለው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት (ኃጢአት ሠርተህ ሳለ) በደለኛ አይደለሁም የምትል ከኾነ ዲያብሎስም አንተን አይወቅስህም፡፡ (በድያለሁ ብለህ ንስሐ የምትገባ ከኾነ ግን) ይህን (ዲያብሎስ ሊወቅስህ እንደሚችል) አስቀድመህ አስብ፡፡ …

ስለዚህ ክብርህን እንዳይወስድብህ ለምን አትከለክለውም? ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?

ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” ብለህ ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም፡- “ንግር አንተ ኃጣውኢከ ቅድመ ከመ ትጽደቅ - ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡

ይህን ለማድረግ ውጣ ውረድ የለውም፤ ዙሪያ ጥምጥም የቃላት ድርደራም አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፤ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አንዲት ቃል ተናገር፤ በደልህን በአንቃዕድዎ አስባት፤ “በድያለሁ” ብለህም ተናዘዛት፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
    https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

09 Oct, 06:07


✞✞✞ እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✞✞✞

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞

✞✞✞ ቅድስት አርሴማ ድንግል ✞✞✞

✞✞✞ እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
¤ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-
1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት::
2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት::
3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::

ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::

ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ 127 ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::

በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::

በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::

ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::

አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::

ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው::

የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::

ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ሃገራችን እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ (ወሎ / ኩላማሶ / ስባ / ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::

ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::"

በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::

✞✞✞ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ✞✞✞

*የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ
*ምድራዊው መልአክ
*የጌታ ወዳጅ
*የድንግል ማርያም የአደራ ልጅ
*የንጽሕና አባት
*ቁጹረ ገጽ
*የፍቅር ሐዋርያ
*የምሥጢር አዳራሽ
*የሐዋርያት ሞገሳቸው
*ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዛሬ ይከብራል::

ምክንያቱም "ቀዳሚሁ ቃል" (ዮሐ. 1:1) ብሎ እንደ ንስር መጥቆ ወንጌሉን በዚህች ቀን ጽፏልና::

✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ለኛ ለባሮቹ የቅድስቷን ጽናት: የወንጌላዊውንም ፍቅር ያድለን:: በረከታቸውን ከማይጐድል እጁ አብዝቶ ይስጠን::

✞✞✞ መስከረም 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት አርሴማ ድንግል (ሰማዕት)
2.ቅድስት አጋታ (እመ ምኔት)
3."119" ሰማዕታት (የቅድስት አርሴማ ማሕበር)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ነባቤ መለኮት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮዽያዊት (በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል ታወጣለች)

✞✞✞ ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
4.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
5.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

✞✞✞ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ:: ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ቃልም እግዚአብሔር ነበረ :: ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ሁሉ በእርሱ ሆነ:: ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም:: በእርሱ ሕይወት ነበረች:: ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች:: ብርሃንም በጨለማ ይበራል:: ጨለማም አላሸነፈውም::" ✞✞✞
(ዮሐ. ፩፥፩)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

08 Oct, 10:37


ሰላም ውድ ቤተሰቦች ይህ ከታች የምትመለከቱት ሊንክ ጠቃሚ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ያቀርባል! subscribe በማድረግ እንዲሁም ተማሪ ልጅ,እህት,ወንድም እንዲሁም ጓደኛ ካለዎት ሼር በማድረግ ይተባበሩን
👉https://youtube.com/@kalgetnet?si=TFq1PUTY95w3TXYh

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

07 Oct, 10:03


እጅግ ክፉው ነገር በኃጢአት መውደቅ አይደለም፤ በዚያ ወድቆ መቅረት እንጂ፡፡ እጅግ አሳዛኙ ነገር ከወደቁ በኋላ ድጋሜ አለመነሣት፣ በሐኬት በስንፍና ተይዞ መቀለድ እንዲሁም የምግባር ጉድለትን በተስፋ መቁረጥ ካባን መሸፈን ነው። ባደረገው ኃጢአት ተስፋ የቆረጠ ክርስቲያን እንዲህ የሚለው ፈጣሪውን የረሳ ነው፦"የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን?" /ኤር.8፥4/።

