Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

@palestine_quds


Ethio🦋 Palestine
በዚህ ቻናል ለፍልስጤም ለኢስላም ትልቅ መሰዋትነት የከፈሉ የታላላቅ ጀግኖች ታሪኮች ስለፍልስጤም አስገራሚ ክስተቶች ፍልስጤም የተላኩ ነብያቶች ታሪክ የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
ሼር አድርጉልን
ለአስተያየት
👇
@Palestinians_bot
🇵🇸ፍልስጢን አቅሳ🇪🇹
#አቅሷ_ትጣራለች

#FREE_PALESTINE✌

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 17:14


የምንወደው የምናከብረው ትዉልደ ግብፃዊ አሜሪካዊዉ ኮሚዲያን ጋዜጠኛ ባሲም የሱፍ እንደተለመደው ነገ ከ ፕሪስ ጋር የጦፈ ክርክር አላቸዉ በጣም ጓጉቻለሁ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 14:26


ሰበር ዜና
እንደሚመረጥ አቅ ነበር ኻሊድ ማሻል የሸሂድ ያህያ ሲንዋር ተተኪ እሱ ሆኖል
ከ36 ዓመት በፊት ከእስራኤል ግድያ ያመለጡት ካሊድ ማሻል ሐማስን በጊዜያዊነት መምራት ጀመሩ፡፡ከዚህ ቀደም ሲመረጥ በህመም ምክንያት አልተቀበለም ነበር
ለያህያ ሲንዋር ግድያ ሐማስ እስራኤል ይበቀላል ሲሉ ዝተዋል

የፊዚክስ መምህር የሆኑት ካሊድ ማሻል ሐማስን ከመመስረታቸው በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 1996 እስከ 2017 ድረስ የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 09:17


ባለጸጋ እስራኤላዊያን በሐማስ የታገቱ ዜጎችን ለሚለቁ የገንዘብ ጉርሻ ማዘጋጀታቸውን ገለጹ
😁
ዳንኤል ብረንቡም የተባሉት ከአልኮል ነጻ መጠጥ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ከታገቱበት በህይወት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ላደረጉ አጋቾች 100 ሺህ ዶላር እንደሚሰጡ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ባለጸጋው ገንዘቡን በካሽ አልያም በቢትኮይን መልክ እከፍላለሁ ያሉ ሲሆን እስካሁን ከ100 በላይ ስልክ እንደተደወለላቸው ተናግረዋል፡፡
ከ100 ሺህ ደዋዮች ውስጥ አብዛኛው የሹፈት ስልኮች ሲሆኑ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑት ግን ትክክለኛ ደዋዮች መሆናቸውን ተከትሎ ጉዳዩን ለእስራኤል መንግስት አሳውቄያለሁም ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በአሜሪካ የሚኖሩ ሌሎች እስራኤላዊን ታጋቾችን ለሚለቁ ሰዎች በተመሳሳይ የገንዘብ ማዋጣት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 07:16


አብዱረህማን እንደፃፈዉ ለወደፊት ሲንዋር የተሰኘ ፊልም መሰራቱ አይቀርም። ስክሪፕቱንም ይሁን የእውነተኛውን ሙሰልሰል ፍፃሜ ደራሲ ደግሞ ራሱ ሲንዋር ነው። አሸውክ ወል ቁሩንፉል (እሾህና ቁርንፍድ) የተሰኘ እውነተኛ ታሪኩን ከልጅነት እስከ ሸሂድነቱ እዚያው ወራሪዋ ቢእር አስ-ሰበእ ወህኒ እያለ ፅፎታል።

ፅዮናውያኑ የድሮኗን ፉቴጅና የየሕያን ፍፃሜ መልቀቃቸው የግዛታቸውን ስረ-መሰረት አናግቶታል። እንደዚህ ስህተታቸውም የሚበሳጩበትና የሚፀፀቱበት ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም ዓለማቀፍ ምልክት ነው ያደረጉት።

