ተአምር ምንድነው?
+++
ፅድቃችሁ የታለ
ተአምር የታለ
እኛስ ሙሴ……
በበትሩ ባህር ከፍሎልናል
ድንጋይ ተሸክመን በመሀሉ አልፈናል
ደመና ከልሎን ከነዓንን ወርሰናል
ከሰማይ ላይ መና ወርዶልን በልተናል
ከራፍዲም አለት ውሀ ጠጥተናል
፡
አንተ አይሁዳዊ
ተአምር ምንድን ነው ትለኝ እንደ ሆነ
የትኛው ይደንቃል ትለኝ እንደሆነ
በል እንግዲህ ስማ እኔም አለኝ ድንቅ
እጅግ የሚጎላ እጅግ የሚረቅ
:
በሙሴ በትር ባህር መከፈሉ
ድንጋይ ተሸክሞ ማለፍ በመሀሉ
እርግጥ ነው ይደንቃል
ይሄ ግን ይጎላል ይሄ ግን ይረቃል
በመስቀሉ በትር ማለፍ ከሞት እሳት
በደሙ ማህተም ወደ ርስትህ መግባት
፡
አንተ አይሁዳዊ
ፅድቃችሁ ወዴት ነው ትለኝ እንደሆነ
ተአምሩ የታለ ትለኝ እንደሆነ
በል እንግዲህ ስማ
በህቱም ድንግልና አምላክን መፀነስ
የቃል ሰጋ በመሆን የአለም መፈውስ
በእናቱ ደመና ከልሎን መሻገር
የእዳ ፅህፈት ቀዶ ሲኦልን መበርበር
:
አንተ አይሁዳዊ….
ከነዓን ስትሻገር ፀሀይ ከከለለህ ከሰማይ ደመና
ታምሬ ማርያም ነች
ያቺ መሶበወርቅ በውስጧ ያለባት የህይወቴ መና
ሙሴ ከከፈለው የኤርትራ ባህር
እኔን የሚደንቀኝ
በመስቀሉ በትር ገሀነምን ማለፍ ሲዖልን መሻገር
ሰዎች ከገነቡት ከኢያሪኮ መፍረስ
እኔን ይደንቀኛል
በመስቀሉ ጉልበት የእዳ ደብዳቤዬ የሀጢያቴ መደምሰስ
አንተን ከሚደንቅህ ከበረሀው መና
እኔስ የሚገርመኝ
አምላክን መወለዷ በህቱም ድንግልና
:
ተአምርስ በለኝ የክርስቶስ መስቀል
ሞትን ለዘላለም ከሰንኮፉ ሚነቅል
:
ተአምርስ በለኝ
ምጥ ሳይሰማት ወለዳ ድንግል እናት ሆነች
ያለዘር ፀንሳ አምላክን ታቀፈች
ይቀጥላል...
+++
"ተአምር ምንድነው"
ሀይማኖተ አበው
ዘ ቅዱስ ኤራቅሊስ
ም፵፱-ቁጥር ፵፭
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን እንዳስተማሩት
+++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
t.me/Menfesawigetmoch