ከመቶ በጎች መካከል የጠፋ አንድ በግ ነበር፡፡ ያ በግ አስቀድሞም የተለየ በግ አልነበረም፤ እንደ ተቀሩት ዘጠና ዘጠኙ በጎች እንጂ፡፡ የኹሉም እረኛቸው አንድ ነው፡፡ ያ በግ ግን ከመንጋው ተለየ፡፡ ወደ ሩቅ ሀገር ተሰደደ፡፡ ወደ ሸለቆው ወረደ፡፡ ሣር እንደ ልብ ከሚያገኝበት፣ ውኃ እንዳሻው ከሚጎነጭበት ርቆ ሔደ፡፡ እረኛው ግን አልተወዉም፡፡ ዘጠና ዘጠኙ ይበቁኛል አላለም፡፡ ፈለገው፤ አገኘውም፡፡ ባገኘው ጊዜ ግን አልገረፈውም፤ አልተቆጣውም፤ በትከሻው ተሸክሞ ከዘጠና ዘጠኙ ጋር ደመረው እንጂ /ሉቃ.15፥4-5/፡፡ አንድ በግ የተባለው እኛው ነን፡፡ ዘጠና ዘጠኝ የተባሉት ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡ እረኛ የተባለውም እግዚአብሔር ነው፡፡ በድለን ልንርቅ እንችላለን፡፡ በድለን ልንሸሽ እንችላለን፡፡ ፈጣሪያችን ግን ይፈልገናል፡፡ ዝም ቢለን ይበልጥ እንርቃለንና፥ አንድም በክፋት ላይ ክፋት እንጨምራለንና ዘጠና ዘጠኙን ትቶ እኛን ፍለጋ ይመጣል፡፡ እኛም ተስፋ ባለ መቁረጥ ንስሐ ገብተን ወደ እርሱ ብንመለስ ይቀበለናል፡፡ ወደ መንጋውም ይቀላቅለናል፡፡ አልቀላቀል ካልን ግን ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በአዳኝ ወይም በአውሬ መበላት ይኾናል፡፡

ቅዱስ አባት ሆይ! ንስሐን ስለ ሠራህልን ክብር፣ ኃይልና ጌትነት ለአንተ ይኹን አሜን!!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

06 Oct, 14:30


​​​​ፆመ ፅጌ / የፅጌ ፆም

የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ።

ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡

በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡

ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡

እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”

የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡

ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡

ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
       https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

