Nejashi Printing Press

@nejashipp


ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።

Nejashi Printing Press

02 Oct, 06:15


መፃሕፍትን እቤትዎ ወይም ሥራ ቦታዎ ድረስ እናምጣልዎ
***

ፕሌይ ስቶርን በማውረድ ወደ Nejashi Bookstore ወይም በዌብሳይታችን WWW.NEJASHIBOOKS.COM በመግባት
የመፃሕፍት ዝርዝሮች በማየት የፈለጉትን መጽሐፍ ይምረጡ። ዋጋው እዚያው አለላችሁ ።

ከዚያም ወደ 0945858585 በመደወል የመረጡትን መጽሐፍ ይዘዙ።
ለአዲስ አበባ ደንበኞች
የትራንስፖርት 50 ብር ብቻ ይከፍላሉ ።

ወደ ክልሎች በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

https://t.me/NejashiPP

Nejashi Printing Press

16 Sep, 07:14


ሶባሐል ኸይር !

ሁለት አዳዲስ መፃሕፍት ልጠቁማችሁ ነው።

1- የሰዒድ ሽፈራውን ሐላልን ፍለጋ መጽሐፍ አንብባችኋል?

አዎ አሁን ደግሞ "ሐቢብ" ብሎ መጥቶላችኋል፡፡ ወይም ደግሞ "ሐላልን ፍለጋ ቁጥር 2" ልትሉት ትችላላችሁ፡፡
መጽሐፉ ኢስላማዊ ታሪክ ወይም ልቦለዳዊ ነው፡፡ ከኢስላማዊ እሴትና አደብ ሳይወጣ ተጨባጭ የሕይወት ታሪካችንን ይዳስሳል፡፡

ታይፓችሁ የሆነ እነሆ ….

2- ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመርን ታውቁት የለ..
አዎን የርሱን መፃሕፍት ካላነበባችሁ ብዙ ነገር አምልጧችኋል፡፡ ጥንቅቅ ጥንፍፍ ያለ፣ በመረጃና ዕውቀት የዳበሩ፣ ብዙ የተደከመባቸው ዝግጅቶች ናቸው፡፡

"አርዓያ" የተሠኘው ምርጥ መጽሐፉን ካነበባችሁ አሁን ደግሞ “አርዓያ ቁጥር 2” በተሠኘ መጥቶላችኋል፡፡
መጽሐፉ የታላቁ አርዓያችንን የነቢያዊውን የሕይወት ዘይብ ይዳስሳል ። ብዙ ብዙ ትማሩበታላችሁ።

ሁለቱንም መፃሕፍት ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኟቸዋል፡፡


https://t.me/MuhammedSeidAbx

Nejashi Printing Press

23 Aug, 14:57


ከኡሳማ ኢብኑ ዘይድ እና አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንደተነገረው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡-

