ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

@moaetewahedob


"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት።
እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል።
ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። "
https://t.me/MoaeTewahedoB

አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️
@sosi5555
ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


🥰🥰

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


ጌታችንን በግልጽ ያየው ነበር፡፡ የሰዎቹም ሁሉ ድብቅ ኃጢአት በግልጽ ይታየው ስለነበር የበቃውንና ያልበቃውን እለየለ ንስሓ ይሰጣቸው ነበር እንጂ በኃጢአት ውስጥ እንዳሉ እንዲሁ በድፍረት ወደ ሥጋወደሙ አያቀርባቸውም ነበር፡፡ በዚህም ብዙዎቹን በቅድስና ጠበቃቸው ነገር ግን ክፉዎች ቀንተውበት ‹‹እራሱ ሚስት አግብቶ ጋለሞታ ይዞ ሳለ ድንግል ሳይሆንና ሳይገባው በወንጌላዊው ማርቆስ መንበር እየኖረ…›› ብለው አሙት፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦለት ‹‹በአንተና በሚስትህ መካከል ያለውን ቅድስና ለሕዝቡ ግለጥላቸው›› አለው፡፡ ድሜጥሮስም ከቅዳሴ በኋላ ሰው እንደተሰበሰበ ደመራ አስደምሮ ልብሰ ተክህኖውን እንደለበሰ በሚነደው እሳት ውስጥ ገብቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ በእሳት ውስጥ እንዳለ ከእሳቱ ፍም አንስቶ በሚከናነብበት ቀጸላ አደረገ፡፡ ሚስቱንም ጠርቶ መጎናጸፊያሽን ዘርጊ አላትና በመጎናጸፊያዋ የእሳቱን ፍም ጨመረ፡፡ ነገር ግን የእርሱን ቀጸላና የሚስቱን መጎናጸፊያ ምንም እሳት አልነካውም ነበር፡፡ በእሳቱም መካከል በአንድነት እየጸለዩ በቆሙ ጊዜ ሕዝቡ ይህን ተመልክቶ እጅግ አደነቀ፡፡ እርሱም የእሳቱን ፍሕም እያነሳ ቢረጨው ሐሜተኞችን ብቻ እየመረጠ አቃጠላቸው፡፡ ሕዝቡም ቅድስናውንና ንጽሕናውን አይተው በመጸጸት ‹‹ይቅር በለን›› ብለው ይቅር ብሏቸው ስለ ኃጢአታቸው ጸልዮላቸዋል፡፡
ቅዱስ ዲሜጥሮስንም የተአምራቱን ምሥጢር በጠየቁት ጊዜ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ይህን ሥራ የሠራሁት ከንቱ ውዳሴ ሽቼ አይደለም፣ እንናተ እኔን አምታችሁ እንዳትጎዱ ከዚህችም ሴት ጋር በመካከላችን ተሰውሮ ያለውን ምሥጢር እገልጥላችሁ ዘንድ የእግዚአብሔር መልአክ ስላዘዘኝ ነው እንጂ፡፡ እርሷ የአባቴ የወንድሙ ልጅ ናት፡፡ በሕፃንነቷም አባቷ ስለሞተ በአባቴ ቤት ከእኔ ጋር አደገች፡፡ አካለ መጠንም በደረስን ጊዜ አባቴ እርሷን አጋባኝ፡፡ ወደ ጫጉላ ቤትም በገባን ጊዜ ‹እኔ እኅትህ ስሆን ለአንተ እንዴት አጋቡኝ› አለችኝ፡፡ እኔም የምትፈቅጂ ከሆነ ድንግልናችንን ጠብቀን በአንድነት እንኑር ይህንንም በመካከላችን ያለውን ምሥጢር የሚያውቅ ማንም አይኑር አልኳት፡፡ በዚህም ተስማምተን በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ አልጋ እየተኛን አንድ መጎናጸፊያም እየተጎናጸፍን 48 ዓመት ያህል ኖርን፡፡ ይህንንም ሥራችንን ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ እኔም እርሷ ሴት እንደሆነች አላወቅኋትም እርሷም እኔን ወንድ እንደሆንኩ አታውቅም፡፡ በየሌሊቱም ሁሉ በንስር አምሳል ወደ መኝታ ቤታችን እየገባ ክንፎቹን አልብሶን ያድራል ሲነጋም ከእኛ ይሠወራል›› አላቸው፡፡