01 Oct, 18:31


✤እንኳን ለመስከረም 21፤ብዙኃን_ማርያም
#ብዙኃን_ሊቃውንት_ለተሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_፤
#ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤
#ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ ሆነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤
#ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት  (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_#በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም
#ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
✤✤✤✤
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ  ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ)
መስከረም ፳፩ የምናከብርበት አንደኛው ምክንያት  መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
   #ግሸን_ደብረ_ከርቤ
ደብረ #ንገሥት  ፣ ደብረ #ነጐድጓድ ፣ ደብረ #እግዚአብሔር በሚባሉ ስም ትጠራ ነበር ፡፡
በመጀመርያም የተመሠረትቸው በአፄ ካሌብ  ዘመን ነበር ፡፡ሁለት ጽላቶች ከናግርን (አጼ ካሌብ ድል አድርጎ ከተመለሰ በኃላ ) በአባ ፈቃደ ክርስቶስ አማካኝንት (መነኰስ) አምጥተዋል ፤ ከዛም ሲመጡ  ወደ ጊሸን ተራራ ሊወጡ ሲሉ በዚያ ንብ ሰፎ ማር ሲንጠባጠብ በማየታቸወው በግእዝና አረብኛ ቋንቋ   #አምባ አሰል ብለው ጠሩት ትሩጉሙም የማር አማባ ማት ነው እስካሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል፡፡ የመጡትንም ጽላቶች በማስገባት የመጀመሪያውን ቤ.ክ ሠረተው ደብሩን መስርተዋል፡፡
  በሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሰማዕታት ሃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ከተረፈው የመንግሥት ቅብዓት ተቀብተው ነገሡ፡ ስመ መንግሥታቸውም #ቆስጠንቲኖስ ተባለ፡ በተወለዱም በሃምሣ ዓመት ‹‹ መስቀሌን በመስቀል ላይ አስቀምጥ የሚል ራዕይ አይተው ›› ጠይቀው ሲረዱ አባታቸው የተረከበው መስቀል በመካ መዲናው አሕዛብ ሹም እንዳለ ተረዱ ክተት ሰራዊት ብለው አደሊዋ ድረስ ዘመቱ በዚህ ጊዜ የምስሩ ንጉሥ የአባትህ ገንዘብ እኔጋ  ስላለ እባክህ ከእኔ ጋር አተዋጋ መስቀሉን ፣ ሥዕላቱን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን እስጥካለሁ አላቸው ( ማብራርያ መስከረም 17 የለጠፋነውን ጽሑፍ ተመልከቱ ) ይህንን ተቀብለው ተመልሰው ለ3 ዓመታት መስቀለኛ ቦታ ፈለጋ በኢትዮጵያ ተራሮች ዞሩ  ቅዱስ ዑራኤልም ይራዳቸው ነበር ፡፡ ከሥስት ዓመት ቦኃላም አምባሰል ደርሰው ቦታዋ  በመስቀል አምሳል የተቀረጸች መሆኗን አዩ፡፡ መግቢያው ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር አረፈው በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ተገልፆ ይህች ደብረ ከዛሬ ጀምሮ ደብረ ከርቤ ትባላለች ፡፡ደብረ ነጐድጓድ ትባለ የነበረውም የካህናትና የነገሥታት መኖርያ ስለሆነች ነው ፡፡ሥላሴን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ፡፡ ወደ ውስጥ ስትገባ ሁለት አብያተ ቤ.ክ ታገኛለህ አንዲቱ #በእግዚአብሔር አብ ስም  የተሠራች ናት፡፡ አንዲቱ ደግሞ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸች ናት፡፡
    እመቤታቸንም ተገልጻለት #በኢትዮጵያ በተሰደድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ስምሽ እስከ ዕለተ ምጽአት ሲመሰገን ይኑርባት ብሎ ሰጥቶኛል እና ሄድ  ብላ ቦታዋን #ጠቆመችው፡፡
    በ1446 ዓ.ም መስከረም 21 ወደ ተራረው ገብተው አይተው ተደሰቱ በታዘዙትም መሠረት ቅዱስ መስቀሉን በእግዚአብሔር ስም በተሰራው መቅድስ #አስቀመጠው፡፡
  መስከረም 21 ቀንም መስቀሉ የተቀመጠበት የእግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ፡፡ ጌታችን በዘባነ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መጣ ፡፡ እጅግም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ለቦታዋም ታላቅ ክብርን ሰጣት ደብረ ታቦርም ትሁንልህ አለው ፡፡
፠፠፠ #ብዙኃን_ማርያም፤
፠2ኛ) ደግሞ ጉባኤ ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ  በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡
ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤
#አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤
#ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤
#ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት #በቅርጫት ይዘውት ነበር ( ማብራርያ የጥቅምት 14 የለጠፍነውን እይ ) ፡፡
ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩  ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት  በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡  ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን  አዘጋጅተዋል፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

18 Sep, 11:06


“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡

ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡

ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡

እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
 https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

12 Sep, 04:03


#አዲሱ_ዓመት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

#ወዳጄ_ሆይ! ገንዘብ የለህምን? ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርግ፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ የምታደርግ ከኾነ ገንዘብ ካላቸው በላይ ባለጠጋ ነህ፡፡ “እንዴት?” ትለኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- የእነዚያ (የባለጠጐቹ) ገንዘብ ያልቃል፡፡ ያንተ ግን ብል አይበላውም፡፡ ጊዜ አይለውጠዉም፡፡ አያልቅም፡፡ ወደ ሰማያት፣ ወደ ሰማየ ሰማያት፣ ወደ ምድር፣ ወደ አየራት፣ ወደ እንስሳቱ ዓይነት፣ ብዙ የብዙ ብዙ ወደሚኾኑት ዕፅዋት፣ ወደ ደቂቀ አዳም በጠቅላላው፣ ወደ መላዕክት፣ ወደ መላዕክት አለቆች፣ ወደ ኀይላት ተመልከት፡፡ እነዚህ ኹሉ የአምላክህ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ የእነዚህን አምላክና መጋቢ ባሪያ መኾን ድኻ መኾን አይደለምና ድኻ አይደለህም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

