ye allah baroche

@yealahbarochh


ወደ አላህ ከትጠራና መልካምንም ከሰራ፣ <<እኔ ከሙስሊሞች ነኝ >> ካለም ሰው ይበለጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

ye allah baroche

22 Oct, 19:58


እኛና ሰላታችን

ye allah baroche

22 Oct, 18:31


ዛሬ በመንገዴ ላይ 🥀

ye allah baroche

22 Oct, 17:12


አስገራሚ ታሪክ

አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ ይገባል። አንድ ቀን የግቢው ባለቤት እግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ስር ቆመ ከዛ ሌባው ዛፉ ስር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ፣ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ...

ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ አየ ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ የቤቱ ባለቤትም፦ “ይህን ያደረኩት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰዉ እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ'ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው።

~ ክፉ ነገር አንስራ፤ ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን ያለብን የፈጠረን እንዳያዝንብን እንጠንቀቅ፤ ከክፉ ነገር
እንታቀብ ሰዉን ሳይሆን ፈጣሪን እንፍራ።

ye allah baroche

22 Oct, 17:09


‎ቀብሬ ላይ የቆምከው ሰው ሆይ!በነገሬ አትገረም!ትናንት እንዳንተው ነበርኩ፣እኔን ትመስላለህ ነገ አንተም ::

ye allah baroche

22 Oct, 17:09


አንድ ቀን እንሞታለን።

ye allah baroche

22 Oct, 17:08


ከበርካታ ግድያዎች የተረፈው፣ ህይወቱን በትግል ሜዳ ያሳለፈው የቀሳሞችን ቤት የመሰረተው ኻሊድ ዐብዱረሂም ኢስማዒል ዐብዱልቃድር ሚሽዐል 'አቡል-ወሊድ' በየህያ ሲንዋር ቦታ መተካቱን ቀሳሞች ይፋ አድርገዋል።

አላህ ይጠብቅህ
አላህ ያበርታህ
አላህ ያግዝህ

ye allah baroche

22 Oct, 13:28


እውቀትን መፈለግ

🎙 ኡስታዝ ኢስማኢል ያሲን

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------

ye allah baroche

22 Oct, 05:04


ውድመት ፣ ረሀብ ፣ ግፍ፣ መከራ በጋዛ ሀይሏል
ምን ላድርግ አትበል እጅህን ከፍ እምባህን ረገፍ አድርገህ ያ አላህ አግዛቸው በል። በለሊቱ መጨረሻ ከዕንቅልፍን ንቃ። ስለወንድሞችህ አንባ። በሐሳብ በኒያ አብረሀቸው መሆንህን አሳይ። ውሏቸውን ተከታተል። የደረሰባቸውን አይተህ እኔን በል። የነካችሁ ይንካኝ አላህ ይርዳችሁ ይሁን ዱዐህ። ስለጀግኖቻቸው ጌታዬ ሆይ የወረወሩት ኢላማውን አይሳት ብለህ ዱዓ አድርግ። በአቅምህ ልክ ተዋጋ። በችሎታህ ልክ ተፋለም።

ሞታቸውን አትላመድ ዜናቸውን አትሰላች። ይህ በኒያህ የሙጃሂዶቹን ደረጃ የምትጎናፀፍበት መዕረካ ነው።

በቀስተኞች ተራራ ላይ ካንተ በቀር ማንም ባይኖር እንኳ ቦታህን አትልቀቅ።

ሰዎች ስለ ጋዛ መፃፍ ቢያቆሙ ህመም ብሶታቸውን ጀግንነት ገድላቸውን መመዝገብ የአንተ ድርሻ እንደሆነ እያሰብክ ጻፍ።

ሲስቁ አብረሀቸው ሳቅ ሲያለቅሱም እንዲሁ አብረህ አንባ። እርዳታውን የነፈጋቸው ሁሉ ፈተናውን ወድቋልና ሰበብ ማድረስህን ለአላህ አሳይ!
@STRONG_IMAN
@STRONG_IMAN

