ይህ ሰው በመርካቶ ንብረታቸው ከወደመባቸው ሰዎች አንዱ ነው።
እንዲ ሲል ተናግሯል።
አልሀምዱሊላህ! በውሳኔህ ተሳስተህ አታውቅም
ብዙ ሰተኸኝ ነበር ጥቂት ወስደህብኛል ክብርና ልቅና ላንተ የተገባ ይሁን!
አሁንም ቢሆን የጉዳት መጠናችን በውል አልታወቀም ቢሆንም የብዙዎች ወንድሞቼ ንብረት በአጠቃላይ በሚባል መልኩ ወድሟል አላህ ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን የተሻለውን አላህ ይተካልን!!
ሲቀጥል ብዙዎቻችሁ CBE account እየተቀባበላችሁ ልታግዙኝ እየሞከራችሁ ነው!!! በጣም አመሰግናለው!! ግን እኔ ከብዙ አላህ ከሰጠኝ ፀጋ በጥቂቱ ስለሆነ የነካኝ ለኔ የምታረጉትን ገቢ ለወንድሞቼ እንድታረጉ በትህትና እጠይቃለው!!! እንዲሁም የኔን የለጠፋችሁትን እንድትሰርዙት በአክብሮት እጠይቃለው!!!!(ሸገር ፕረስ)
Via: ሐሩን ሰዒድ
አንተና እኔ ብንሆንስ ምንድን ነበር የምንለው????
የኔን ለኔው ተውት ሁሉም እራሱን ይፈትሽ ትዕግስት! ትዕግስት! ትዕግስት!
ስንቶቻችን ሀዲስና ቁርአንን እናነበንበዋልን እስከ ወበሺሪ አሷቢሪን ድረስ ነገር ግን
ስራ የለም
ስራ ቀዝቅዟል
ወይኔ ልጆቼ ምን ላበላቸው ነው?
አንድ ቀን እንኳን አሏህን በስርአቱ ሳናመስግን ውለን እንገባለን።
ይህ ሰው ግን ንብረቱ ወድሞበትም ያለው ቃል ቢኖር (ኧልሐምዱሊላህ በውሳኔህ ተሳስተህ አታውቅም ብዙ ሰጥተኸኝ ትንሽ ወሰድክብኝ)
ያአሏህ አንተም በመልካሙና በበላጩ ተካለት!!!!አሚን