“የቂያማ ዕለት፣ ከሰው ሁሉ ወደ ኃያሉና የተከበረው አላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆኑት፣ ዱንያ ላይ እያሉ ርሃቡ፣ ጥሙ እና ሐዘኑ የረዘመባቸው፣ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱ፣ አላህን የሚፈሩ፣ በአንዳች ቦታ ላይ ቢገኙ የማይታወቁ፣ ቢቀሩም ሰው የት ጠፉ ብሎ የማይጠይቃቸው፣ ግና አካለ ምድር ሁሉ የምታውቃቸው፣ መላእክት የሚያጅቧቸው ናቸው። ሰዎች የዱንያን ፀጋ አጣጣሙ፤ እነርሱ የአላህን ትዕዛዝ በመፈፀም ረኩ። ሰዎች ፍራሽ እና ወፋፍራም ሴቶች ላይ ተጋደሙ፤ እነርሱ ግን በግንባሮቻቸው እና ጉልበቶቻቸው ለአላህ ተደፉ። ሰዎች የነቢያትን ፈለግ እና መልካም ባሕሪዎቻቸውን ተዉ፤ እነርሱ ግን አጥብቀው ያዙ። ምድር እነርሱን ስታጣ ታነባለች። አላህ እነርሱ የሌሉበትን መንደር ሁሉ ይጠላል። ውሾች በክት ላይ እንደሚረባረቡት ዱንያ ላይ አልተረባረቡም። ከማንኪያ ትራፊ ላሱ፤ እራፊ ጨርቅ ለበሱ፤ የተንጨባረሩና ትቢያ የለበሱ ናቸው። ሰዎች ሲያዩዋቸው ታመዋል ብለው ያስባሉ፤ እነርሱ ግን ታመው አይደለም። ይዘባርቃሉ አዕምሯቸውን የሳቱ ናቸው ይሏቸዋል፤ ግና በአዕምሮ ጤናማ ናቸው። ነገርግን እነርሱ የአላህን ጉዳይ በቀልቦቻቸው ስላዩ የዱንያን ጉዳይ እርግፍ አድርገው ተዉ። እነርሱ በዱንያ ሰዎች ዘንድ አዕምሮ የሌላቸው ተብለው የሚታሰቡ ናቸው፤ ባይሆን ብዙዎች አዕምሮ በሌላቸው ዘመን እነርሱ ኖራቸው። በመጨረሻው ዓለም ትልቅ ክብር አላቸው።” እንዲህ አሉት ለኡሳማ <ኡሳማ ሆይ፣ እነርሱን ያገኘህ እንደሆነ ለአንድ አገር የደህንነት ዋስትና መሆናቸውን ዕወቅ። አላህ እነርሱ የሚኖሩባትን አገር ሕዝቦች አይቀጣም። አላህ በነርሱ ተደስቷል፤ ከነርሱም ወዷል። ወንድሞች አድርገህ ያዛቸው። በነርሱ ምክንያት ትድን ይሆናልና። ሆድህ ተርቦ፣ ጉበትህ ተጠምቶ ሞትን ማግኘት ከቻልክ አድርገው። ከዚህ የተነሳ ክብር ታገኛለህ። ከነቢያት ጋር ታርፋለህ። መልኣክ ነፍስህን ሊያወጣ በመጣ ግዜ ትደሠታለህ። ጀባር (ጠጋኙ) አላህ ምህረቱን ያሰፍንብሃል።”

(አል-ኸጢብ አል-በግዳዲ ዘግበውታል፡፡)

https://t.me/NejashiPP

Nejashi Printing Press

22 Aug, 04:40


.......የፈራ ማልዶ ይነሣል፡፡ እወድቃለሁ ብሎ የሠጋ በርትቶ ያጠናል። የድህነትን ክፋት የፈራ በርትቶ ይሠራል፡፡ በጊዜ ሂደትም ድህነትን ይገላገላል፡፡ እውቅናን ማግኘት ዓላማው የሆነ ሰው መግባት መውጣት፤ መቆም መነሣት ፤ በአደባባይ መታየት ከፊት ለፊት መገኘት ያዘወትራል፡፡ በዚህም ከጊዜያት በኋላ የሃሣቡን ያሣካል፤ የኒያውም ይሞላለታል፡፡ ለብር የቋመጠ ሰው በእንቅልፍ ልቡ ሲዞር ያድራል፤ በጧት ተነስቶ ይሮጣል፤ በቀን አብዝቶ ይደክማል፤ ምሽቱን ገፍቶ ይተኛል፤ ኋላም ሀብት ያገኛል፡፡ ለትዳር የተመኛትን ከእጁ ማስገባት የፈለገ ሰው መላዎችን ያውጠነጥናል፤ ዘዴዎችን ይቀይሣል፤ በዚህም በዚያም ይጥራል፤ ከብዙ ድካምና ልፋት በኋላም የሀሣቡን ያሣካል የምኞቱን ያገኛል፡፡ የሰው ልጆች እንዲህ ለዱኒያዊ ስኬቶች እንለፋለን፡፡ ለዓለማዊ እድገቶችም በብዙ መልኩ ስንጥር እንታያለን፡፡ የጥረትን ውጤት የድካምን ፍሬ እናውቃለንና ብዙ የምንደክምላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለብር እንደክማለን፡፡ ለትምህርት እንደክማለን። ለእውቅና እንደክማለን፡፡ ለጥሩ ትዳር እንደክማለን፡፡ የምንደክምላቸው ነገሮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር የዋጋውን ያህል ያልደከምንለት አገር ቢኖር ጀነት ነው፡፡ ጀነት ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች በላይ ሁሉ ውድ ሆኖ ሳለ ብዙም ግምት የሰጠነው አይመስልም፡፡ አብዛኞቻችን ተዘናግተናል፡፡ ኑሮአችንም የደመነፍስ ሆኗል.......

ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ ሣለን በዚህች ዓለም ላይ የተሠጠን እድሜ አልቆ ቆይታችንም አብቅቶ ያ ስሙ እንኳ እንዲነሳ የማንፈልገው ሞት ድንገት 'መጣሁ' ቢለን ያኔ ምን ሊውጠን መሸሻችን ወዴት ነው… መጠጊያችንስ ከየት ይሆን? ሰማይ እንደሆነ ሩቅ ነው፡፡ መሰላል ተይዞ አይወጣ፡፡ መሬት እንደሆነች ክብ ናት ብንዞርም አንለያት፡፡ ወይ ወደ እናት ማህፀን አይመለሱ ነገር። 'አፈር በሆንኩ' ም አይጠቅም፡፡

ስለሆነም አሁኑኑ በአጭሩ እንታጠቅ፡፡ ለአኼራችን በወጉ እንሰንቅ፡፡

ብንኮራ መሬት ላንሰምጥ የተራራን ያህል ላንረዝም ምነው መንጠባረር መወጠሩ… ሞት ላይቀር ነገር ምን ቢኖሩ!!
-----
'ልብ ላላሉ ልቦች' ከሚለው የMuhammad Seid Abx መፅሃፍ የተወሰደ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

Nejashi Printing Press

21 Aug, 15:11


የርሃብ ጥቅም
**
ኢማም አልገ-ዛሊ - ኢሕያእ ዑሉሚዲን በተሠኘው መጽሐፋቸው ውስጥ ስለ ርሃብ ጠቀሜታ ሐዲሦችን፣ የሶሐቦችንና የደጋግ ሰዎች አባባሎችን አስፍረዋል፡፡

መጽሐፉ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡
*
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) “ከሰው ሁሉ የሚልቅ ማነው?” ተብለው ሲጠየቁ፦ “ምግቡና ሳቁ የተመጠነ፣ ኃፍረተገላውን የሚሸፍንበትን ነገር የወደደ ነው” ብለዋል።

ዓኢሻ (ረ.ዐ.)፣ “መጥገብ ብንሻ ኖሮ እንጠግብ ነበር፤ ነገር ግን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የሰውነታቸውን መራብ ይመርጡ ነበር፡፡” ብላለች።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)፣ “ምግብና መጠጥ በማብዛት ቀልቦችን አትግደሉ፤ ቀልብ ውሃ ሲበዛበት እንደሚሞት ተክል ነው::” ብለዋል።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡- “የሰውን ልጅ የሆዱን ያህል የተሸከመው ስልቻ የለም። ጀርባውን የሚያቆምበት የተወሰኑ ጉርሻዎች ይበቁታል፤ የግድ ከሆነ ደግሞ አንድ ሦስተኛውን ለምግብ፣ አንድ ሦስተኛውን ለመጠጡ፣ አንድ ሦስተኛውን ለእስትንፋሱ መተው አለበት።”

ዑመር (ረ.ዐ.) እንዲህ ብለዋል፦ “አደራችሁን ከልክ በላይ ጠግባችሁ አትመገቡ፤ ጠግቦ መብላት በምድር ላይ ለሰውነት ክብደት ያጋልጣል፤ በሞቱ ጊዜም ጥንብነት ነው።”

በሌላም መልዕክታቸው፣ “ሸይጧን፣ በሰው ልጅ ደም ውስጥ ይዘዋወራል፤ መዘዋወርያውን በርሃብ አጥቡበት::” ብለዋል። (ኢብኑ አቢ ዱንያ ዘግበዉታል፡፡)

በሌላም መልዕክታቸው፣ “ሙእሚን በአንድ ሆድ ነው የሚመገበው፤ ሙና ፊቅ ግን በሰባት አንጀቶች ነው የሚበላው” ብለዋል።
ይህም፣ ካፊር ሙእሚን ከሚመገበው ሰባት እጥፍ ይመገባል እንደ ማለት ነው። ወይም ደግሞ የመመገብ አምሮቱ ሰባት እጥፍ ነው ማለት ነው። የስሜት መነሻው ደግሞ ሆድ ነው፤ ሆድ ሲጠግብ ስሜት ይከተለዋልና። እንጂ በተጨባጭ ሰባት አንጀቶች በሆዱ ውስጥ አለ ማለት አይደለም።

