UMERSEMETER SECONDARY SCHOOL

@umersemeter1


UMERSEMETER SECONDARY SCHOOL

22 Oct, 15:25


ጉዳዩ፡- የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት  እቅድን ይመለከታል

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ በአለምም ሆነ በአገራችን ኢትዮጵያ በሴቶች ላይ ህመምና ሞት በማስከተል ከፍተኛ የጤና ችግር መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ይህንን በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንዱና ዋነኛዉ የማህፀን በር ጫፍ ካንስር መከላከያ ክትባት እድሜያቸዉ ከ 9 -14 ዓመት ለሆነ ታዳጊ ሴት ልጃገረዶች መስጠት ነዉ ፡፡

መከላከያ ክትባቱ በአገራችን ከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ እድሜያቸዉ 14 ዓመት ለሆናቸዉ ታዳጊ ሴት ልጆች እተሰጠ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በ 2017 በጀት ዓመት ጤና ቢሮ እንደገለፀዉ በዚህ ዓመት ከ9-14 ዓመት ያሉ ታዳጊ ሴት ልጆችን ( Mut Age Cohon ) ክትባቱን ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ክትባቱ ከህዳር 9-13 / 2017 ዓ.ም ድረስ በዘመቻ እንደሚሰጥ አሳዉቆናል ፡፡

ስለሆነም እድሜያቸዉ ከ9-14 ዓመት ሴት ታዳጊ ልጃገረዶች በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች ክትባቱን ለመስጠት የዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቅን ስለሆነ በአስተዳደሩ ትምህርት ጽ / ቤት ስር ለሚገኙ ከመንግስትና ከግል ትምህርት ቤቶች መረጃዉ በአግባቡ ተሰብስበዉ እስከ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም እንዲመጣ እዉቅናና የስራ አመራር እንዲሰጥ ትብብራችዉን እንጠይቃለን ፡፡

ከሠላምታ ጋር ”