[መንሀጁል አንቢያዕ]

@menhajualanbiya


قال ابن القيم: ( والجهاد بالحجة واللسان مقدم على الجهاد بالسيف والسنان )"
🔺ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ በመረጃ ና በአንደበት ትግል ማድረግ በሰይፍ ና በመሳሪያ ትግል ከማድረግ ቀዳሚ ነው አሉ!!
📜 مقدمة منظومته الكافية الشافية ص/ 19

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:23


ተጀምሯል
التصفية والتربية
አት-ተስፊየህ ወ'ተርቢየህ (ተከታታይ ሳምንታዊ የእሁድ ኮርስ)
ሊሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

ገባ ገባ 👇👇👇 በሉ
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=66cecb17ebc3ddb68a

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:23


👉የነገ እሁድ ኮርስ አለ
ደርሱም👇👇 እንደተጠበቀ ነው

የዳር አስ-ሱንና ሳምንታዊ የእሁድ ደርስ እንደተጠበቀ ሆኖ ሸይኽ ሑሰይን መደበኛ ሳምንታዊ ኮርሳቸውን ይቀጥላል። ከኮርሱ በኋላ ደርስ ስለሚቀጥል በጊዜ ይገኙ!

ዘውትር እሁድ 3:30 እስከ 6:00 የሚሰጡ ት/ቶች

1, አት-ተስፊየህ ወ'ተርቢየህ (ተከታታይ ሳምንታዊ የእሁድ ኮርስ)
ሊሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

2,  አል ኢርሻድ ኢላ ሶሂህ አል ኢዕቲቃድ
ሊሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ)
በሸይኽ አህመድ አወል (ሀፊዘሁላህ)

ከአሱር በኋላ
1, ሸርሁ ከሽፍ አሽ-ሹብሃት በኢብኑ ዑሰይሚን ሸርህ

2, ሶርፍ

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
አዲስ አበባ አለምባንክ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:22


ኢስቲግፋር
——
ኢብን ተይሚያህ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:-
"ኢስቲግፋር፣ ከወንጀል ወደ አላህ ተፀፅቶ መመለስ ባሪያውን ከተወገዘ ተግባር ወደሚወደድ ተግባር  ከጎደሎ ስራ ሙሉ ወደሆነ ስራ ያስወጠዋል። ባሪያውን ከዝቅተኛ ደረጃ ወደ ከፍተኛና ሙሉ ወደ ሆነ ደረጃ ያስወጠዋል። አላህን አምላኪና በአላህ ላይ አዋቂ የሆነ ሰው፣ በሁሉ ቀንና ሰዓት ይልቁንም በሁሉም ቅፅበት በአላህ ላይ  ያለው እውቀት ይጨምራል።
[አል ፈታዋ 11/696]
✍🏻ኢብን ሽፋ #join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:22


ተጀምሯል

صريح السنة
للإمام أبي جعفر محمد بن جرير الطبري رحمه الله
ሶሪህ አስ-ሱንና
ሊል ኢማም አቢ ጀዕፈር ሙሀመድ ኢብኑ ጀሪር አጥጦበሪ የሞቱት በ310 ዓ.ሂጅራ ነው

በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

ዘውትር:- ቅዳሜና እሁድ፣ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

👇ገባ ገባ 👇 በሉ
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=c342e75ead2d25f064

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:21


ተጀምሯል     

منظومة البيقونية
መንዙመቱ'ል በይቁኒየህ
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ (ሀፊዘሁላህ) ሸርህ ይደረጋል

ቀን:- ዘውትር ሐሙስና ጁምዓ
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ


ገባ 👇ገባ 👇በሉ

https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=d3036bcccc0f150dbb

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:20


ተጀምሯል

خلق أفعال العباد والرد على الجهمية وأصحاب التعطيل
للإمام محمد ابن إسماعيل البخاري رحمه الله
ኸልቁ አፍዓል አል'ዒባድ

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ (ሀፊዘሁላህ)
👇👇👇ገባ ገባ በሉ
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=2dee5824a56a6ffccc

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:19


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:18


የየመኑ ሙሀዲስ ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ) እንዲህ ሲሉ ይመክራሉ:-

“በሱንና ላይ ታገስ አንተ ሱኒይ ሆይ!
በድህነት ላይ ታገስ አንተ ሱኒይ ሆይ!
ታገስ! አላህ እንዲህ ብሏል:-

تِلْكَ الدَّارُ الْآخِرَةُ نَجْعَلُهَا لِلَّذِينَ لَا يُرِيدُونَ عُلُوًّا فِي الْأَرْضِ وَلَا فَسَادًا ۚ وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ

«ይህች የመጨረሻይቱ አገር ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመፅን ለማይፈልጉት እናደርጋታለን፡፡ ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡» አል ቀሶስ 83

ታገስ! በድህነትና በሱንና ላይ ታገስ!!