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንዳስተላለፉት፣ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ለሦስት ተከታታይ ቀናት ቤተሰቦቻቸውን የስንዴ ዳቦ አጥግበው አያውቁም፤ ይህችን ዓለም እስኪለዩ ድረስ።” (ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት፡፡)

ሉቅማን ልጃቸዉን ሲመክሩ “ ልጄ ሆይ ሆድ ሲሞላ ማሰላሰል ይሞታል፣ ጥበብ ይሰናከላል፣ ሰውነት ከዒባዳ ይተሳሰራል ፡፡” ብለዉታል፡፡

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ለራሱ እንዲህ ይል ነበር፣ “ነፍሴ ሆይ ምንድነው የምትፈሪው? እራባለሁ ብለሽ ትሰጊያለሽን?! እሱን አትፍሪ፤ አንቺ አላህ ዘንድ ከዚያ በታች ዋጋ ነው ያለሽ፤ ሙሐመድ እና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ይራባሉ።”

ሰህል ኢብኑ ዐብዱላህ አት-ቱስቱሪ፣ “በአመጋገብ ሥርዓት የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ.) ፈለግ በመከተል ትርፍ መመገብ መተውን የበለጠ የትንሳኤ (ቂያም) ዕለት ሚዛንን የሚሞላ መልካም ሥራ የለም፡፡” ብለዋል።

እንዲህም ብለዋል፡- “ ለዲንም ሆነ ለዱንያ ከመርራብ በላይ ጠቃሚ የሆነ ነገር የለም፡፡”
በሌላም ንግግራቸው፡- “ለአኺራ ተማሪዎች ምግብ ከማብዛት በላይ ጎጂ የለም፡፡” ብለዋል፡፡

እንዲሁም “ጥበብ በዕውቀትና በርሃብ፤ ኃጢኣት ደግሞ በመሃይምነት እና በጥጋብ ውስጥ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

“ራሱን ያስራበ ሰው የሰይጣን ጉትጎታ ከሱ ይወገዳል፡፡” ብለዋል፡፡

https://t.me/NejashiPP

Nejashi Printing Press

19 Aug, 10:57


የደጋግ ሰዎች ንግግሮች - ስለ ዱንያ
**

 ዐብዱላህ ኢብኑ ሙስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡-
‹ይህች ዱንያ አገር የሌለው ሰው አገር፤ ገንዘብ የሌለው ሰው ገንዘብ ናት፡፡ እሷን የሚሰበስባትም ዐቅል የሌለው ነው፡፡›

 ሱፍያን አስ-ሠውሪይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ (የቅርቢቱ ዓለም) ዱንያ የተባለችው ቅርብ ስለሆነች ነው፡፡ ማል (ገንዘብ) ማል (ዘንባይ) የተባለው ባለቤቱን ወደራሱ እንዲያዘነብል ስለሚያደርግ ነው፡፡›

 ወህብ ኢብኑ ሙነበህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ ለብልሆች መስሪያ አገር ናት፡፡ መሃይማን ደግሞ በሷ ላይ ተዘናግተዋል፡፡ ከሷ እስኪለቁ ድረስ ስለሷ ምንም አላወቁም፡፡ ወደኋላ ለመመለስ ፈልገው ቢጠይቁም መመለስ አልቻሉም፡፡›

 አል-ሐሰን አል-በስሪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አራት ነገሮች የዕድለ ቢስነት ምልክቶች ናቸው፡፡ የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ረጅም ምኞት እና በዱንያ ላይ ለመቆየት መስገብገብ፡፡›

 ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ለዱንያ ባለህ ሀሳብና ጭንቀት ልክ ለአኺራ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡ ለአኺራ ባለህ ጭንቀት ልክ ለዱንያ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡›

 ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህም ብለዋል፡-
‹ለዱንያ በተደሰትክ ልክ የአኺራ ጥፍጥና ከልብህ ውስጥ ይወጣል፡፡›

