ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

@wku_gg_media


ይህ በወልቂጤ ማዕከል ግቢ ጉባኤ ማሰተባበሪያ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግ.ጉ አባላት መረጃ መለዋወጫ 'የቴሌግራም' ገፅ ነው።


👇👇👇ተከታዮቹን ገጾች ይቀላቀሉ 👇👇👇

Telegram፦ https://t.me/wku_gg_media

YouTube፦ https://www.youtube.com/@MKWolkiteGibiGubae

ለሃሳብና አስትያይቶ @wku_gg_media_bot

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

22 Oct, 02:55



ሚካኤል ሆይ መብረቅን ለተጐናጸፈ መልአካዊ ረቂቅ ርእስህ ሰላም እላለሁ ተፈጥሮአቸው ከእሳት የሆነ የሰማያውያን የመላእክት ሠራዊት አለቃቸው የምትሆን ሚካኤል ሆይ በኃጢአት ተሰነካክየ ወድቄ አንዳልፍገመገም አንተን ድጋፍ አድርጌአለሁና ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ
ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ።

« መልክአ ሚካኤል »


👉ሐሳብዎን በ @wkugg_bot ያጋሩን!


ወ | ዩ | ግ | ጉ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

21 Oct, 19:07


የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነገ ማታ 11:30 ጀምሮ የቅዱስ ሚካኤል ጽዋ መርሐ ግብር ስላለ ሁላችሁ ተቀሳቅሳችሁ በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ ሁኑ።🙏

አምሽቶ ወደ ግቢ መግባት ስለማይቻል በሰዓቱ እንገኝ!!

ቦታ➲ቅ/ሚ/ቤ/ክርስቲያን ትልቁ አዳራሽ
👉ሐሳብዎን በ @wkugg_bot ያጋሩን!



ወ | ዩ | ግ | ጉ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

20 Oct, 07:05


እንደምን አደረችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የኮርስ መጽሐፈት ለምትፈልጉ ሁሉ እንሆ ትላለች ግቢ ጉባኤ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 20:06


ነገ ቅዳሜ ማለትም በ 9/02/17 በነዳያን ጥየቃ ላይ የመወያያ ሐሳቦች

1. እመቤታችን በሰማዕትነት አላረፈችም ታዲያ እንዴት ነው የሰማዕታት እናት የምትባለው?  ይህ እንዴት ይታያል ?


2. ሄሮድስ  በእስራኤል ያሉ ሕጻናትን  ሁሉ እንደገደለ ይታወቃል። በዛ ጊዜ የተረፈው ጌታ ብቻ ነበር ወይስ ሌሎችም ሕጻናት ነበሩ? እነማን ነበሩ ? እንዴት ዳኑ (ተረፉ)



3,  የእመቤታችን ስደት ሲታሰብ አምላክን አቅፋ እንደሆነ ይታወቃል እና ይህ ስደት ከሌሎች ስደተኞች በምን ይለያል  ? ምንስ እንማርበታለን  ?

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 11:27


አንቲ ተዐብዪ እምብዙኃት አንስት"

ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ። አንዲቱማ ከአንዲቱ ብትበልጥ ምን ይደንቃል!!

"እለ ነሥአ ጸጋ ወክብረ"
አንቺ ግን ክብር የክብር ክብር ከአላቸው ሴቶች ይልቅ እጅግ ትበልጫለሽ። ጸጋ፣ክብር፣ልዕልና፣ቅድስና ከአላቸው ሰዎች ሁሉ ትበልጫለሽ። ለዚህም ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ትባያለሽ። ምክንያቱም፦ ንጉሥ በከተማ ዙፋን አድርጎ እንዲኖር ጌታም ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አድርጎ ኖሯልና። "ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር" "የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የሚደረገው ነገር ድንቅ ነው" ብሎ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ እንደተናገረው።

