Lij Tedla Melaku

@negedeyehuda


Lij Tedla Melaku

22 Oct, 16:29


https://youtu.be/BVwMCQQ1Lzs

Lij Tedla Melaku

14 Oct, 17:32


ወሳኝ መልእክት!

https://youtu.be/dqqAliKjRGc?si=Hk-6-0YNBa32YGhY

Lij Tedla Melaku

07 Sep, 18:51


https://www.tiktok.com/t/ZP8JAkB3T/

Lij Tedla Melaku

31 Aug, 12:40


ዘራፍ አማራ!

በጀግናው አርበኛ መከታው ማሞ የሚመራው ምድር አንቀጥቅጡ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
(ይህ የአንድ ክፍለ ጦር አንድ ብሪጌድ ብቻ ነው)

Lij Tedla Melaku

30 Aug, 22:41


በጀግናው አርበኛ መከታው ማሞ የሚመራው አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ!

ይህን በእሳት ተፈትኖ ለዚህ የበቃ ግዙፍ ዕዝ በድንቁርናና በስድብ ማሸማቀቅ የሚቻል የሚመስላቸው እውን የዋሆች ናቸው። ጊዜ እንጅ ከሸዋ ዕዝ ወንድሞቻቸው ጋር ወደ አንድንት እንደሚመጡ ለአፍታም አንጠራጠርም ስንል በመተማመን ነው።

Lij Tedla Melaku

25 Aug, 03:24


"እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች. . . እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች፥ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?" -ኢየሱስ ክርስቶስ
(የማቴዎስ ወንጌል 23)

Lij Tedla Melaku

01 Aug, 21:25


https://youtu.be/mpc7g2TLArY

Lij Tedla Melaku

23 Jul, 03:30


አርበኛ መከታው የሚመራው ዕዝ እና ኮማንደር አሰግድ የሚመራው ወደ አንድ እንዲመጡ ለወራት ዕንቅልፍ እያጣን ስንለፋ ከቆየን በኋላ እንደ "ዋን አማራ" ባሉ ተልእኮ ያላቸው ሰርጎ ገቦችና ሌሎች ጣልቃ ገቦች ምክንያት ይህ በመሆኑ ማዘናችን እሙን ነው። ጠላት ደስ ቢለውም የአማራው ትግል በዚህ አይሰናከልም። ደፍርሶም ቢሆን ይጠራል። አማራ አንድነቱን አጽንቶ ያሸንፋል። መላው የሸዋ አማራ ፋኖ [ከፍ ሲልም መላው የአማራ ፋኖ] የልዩነት ምክንያቶችን ንቆ ሕዝብን በማስቀደምና ወደ አንድ በመምጣት ጠላትን (አገዛዙን) ያሳፍር ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ። አሉ የሚባሉ የመርሕ ጥያቄዎችና የርእዮተ ዓለም ጉዳዮች በውይይትና በሙግት፣ በጥበብና በምሁራዊ ክሕሎት፣ ብሎም በሠለጠነ መንገድና በአማራዊ ባህል ይፈታሉ። መሪዎችም ዘለዓለማዊ አይደሉም።

ድል ለአማራ ሕዝብ።

Lij Tedla Melaku

20 Jun, 19:29


ዛሬም ድረስ ደ|ም የሚያፋስሰው የማርክስ ሰይጣናዊ ፍልስፍና 👇🏼

https://youtu.be/9zbLs_vJpog?si=tGbe7Sr9_Vqw0CjP

Lij Tedla Melaku

07 Jun, 20:18


ከ5 ደቂቃ በኋላ ቲክቶክ ላይ እንገናኝ
ርዕሰ አንቀጽ፥ የፋኖ አንድነትና ተግዳሮቶች (2)

https://www.facebook.com/share/p/mxW2abKCG4JMcrmd/?mibextid=qi2Omg

Lij Tedla Melaku

31 May, 23:45


የአሜሪካን መግለጫ ተከትሎ በአማራ ዙሪያ የሚነሱ ነጥቦች
👉🏽 https://youtu.be/u5EN6tnEDSk

Lij Tedla Melaku

29 May, 20:34


1. የትርክትና የሥነ ልቡናውን ጦርነት ካሸነፍን
2. በዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ላይ ተጽእኖ ካሳረፍን
3. መሬት ላይ ያለው አመራርና ኃይል በጋራ መዋቅርና በራዕይ አንድነቱን ካፀና

ጨዋታው ያበቃል

(ልጅ ተድላ መልአኩ ወረደ)

Lij Tedla Melaku

28 May, 01:14


"ዋን አማራ" የሚባለውን ሰርጎገብ አደረጃጀት በተልእኮ ያሠማራው ማን ነው?"