ye allah baroche

22 Oct, 05:02


🎧🌹🎧

ye allah baroche

22 Oct, 05:02


🌺

ye allah baroche

22 Oct, 04:24


ወዳጄ {አሲፍ} :
⇏ «እባክሽን ታጋሽ ሁኚ»
·
♡ በጣም የሚዋደዱ በኢማናቸው ጠንካሮች የሆኑ ባለትዳሮች ነበሩ። አንድ ቀን ሚስት ከባሏ እና ከቤተሰቦቿ ጋር የማምሸት ፕሮግራም ትይዝና ለቧሏ ቀድማ ትነግረዋለች። ባል ግን በዛ ቀን ከቀጠሮው ሰአት አሳልፎ እንደውም ያመሻል።
·
ሚስት ስትደውል ስልኩ አይሰራም። በጣም ትናደዳለች። ባልም አምሽቶና ደክሞት ቤት ሲገባ ሚስቱም «ከቤተሰቦቼ መቅረቴ ሲገርመኝ እንዲህ አምሽተክ ትመጣለክ? ለምን አታድርም ነበር ...... ?» በጣም ጮክ ብላ ትናገረዋለች ባል የሆነውን ሊያስረዳት ቢሞክርም ልትሰማው አልፈለገችም በጣም ደክሞት ስለነበር ትቷት ወደ መኝታው ይሄዳል።
·
በሁለተኛ ቀን ድጋሚ ያመሻል ሚስት ስትደውል ስልኩን ያነሳችው ሴት ነበረች «ሄሎ» ስትላት ስልኳን ተናዳ ትዘጋዋለች። ባል ሲገባ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ትጠብቀዋለች። ባሏም እንደገባ እንዲህ አለችዉ።
·
ሚስት፦ «እኔ ምንክ ነኝ ላንተ ?»
·
ባል፦ «ውድ ሚስቴ ነሻ።»
·
ሚስት፦ «ያቺስ»
·
ባል፦ «ከወደሁላው ዘወር ዘወር ይልና የቷ ?
·
ሚስት፦ «ስልኩን ያነሳችው ወይዘሮ»
·
ባል፦ «ስልኩን ለማውጣት እጁን ወደ ኪሱ ሲያስገባ ስልክ የለም። «ማሬ ስልኬ የለም፣» ይደነግጥና ማፈላለግ ይጀምራል።»
·
ሚስትም ሊዋሻት የፈለገ ስለመሰላት አላመነችው በቃ እንዲፈታት ትነግረዋለች። ባል ሊያረጋጋት ቢሞክርም አልቻለም። ባልም እሺ ይንጋና ነገ ወደ ቤተሰቦችሽ ትሄጃለሽ ብሎ ይለምናታል። በዚህ መልኩም እሱ መኝታ ቤት እሷ ደሞ የሳሎኑ ሶፋ ላይ ተለያይተዉ ተኙ።
·
በጠዋት የቤታቸው በር ይንኳኳል ሚስትም ከተኛችበት ሶፋ ላይ ነቅታ በሩን ስትከፍት አንድ አርጀት ያሉ ሴትዮ ከወጣት ሴት ልጃቸው ጋር ይመጡና ባሏ እንዳለ ይጠይቋታል። እሷም ትጠራዋለች ሴትዮዋም ስልኩን እርሳቸው ጋር እረስቶት እንደነበረ ነገረው ይሰጡትና በጣም ሲመርቁት ታያለች።
·
ሚስት፦ «ለምንድን ነው ብላ ስትጠይቅ ?»
·
የልጁ እናት፦ «ባልሽ በጣም ጥሩ ሰው ነው። ከቀኖች በፊት ለወንዱ ልጄ ደም ለግሶ የልጄን ሂወት ታደገልኝ።» የልጁ እናትም አስከትለዉ
«ትላንት ደግሞ ልጄን ሊጠይቅ መጥቶ ሳለቅስ አየኝ ለምን እንዳለቀስኩ ጠይቆኝ ለልጄ ከሆስፒታል የታዘዘለትን መድሀኒት መግዣ እንዳልነበረኝ ስነግረው በየ ሱቁ ሲፈልግ አምሽቶ ገዝቶ አመጣልኝ። እናም ሆስፒታል ዉስጥ ስልኩን እረስቶት ሄደ ስትደውይ ልጄ ነበረች ያነሳችው።»
·
ትላታለች ሚስትም በባሏ ታጋሽነትና ቸርነት ተገርማ ይቅርታ ትጠይቀዋለች።
·
ውድ እህቴ ከታሪኩ  ለነገሮች ኡዙር መስጠት እንዳለብሽ ነው። ባልሽ ላንቺ ታመኝ መሆኑን ልብሽን አሳምኝው። በትንሽ ነገር የአላህን ስጦታና የቤትሽን ጣፋጭ ደስታ ምድራዊ ጀነትሽን በቀላሉ አታበላሺዉ። እሱ ያንቺ ደስታ ነው የሚያስደስተው ግን የተቸገሩትንም መርዳት እንዳለበት አትርሺ።
·
ሁል ጊዜ ቤትሽን አስታዉሺ ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ቤተሰብሽ ለአላህም ብለሽ።

ye allah baroche

22 Oct, 04:24


#አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
፨፨፨ መቼም ዘውጅ ሲባል ልቡ ማይናፍቅ የለም አይደል??? እነሆ ይህን እውነተኛ
ታሪክ ከልጅትዋ ማስታወሻ ላይ ጀባ ብያለው!!!!