ቅዱስ ድምጥሮስ መንፈስ ቅዱስ አድሮባልና የብሉይና የሐዲሳትን መጻሕፍት ሁሉ አንብቦ ተረጎማቸው፣ ምሥጢራትም ተገለጡለት፡፡ ባሕረ ሀሳብ የተባለውንም ድንቅ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ሠርቶ ያዘጋጀው ይህ ቅዱስ ድሜጥሮስ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህ ጻድቅ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የቀመረውን ይህን የድሜጥሮስን ቀመር በሚገባ እየተጠቀመችበት ነው፡፡ በዚህ የቀን አቆጣጠር ቀመር መሠረት የደብረ ዘይት፣ የሆሳዕና፣ የትንሣኤና የጰራቅሊጦስ በዓላት ሁልጊዜ በየዓመቱ ከእሁድ አይወጡም፡፡ ስቅለትም ሁልጊዜ ከአርብ አይወጣም፡፡ የጌታችን የዕርገቱም በዓል ከሐሙስ አይወጣም፡፡ ቀመሩንም አዘጋጅቶ ሲጨርስ ለኢየሩሳሌም፣ ለሮሜ፣ ለኤፌሶንና ለአንጾኪያ አገሮች ላከላቸው፡፡ ጻድቁ አርጅቶና ሸምግሎ በደከመ ጊዜም ሕዝቡ በአልጋ ላይ አስቀምጠው ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ያደርሱትና ያስተምራቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ በተወለደ በ115 ዓመቱ ጥቅምት 12 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፏል፡፡
የቅዱስ ድሜጥሮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን አሜን፡፡
https://t.me/MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 12-ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ድንግልና ንጹሕ የዋሕ የሆነ ተካሌ ወይን የተባለ ቅዱስ ድሜጥሮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለቅዱስ ዳዊት ጎልያድን የሚገድልበትን ልዩ ኃይል ሰጥቶታል፡፡   
+ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ቅዱስ ዳዊትን በሳኦል ፈንታ እንዲሾመው ለሳሙኤል የነገረበት ዕለት ነው፡፡      
የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዚህች ዕለት ወደ ነቢዩ ሳሙኤል ዘንድ ተልኮ የዳዊት አባት ወደሆነው በቤተልሔም ወደሚኖር ወደ እሴይ ቤት ሄዶ በሳኦል ፈንታ ቅዱስ ዳዊትን ያነግሠው ዘንድ አዘዘው፡፡ ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሄዶ ‹‹ልጆችህን ሁሉንም አቅርብልኝ›› አለው፡፡ እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉንም አቀረባቸው፡፡ እርሱ ዳዊት በእርሻ ውስጥ በጎችን ይጠብቅ ነበርና፡፡