አረበኛ የገራላችሁ አንብቡት

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 07:11


ሲንዋር ያቺን ሰዓት

እንዳወሩበት ሳይሆን እንደ ወንዶቹ ፊት ለፊት ከመሬት በላይ ሆኖ ሲዋጋና ሲያዋጋ ቆየ። በአንድ አጋጣሚ ከሁለት አጃቢዎቹ ጋር በቅኝት ላይ ሳለ የወራሪ ሀይሎች ታንክ ሳይቀር ታጥቀው ሲንቀዋለሉ አይን ለአይን ተፋጠጡ። ሶስቱ ጀግኖች ከባድ መሳርያ የታጠቁትን ወራሪዎች ለመጋፈጥ ደጀን ፍለጋ ወደ አንድ ህንፃ ገቡ። ቦቅቧቆቹ ግን ለሶስት ነፍስ አንሰው ህንፃውን በታንክ ደጋግመው መቱት። ህንፃው በከፊል ፈረሰ። ውስጥ ያሉት ጀግኖች ቆሳሰሉ። ብዙም ሳይቆይ በድጋሜ ሌላ የታንክ አረር ህንፃውን መታው ያኔ ሁለቱ አጃቢዎቹ በክብር ተሰዉ። የህንፃው ውስጥ ከነቤት እቃው በአቧራ ተሞላ። ሲንዋር ቀኝ እጁ እና ወገቡ ገደማ ላይ በታንክ ፍንጥርጣሪ ክፉኛ ቆሰለ። እናም የስንብቱን ታሪካዊ ክዋኔ ጀመረ።

ሲንዋር ወታደራዊ ዩኒፎርሙን እንደለበሰ ክላሹን ተደግፎ በቤቱ ጥቅ ያየውን በትር አነሳና በሱ ተመርኩዞ የወንድሞቹን ፊት ሸፍኖና ዱዓ አድርጎላቸው ክህንፃው ብዙም ወዳልተጎዳው ክፍል አዘገመ። በተረጋጋ መንፈስ የሸሀዳውን ፅዋ ለመጨለጥ አቧራ ለብሶ አቧራ ለበሱ ሶፋ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ። ወታደራዊ ዩኒፎርሙን ከነ ጥምጣሙ በአንድ ሙጃሂድ ኩነት አስተካከለ። ጀርባውን ለወራሪዎች መግቢያ በር ሰጥቶ ፊቱን ደግሞ ወደ ቁድስ አቅጣጫ አቅጣጭቶ ጉዞውን ሊቋጭ ዝግጁ ሆነ። የቆሰለውን እጁን በቅዳጅ ጨርቅ ግጥም አርጎ አሰረ። ክላሹን በእግሮቹ መሀል አፈሙዙን ውደላይ ሰድሮ አቆመው። በትሩን ባልተጎዳው የግራ እጁ ያዘው። በተጎዳ እጁ ከወራሪ ኮረኔል የማረከውን ሳይለንሰር የተገጠመለት ሽጉጥ ይዟል። በከፍተኛ ተመስጦ ደረቱን ነፍቶ ከጌታው ጋር እያወራ ወራሪዎችን መጠባበቅ ያዘ። ነገር ግን 24 ሰአት ሙሉ ዝር ያለ የጠላት ወታደር የለም። ፍርሀታቸው ካልሞቱስ በሚል እሳቤ ደጅ አቁሟቸዋል።