#ተወዳጆች_ሆይ! ቀናትን ቆጥሮ በዓል ማድረግ የክርስቲያን ግብር አይደለም፤ የአሕዛብ ግብር እንጂ፡፡ እንዴት? የክርስቲያኖች ተፈጥሮ በቀንና በወር የተገደበ አይደለምና፡፡ አገራችን ሰማይ ነው፡፡ ግብራችን ሰማያዊ ነው፡፡ ኅብረታችንም ከሰማያውያን መላዕክት ጋር ነው፡፡ በዚያ መዓልት ለሌሊት ስፍራውን አይለቅም፡፡ ሌሊትም በተራው ለመዓልት አይለቅም፡፡ እዚያ ኹሌ መዓልት ነው፡፡ እዚያ ኹል ጊዜ ብርሃን ነው፡፡ ስለዚህ “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ” እንደተባልን ኹል ጊዜ ማሰብ ያለብን ይህንን ነው (ቈላስ.3፡1)፡፡ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችን ከዚህ ምድራዊ አቈጣጠር በላይ ነው፡፡ በንጽህና በቅድስና እየኖርን ዘወትር በዓልን የምናከብር ከኾነም የዚሁ ዓለም ሌሊት ለእኛ ሌሊት አይደለም፤ መዓልት ነው እንጂ፡፡ ዘመናችንን በሙሉ በገቢረ ኀጢአት፣ በስካር፣ በዘፈን የምናሳልፈው ከኾነ ግን መዓልቱ ለእኛ መዓልት አይደለም፤ ሌሊት ነው እንጂ፡፡ ፀሐይዋ ብትወጣም ልቡናችን ገና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖራልና ቀን እንደወጣ አይቈጠርም፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

09 Sep, 12:27


“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እህቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ  ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንሆናለን፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                      •➢ ሼር // SHARE

 https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

06 Sep, 18:09


ጳጉሜን

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡

ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ ጳጉሜን ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባ ትታወቃች ትለያለች፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ በዘመነ ሉቃስ ማብቂያ  ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 15 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል

በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡

የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ዮዲ 8፥2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

   https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

31 Aug, 10:46


በየቀኑ እነዚህን አምስት(5) ጸሎቶች ይጸልዩ

እግዚአብሔርን በጸሎት የምንጠይቅባቸው ልዩልዩ ጉዳዮችና ምክንያቶች ቢኖሩም እንዚህን አምስት የጸሎት ክፍሎች ግን አዝወትሮ መጸለይ ይገባል።

1.  የምስጋና ጸሎት:- ስላለፈው ትናንትና፣ ስላለህበት ዛሬ፣ በተስፋና በእምነት ስለምንጠብቃት ነገ ማመስገን ይገባል። “ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ተሰሎንቄ 5:17

2.  አቅጣጫ/ምሪት ለመቀበል:- ተመሳሳይ ሕይወትን ላለመምራት /ሁልጌዜ ያለንሰሐ ከመመላለስ ለመጠበቅ/፣ በየቀኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ በጎ ምሪት/አቅጣጫ ለመቀበል እርሱ ቅዱሳኑን በራሱ መንገድ እንዲመራቸው እኛንም እንዲመራን መጸለይ አስፈላጊ ነው። “አቤቱ መንገድህን ምራኝ በእውነትህም እሄዳለሁ”። መዝ-86:11

3.  ለጤንነትና ለመለኮታዊ ጥበቃ:-በየቀኑ ጤንነታችን እንዲጠበቅ፤ እንዲሁም ከምታዩትና ከማታዩት  የክፉ ፍላጻ እንድንሰወር መጸለይ አስፈላጊ ነው። “ከቀስትህ ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትል ሰጠሃቸው።” መዝ-60:4

4.  እግዚአብሔር እንዲጠቀምብን:- በየአንዳንዱ የሕይወት አጋጣሚ ውስጥ እግዚአብሔር ቅዱሳንን እንደተጠቀመባቸው እኛንም እንዲጠቀምብን መጸለይ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም በየአንዳንዱ የምድር ጥያቄ የእግዚአብሔር መልስ ያለው በእኛ ውስጥ ነው።