ሳሙኤልም የመንግሥት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ላይ ከፍ ከፍ ባደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም፡፡ ነቢዩ ሳሙኤልም እሴይን ‹‹ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸውን?›› ብሎ የጠቀው፡፡ እሴይም ‹‹በጎች የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ›› አለው፡፡ ሳሙኤልም ደግሞ እሴይን ‹‹እርሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው›› አለው፡፡ እሴይም ዳዊትን ልኮ አስመጣው፡፡  መልኩም ቀይ፣ ዐይኖቹ የተዋቡ፣ አርአያውም ያማረ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ‹‹ይህ ይበልጣቸዋልና ተነሥተህ ቅባው›› አለው፡፡ በዚያም ጊዜ ሳሙኤል ለዳዊት የመንግሥት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው፡፡ ከዚያችም ቀን ጀምሮ ሁልጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ አደረበት፡፡ በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ፡፡
የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው አይለየን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ፡- የመጀመሪያ ስሙ ሌዊ ሲሆን በቀድሞ ሥራውም ቀራጭ (ባንክ መንዛሪ) ነበር፡፡ ግብር ከሚያስገብርበት ቦታ ተቀምጦ እየቀረጠ ሳለ ነው ጌታችን በአጠገቡ አልፎ ‹‹ሌዊ ተከተለኝ›› ብሎ የጠራው፡፡ እርሱም ሳያቅማማና ሳያመነታ ወዲያው ተነሥቶ ተከተለው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ጌታችን ቀድሞ በነቢያት የተነገረለት መሢሕ መሆኑን ለማስረገጥ ሲል አንድን ታሪክ ከጻፈ በኋላ ‹‹በዚህም… ተብሎ በነቢይ የተነገረው (የተጻፈው) ተፈጸመ›› ብሎ ይመሰክራል፡፡ ከፍልስጤም ተነሥቶ በእስያ አድርጎ ደቀ መዝሙሩን ማርቆስንና ሌለቹን በግብፅ ትቶ እርሱ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ መጥቶ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ብዙ ሀገሮች ተዘዋውሮ ወንጌልን ከሰበከ በኋላ ወደ ካህናት አገር ደረሰ፡፡ አንድ ወጣትም አግኝቶ ወደ ከተማው እንዴት እንደሚገባ ጠየቀው፡፡ ወጣቱም ‹‹ራስህንና ጺምህን ተላጭተህ በእጅህ ዘንባባ ይዘህ ካልሆነ መግባት አትችልም›› አለው፡፡ ይህም ነገር ቅዱስ ማቴዎስን እያስጨነቀው እያለ ያ መጀመሪያ ያገኘው ወጣት ቅዱስ ማቴዎስን በስሙ ጠራው፡፡ ማቴዎስም በስሙ ስለጠራው ደንግጦ ‹‹ስሜን ወዴት ታውቀዋለህ?›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹እኔ ጌታህ ኢየሱስ ነኝ፣ አሁንም እንደነገርኩህ አድርግ እኔም ከአንተ ጋር አለሁ ከአንተም አልርቅም›› አለው፡፡ ማቴዎስም እንደታዘዘው ራሱንና ጺሙን ተላጭቶ በእጁም ዘንባባ ይዞ ወደ ከተማዋ ገባ፡፡ እንደገባም ለአማልክት ካህናት አለቃቸው የሆነውን አርሚስን ተገናኘውና ከእርሱ ጋር ስለ አማልክቶቻቸው አወራ፡፡ ድንቅ ተአምርንም በማድረግ ጣዖቶቻቸውን አቃጠላቸው፡፡ አርሚስንና የአገሩንም ሰዎች ሁሉ አስተምሮ በማሳመን አጠመቃቸው፡፡ ከሰማይም ማዕድ አውርዶ መግቧቸዋል፡፡