ሙሉ ቀን ከነ ለሊቱ ካለፈ በኋላ በአስርት የሚቆጠሩት ወታደሮች ሲንዋር ወዳለበት ለመግባት አልደፈሩም። በስተመጨረሻም ፈሪ ወደ ህንፃው ከመግባቱ በፊት ውስጡን ለመሰለል ድሮን ካሜራውን ላከ። ሲንዋር በእርጋታ በተቀመጠበት የጠላቱን ድሮን ድምፅ ሰማ። ደሙ ለ 24 ሰአት ሲፈስ እና ያለምንም የህክምና እርዳታ ቢቆይም ባለ በሌለ ሀይሉ በእጁ የያዘውን በትር ወደ ድሮኑ ወረወረ። የመጨረሻውን አቅሙን ለጥቃት ተጠቀመበጥ እስከመጨረሻው ተጋደለ። ድሮኑን የሚያበረው ፈሪ የወራሪ ወታደር ከፍርሀቱ ብዛት ድሮኑን ለቀቀው። ትዝ ሲለው ቦታው ላይ ያለው ድሮኑ እንጂ እሱ አይደለም። እናም መልሶ ድሮኑን ተቆጣጥሮ ተረጋጋ። ውስጥ ያለው ሲንዋር መሆኑን ገና አሁን ማወቃቸው ነበር። እስከዚህ ቅፅበት ድረስ ተራ የሃማስን ወታደሮች እየተዋጉ እንጂ ሲንዋርን መጋፈጣቸውን አያውቁም ኖሯል። ፈሪነት ቤት ሲሰራ የእስራኤልን ወታደር ይመስላል። ለአንድ ነፍስ ድሮን እና ታንክ የሚተኩስ ወታደር የእስራኤል እንጂ የሌላ አይደለም። ወታደሮቹ ሲንዋርን ከበነዋ ብለው አሳወቁ ቴላቪቭ ውሸት አለች። ሲንዋርኮ በቀላሉ አይገኝም አሉ። እንደነሱ መስሏቸው። ቢሆንም ህንፃውን ምቱትና ግደሉት ከዛ ጣቱን ቆርጣቹ ላኩት ብለው ትዕዛዝ አስተላለፉ። ሲንዋር እንደዚያ ተጎድቶም ሊጠጉት አልደፈሩም። ከርቀት በታንክ ህንፃውን ደጋግመው መትተው ናዱት። የሲንዋር ሶፋ ሲንዋርን ይዞ ፍርስራሽ ውስጥ ገባ። ናዳ ተጫጫነው። ሲንዋን እንደ ጀኛ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ሞተ። የጀግናውን ወኔ ድሮኑ ነግሯቸዋል። ቢገቡ አስሩን ጥሎ እንደሚወድቅ አውቀውታል። እነሱ ህይወታቸውን በሚወዱት ልክ ሲንዋር ሞቱን ይመኘው ነበር። እናም ተሳካለት። ታላቁ ሙጃሂድ ትጥቁን እንደታጠቀ ሰማዕትነትን ተቀበለ። ታሪክ ፅፎ አለፈ። ህያው ትግልበአስረክቦ ነጎደ። በኋላም ከፍርስራሽ መሃል ሲንዋርን አዩት። ለአንድ ሰው በሚሊዮን ዶላር የሚገመት መሳርያ ማፍሰሳቸው አሳፈራቸው። ለአንድ ሰው ታንክ መተኮሳቸውን ዓለም አውቆ እንዳያፌዝባቸው ሰጉ። እናም የሞተውን የሲንዋር ግንባር በጥይት ነደሉት። በተኩስ ልውውጥ የሞተ ለማስመሰል። ጀግናው ግን ህይወቱን ለሰጠለት ዓላማ የመጨረሻ ህቅታውን ሰጠ። ዘመን የማይረሳው ደናቅና አክብሮት የሚያስቸር አሟሟት። ታሪካዊ ማንነት። የጀግና ምሳሌ። የህያ ሲንዋር። ድል ለፍልስጤማውያን!

Ⓒሳሊህ አስታጥቄ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

21 Oct, 15:09


“በእሳት እየተቃጠልን እያያችሁ ዝምታን መረጣችሁ” - እናት እና ልጆች በእሳት ቃጠሎ ያጣው ቤተሰብ




ማሳሳቢያ፡ ይህ ታሪክ አንባቢያንን የሚረብሽ ገለፃ ይዟል

ሰብዓዊነት የጠፋ ይመስላል። አቅም ያላቸው የሚባሉ መሪዎች እንኳ እያዩ ምንም እያደረጉ አይደለም።

አሕመድ አል-ዳሉ እንዲህ ነው እምነቱ። ቤተሰቡ በእሳት ሲቃጠል ተመልክቷል። ይህ ምሥል መቼም ከአእምሮው የሚጠፋ አይመስልም።

“ከአሁን በኋላ ሕይወት የለኝም” ይላል።

ሰኞ ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም. ወንዶች ልጆቹ እና ሚስቱ ጋዛ ውስጥ አል-አቅሳ በሚባል ስፍራ በእሳት ተቃጥለው ሞቱ። ከዚህ በኋላ በሕይወት ላይ ተስፋ ቆርጧል።

ከፊት ለፊቱ በጨርቅ የተጠቀለለ አስከሬን አለ። የ12 ዓመት ወንድ ልጁ አብዱልራህማን አስከሬን ነው። የመጨረሻ ልጁ።

በእስራኤል ጥቃት በተነሳ እሳት ምክንያት ነው ልጁ ተቃጥሎ የሞተው። በቃጠሎው ተጎድቶ አራት ቀናት ሆስፒታል ቆይቷል። ከመሞቱ አንድ ቀን ቀድሞ አሕመድ ሆስፒታል ተገኝቶ ልጁን አይቶት ነበር።