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:15


የመፅሃፍ pdf 👉 አጭር ናት ትነበብ!

ርእስ:- ጥቅል የሆነ አንገብጋቢ ምክር

አዘጋጅ:- አል ኢማም ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ)

ትርጉም:- ኢብን ሽፋ

የተርጓሚው መግቢያ
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
ምስጋና ለዓለማቱ ብቸኛ ተማላኪ ከርሱ በቀር በእውነት ሊመለክ የሚገባው የሌለ ለሆነው ጌታችን አላህ ይሁን!፡፡
የአላህ ሰላምና ውዳሴ በረከት፤ ለዓለም መደምደሚያ ነቢይ ሆነው በተላኩት የመጨረሻው ነቢይ፤ ነቢዩ ሙሀመድ ላይና በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው የእነሱንም መንገድ በትክክል እስከ እለተ-ትንሳዔ በተከተሉት ላይ ይስፈን!!

ይህቺን ታላቁ ዓሊም ኢማሙ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) ራሷን በቻለች መልኩ ከሌሎች ኪታቦች ሳትያያዝ አጠር አድርገው ያዘጋጇትን በራሪ ወረቀት (Pamphlet) ተርጉሜ በሶፍት ኮፒ/PDF ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ፤ አጠር ያለች ሆነ ሁሉን አካታች መሆኗ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም አንብቧት ቆም ብሎ ራሱን ከፈተሸባት እጅግ በጣም ጠቃሚ ሆና ያገኛታልና በተቻል መጠን ሁሉም አንብቦ ለሌሎችም ያሰራጫት፡፡
እርምት ወይም አስተያየት ያለው በዚህ አድራሻ መጠቀም ይችላል፡- [email protected]

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:15


ለሶላት ጥሪ (አዛን) እየተደረገ ወደ መስጂድ የማይሄድን ሰው የሚመለከት ብይን!
—————
ጥያቄ:- አዛን እየሰማ ወደ መስጂድ መሄድ ሳይፈልግ ቀርቶ ሁሉንም ሶላቶች ቤትና የስራ ቦታ ላይ የሚሰግድ ሰው ብይኑ ምንድነው?!

መልስ: ከታላቁ ዓሊም አል ኢማም ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ):-
ይህ አይፈቀድም!። በርሱ ላይ ግዴታ የሚሆነው የሶላት ጥሪን አክብሮ መሄድ ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “የሶላት ጥሪ ሰምቶ ያለ (ሸሪዓዊ) ምክንያት ወደ መስጂድ ያልመጣ ሰው ለርሱ ሶላት የለውም።” ኢብኑ ማጀህ፣ ዳራ ቁጥኒና ኢብኑ ሂባን በሶሂህ ሰነድ ዘግበውታል። ለኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ምክንያት ሲባል ምን አይነት ምክንያት ነው? ተብሎ ተጠየቀ፣ "ፍርሃት ወይም መታመም ነው" ብሎ መለሰ።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ ዐይኑ የማይመለከት አንድ ሰው መጣና የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ወደ መስጂድ እየመራኝ የሚወስደኝ ሰው የለምና ቤቴ ውስጥ እንድሰግድ ሸሪዓው የሚያገራልኝ ነገር አለን? አላቸው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉት:- “የሶላት ጥሪ (አዛን) ትሰማለህን? አዎን አላቸው፣ ጥሪውን እሺ በል (ወደ መስጂድ ሂድና ስገድ) አሉት።” ሙስሊም ዘግበውታል።

ዐይኑ ማየት የማይችልና ወደ መስጂድ እየመራ የሚወስደው የሌለው ሰው ላይ ግዴታ ከሆነ በሌላው ላይ ይበልጥ ግዴታ ይሆናል።

በሙስሊሞች ላይ ግዴታ የሚሆነው ሶላትን በጊዜው መስጂድ በጀመዓ በመስገድ ላይ መሽቀዳደም ነው። ቤቱ ሩቅ ሆኖ የሶላት ጥሪ (አዛን) የማይሰማ ከሆነ ግን ቤቱ ቢሰግድ ችግር የለውም። ችግሩን ተቋቁሞ በትግስት ጀመዓ ወዳለበት መስጂድ ሄዶ መስገድ ከቻለ ይህ ለርሱ ጥሩና በላጭ ነው።
[ኢብኑ ባዝ: ፈታዋ ዓጂለህ 46]