5.   ጥበብ እንዲሰጠን:- መለኮታዊ ጥበብን ለማግኘት ውስጣችን በንሰሐ ክፍት መሆን አለበት። በዚህ ጥበብ ለመሞላትም ዘውትር መጸለይ አለብን። “ከመካከላችሁ ጥበብ የጎደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን በጸሎት ይጠይቅ፤ እግዚአብሔር ለሚጠይቁት ሁሉ ቅር ሳይሰኝ በደስታ የሚሰጥ ቸር አምላክ ስለሆነ።” ያዕቆብ 1:5

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

  https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

30 Aug, 03:12


#ዕጣንና_ጽንሃ_በቤተክርስቲያን

#ዕጣን
ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለአለም ድህነት የሚለምኑበት ነዉ፡፡ በቤተክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት ፡ በነገህ ጊዜ በቅዳሴ ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና ልመናዉን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል ፡፡

ስለ እጣን የመፅሀፍ ቅዱስ ማስረጃ

ዘጸ 30፥1 የዕጣን መሰዊያዉን ስራ ከግራር እንጨት አድርገው።

ዘጸ 30፥35 በቀማሚ ብለሀት እንደተሰራ፥ በጨዉም የተቀመመ ንጹህና ቅዱስ እጣን አድርገው፡፡

ዘጸ 30፥34 እግዚአብሄርም ሙሴን አለዉ፦ ጣፋጭ ሽቱ ዉሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ በዛጎል ዉስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ዉሰድ የሁሉም
መጠን ትክክል ይሁን፡፡

ዘፀ 40፥5 ለዕጣንም የሚሆነዉን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ታኖራለህ፥ በማደሪያዉም ደጃፍ ፊት መጋረጃዉን ትጋርዳለህ፡፡ ዘጸ 40፥27 የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን አጠነበት፡፡

ዘሌ 10፥1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብድዩድ በየራሳቸዉ ጥናዉን ወስደዉ እሳት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት በእግዚአብሔር ፊት እሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ፡፡

ዘሌ 16፥12 በእግዚአብሔር ፊት ካለዉ መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናዉን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ እጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ወደ መጋረጃውም
ዉስጥ ያመጣዋል፡፡

ዘኁ 16፥7 ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች
ሆይ እጅግ አብዝታችኀል ብሎ ተናገራቸው፡፡

ዘዳ 33፥10 ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ህግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሰዊያህም የሚቃጠል መስዕዋት ይሠዋሉ፡፡

መዝ 140፥2 ጸሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ ፥ እጅ መንሳቴም እንደሰርክ መስዕዋት ትሁን፡፡

ማቴ 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ህጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር እዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥኖቻቸዉንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤን አቀረቡለት፡፡

ሉቃ 1፥10 በዕጣንም ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በዉጭ ቆመውዉ ይጸልዩ ነበር፡፡

ራእ 5፥8 መጽሀፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንሰሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳዳቸም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ፡፡

ራእ 8፥3 ሌላም መለአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለዉ በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ
እጣን ተሰጠዉ

#ጽንሃ

ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ ወይም ማጠኛ ነው። ሦስት ሰንሰለቶች አሉት። ሰንሰለቶቹ ሶስት መሆናቸው የሚስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው። በሰንሰለቶቹ ላይ ቢያንስ አስራ ሁለት (12) ቢበዛም ሃያ አራት (24) ሻኩራዎች ይኖሩታል።
‘’ሻኩራ’’ ማለት ሶስቱ ሰንሰለቶች ላይ ያሉት ክብ ነገሮች ናቸው። የሻኩራዎቹ ቁጥር አስራ ሁለት (12) መሆኑ የሐዋሪያት ምሳሌ ነው። ሃያ አራት (24) መሆኑ ደግሞ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው ። ከስሩ እጣኑ የሚቀመጥበት ሙዳይ የመሰለ ክፍል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሲሆን: መለኮት ከሥጋዋ ሥጋ ነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ያመለክታል።  ፍሙ የጌታችን የመለኮትነቱ ምሳሌ ሲሆን እጣኑ እንደሚቃጠልና መዓዛው ሁሉን እንደሚያውድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ብዙዎች ኃጢያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ አቅርቦ ዓለሙን ሁሉ ማዳኑን ያሳያል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

  https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

28 Aug, 09:16


ወንድሞቼ "እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡

ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡ እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