“አባዬ አታስብ፤ ደኅና ነኝ። ደኅና ነኝ አባዬ። አትፍራ” ለመጨረሻ ጊዜ ከልጁ የሰማው ድምፅ ነበር።

አሕመድ እንባ እየተናነቀው ነው የሚናገረው።

“ሦስት ጊዜ ከእሳት ውስጥ ላወጣው ሞከርኩ። ነገር ግን ሰውነቱ ወደ እሳቱ ወደቀ” ይላል።

ታላቅ ወንድሙ የ19 ዓመቱ ሻባን እና የ37 ዓመት እናቷ አላ በዚሁ ምሽት በተነሳው እሳት ሞተዋል።

ሻባን የጋዛ ስቃይ መለያ ምልክት ሆኗል። በሕይወት ሳለ በእሳት ሲቃጠል የሚያሳይ ዘግናኝ ምሥል በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ተሠራጭቷል።

አሕመድ ፊቱ እና እጁ በእሣት ተቃጥሏል። ሚሳዔሉን የተኮሰው ፓይለት እና ትዕዛዙን የሰጡት መሪዎች “ልቤን ሰብረውታል፤ ቅስሜን ሰብረውታል. . . እሳቱ ቢበላኝ ይሻል ነበር” ይላል።

የምስሉ መግለጫ,አሕመድ አል-ዳሉ ከእሳት ቃጠሎው ቢተርፍም ፊቱ እና እጁ ላይ ጉዳት ደርሶበታል

ጥቃቱ የተፈጸመው ሰኞ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ለሊት 7፡15 ሰዓት አካባቢ ነው።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይዲኤፍ) ዒላማ ያደረግነው የሐማስን “የዕዝ እና የቁጥጥር” ማዕከል ነው ይላል። ጥቃቱ የደረሰው ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በአል-አቅሳ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ነው።

ሐማስ ሆስፒታሎች ውስጥ አልገኝም ሲል ወቀሳውን ያስተባብላል።

በጥቃቱ ምክንያት አራት ሰዎች ወዲያውኑ ሲገደሉ በርካቶች ከፍተኛ የተባለ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የእስራኤል መካለከያ ኃይል ሁኔታውን “እያጣራሁ ነው” ብሏል።

የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ የእሳት ቃጠሎው ምሥሎች “እጅግ የሚረብሹ ናቸው” ብለው እስራኤል ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ የበለጠ ጥንቃቄ እንድታደርግ አሳስበዋል።

“እስራኤል ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የመጠበቅ ግዴት አለባት። አሁን የተፈጠረው ነገር በጣም የሚረብሽ ነው። ሐማስ በሆስፒታሉ አካባቢ ሰላማዊ ዜጎች እንደ ምሽግ ቢጠቀም እንኳ የሆነው ነገር የሚረብሽ ነው።”

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ እና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት በጋዛ ጦርነት ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳስቦናል ብለዋል።



የምስሉ መግለጫ,የተፈናቀሉ ሰዎች የተጠለሉበት ቦታ ላይ የደረሰውን የሚሳዔል ጥቃት ተከትሎ የተነሳው እሣት

በጋዛው ጦርነት ሰዎች በእሳት እየተቃጠሉ ነው፤ በከባድ የጦር መሣሪያ እየተገደሉ ነው፤ በየቀኑ እየተተኮሰባቸው ነው።

ከፍርስራሶሽ ውስጥ የተረፉ ሰዎችን ለማውጣት የሚደረግ ጥረት፣ ሆስፒታሎች ውስጥ ያለው መረበሽ፣ መጨረሻ የሌለው ቀብር በካሜራ ዕይታ ውስጥ ገብተው ይሆናል። ብዙውን ጊዜ ግን እነዚህ ግድያዎችን በካሜራ ስላልተቀረጹ ዓለም አላያቸውም።

የሻባን አል-ዳሉ አሟሟት ይለያል። እጆቹ ከእሳቱ ለመውጣት ሲሞክሩ ይታያሉ። በፍም እሳት የተከበበ ሰው ይታያል። የሚደርስለት ግን አጥቷል።

ከቃጠሎው በኋላ የሻባን ቪድዮዎች እና ፎቶዎች በማኅበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት መሰራጨት ጀምሯል። ሻባን ታዳጊ ነበር። የማኅበራዊ ሚድያን ኃይል ያውቀዋል። የየዕለት ተግባሩን በስልኩ ካሜራ ያስቀምጣል።