"ፈለግ ዘይውኅዝ ያስተፌሥሕ ሀገረ እግዚአብሔር" "ደስ የሚያሰኝ ወንዝ የሚፈስብሽ ሀገረ እግዚአብሔር አንቺ ነሽ"።
አባቶቻችን ስለእመቤታችን ባመሠገኑበት አንቀጽ በርካታ የሆኑ ድርሰቶችን ደርሰዋል። ለዚህም ምስክር ሊሆነን ቅዱስ ኤፍሬም "አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ዘጋከ"
አቤቱ "የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ"
እስከ ማለት ደርሷል።
https://t.me/wku_gg_media

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 03:01


👉ኑ ነደያንን እንጠይቅ!👈


ውድ የግቢ ጉባኤያችን አባላት እንደምን ሰነበታችሁ?
ዛሬ ጠዋት የቁርስ ዳቦአችሁን ካፌ በር ላይ ለሚጠብቋችሁ ወንድምና እህቶች በማቀበል ነገ ጠዋት 2፡30 ከቁርስ በኋላ ነደያንን በጋራ እንጠይቅ ይላል ግቢ ጉባኤያችን!



ሀሳብ እና አስተያየቶን
➟➟➟➟@wkugg_bot
ያስቀምጡልን


✝️ ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

17 Oct, 19:09


አንቲ ውእቱ ዕፅ ዘርእየ ሙሴ በነደ እሳት ወኢትውዒ"
በነደ እሳት ተከባ፣ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ከነደ እሳት ጋራ ተዋሕዳ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 15:56


👉ኑ ነደያንን እንጠይቅ!👈
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞
የፊታችን ቅዳሜ(09/02/2017) በሙያና በጎ አድራጎት ክፍል አስተባባሪነት ልዩ የነደያን ጥየቃ መርሐግብር ተዘጋጅቶልናል።በመሆኑም ይህ ታላቅ በረከት እንዳያመልጠኝ የምትሉ አርብ ጠዋት ዳቦአችሁን ካፌ በር ላይ ለሚጠብቋችሁ ወንድምና እህቶች በማቀበል በዕለተ ቅዳሜ ሁላችንም ተሰባስበን ነደያንን በጋራ እንጠይቅ🙏
🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞🍞

የነደያን በረከት እንዳያመልጣችሁ!

◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇
"እውነት እላችዃለኹ፥ከዅሉ ከሚያንሱ ከነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችኹት ለእኔ አደረጋችኹት ይላቸዋል።" ማቴ ፳፭÷፵
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

#ሙያና_በጎ_አድራጎት_ክፍል


ሀሳብ እና አስተያየቶን
➟➟➟➟@wkugg_bot
ያስቀምጡልን

✝️ወ▮ዩ▮ግቢ ጉባኤ✝️

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

13 Oct, 12:46


መልዕክት
📣📣📣


የበገና ትምህርት መማር የምትፈልጉ ዛሬ ከ11፡00 - 12፡00 ሰዓት በቤተ ዳዊት ምዝገባ ይካሄዳል ስለሆነም የመመዝገቢያ 50 ብር እና የወርሃዊ ክፍያ 250 ብር በመያዝ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

👉ማሳሰቢያ
✍️Aparent የምትወጡ መመዝገብ አይቻልም።

✍️ያለን ቦታ ትንሽ በመሆኑ ቀድመው የመጡ 75 ተማሪዎችን ብቻ የምናስተናግድ ይሆናል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

12 Oct, 06:38


የሳምንቱ መልዕክት
📣📣📣📣

1.ነገ ማለትም በቀን 03/02/2017 የዚህ ዓመት የመጀመሪያው የክፍላት ስብሰባ ስላለ ሁላችሁም በተለመደው የመሰብሰቢያ ቦታ 9:00 ላይ እንድትገኙ ይሁን።