28 Aug, 06:18


😐😐😐ዝምታ😐😐😐

አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከቃላት ይልቅ ውጤታማ፣ ይበልጥ ተገቢና እጅግ ጠቃሚም ነው። ወይም ደግሞ ቢያንስ - ቢያንስ ተናግሮ ከሚመጣ ጉዳት ይልቅ ሳይናገሩ የሚመጣ ጉዳት ይሻላል። በዝምታ ውስጥ ጥበብና ጥንካሬ ከመኖራቸው በተጨማሪ ክብርና ሞገስም አሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ እኛ ዝም እንላለን፣እኛ ልንናገር ከምንወደው ከማንኛውም ነገር የበለጠ የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ኃያል ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው! «እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤እናንተም ዝም ትላላችሁ. . » ዘጸ 14፥14።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በዝምታ ቆይቷል። በዚያን ጊዜ እርሱ  አፉን አልከፈተም ራሱንም አልተከላከለም። ጌታ ዝምታን በመረጠ ጊዜ ጲላጦስ "ይህን ጻድቅ ሰው የምወነጅልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አላገኘሁም" በማለት ተናግሮ ነበር፡፡

ዝምታ ትርፍ አስገኚ ይሁን እንጂ የተወሰነ መመሪያ አይደለም፡፡ ወርቃማው መመሪያ፡- ሰው ሊናገር የሚገባው በትክክለኛው ጊዜ መሆኑና ዝም ማለት የሚገባውም ዝም ማለት በሚገባው ትክክለኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

ሰው ዝም ሲል ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲነጋገር ስለሚፈቅድ በእርሱ ፈንታ ጌታው እንዲናገር ይጠይቃል ማለት ነው፡፡

(አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ - የሕይወት ልምድ ገጽ 14 - በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