የሀገሩም ንጉሥ ይህን ሲሰማ እጅግ ተቆጥቶ ቅዱስ ማቴዎስንና አርሚስን እሳት ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ፈወሳቸው፡፡ ንጉሡም የሚያሠቃይበትን ነገር ሲፈልግ ድንገት ልጁ ሞተ፡፡ ማቴዎስም ንጉሡን ‹‹ልጅህን ከሞት እንዲያነሡት ወደ አማላክትህ ለምን አትለምንም?›› አለው፡፡ ንጉሡም ‹‹አማልክት እንዴት የሞተን ያስነሣሉ›› ብሎ መልሶ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስም ‹‹ብታምን ግን የእኛ አምላክ የሞተውን ልጅህን ያስነሣልሃል›› አለው፡፡ ንጉሡም ‹‹ልጄ ከሞት ከተነሣ በአምላክህ አምናለሁ›› አለው፡፡ ማቴዎስም ወደ ጌታችን ከጸለየ በኋላ ልጁን ከሞት አስነሣው፡፡ ይህንንም ያዩት ንጉሡና የሀገሩ ሰዎች በጌታችን አመኑ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው አገልጋዮችን ሾመላቸውና ወደ ሌላ አገር ሄደ፡፡ በዚያም አስተምሮ ብዙዎችን አሳምኖ እንዲጠመቁ በማድረጉ አገረ ገዥው ማቴዎስን ይዞ አሠረው፡፡
በአሥር ቤትም አንድን የሚያሳዝን ሰው ተጨንቆ ሲያለቅስ አገኘው፡፡ ምን እንደሆነም ሲጠይቀው የጌታው ብዙ ገንዘብ ከባሕር ውስጥ እንደሰጠመበት ነገረው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስም ያንን ምስኪን ገንዘቡን ከባሕሩ ዳርቻ እንደሚያገኘውና ወደ ወንዙም ሄዶ ገንዘቡን ወስዶ ለጌታው እንዲሰጠው ነገረው፡፡ ሰውየውም ወደ ባሕሩ ሲሄድ ማቴዎስ እንደነገረው ገንዘቡን ከባሕሩ ዳርቻ አገኘው፡፡ ይህንንም ያዩ የሀገሩ ሰዎች በጌታችን አመኑ፡፡ አገረ ገዥውም ይህን ሲሰማ በቁጣ ገንፍሎ ቅዱስ ማቴዎስን ጥቅምት 12 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ሰውነቱንም ብዙ ቦታ ቆራርጦ ሥጋውን ለሰማይ ወፎች ሰጠው፡፡ ምእመናንም ሥጋውን በሥውር ወስደው በመልካም ቦታ አኖሩት፡፡ ከሥጋውም ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡
የወንጌላዊው የቅዱስ ማቴዎስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + +
ቅዱስ ድሜጥሮስ ተካሌ ወይን፡- ዲሜጥሮስ ማለት ‹‹መስተዋት›› ማለት ነው፡፡ ይህም ታላቅ ጻድቅ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 12ኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ነው፡፡ ከአባቱ ከአርማስቆስና ከእናቱ ኢላርያ መጋቢት 12 ቀን ተወለደ፡፡ አስቀድሞ መጻሕፍትን ያልተማረ ሕዝባዊ ገበሬ ስለነበር በወላጆቹም የወይን አትክልት ቦታዎች ይሠራ ነበር፡፡
በትንሽ ዕድሜውም ልዕልተ ወይን የምትባል ሚስት አጋቡት፡፡ እርሷም የአጎቱ ልጅ ነበረች፡፡ ባልና ሚስት ሆነው በአንድ አልጋ አብረው እየተኙ ነገር ግን በግብር ሳይተዋቁ መልአክ እየጋረዳቸውና እየጠበቃቸው ለ48 ዓመታት አብረው ኖሩ፡፡ ድንግልናቸውን ንጽሕናቸውን እየጠበቁ ሲኖሩ ይህንን ምሥጢራቸውን ከእግዚአብሔር በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፡፡ ከሐዋርያው ማርቆስ ቀጥሎ በእርሱ መንበር 11ኛው ሊቀ ጳጳሳት የነበረው አቡነ ዮልዮስ ዕረፍቱ በደረሰ ጊዜ መልአክ ተገልጦለት ‹‹ነገ የወይን ዘለላ ይዞ ወደ አንተ የሚገባ ሰው አለ፣ ከአንተ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት የሚሆነው እርሱ ነውና ያዘው›› አለው፡፡ በዚያችም ቀን ድሜጥሮስ ወደ አትክልቱ ቦታ ገብቶ ሳለ ያለጊዜዋ ያፈራች የወይን ዘለላ አገኘ፡፡ እርሱም ‹‹ይህችንስ የወይን ዘለላ ለሊቀ ጳጳሳቱ ሰጥቻቸው በረከት እቀበልባታለሁ›› ብሎ አሰበና ወደ አባ ዮልዮስ ዘንድ ይዞ ሄደ፡፡ በመንገድም ሳለ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ዮልዮስ ዐርፈው ጳጳሳቱና ሕዝቡ ሊቀብሯቸው ሲወስዷቸው አገኛቸው፡፡ እርሳቸውም ከማረፋቸው በፊት ከእርሳቸው በኋላ ማን እንደሚሾም ለሕዝቡ ምልክት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ይኸውም ‹‹ያለጊዜዋ ያፈራች የወይን ዘለላ ይዞ የሚመጣውን ሰው በእኔ ቦታ እንድትሾሙት የእግዚአብሔር መልአክ አዞኛል›› ብለው ነግረዋቸው ስለነበር አሁን ሊቀብሩ ሲወስዷቸው ድምጥሮስን ያለጊዜዋ ያፈራች የወይን ዘለላ ይዞ ሲመጣ አገኙትና ከቀብራቸው በኋላ ወስደው በሐዋርያው በቅዱስ ማርቆስ መንበር 12ኛው ሊቀ ጳጳሳት አድርገው በተወለደበት ዕለት መጋቢት 12 ቀን ሾሙት፡፡ከሹመቱ በኋላ በቍርባን ጊዜ