2. እንደሚታወቀው በመዝሙርና ስነጥበባት ክፍል ውስጥ በስነጥበባት ንዑስ ክፍል ውስጥ አንዱ የሆነው የስነ ስዕል ዘርፍ በቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ስልጠና መስጠት ይጀምራል ስለሆነም ፍላጎቱ እና ችሎታው ያላችሁ ልጆች የእድሉ ተጠቋሚ እንድትሆን እናሳስባለን።
👉ቦታ እና ሰዓት ለወደፊት የምንገልፅ ይሆናል።

3. የተለያዩ መገልገያ እቃዎችን (ሳፋ፣ባልዲ፣መጥረጊያ፣ጄርካን....) መግዛት የምትፈልጉ ግቢ ጉባኤያችን ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደቆየው፤ ባለፈው ዓመት ተማሪዎች ሲገለገሉበት የነበረውን ዕቃዎች አሰባስቦ በታላቅ ቅናሽ እየሸጠ ይገኛል። በመሆኑም  ከታች በተጠቀሰው ቦታ ተገኝታችሁ በመግዛት ይህንን መልካም አጋጣሚ እንድትጠቀሙ ስንል እናሳስባለን።

ቦታ፦ቤተማርያም

ሰዓት፦ ዘወትር ጠዋትና ማታ
📱0930718739


4. የበገና ትምህርት መማር የምትፈልጉ
ነገ ማለትም በቀን 03/02/2017 ከ 11፡00 - 12፡00 ሰዓት በቤተ ዳዊት ምዝገባ ይካሄዳል ስለሆነም የመመዝገቢያ 50 ብር እና የወርሃዊ ክፍያ 250 ብር በመያዝ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

👉ማሳሰቢያ
✍️Aparent የምትወጡ መመዝገብ አይቻልም።

✍️ያለን ቦታ ትንሽ በመሆኑ ቀድመው የመጡ 75 ተማሪዎችን ብቻ የምናስተናግድ ይሆናል።


5. በመንፈስ የምትታመሙ እኅቶች(ወንድሞች) ከዚህ በታች ባለው ስልክ በመደወል በማንኛውም ሰዓት አስፈላጊውን ትብብር ማግኘት ትችላላችሁ።

📱0954705334_ኤርምያስ
📱0988820408_ለአለም

6. የአብነት_ትምህርት መማር የምትፈልጉ ወንድሞችና እኅቶች ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት(11:30_1:30) እና ማታ (11:30_1:30) ስለሚኖር ቤተ_ማርያም በመገኘት መማር ትችላላችሁ።

👉 ዘወትር አርብ ምሽትና የጽዋ መርኃግብራት በሚውሉበት ቀናትን (12፣16፣21፣27) ሳያካትት!


ሀሳብ እና አስተያየቶን
➟➟➟➟@wkugg_bot
ያስቀምጡልን

✝️ ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ ✝️

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

10 Oct, 19:21


የተወደዳችሁ የግቢ ጉባኤያችን አባላት እንኳን ለ2017 የትምህርት ዓመት አደረሳችሁ እያልን የመክፈቻ ጉባኤ አርብ ማለትም ቀን 1/02/17 የምናደርግ በመሆኑ ሁላችሁም እንድትገኙልን በእግዚአብሔር ስም እንጋብዛቹሀለን ::

ቦታ :- ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
🕦ሰዓት :- 11:30


📩 ለማንኛውም አስተያየት @wkugg_bot' ን ይጠቀሙ

🌼 ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ 🌼

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

07 Oct, 08:38


ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ pinned «+ ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል + ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት…»

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

07 Oct, 08:36


+ ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል +

ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . .

ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ

ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ  የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤

‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት

‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት  . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ

‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣  ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል

‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም  . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣  . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ  . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው. . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ›› 
አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤


‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣


‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ››አልኩ አምላኬን፣     
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት

ዲ/ን አብርሃም ይኄይስ እንደጻፈው

ሀሳብ እና አስተያየቶን
➟➟➟➟@wkugg_bot
ያስቀምጡልን።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

07 Oct, 05:20


የተከበራችሁ የግቢ ጉባኤያችን አባላት እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን ዛሬ የመድኃኔዓለም ጽዋ መርሃ ግብር ይኖረናል።
በመሆኑም  ግቢ የገባቹ ወንድም እህቶቻችን በአንድነት ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ትመጡልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🙏


⛪️ ቦታ፦ ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ  ቤተክርስቲያን
⌚️ሰዓት፦ ማታ 11:30


ሀሳብ እና አስተያየቶን
➟➟➟➟@wkugg_bot
ያስቀምጡልን


ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

06 Oct, 05:53


 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም እና ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ ለወርኃ ጽጌ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።

🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

✞ ወርኃ ጽጌ   ✞

🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

[ ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ]

“እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ”

[ ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን እያቀፍሽው በተአምርና በንጽሕና ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ድንግል ማርያም ሆይ ከልቅሶ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ መልካማዬ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ]


[ አባ ጽጌ ድንግል ]
🥀🥀🥀🥀🥀

▬▬▬እንኳን አደረሳችሁ🙏▬▬▬

✉️ ለማንኛውም አስተያየት  @wkugg_bot' ን ይጠቀሙ


🥀 ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ 🥀           

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

30 Sep, 07:01


💬 መልዕክት📣

የተወደዳችሁ የግቢ ጉባኤያችን አባላት፤የተለያዩ መገልገያ እቃዎችን (ሳፋ፣ባልዲ፣መጥረጊያ፣ጄርካን....) መግዛት የምትፈልጉ ግቢ ጉባኤያችን ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደቆየው፤ ባለፈው ዓመት ተማሪዎች ሲገለገሉበት የነበረውን ዕቃዎች አሰባስቦ በታላቅ ቅናሽ እየሸጠ ይገኛል። በመሆኑም  ከታች በተጠቀሰው ቦታ ተገኝታችሁ በመግዛት ይህንን መልካም አጋጣሚ እንድትጠቀሙ ስንል እናሳስባለን።

ቦታ፦ቤተማርያም

ሰዓት፦ ዘወትር ጠዋትና ማታ

🤳
0930718739

📩 ለማንኛውም አስተያየት 
@wkugg_bot' ን ይጠቀሙ

🌼 ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ 🌼
✥┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•═
═╯

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

28 Sep, 10:09


መ      ስ      ቀ      ል

ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና”
  — ፊልጵስዩስ 3፥18

✞ በአምላኩ ደም የተቀደሰ ከፈጣሪው ጐን በወጣ ውሃም የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ለገነት ዛፎች አክሊል፤ ለገዳም ዛፎችም ክብር የኾናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ለአሸናፊ የእግዚአብሔር በግ መሠዊያ የኾነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ለእስራኤል አምላክ የፋሲካው መሠዊያ የኾነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ የጎልጎታዊዉ የምስጢር ወይን መፍለቂያ የኾነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ከርሱ ምእመናንን ለማተም የሚኾን የሕግንና የሥርዐት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዐይነት ነው!

✞ ቡሩካን በጎችን ለማጠቢያ የሚኾን ምንጭን ያወጣ ዕፅ ምን ዐይነት ነው!

✞ ምድርን የቀደሳት ሰማይንም ያማተበበት፤ ዓለምንም ኹሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ሰማያውያንን ከምድራውያን ያስተባበራቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው! አዳምን ከስሕተት ያዳነው ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኛነት ነጻ ያወጣት ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ስለ ርሱ በኦሪትና በነቢያት የተነገረ በሐዋርያትም በገሐድ የተሰበከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ የተከሉትን የበተናቸው ያመኑትንም የሰበሰባቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!

✞ ቤተ ክርስቲያንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ላይ የመሠረታት ዕፅ እንደምን ያለ ነው!"

       #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ

💫ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ 💫
🌤🌤🌤🌤🌤🌤🌤🌤🌤🌤🌤

2,226

subscribers

3,003

photos

69

videos