ውድና የተከበራችሁ የሃራ ውላጋ እና አካባቢዋ የምትገኙ ብርቅየ ሰለፍዮች ሆይ አዋጅ ስሙ ‼️
እንደሚታወቀው ሱናን መርዳት ያለብን በተግባር በሁለተናችን በምንችለው አቅም መጠናከር ስላለብን ይህ ወር የከስብ ወር እንደሆነ የሚታዎቅ ነገር ነው
በጤፍ አጨዳ በማሽላ ጋጠጣና ቆረጣ የመውቃትና የአገዳ መከመር ሂደቱ ይቀጥላል መሰል የግብርና ስራላይ ለተሰማሩ የሱና ወንድሞችንና እንድሁም የየቲሞችን በጠና ታመው ከስብ መከሰብ ለማይችሉ አቅም ያጠራቸውን ወንድሞቻችን ችግራቸው የኛም ችግር እንደሆነ አውቀን ልናግዛቸው ከጎናቸው ልንቆም ይገባል አላህ እኛንም ያግዘናል ይረዳናል በባለፉት አመታቶች ለምን ድናችሁን ተማራችሁ በማለት ለድን ትኩረት በሰጠት የሱና ወንድሞች ላይ ካሃገር ከቀየ ከዕድርና ቅሬ ማሓበራውይ ኑሮ በቀላሉ ከህዝበ ሙስሉሙ ጋር ተረዳድተው እንዳይ ሰራ በማሴር ሲሳደዱ የነበሩ የሱና ሰዎች ነበሩ
እኛም በምንችለው ከጎናቸው እንደሆን በተግባር አብሮነታችነን አሳይተናል ከነሱ ጋር አረም በማረም አጨዳ በማጨድ አገዳ በመጋጠጥ በመውቃትና እንድሁም የመኖሪያ ቤት ሳይቀር ሰርተናል አሁላይ በዳዕዋ መስፋፋት ምክኒያት ትልቅ ተፅኖ ፈጥሮ ትናንት ባይተዋር ብቸኛ የነበሩት የሱና ወንድሞች ዛሬ ብዝተው ተባዝተው ለራሳቸው አልፎው ለሌላም የሚተርፉ ኡማ ሁነዋል አልሃምዱሊላሂ ረቢል አለሚን ለዛ ነው
ዘንድሮ የግብርና ስራላይ የእርዳታ ጥሪ ያልተደረገው ለውጥ አለ ከባለፈው አመት
ስለሆነም ለየቲሞችና ታመው መከሰብ ያልቻሉ የሱና ወንድሞችን እንድሁም ለሰራተኛ የሚከፍሉት ገንዘብ አጥተው የሚሳሱለትን አዝመራቸውን በዝናብና መሰል የሸተውን አዝሪት የነሱ ወደ ኋላ በመቅረት ከብት ሊነጥቃቸው ያሉትን የሱና ዎንድሞቻችን በገንዘባችን በጉልበታችን አሁንም መርዳት አለብን እንረዳቸው
ስለሆነም ነገ ታሪክና አሻራ ጥለን ለመመለስ አስበናል እናንተም ያአጅሩ ተካፋይ ሁኑ ኑኑኑ የፊታችን እሮብ ጥቀምት ቀን/13/2017/ነገ እሮብ አንድ የሱና ወንድማችን በጠና ታሞ ቆይቷል አሁላይ ከህመሙ ቢገግምም ከስብ ለመከሰም አልቻለምና በመተኛቱ ምክኒያት ጤፉ ሊፈስበት ስለሆነ ነገ በመስጅዴ ሶፋ ግቢ በመገኘት ተሰባስበን ጉዞ ወደ አላ ውሃ ይሆናል እንዳትረሱ አስታውሱ
የነገ ስምሪታችን ኢንሻ አላህ ወደ አላ ውሃ ይህ ወንድማችን የቀዶ ህክምና ቆይታ ስለነበረው ተቀምጦም ቆሞም ስራ መስራት ስላልቻለ ካለበት ሃሳብ እንታደገው በምንችለው አቅም አይዞህ ልንለው ይገባል
ማሳሰቢያ ለአዝመራው መሰተሪያ የሚወሉ መሳሪያዎችን የመሰተሪያ ግባአቶችን እንዳንረሳ እነሱም ጋሽ ማጭድ ናቸው የለለን በጎረቤት ለምነን ቢሆንም ይዘን መገኘት አለብን እንዳንረሳ ከሱቢሂ ሶላት ቦኋላ ወደ ተባለው ቦታ በጧት ስለምናመራ እንዳታረፍዱ አደራ አጭደን ከምረን ነገሩን አሳምረን ለቁርስ በጧት መመለስ እንዳለብን ንያ እንናፍስ _
ባረከሏሁ ፊኩም
ጥቅምት ቀን/13/2017የፊታችን እሮብ
https://t.me/hussenhas
ሃራ ውላጋ
https://t.me/hussenhas