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር
***
በብዙ መልካም የሆነ ሰውን አንድ ክፉ ነገር ብናይበት ብዙ መልካም ነገሩን ሳይሆን ክፉ ነገሩን አይተን ጉድለት ይሰማናል። አእምሯችን ነጭ ወተት ላይ አንዳረፈ ዝንብ ክፉውን ትኩረት ሰጥቶ ያያል፤ ልባችንም መውደድ ይከብደዋል። ይህ ግን የሥጋ እውቀትና ግብር ነው።
እግዚአብሔር እንደዚህ ቢሆን ኖሮ መወደድ እና መዳን አይገኝም ነበር። በእርሱ ዓይን ብዙ ክፋታችን የተገለጠ ነውና። ነገር ግን እርሱ መልካም ስለሆነ በኃጢአት እየኖርን ጠላቶቹ እያለን ወደደን፤ ያውም እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር። ለዚህ ቸርነትና ፍቅር አንክሮ ይገባል! (ሮሜ. 5፥10)
ይህ አምላካዊ ቸርነት በእኛ ዘንድ ለእምነት፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ምንጭ ነው። እምነት ማለት ሳይገባን ክፉዎች ሆነን የወደደን እና ቀድሶ እና አክብሮ መልካም ልጆቹ ያደርገን ዘንድ ወደ እርሱ የጠራን አምላክ መኖሩን ተረድቶ በእርሱ ታምኖ መኖር ነው። ከዚህም ምሥጋና እና ደስታ ይወጣል። (ዮሐ. 14፥1)
ፍቅር ደግሞ በሥራ እግዚአብሔርን መምሰል ነው፤ እሱ ያለ ጥቅም እና ማዳላት ሁሉን ይወዳልና፤ ጠላቶች ሆነን ሳይቀር ወዶናልና። በእኛ ውስጥ ያለውን ክፋት አይቶ ሳይተወን መልካም አድርጎ መፍጠሩን አስቦ ሊያድነን መጥቷልና።
ተስፋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና ርስትን እየጠበቁ መከራን መታገስ እና የክርስቶስን መምጣት መጠበቅ ነው። እኛን ያድን ዘንድ አንድያ ልጁን ለመከራ አሳልፎ የሰጠ መልካሙ እረኛችን እና አባታችን የማይሰጠን ምን ነገር አለ? የሚጠቅመንን እና ቃል የገባልንን ሁሉ ይሰጠናል። (ሮሜ. 8፥32)
ፍቅር ግን ከሁሉም ይበልጣል አለ ሐዋርያው። እውነተኛ ፍቅር ያለው ሰው ሕግን ሁሉ ፈጽሟልና። (1ኛ ቆሮ. 13፥13)