አንድን ሰው ወይንም ድርጅት ማንነቱንና ተልእኮውን መርምረህ ለማወቅ ከፈለግክ እንቅስቃሴውን አጥንተህ፣ ምግባሩንና የሥራውን ውጤቶች አይተህ ማንነቱን ትለየዋለህ (inferring the intention by examining the action)።

ያሠማራው ኃይል የአማራ አደረጃጀቶችና ተቋማት በራሱ በአማራ እንዲፈርሱ፤ የአማራ ድምጽ የሆኑ ተሟጋቾች፣ ታጋዮችና ተጽእኖ ፈጣሪዎች በራሱ በአማራው ዘንድ በተሳሳተ ገጽታ እንዲጠለሹ፤ የአማራ ፋኖዎች እርስ በርስ እንዲጫረሱና በሕዝብ እንዲጠሉ የሚፈልገው ኃይል ነው። ይህ በፖለቲካው ዓለም "psychological operation" (psyop) ይባላል።

ይህን ውጤት የሚፈልገውን ኃይል ካወቅክ ማን እንዳሠማራቸው አወቅክ ማለት ነው። አገዛዙ ለዚሁ ዓላማ ኢንቬስት ያደረገው ግንዝብ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን በዚሁ ትረዳለህ። ይህም አማራን መምታትም ሆነ ማሸነፍ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከውጭ ሆኖ በመውጋት ሳይሆን ከውስጥ ሆኖ በማፍረስና በማመታታት በመሆኑ ነው።

Lij Tedla Melaku

13 May, 22:41


https://youtu.be/gpld12LkdGU?si=mbH68e4lbCMBwdQV

Lij Tedla Melaku

12 May, 19:35


በአማራ ብሔርተኝነት ጭንብል የአማራ በደል አስቀጣይነትና የብሔር ብሔረሰቦች የበላይነት ፖለቲካ አስጠባቂነት በአማራ ሕዝብ ላይ ከመሳለቅም ያለፈ ጠላትነት ነው። ኦሮሞ ክልል የኦሮሞ፣ ትግራይ ክልል የትግሬ፣ አማራ ክልል ደግሞ የብሔር ብሔረሰቦች የሚልን ሕገ መንግሥት፣ የአማራን ታሪካዊ ርስቶች የሌሎች ንብረት አድርጎ አማራን አገር አልባ በማድረግ ያስጨፈጨፈን ሕገ መንግሥት ባፈጠጠ ሴራ በአማራ ትግል ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚጋጋጡ አካላት የአማራ ሕዝብ የጠላቶች ሁሉ ቀዳሚ ጠላት ናቸው። የብአዴንነትም ትክክለኛ ትርጕም ይህ ነው።

Lij Tedla Melaku

02 May, 00:25


ሐተታ ቻነልን ለማጠናከርና ያቀድናቸውን (የተቋም ግንባታና የዶክሜንተሪ) ፕሮጄክቶች ተፈጻሚ ለማድረግ የሚከተለውን QR Code በመጠቀም የበኩልዎን ድጋፍ ያድርጉ፥

Lij Tedla Melaku

02 May, 00:14


በርካታና ሁነኛ መረጃዎችን፣ የታፈኑ ሐቆችን፣ የተደበቁ እውነቶችን እያተትን የምናሰራጭበት ቻነል ነው። የውሸት ትርክቶችን የምናጋልጥበት፣ ታሪክን፣ ፖለቲካን ማዕከል ያደረገ የሥነ ልቡና ፍልሚያ የምናካሂድበት መድረክ ነው። የሚከተለውን የyoutube ሊንክ ተጭነው ይወዳጁ። "Join" የሚለውን በመጫን የቻነሉ አባልና ቤተሰብ ይኹኑ።
https://youtube.com/@tedlamelakuerc?si=hsOBjDXLPe74Ln4a

Lij Tedla Melaku

29 Apr, 15:50


https://youtu.be/9LlNXNL4Y4o?si=UIxeYTO7Lh7tq3fy

Lij Tedla Melaku

28 Apr, 21:58


በአንዳንዱ ላይ የዋለልኝ፣ የደርግ፣ የሕወሐት፣ የብአዴንና የኦነግ ፖለቲካ የሥነ ልቡና ስብራት እንዳስከተለበት አንዱ ማሳያ አማራ ሆኖ ሳለ የአማራ ኃያልነትና ክብሩ የሚገለጥባቸውን ትውፊታዊ የማንነት ዕሤቶች ዋጋቸውን ሳያውቅና ሳይፈትሽ "ፊውዳል" እና "ኋላቀር" እያለ ራሱን በራሱ የሚያዋርድ፣ አንሶ መታየትን የተለማመደ መሆኑ ነው። የተሰበረውን ሥነ ልቡና መጠገን በራሱ የዚህ ትግል አንዱ ዓላማ ነው።