25 Aug, 06:38


"እኔ ነኝ" ዩሐ 9፥9

ጌታችን ከቤተመቅደስ አስተምሮ ሲወጣ በመንገድ ሲያልፍ እውር ሆነ የተወለደውን አየ። ይህን ሰው ምራቁን እንትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ዐይን ሠርቶ ሂዲና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው ያም እውር ሒዶ ታጠበና እያየ ተመለሰ። በመንገድ በሚመጣበት ወቅት ቀድሞ ያውቁት የነበሩት ሠዎች 'ይህ በመንገድ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን? ' ብለው መጠየቅ ጀመሩ ገሚሶቹም እርሱ ይሆን አለ? ገሚሶቹ 'አይደለም እርሱን ይመስላል እንጂ'  አሉ፤ እርሱ ግን "እኔ ነኝ" አላቸው።
    ልክ እንደዚህ እውር ዛሬም በጨለማ የነበርኩ ሆኜ ሣለሁ ብርሃንህን አይ ዘንድ ውሣጣዊ ዐይኔን ብሩህ አርገህ ከጨለማ ያወጣኸኝ። ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደንቅ ብርሃን በፍቅርህና በምህረት የጠራኸኝ። ሥራዬ እጅግ የከፋ በበደሌ በሠው ሁሉ የታወቅኩ በመጨለማ መሆኔ ለሠው ሁሉ የተገለጠ እኔን በፍቅርህ  የሣብከኝ "እኔ ነኝ" መዓዛዬ በኀጢኣት የከረፋ ሆኜ ሣለሁ በነውሬ ብዛት መሽተቴን ሣትጠየፍ ወደእኔ መጥተህ ምዑዝ  የሆነ መዐዛህ የሠጠኸኝ በኃጢያት ባህር በጥልቁ ሠምጬ ሣለሁ የንስሐን ገመድ የምህረትህን እጅ ልከህ ከኀጢያት ያወጣኸኝ እኔ ነኝ።
      ሠዎች በቤትህ ለልጅነት መሾሜን በፍቅር መጠራቴን አይተው ይኸህ በጨለማ ህይወት ይኖር የነበረው አይደለምን ይላሉ። አዎን "እኔ ነኝ" የማይወጡትበት የኃጢያት ረግረግ የተዋጣኩ የማይነጋ በሚመስለው ጨለማ ውስጥ የተቀመጥኩ ብሆንም እርሱ ግን ሳይንቀኝ ወደ እኔ ቀረበ ፍቅሩና ቸርነቱን አበዛልኝ ከረግረጉ ጎትቶ ያወጣኝ ጨለማውን ገላልጦ ብርሃኑን ያበራልኝ "እኔ ነኝ"። የምህረቱና የቸርነቱ መጠን ማሳያ እኔ ነኝ። ሊቁ "ብዙ ኃጢያት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች" ብሎ እንደመሠከረ ከሁሉ የበደልኩ ሆኜ ሣለ ከሁሉ ይልቅ የምህረትህን የችሮታህን ጸጋ ያበዛልኝ እኔ ነኝ።
        አሁንም በፍቅርህና በምህረትህ ጠርተኸኝ ከጨለማው አላቀኸኝ ብርሃንህን አሳይተኸኝ ዐይኔን አብርተህልኝ ወደ ጨለማው የምናፍቅ ከኀጢኣት ጽልመት አርቀህ ወደ ጸአዳነት መልሰኸኝ ማረፊያ አጥቼ ስዋልል የነበርኩትን በቤትህ አሳርፈኸኝ ተርቤ የነበርኩትን ሥጋህናን ደምህን መገበኸኝ ሁሉን ሰጥተኸኝ ሣለ አሁንም ከብርሃን ይልቅ ጨለማውን የምናፍቅ ከጽድቅ ብርሃን ይልቅ ጽልመትን የምመኝ ከዘላለም ማረፊያዬ ይልቅ ስደተኝነትን የምከጅል እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ የምል ልጅህ እኔ ነኝ።
         ዛሬም ምህረትህ የሚያስፈልገኝ ጥሪህ የሚናፍቀኝ በቤትህ በቅጥርህ ሆኜ ባስቀመጥከኝ ያልተገኘው የጠፋው ባሪያህ  እኔ ነኝ። በቅዱሱህ ስፍራህ ያለውኝ ቅድስናን ግን ገንዘብ ማድረግ ያቃተኝ በብርሃን ሆኜ መንገዴ የጠፋብኝ። ብዙ የተቀበልኩ ብዙ የሚጠበቅብኝ ሆኜ ሣለው ምንም የሌለኝ  ከጽድቅ የተራቆትኩትኩኝ ባዶ እኔ ነኝ። ልክ እንደ ድሪሙ በቤትህ ሆኜ ዘወትር ከቅጥርህ ሣልጠፋ ነገር ግን ቆሻሻ በሆነ ህይወት በኀጢኣት ውስጥ የጠፋው በብርሃንህ ሥፍራ ብገኝም ኀጢኣቴና በደሌ አይኔን አዉሮኝ ጽድቅህንና ብርሃንህን ማየት የተሣነኝ ልጅህ እኔ ነኝ። አሁንም ምራቅህን ጥቅ ብለህ አንተን ማየት የሚችሉ ዓይንን ፍጠርልኝ። በፊቴ ላይ ቅዱስ ምራቅህን ጥቅ በልብኝ በፍቃዴ ያጠፋውትን ዓይኔንም አብራልኝ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

24 Aug, 14:46


ሴቶች በክርስቶስ መዐዛ ምዑዛን ይሁኑ
አንጂ በቆዳ ቅባትና በሽቱ አይደለም ::

ቀለሚንጦስ ዘእስክንድርያ

ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ
እጅግይበልጣል:የባሏም ልብ ይታመንባታል። ውበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ምሳ 31:10

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

23 Aug, 17:55


🎚 መንፈሳዊ ᴡᴀᴠᴇ Ғᴏʟᴅᴇʀ መግባት የምትፈልጉ ቻናላችሁ ከ 5ᴋ በላይ የሆናችሁ


አናግሩን ➛
@oparina2

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

23 Aug, 10:10


ድንግል ሆይ !