ስልኩ ውስጥ የተገኙት ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ብዙ ነገር ያሳያሉ። ደም ሲለግስ ይታያል። ሌሎችም እንዲለግሱ ያበረታታል።

ቢቢሲ ከቃጠሎው የተረፉትን የሻባንን ቤተሰቦች አናግሯል። ቢቢሲ አካባቢው ባሉ ወኪሎች አማካይነት ነው ይህን ማድረግ የቻለው። ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ወደ ጋዛ ሄደው እንዲዘግቡ ከእስራኤል ፈቃድ አልተሰጣቸውም።

ሻባን በጋዛው ጦርነት ምክንያት ከቤተሰቡ ጋር ሦስት ጊዜ ተፈናቅሏል። ሁለት እህቶች እና ሁለት ታናናሽ ወንድሞች አሉት።

“የምንኖርበት ሁኔታ አስከፊ ነው” ሲል በቀረጸው ቪድዮ ላይ ይታያል። “ቤት የለንም፣ ምግብ አጥሮናል፣ መድኃኒትም የለንም” ይላል።

ይህን ቪድዮ ሲቀርጽ ከኋላው የእስራኤል ድሮን ድምፅ ይሰማል። ድሮኗ አካባቢውን ትሰልላለች። ይህ የጋዛ ነዋሪዎች የዕለተ ዕለት እውነታ ነው።

የሻባን እና አብዱልራህማን ወንድም ሞሐመድ አል-ዳሉ ታላቅ ወንድሙን ለማዳን ወደ እሳቱ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ለቢቢሲ ይናገራል። ነገር ግን ሌሎች ሰዎች ይዘውት ነው የተረፈው። የዚያን ዕለት ውጪ ነው ያደረው። መንገድ ላይ ተኝቶ የወንድሞቹን ዕቃ እየጠበቀ።

የምስሉ መግለጫ,የሻባን እና አብዱልራህማን ወንድም የሆነው ሞሐመድ አል-ዳሉ

ሞሐመድ ወንድሞቹ ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ አቅራቢያ አነስተኛ ጥላ ዘርግተው ምግብ ይሸጡ እንደነበር ያስታውሳል።

“ጠንክረን ሠርተን ያገኘውን ነገር በጥንቃቄ እንጠቀማለን። ያለን ነገር ሁሉ ሠርተን ያገኘነው ነበር። ሠርተን እንበላለን፤ ሠርተን እንጠጣለን። አሁን ግን ያለ ነገር ሁሉ ወድሟል።”

ሞሐመድ የቤተሰቡን የተቃጠለ አስከሬን ቢመለከትም ማወቅ የቻለው የእናቱን ብቻ ነው። ምንም እንኳ የእናቱ ሰውነት በእሳት ክፉኛ ቢጎዳም እጇ ላይ ባደረጉት አምባር ምክንያት ለይቷቸዋል።

“አምባሩን ባላየው ኖሮ እናቴ መሆኗን እንኳ መለየት አልችልም ነበር። እጇ ከሌላው የሰውነት ክፍሏ ተለያይቶ ነበር። ነገር ግን አምባሯ አለ። ከእጇ ላይ ወስድኩት።”

የእናቱ አንድ የቀረው ማስታወሻ ከእሳት ከተረፈው አስከሬኗ ላይ ያገኘው አምባር ነው።

የአል-ዳሉ ቤተሰብ ድንጋጤ ላይ ነው። የተረፉት ሐዘን ላይ ናቸው። “መግለፅ ይከብደኛል” ይላል ሞሐመድ።

“ለሰዎች ለማስረዳት እሞክራለሁ፤ ነገር ግን አይሆንልኝም። የገዛ ወንድሜ በእሳት ሲቃጠል አየሁት። እናቴም በእሳት ተቃጥላ ስትሞት አየኋት” ይላል።

“ምን እስኪሆን ነው የምትጠብቁት? ምን እስኪሆን ነው ዝም የምትሉት? በእሳት ስንቃጠል እያያችሁ ዝምታን መረጣችሁ?” ሲል የዓለም ማኅበረሰብን ይጠይቃል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

21 Oct, 14:52


አጫጭር መረጃ

ዬዲዮት አህሮኖት በጀባሊያ በቀጠለው ውጊያ ውስጥ የሚገኙትን የእስራኤል መኮንኖች ጠቅሶ እንደዘገበው "ቀደም ሲል በእስራኤል ጦር የተመቱ የሃማስ ሃይሎች ዋሻዎች እንደገና መገንባታቸው አስገርሞናል" ሲሉ ገልጿል።