እኔ በጣም በትምህርት በጣም ጎበዝ ከሚባሉ ተማሪዎች አንዷ ነበርኩ ፧

💢💢አንድ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ ስለነበር ከቤተሰብ ጋር ወደ አንድ ሀገር ለሽርሽር ሄድን ምንሄድበት ሀገር በጣም እሩቅ ስለነበር በመሀል እረፍት አስፈልጎን ሁላችንምም ከመኪና ወረድን.. እና እኔ በአካባቢው ውበት በጣም ተማርኬ ስለነበር #ካሜራዬን ይዤ ለፎቶዬ ሚመች ቦታዎችን እየመረጥኩ ማንሳቴን ተያያዝኩት

ቦታው እጅግ በጣም ትንግርት ሆኖብኝ ፎቶዬን ማንሳት ተያያዝኩት...ሳላውቀው በጣም ረጅም ጉዞ ተጎዤ መመለሻው ጠፋኝ ግራ ግብት ጭንቅ አለኝ እናም ማደርገው ግራ ገብቶኝ ተጣራው ጮሁኩኝ መልስ ሚሰጠኝ ግን አነበረም...ዝም ብዬ እግሬ ወደመራኝ ጉዞ ጀመርኩ የጫካውን ዳር ይዤ ጉዞዬን ተያያዝኩት..

ስሄድ ..ስሄድ.. ቀኑ ቦታውን ለምሽቱ ማስረከቡን ተያያዘው.. በጣሙኑ ጭለማው ልቤን ማራድ ማናወጥ ጀመረ

💫💫💫ግራ ገብቶኝ በፍርሀት ተውጬ ጉዞየን ቀጠልኩ ..ግና የሆነ ብርሀን ነገር
ሳላስበው ከርቀት አየው በደስታና በፍርሀት መሀል ሆኜ በፍጥነት ወደዛ መብራት ጉዞየን ቀጠልኩት ... ፈራ ተባ እያልኩ ቀረብኩኝ ስደርስም ደሳሳ ጎጆዎችን ተመለከትኩ ጠጋ ብዬ ኲዋ ኩዋ ... በሩን አንድ ወጣት
ከፈተልኝ

💫💫💫የሆንኩትን ነገር ነገርኩት ወደ ውስጥም እንድገባ ፈቀደልኝ ... ከዛም
እንዲ አለኝ እኔ እዝችው እያነበብኩኝ አድራለው አልጋው ላይ መተኛት ትችያለሽ... ብሎ ወደ መደቡ አመላከተኝ ፈራ ተባ እያልኩ ወደጥግ ነገሬንም ወደ አንድዬ እያስጠጋው ጥቅልል ብዬ ካሁን አሁን ተከመረብኝ እያልኩ መጠበቅ ጀመርኩ... እሱም ማንበቡን ተያያዘው... በመሀል ትኩር ብዬ ስመለከት

🍃🍃🍃🍃 #ጣቶቹን #ተራ #በተራ #በተለኮሰው #ጧፍ #ማቃጠል #ጀምሯል
🍂🍂🍂ግራ ገባኝ ልቤም ምቱን ጨምሯል .... ለሊቱ እርዝመቱ.... አሁንም ያነባል ትንሽ ቆይቶ ጣቶቹን በዛ እሳት 🔥🔥🔥ያቃጥላል...

እንደዛ ሲደጋግም ግራ ተጋባው... አይነጋም የለ ጎህ ሲቀድ ጭለማ ቦታዋን ለብርሀን አስረከበች ሚቀመሰውን ቀማምሼ ልጁ መንገዱን ጠቁሞኝ አመስግኜው ተሰናብቼው መንገዴን አስፓልቱን ይዤ ጉዞየን ቀጠልኩ ... ከዛም አንድ አካባቢ ላይ ብዙ ሰዎች ተሰባስበው ተመለከትኩ ዳሩ ግን እነዚህ ሰዎች እኔን ፍለጋ ነበር የመጡት... ከዛም ከምወዳቸው #ቤተሰቦቼ #ጋር #አላህ በሰላም አገናኘን .....