( በረከት አዝመራው )

@MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


🕰🔔

11:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


🕰🔔

9:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡

"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡

አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ለመዳን፣ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ

@MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:25


🕰🔔

6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:24


#የፍቅር #ትርጓሜ  አንብቡት

🥀ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል።
                   
                   https://t.me/MoaeTewahedoB 
🥀ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል።
                    
              https://t.me/MoaeTewahedoB  
🥀ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን🤲
  
አስተማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት ቴሌግራም
  ተቀላቀሉ
https://t.me/MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:24


🕰🔔

3:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:24


ውዳሴ ማርያም በግዕዝ ትርጓሜ
የእለተ ሰኞ ውዳሴ ማርያም

https://t.me/MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:24


🥰

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:24


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 11-ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ግዝትህን አንሣ" ብሎ እስካዘዛቸው ድረስ የዓባይን ወንዝ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ በጸሎታቸው ገዝተው ያቆሙት የውቅሮው አቡነ ኤልያስ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ በአንጾኪያ አገር አስቀድማ በኃጢአት ትኖር የነበረችውና በኋላም በንስሓ የተመለሰችው ገድለኛዋ ቅድስት ጲላግያ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ያዕቆብ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ቅዱስ አባት አርዮሳውያን መናፍቃን በተደጋጋሚ እያሳደዱት በስደት ደሴት ላይ ሰባት ዓመት የኖረ የሃይማኖት አርበኛ ነው፡፡ ስለቀናች ሃይማኖቱ ብዙ መከራን ተቀብሏል፡፡  ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!      

ቅድስት ጲላግያ፡- ከአንጾኪያ አገር የተገኘች ቅድስት ናት፡፡ ወላጆቿ የማያምኑ ከሃድያን ናቸው፡፡ እርሷም አስቀድማ ከረከሰች ሃይማኖቷ ጋር በረከሰ ሥራ ጸንታ ጸንታ መኖርን ገንዘብ ያደረገች ነበረች፡፡ በመሸ ጊዜ በጨዋታ ቤት በመዋል ስትሣለቅና ስትዘፍን ስታመነዝርም ኖራለች፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ የረከሰ ሕይወት ውስጥ ከኖረች በኋላ ግን ከዕለታት በአንደኛው ቀን የገሀነም እሳትና የዘላለም ሥቃይን እንደሚጠብቃቸው እያሳሰበ ዝንጉዎችንና አመንዝራዎችን ሲገሥጻቸው ኤጲስቆጶስ ጳውሎስን ሰማችውና ምክሩን በልቧ አሳደረች፡፡

ከዚህም በኋላ ቅድስት ጲላግያ ሲያስተምር ወደሰማችው ኤጲስቆጶስ ጳውሎስ ዘንድ ሄዳ  የሠራችውን ኃጢአቷን ሁሉ ተናዘዘች፡፡ እርሱም አጽናንቶ የቀናች ሃይማኖትን አስተማራትና ከነበረችበት የእርኩሰት ሕይወት አወጣት፡፡ አስተምሮ ካሳመናትም በኋላ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት፡፡ እርሷም በቀደመው ክፉ ሥራዋ እየተጸጸተች በጾም፣ በጾሎት፣ በስግደትና በመልካም ሥራዎች ሁሉ እየተጋች ሰውነቷን ማድከም ጀመረች፡፡ ተጋድሎዋንም ለማብዛት ባሰበች ጊዜ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ የከበሩ ቅዱሳት ቦታዎች ሁሉ ተሳልማ ሰገደችና ወደ ኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ዘንድ ሄደች፡፡ እርሱም ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ ወደሚገኘው የደናግል ገዳም አስገባት፡፡ እርሷም የምንኩስናን ልብስ ለብሳ በጽኑ ገድል ተጠምዳ 30 ዓመት ኖረች፡፡ እግዚአብሔርንም እያገለገለች በጽኑ ተጋድሎ ኖራ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈች፡፡       
ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን!      
+ + + + +

አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮ፡- አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮ የትውልድ ሀገራቸው አክሱም ነው፡፡ የአቡነ አረጋዊ 3ኛ የቆብ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው ውቅሮ የሚገኘው የጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ቤተ መቅደስ አጣኝ ነበሩ፡፡ ይህ ጻድቅ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ገድል አላቸው፡፡ በቀን 548 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን እየጸለዩ 666 ጊዜ ይሰግዱ ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዓባይ የሀገራችንን አፈርና ዛፉን ሁሉ ጠራርጎ ሲወስድ ቢመለከት ድምጹን ከፍ አድርጎ ኦ አባይ አይቴ ተሐውር ወለመኑ ተሐዲጋ ለኢትዮጵያ ብሎ ሲዘምር ዓባይ ቀጥ ብሎ ቆሟል፡፡ መልአኩም ወዲያው መጥቶ ‹‹ለምን ትደክማለህ? ለምንስ ተፈጥሮን ትከለክላለህ? ሕጉን አታፍርስ›› ሲለው ቅዱስ ያሬድ ደንጎጦ ‹‹አጥፍቻለሁ ዓባይ ሆይ ሂድ የተፈጥሮ ግዴታህን ፈጽም›› ብሎ አሰናብቶታል፡፡ የኢትዮጵያ ብርሃኗ ቅዱስ ያሬድ በዜማው ዓባይን ቀጥ አድርጎ እንዳቆመው ሁሉ አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮም በጸሎታቸው ዓባይን ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ አድርገውት ነበር፡፡

ታቦተ አብርሃ ወአጽብሓን ይዘው ከኢትዮጵያ ጠረፍ ዳር ኑብያ ሄደው ድንጋይ ከዓባይ ዳር ደርድረው ታቦቱን አስቀምጠው ሥዕለ ማርያምን አድርገው መሥዋዕት ሰውተው ‹‹ዓባይ ከኢትዮጵያ እንዳትወጣ ገዝቼሃለሁ›› ሲሉት ዓባይም ተመልሶ ቆሟል፡፡ ዓባይ ምድረ ኑብያን ሲያጥለቀልቃት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ ‹‹ለምን የእግዚአብሔርን ስነ ፍጥረት ታስጨንቃለህ?›› ብሎ ተቆጣቸው፡፡ ጻድቁም ‹‹ውኃው ይሂድ ግን ዛፉን አፈሩን ይዞ ከኢትዮጵያ አይውጣ›› ብለው መልአኩን ጠየቁት፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ‹‹ውኃ ሲሞላ ዛፉን ቅጠሉን ይዞ መጓዙን እንዴት ትረሳዋለህ? የጸሎት ጊዜህ ደርሷልና ወደ በዓትህ ተመለስ›› ብሎ በቁጣ የእሳት ሰይፉን ሲያዛቸው ግዝታቸውን አንሥተው ታቦታቸውን ይዘው ወደ በዓታቸው ውቅሮ ተመልሰዋል፡፡ አባቶቻችን እንዲህ ናቸው እንኳን ሃይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ስብዕና ማንነታችንን ይቅርና የሀገራችንን አፈር እንኳን ለባዕድ አሳልፈው የማይሰጡ ቅዱሳን ጻድቃን ነበሩ፡፡ የአባ ኤልያስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን አሜን፡፡
https://t.me/MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:24


🕰🔔

3:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:23


የመስቀል ዓይነቶች
https://t.me/MoaeTewahedoB

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

21 Jan, 00:23


የአሀት አቢያተ ክርስቲያናት አባቶች በጋራ ሲጸልዩ💖
https://t.me/MoaeTewahedoB

11,357

subscribers

3,305

photos

168

videos