 አል-ፉዶይል ኢብኑ ዑያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
‹አምስት ነገሮች የዕድለቢስነት ምልክቶች ናቸው፡- የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ጥሩ ጓደኛን አለመምረጥ፣ ለዱንያ ማዘንበል እና ረጅም ምኞት፡፡ አምስት ነገሮች ደግሞ የደስታ ምልክቶች ናቸው፡- በቀልብ በአላህ ላይ እርግጠኛ መሆን፣ በዲን አላህን መፍራት፣ ከዱንያ መብቃቃት፣ ሐያእ እና እውቀት ናቸው፡፡”

 አል-ፉዶይል ረሒመሁላህ እንዲህም ብለዋል፡-
‹ዱንያ ከነሙሉ ግሳንግሷ በመጨረሻው ዓለም የማልመረመርባት ሐላል ሆና ብትቀርብልኝ፤ አንዳችሁ ጥንብ ባየ ጊዜ እንዳይነካው እንደሚጠየፈው ሰው ሁሉ ተጠይፌያት በራቅኩ ነበር፡፡›

 ሰለመህ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹በዱንያ አንድም የሚያስደስትህ ነገር አይኖርም በሌላ በኩል የሚያስከፋህ ነገር የተጣበቀበት ቢሆን እንጂ፡፡›

 ዐብዱላህ አርራዚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የዒባዳን ጥፍጥና ማግኘትና የጥፍጥናው ጣሪያ መድረስ ከፈለግክ ባንተና በዱንያ ስሜቶች መካከል ከብረት የሆነ ግድግዳ አብጅ፡፡›

 ሰዕድ ኢብኑ መስዑድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አንድ ሰው ዱንያው ስትጨምርና አኺራው ስትቀንስ እሱም ይህን ሁኔታውን ወዶ የሚኖር መሆኑን ካየህ የዚህ ዓይነቱ ሰው የተታለለና ሳያውቅም በራሱ የሚጫወት መሆኑን እወቅ፡፡›

 ከሢር ኢብኑ ዚያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያችሁን በአኺራችሁ ሽጡ፡፡ ወላሂ ሁለቱንም ታተርፋላችሁ፡፡ አኺራችሁን በዱንያ አትሽጡ ወላሂ ሁለቱንም ትከስራላችሁ፡፡›

 ዑበይድ ኢብኑ ዑመይር አልለይሢይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ የተወሰነ ዕድሜ አላት፡፡ አኺራ ደግሞ ዘላለማዊ ናት፡፡›

 ዐውን ኢብኑ ዐብደላህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የዱንያን ማማር አትመልከቱ፡፡ እሷ በየትኛውም ጌጥ ብትዋብና ብታሸበርቅ ውሸት ናት፡፡ ትልቅ ትርፍና ሀብት የሚገኘው ነገ በአኺራ ነው፡፡ እኛ ደግሞ በቀደሙትና ወደ ኋላ በቀሩት ሰዎች መካከል ነን፡፡›

 ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ልጄ ሆይ! ወደዚህች ምድር ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ ለዱንያ ጀርባህን እየሰጠህ ነው፡፡ አኺራ ደግሞ እየመጣች ነው፡፡ አንተም ርቆ ከሄደው ይልቅ እየቀረበ ላለው ቅርብ መሆንህን አስተውል፡፡›


https://t.me/NejashiPP

Nejashi Printing Press

12 Aug, 05:46


ከዚህ ቀደም የዓለማት እዝነትን እና
የኸሊፋ አቡ በክርን ታላላቅ መጽሐፎች ተርጉሞ ያቀረበልን ኡስታዝ አሕመድ ሑሴን አቡ ቢላል በቅርቡ ደግሞ የኸሊፋ ዑመርን ታሪክ የያዘውን መጽሐፍ አጠናቋል ።

ወደ 900 የሚጠጉ ገፆችን የያዘው ይህ መጽሐፍ በቅርቡ በነጃሺ ማተሚያ በኩል ታትሞ ለንባብ ይቀርባል ኢንሻአላህ ።

https://t.me/NejashiPP

Nejashi Printing Press

16 Jul, 16:37


ለልጆች ☝️

https://t.me/NejashiPP

3,836

subscribers

508

photos

9

videos