Lij Tedla Melaku

26 Apr, 20:21


እነ አበበ ካሳሁን ("አቤል ጆሴፍ") ሲጋለጡ የቆጡንና የባጡን መቀባጠሩን ተያይዘውታል። ለራሳቸው የሥልጣን ጥም ሲሉ ፓርቲ መስርተው የጎንደርን አባት አርበኛ ፋኖዎች ለመከፋፈል ሲጣጣሩ አንድ ሆኑባቸው። እኛ እያለን "ኦሮሞ" (ዘመድኩንን መሆኑ ነው) አስታረቀብን እያሉ ሲዘባርቁ ታዩ። ያ አልበቃ ብሏቸው የሸዋን ፋኖ በመከፋፈል ተጠምደው ያንድ ወገን አንጋሽ መስለው ውስጥ ውስጡን ደግሞ ሌላኛውን ወገን በከንቱ ክሶች ለማሳጣት ሲንቀሳቀሱ ተደረሰባቸው። በዚህ መጋለጣቸው ምክንያት እኛኑ "የመንገሥ ህልም ስላላቸው አርበኛ መከታውን ይዘው አራት ኪሎ ሊገቡ ፈልገው" እያሉ እየቀባጠሩ ይገኛሉ። እንዲህ ያለ ውርደትና የአስተሳሰብ ዝቅጠት በአማራ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም። የአማራን ታሪካዊና ሥነ መንግሥታዊ ትውፊት፣ እንዲሁም የምንኮራበትን አማራዊ የልዕልና ሌጋሲ ከፍ አድርገን የጠላትን የውሸት ትርክት በመታገላችን ብቻ ዛሬ ላይ የሥልጣን ጥም የሚያሰቃያቸው እነዚሁ የደረቁ ዕንጨቶች በምናባቸው ተፎካካሪአቸው መስለናቸው እኛን በሥልጣን ፈላጊነት ለመክሰስ (የእምዬን ለአቢዬ መሆኑ ነው) ይዳዳቸዋል። እኛስ በመከታውና በአሰግድ መኻል ልዩነቶችን ለማጥበብ የኼድንበትን ርቀት የሁለቱም ዕዞች አመራሮችና ሽማግሌዎች ምስክር ናቸው፥ በሁለቱም ወገን የተጠየቅነውን ፈጽመን የበኩላችንን ሐላፊነት ተወጥተናልና። እንደነሱ ዕድሉን ባገኘን ጊዜ ሁሉ ለሥልጣን በመሯሯጥ የምንታወቅ አይደለንም (የማትታወቁ እንዳይመስላችሁ)። ይህ ዓይነቱ አጭበርባሪነትስ ከብአዴናውያን በምን ይለያል? ከሁሉም አስገራሚው አርበኛ መከታውን "ብቸኛው እኛን (እነሱን) ማግኘት ያልፈለገ" ብለው የከሰሱበት ክስ ነው። ያልገባቸውም ነገር እነ አርበኛ መከታውን የማሽከርከር ዐቅም ያለው ማንም የውጭ ኃይል የሌለ መሆኑን ነው። የራሳቸው አመራርና መዋቅር ያላቸው እንጅ የየትኛውም ፓርቲም ሆነ ግለሰብ ጀሌዎች አይደሉምና። በእንደዚህ መታሰቡ በራሱ ከድፍረት ይቆጠራል። አርበኛ መከታው በምን አይታማም ቢሉ በየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ያልተጠለፈ በመሆኑ ነው። ዕዙ ፋኖ እስክንድር ነጋን በአማራዊ ባህል ተቀብሎ አስተናግዷል። ከዚህ ባለፈ እኛ ብቻችን የግንባሩ ወይንም የሌላ ሠራዊት ነን ብሎ መግለጫ ሰጥቶ አያውቅም። "ከትግሉ ዓላማ ውጭ ከሆኑ ቡድኖች ጋር ተመሳጥሮ ብቻውን አራት ኪሎ ሊገባ አስቧል" እያሉ ነጭ ውሸት በተንኮልና በሴራ ማዛመት በራሱ ትልቅ ወንጀል ብቻም ሳይሆን በፋኖ መኻል ለሚፈጠር ክፍፍልና ግጭት ዋና ተጠያቂ የሚያደርግ ነው። ለዚህ ግብራችሁም ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ እናረጋግጣለን። ምስኪኖችን ከጨፍጫፊዎች እናድናለን ብለው ጫካ የገቡን ፋኖዎች በምናባችሁ ውስጥ ባለው የሥልጣን ቅዠት ከፋኖን ተሳዳቢው የሚዲያ ቡድን ጋር ተቀናጅታችሁ ልታጫርሱ በመሞከራችሁ ታሪክ ይጠይቃችኋል።