- 7 እስራኤላውያን አይሁዶች ለኢራን ሲሰልሉ እንደነበር በመግለጽ በቁጥጥር ስር አውላለች። የእስራኤል ጦር የደህንነት ተቋማት ፎቶግራፎችን አንስተው ለኢራን ሲያስረክቡ ነበር ተብሏልም።

-እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት ያወጣችዉ እቅድ መረጃ ማፈትለኩን በተመለከተ አሜሪካ ጉዳዩን እንደምታጣራ አስታወቀች


-የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በጋዛ የሚገኘውን የ401ኛ ጦር መሪ የነበሩት ኮሎኔል ኤሳን ዳክሳን ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
ወታደራዊ አዛዡን በሃማስ ያጣው የእስራዔል ጦር በዛሬው ዕለት የሃዘን ቀን አውጆ ውሏል፡፡ 

-እስራኤል ሄዝቦላህን ይደግፋሉ ያለቻቸውን በመዲናዋ ቤይሩት እንዲሁም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ባንኮች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

20 Oct, 19:55


ይህቺ የሸሂድ ሲንዋር ስታይል በጣም ታስገርመኛለች ሶፋ ላይ ተቀምጦ በፈራረሰዉ ጋዛ የለቀቀዉ ፎቶ ዝነኛ ነበር ሲሞትም ሶፋላይ ተቀምጦ ነበር ታዲያ ወራሪዋ እስራኤል የያህያ ሲንዋር አስክሬን ፎቶ በወረቀት ስትበትን ነዉ የዋለችዉ ፁሀፋም ከዚህ ቡኋላ ሲንዋር የለም ሀማስ የለም ይላል በሰላም መኖር የፈለገ እጅ ይስጥ ይላል ለወራሪዋ ጋዛዊያን የሰጡት ምላሽ ፎቶዉን እንደምታዮት አጋርተዋል በዚህ የተበሳጩት አይሁዳዊያን የህያ ሲንዋር ጠላቶቹን እየተዋጋ የተሰዋበትን ቤት ከ ደቂቃዎች በኋላ አፈነደዋለሁ በማለት የወራሪዋ ጦር መግለጫ ማውጣቱን አልጀዚራ ዘግቧል።
በቀጣይ ልክ እንደ የህያ ሲንዋር አይነት ሚሊዮን ሲንዋሮችን እናያለን ኢንሻአላህ ።
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

20 Oct, 15:20


ይህን አሳማሚ መረጃ ልንገራችሁ!!
የአረብ ሀገራት በተለይም ኢማራት የቀይ ጨረቃ በሚባለው የግብረሰናይ ድርጅታቸው አማካኝነት ወደ ጋዛ የእርዳታ አከፋፋይ ሰዎችን ይልካሉ።
ያው ሀማስም ሙሉ ውጊያ ላይ በመሆኑና የሚቆጣጠር አካል ስለሌለባቸው ገብተው የሚሰሩት ስራ እርዳታ ማከፋፈል አይደለም።

ከዚያ ይልቅ የሀማስ እዝ የት እንዳለ ፣ ሮኬቶችን ከየት ቦታ እንደሚያስወነጭፍ ፣ አመራሮቹ የት ሆነው እንደሚያዙ ፣ የእዝ ሰንሰለቱ ምን አይነት እንደሆነ ወዘተ ሁሉንም ነገር ለእስራኤሉ ሞሳድ ፣ ሺን ቤት እና ለአሜሪካው ሲአይኤ መረጃዎችን የማቀበል ስራ ይሰራሉ።
ይህ የተረጋገጠ ሀቅ ነው የምነግራችሁ። አረቦች በአንድ ነገር ደስተኛ አይደሉም እርሱውም እስራኤል ጦርነቱን ቶሎ ባለመጨረሷ ነው። በዚህ አሜሪካም ደስተኛ አይደለችም።

በአሁኑ ሰአት ለሙስሊሙ አለም ከአረቦ ነገስታቶች በላይ ጠላት የለውም። ነገርታቶቹ የህዝባቸውን አእምሮ ማጠብ የቻሉትን አጥበው የተቀረውንና አልሰማም ያለውን ደግሞ አሳማሚ ቅጣት እየቀጡ ባሪያ አድርገውታል።