ብይኑ ሴቶችን አይመለከትም!። ለሴቶች በላጩ ቤታቸው መስገድ ነው!።
ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:12


እስልምና ሁሌም በየትኛውም ጊዜ የበላይ እንደሆነ ታውቃለህ?!
—————
እስልምናን ከሌሎች ሀይማኖቶች ሁሉ የበላይ ሀይማኖት እንደሚያደርገው ቃል ገብቷል፣ የበላይም ነው!!። በተለያየ ጊዜ መልኩን ቀያይሮ የተለያየ ፈተና ይደርሳል፣ ታዲያ ወደ ራሳችን መመለስና ጠንክረን የበለጠ ለመታገል ዝግጁ መሆን ነው እንጂ በጭራሽ መስነፍና የሞራል መውረድ የሚባል ነገር ሊኖር አይገባም። በአላህ ላይ ተመክቶ በፅናት የሚታገል ትውልድ ለዲኑ በመታገሉ ሰበብ የበላይነት እንደሚጎናፀፍም አላህ ቃል ገብቷል:-

وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

«እናንተም የበላዮች ስትሆኑ ምእመናን እንደሆናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡» አል ዒምራን 139

እስልምና ተረገጠ የበታች ሆነ አትበል! እኛ ላይ ነው በሙስሊምነታችን የተለያዩ ወንጀሎችን በመዳፈራችን ሰበብ፣ ተውሒድን ትተን ሺርክን ስንመርጥ፣ በስመ ሙስሊምነት ውስጥ ሆነን ከኩፋሩ ጋር የኩፍር ተግባር ስንፈፅም፣ የሰዎችን ውዴታ ፈልገን አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ስንፈፅም፣ ከአላህና ከመልእክተኛው ትእዛዝ በማፈንገጣችን፣ ሀላሉን ርቀን ሀራሙን በመዳፈራችን፣ ሱንናን ትተን ቢድዓን ስንመርጥ ነው እኛው ራሳችን የባታች የምንሆነውና የምንረገጠው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ አስቀድመው “ውርደት እና ክብረቢስነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ሆነች” ብለው ነግረውናል፡፡
እስልምናማ ሁልጊዜም ከሁሉም ሀይማኖት የበላይ የሆነ ድንቅ ሀይማኖት ነው!!። የበላይ ስለሆነም ነው በማስረጃ መርታት ስለማይችሉ ጡንቻ ባገኙበት አጋጣሚ ተከታዩን በተለያየ ምክንያት እያደረጉ ጡንቻቸውን የሚያሳዩት። እስልምናን በሀሳብ መርታት ፈፅሞ! አይቻልም!፣ እስልምናን በእውቀት ሀይል መርታት ቅዠት እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ!!። ዓለም ላይ አትመለከትም እንዴ በሆነች አጋጣሚ በሀሳብ በውይይት በእውቀት ሲፋለሙ ምን ያህል ህዝብ እንደሚሰልም?? እስልምና አውሮፓን ያለ አንዳች ሀይል በእውቀት በማስተማር እያጥለቀለቃት አይደል እንዴ?!። እስልምናን በምንም መልኩ ማሸነፍ ስለማይቻል እስልምና ሁልጊዜም ከሌሎች ሀይማኖቶች የበላይ ነው!!።

እኛም ከሁሉ ሀይማኖት በላይ የሆነውን እስልምናን ይዘን ክብራችን ያልተጠበቀበትን ምክንያት ራሳችን ጋር ፈትሸን ችግሩን ለመቅረፍ እንጣር እንጂ አላህ እስልምናን ሁልጊዜም የበላይ ሀይማኖት እንደሚያደርገው ቃል ገብቷል። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-  «አላህ ‘እስልምናን’ ከሁሉም ሀይማኖት በእውቀትና ግልፅ በማድረግ የበላይ እንደሚያደርገው ቃል ገብቷል፣ እንዲሁም የሰይፍና የመሳሰሉ ነገሮችንም የበላይነት እንደሚያጎናፅፈው ቃል ገብቷል፣ ከሁሉ በላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል:

﴿هُوَ الَّذي أَرسَلَ رَسولَهُ بِالهُدى وَدينِ الحَقِّ لِيُظهِرَهُ عَلَى الدّينِ كُلِّهِ وَلَو كَرِهَ المُشرِكونَ﴾ التوبة ٣٣

እርሱ ያ: አጋሪዎች ቢጠሉም መልእክተኛውን (ሙሀመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛው ሀይማኖት ላይ ከሀይማኖቶች ሁሉ የበላይ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው።” አትተውባ 33» [አልጀዋቡ ሶሂህ 1/239]