❝አንቺን የወለደ ማህጸን እንዴት ያለ ብሩክ ነው❞ አንቺን የታቀፉ ክንዶችስ እንዴት ያሉ ድንቅ ናቸው ! አስራ ሁለት ዓመት ወደ ቤተመቅደስ የተመላለሱ እግሮችሽስ እንዴት የከበሩ ናቸው ! የቅዱሱን መልአክ ብሥራት የሰሙ ጆሮዎችሸስ እንዴት ያሉ ንቁ ናቸው ! ❝የቃልን ሰው መሆን ያመነው ልብሽ እንዴት ያለ ንጹሕ ነወ ! ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ጌታን የተሸከመው ማሕፀንሽ እንዴት ያለ ግሩም ነው ! ይህን ታላቅ አምላክ የታቀፉ ክንዶችሽስ እንዴት ያሉ ጽኑ ናቸው ! ጌታዬን ያጠቡት ጡቶሽን እንዴት የለመለሙ ናቸው ! ድንግል ሆይ ክብርሽ ከፍ ያለ ነውና አከብርሻለሁ❞ ሰላሳ ሶስት ዓመት ከሶሶት ወር ከጌታ ጋር ያኖረሽን እምነት እኔ ልጅሽ ለአንድ ሰዓት እንኳ የለኝምና እጅግ ጎስቋላ ነኝ ። አስራ ሁለት ዓመት ከወንጌላዊው ዮሐንስ ቤት ያኖረሽን ልበ ሰፊነት እኔ ደካማው ልጅሽ ለአንድ ሰዓት እንኳ ከምወደው ጋር ለመሆን አልታደልኩምና እጅግ ደካማ ነኝ ! ቅድስት ሆይ የምልጃሽ በረከት የእግዚአብሔርን እገዛ ይላክልኝ ። ፍልሰትሽ መጪውን የምዕመናንን ትንሳኤ ጎልቶ ያሳያል ።  ዕርገትሽ መጪውን የምዕመናን ዕርገት በግልጥ ያስተምራል ። ከሚታስበው በላይ  ቅድስት ፣ ከሚነገረው በላይ ትሁት ፣ ከምሰማው በላይ ቡሩክት ፣ ከጻፉልሽም በላይ ንጽህት ፣ ከተረኩሽም በላይ ልዕልት ነሽና ልቤ ታመሰግንሻለች !


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido
 

ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

23 Aug, 10:10


እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳቹ።

የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው። እነዚህ አመታት ሲተነተኑ ሦስት አመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ አስራ ሁለት አመት በቤተ መቅደስ፣ ሰላሳ ሶስት አመት ከሶስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አስራ አምት አመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው።

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ49 ዓ.ም ነው። ባረፈችም ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ስጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ፣ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፣ ተመልሶም ይህንን አለም ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል። አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ።

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ስጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ስጋዋን ያለበትን የአልጋ ሽንኮር ሲይዝ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፣ ከዚህ የጥፋቱ ስራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች።

ከዚህም በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችን የተቀደሰ ስጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ስር አስቀመጠው። ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው። እነሱም የእመቤታችንን ስጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሳ  ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ።

ከሁለት ሱባኤ ቆይታ በኋላ ማለትም በአስራ አራተኛው ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ስጋ ሰጣቸው። ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌታ ሴማኒ ቀበሯት። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት "አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት" ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት "ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ ወደ መንግስተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ" ብለው ያመሰጥሩታል። /መዝ.131÷8።

የእመቤታችን ቅድስት ስጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን(የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ። ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል።

ለበረከት የሰጠችውን ሰበን ያካፍላቸዋል፣ ሐዋርያት "ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል" ብለው በዓመቱ ማለትም በ50 ዓ/ም ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ። ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ(ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው።

በትህትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1 እስከ 16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ስርዓት ሰራችልን።

በነቢያት እና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋህዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም ሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፣ ሆነናልም። እግዚአብሔር አምላክ ሀገራችንን ሰላም አድርጎ ከቁጥር ሳያጎል በሰላም በጤና ጠብቆ ለአመቱ ያድርሰን🙏

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን። አሜን🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/Ortodokstewahido
https://t.me/Ortodokstewahido

25,783

subscribers

285

photos

7

videos