አረቦች የገዛ ዜጎቻቼውን የሚሰልሉት በእስራኤል እና አሜሪካ የስለላ ተቋማት አማካኝነት ነው። ከነርሱ እይታ የሚወጣ አንድም ነገር የለም። የአረቦችና የእስራኤል የስለላ ተቋማት በጥምረት ነው የሚሰሩት። የጋራ ጠላቶቻቼው የሆኑትን የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄና የኢራን መሩን የትግል ግንባር ለማፍረስና ለመቋቋምም አብረው ይሰራሉ።

እና የሙስሊሙ አለም ነፃ የሚወጣው እነዚህን ባሪያ መሪዎች ሲያስወግድ ብቻ ነው። እስከዚያ ዋጋ እየከፈለ ይቀጥላል!

የኢማራት አገዛዝ ፈራርሶ አላህ ያሳየኝ!
ይህች ሸይጧን ሀገር በሙስሊሙ ላይ ያደረሰቺው ውድመት ተገልፆ አያልቅም! በመካከለኛው ምስራቅ ሸይጧናዊነትን በማስፋፋት የሚቀድማት አንድም ሀገር የለም!

via sied mohamed
https://t.me/palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

20 Oct, 09:28


ማንኛውም የቴሌቪዥን የሚዲያ ሞስኮት የምመለከትበት ጊዜም ሰዓቱም የለኝም እኔ የሚቀናኝ በስልኬ የምመለከታቸዉ ፕላትፎርም የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ብቻ ነዉ እነዚህ የ NBC ETHIOPIA TV በ ዮቲዮብ አንዳዴ ይደርሱኛል እንደነዚህ ሰዎች የመካከለኛው ምስራቅ ኢሲያ ጂኦፖለቲካ የገባቸዉ የለም ይተነትኑታል አይገልፅም ያሰላም ።ከእዉነት ጋር የቆመ ጋዜጠኛ ይመቸኛል ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 18:54


እነዚህ ቀሽም ኢማራቶች

አረብ ኤሚሬትስ በሶማሊላንድ እስራኤል ወታደራዊ ሰፈር እንድትገነባ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በአፍሪካ ቀንድ “ስትራቴጂካዊ” የእስራኤል ወታደራዊ ኃይልን ለመመስረት አቅዳለች።

ኤሚሬትስ ሌክስ እንደዘገበው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ይህን ሃሳብ በሚስጥር ያቀረበች ሲሆን ለእስራኤል ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብታለች።

አቡ ዳቢ የሶማሊላንድ ባለስልጣናትን እስራኤል ለሶማሌላንድ ይፋዊ እውቅና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን በማቅረብ ማሳመን ችላለች።
ሶማሌ ላንድ ለሀገር እዉቅና ስትል ለእስራኤል ከፈቀደች ፍልስጤማውያን እንደካደች እቆጥረዋለሁ እስራኤል የመን ሀዉቲዎች የዘጉባትን ወደብ በሶማሊያ መጠቀም ስለፈለገች ነዉ እንዲሁም ኢራን እና ቱርክ የሶማሊያ ላንድ የባህር ሀይል ስላሰጋት ነዉ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 11:33


ብሎ ነበር

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 11:31


ሃማስ ከጋዛ ውጪ ከሚገኙ አባላቱ አዲስ መሪ ለመሾም እየተመካከረ ነው
የሞቱ መሪዎቹን በፍጥነት የመተካት ልምድ ያለው ሀማስ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል በሆነው የሹራ ካውንስል አዲስ መሪ እንደሚሾም ይጠበቃል። የሟቹ ያህያ ሲንዋር ወንድም ሞሀመድ ሲንዋር በጋዛ ከእስራኤል ጋር የሚደረገውን ውግያ በማስተባበር እና በመምራት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ግምት አግኝቷል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 08:00


የኔታኒያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ።

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ቡድን በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።

የድሮን ጥቃቱ በሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ መፈጸሙ ነው የተነገረው።ግን በቤቱ ዉስጥ ከነቤተሰቡ አልነበረም

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

18 Oct, 16:43


ቀጣይ የሀማስ መሪ ማን ነዉ የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ነዉ ።መልሱ የሀማስ መሪ ከዚህ ቡኋላ ይፋ እንደማይሆን ተረጋግጧል ይህም ጠላትን ያስፈራል ።

2,575

subscribers

1,489

photos

864

videos