በድጋሚም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል:- «በማስረጃዎችና በእውቀት በተመሰረቱ እውነት እንደሆነ ግልፅ በሚያደርጉ ምልክቶች የበላይ ያደርገዋል፣ በድጋሚም በተቃራኒዎቹ ላይ በመርዳትና በማጠናከር የበላይ ያደርገዋል። እውነተኛ ሀይማኖትና ቅን መንገድ እንደሆነ ግልፅ እንዲያደርገው የበላይነቱ በእውቀትና በምላስም ይሆናል፣ የተረዳና ጠንካራ እንዲሆንም በእጅና በመሳሪያም የበላይ ይሆናል።» [አልጀዋቡ ሶሂህ 3/103]

እራሳችን ዘንድ ያለውን ችግር እናርም! ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት እናሳምር፣ አላህ እና መልእክተኛው ﷺ ያዘዙንን እንታዘዝ፣ ከከለከሉን ነገር ሁሉ እንቆጠብ! የምር መልእክተኛውን የምንወድና በመልእክተኛው አማኝ ከሆንን የአይሁድና ክርስቲያኖችን ፋና ትተን እውነተኛውን የመልእክተኛው ﷺ ፋና እንከተል!! ይህን ጊዜ የበላይነት ይመጣል።
ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:12


ተጀምሯል

صريح السنة
للإمام أبي جعفر محمد بن جرير الطبري رحمه الله
ሶሪህ አስ-ሱንና
ሊል ኢማም አቢ ጀዕፈር ሙሀመድ ኢብኑ ጀሪር አጥጦበሪ የሞቱት በ310 ዓ.ሂጅራ ነው

በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

ዘውትር:- ቅዳሜና እሁድ፣ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

👇ገባ ገባ 👇 በሉ
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=87a11e3c66265d9e43

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:12


https://chat.whatsapp.com/KCFZHu72EeuEEmVfq9aTor

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:12


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ የአል-ኢስላሕ መድረሳ ሳምንታዊ የእሑድ ደርስ ተከታታዮች:-
ዘወትር እሑድ በየሳምንቱ የሚሰጠው የኪታብ ቂርኣት ደርሳችን በሰዓቱ የሚቀጥል  ይሆናል።

1. የተፍሲር አስሰዕዲ ማብራሪያ (ሰአት ከ 2:30 እስከ 3:30)
በኡስታዝ አቡ ሐመውያ ሸምሱ ጉልታ ሐፊዘሁሏህ

2. ሙቀዲመቱል ኣጁሩሚየቲ ፊ ነሕው (ሰአት ከ 3:30 እስከ 4:00)
በኡስታዝ ዐብዱሶመድ ሙሐመድ ሐፊዘሁሏህ

3. አልሐቁል አውከድ ዐላ ጀሚዒል ዒባድ (ሰአት ከ 4:00 እስከ 5:00)
በኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን ሐፊዘሁሏህ

4. አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ (ሰአት ከ 5:00 እስከ 6:00)
  በኡስታዝ በሕሩ ተካ ሐፊዘሁሏህ


https://t.me/medresetulislah?livestream

አል ኢስላሕ መድረሳ
t.me/medresetulislah

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:10


ኮንፈረንሱ የሚካሄድበት ቀን መተላለፉን ስለማሳወቅ

ጥቅም 3 አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ኮንፈረንሱ የሚካሄድበትን ጊዜ ወደ ፊት የምንገልፅ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናስታውቃለን።

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:10


ቀጥሏል

كتاب صحيح البخاري

بفضيلة الشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله
ገባ ገባ በሉ 👇👇👇
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=e8517bea02b7ad495c

[መንሀጁል አንቢያዕ]

21 Jan, 00:09


ታላቅ ብስራት ለሰለፍዮች በሙሉ
~~~~>

በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ

የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “ዲናችንን ማወቅ መተግበርና ማስተማር”

🏝 የኢትዮጵያ አህለ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ታላቅ ሀገር-አቀፍ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጥቅምት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አስቧል።
=> ለዚህ ፕሮግራም የአዳራሽ ኪራይ፣ ለተሳታፊዎች ሻይ ቡና ፣ ለዑለማዎች ትራንስፖርትና ማረፊያ ወዘተ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት 1000 ብር ነው

🔹 ስለሆነም ትኬት በአካል መግዛት ለምትፈልጉ፦
➡️  አል ኢስላሕ መድረሳ
➡️  ዳሩ ሱና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🔹በባንክ አካውንት ለምትጠቀሙ
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000650550718
          ሙሒዲን ሳሊሕ እና ዩሱፍ ኸድር

   የኢትዮዽያ አህሉ ሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

1,044

subscribers

1,498

photos

566

videos