⭐️⭐️⭐️እቤት ገብቼ የሆንኩትን ታሪክ ለቤተሰቦቼ ነግርኲዋቸው አባቴ በነገርኩት ታሪክ ልቡ ተነካ

... ከዛም ወደተባለው አካባቢ አባት እውነታውን ለማጣራት ሄዱ አመሻሹን #ሲሆን #አባት #በተራቸው.. ያችን በር አንኲዋኩ... አሁንም ያ ወጣት በሩን ከፍቶ አስገባቸው ይህ ልጅ የልጅቷ አባት መሆናቸውን አላወቀም.....🍃🍃🍃🍃.ጨዋታው ተጀምሯል... በዚ መሀል የልጅቷ አባት ጠየቀ... #ልጄ #ምን #አገኘህ #እጅህን???

💐💐💐ልጁም መለሰ.. ትላንት ልክ እንደ እርሶ መንገድ የጠፋት ለግላጋ ወጣት #ማደሪያ #አጥታ #አሳድሪያት ነበር በመሀል እያነበብኩ ሳለ ስሜቴ በጣም ስታስቸግረኝ ጣቴን አንድ በአንድ እያቃጠልኩ አኼራ ከዚህ የከፋ መቃጠል ይጠብቅሻል እያልኩ ስሜቴን ገታዋት አላቸው... የልጅቷ አባትም ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ..😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭.. እቅፍ አድርገውም ሳሙት
...
#ልጅ #በጣም #ግራ #ተጋብቷል.... ምነው አላቸው??? እኔ የልጅቷ አባት ነኝ... ተቃቅፈው ተላቀሱ.😭😭😭😭.... አባት እንዲ አሉ ከዚህ እንሂድ #ልጄንም #ልዳርልህ
#ተስማሙ ጉዞ ወደ ልጅቷ ጋር..... ጊዜው ተቆረጠ... ኒካውም ታሰረ.....!!!!💢🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

ሱብሀነላህ!!!!!! ከዛም ልጅቷ ማስታወሻዋ ላይ እንዲ ብላ ፃፈች!!! መን ተረከ ሊላህ ሸይአን አዕጧ ኸይረን ሚንሁ!!!!

↘️↘️ለ አላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ
አላህ በተሻለ ይተካለታል፨፨፨፨፨፨፨፤፤፤፤፤፤🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃፧፧፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፨

ye allah baroche

21 Oct, 17:06


30 ምክሮች ለሙስሊሟ እህቴ!
~
1- ሒጃብሽ ሰፋ ያለና ረዘም ያለ ይሁን ።
2- አካሄድሽ ረጋ ያለና አደብ የተላበሰ ይሁን ።
3- በየቀኑ ብታጠፊ በየቀኑ ወደ አላህ ተመለሺ።
4- በአለባበስሽና በሥነ-ምግባርሽ ለሌሎች ሴቶችና ለሴት ልጆችሽ ምሳሌ ሁኚ።
5- ሊፕስቲክ ተቀቢዎች በዝተዋል፤ ግና ብዙዎች ስላደረጉት ጉዳዩ ትክክል ነው ማለት አይደለም ።
6- አዝማሚያው ያላማረሽን ቅርርብ በአጭር ቁረጪ።
7- ስትቀመጭ ሰብሰብ ሰተር ብለሽ ተቀመጭ።
8- ያልተፈቀደልሽን ባዕድ ወንድም ሆነ ሊያገባሽ የሚፈቀድለትን የቅርብ ዘመድ አትጨብጭ።
9- ከላይ አላህን ሳይታዘዙ፤ ዉስጤ ንፁህ ነው አላህን ፈራለሁ ማለት ቅጥፈት ነው።
10- ከባዕድ ወንድ ጋር ስታወሪ መቅለስለስ በሽታ ያለበትን በሽታውን መቀስቀስ ነው።
11- መስመር እየሳቱ የሚመስሉ የስልክ ወሬዎችንና ቻቶችን ቁረጪ።
12- በማይረባ ነገር እና ማ/ዊ ሚዲያ ላይ ዉድ ጊዜሽን አታጥፊ።
13- ወንድ ከኋላ እየተከተለ ደረጃ አትው።
14- ሙዚቃ የተቆጣጠረዉን ልብ ቁርአን ለቆት ይወጣል ።
15- እየተኳኳሉና እየዘለሉ አላህን እና መልዕክተኛዉን እወዳለሁ ማለት ዉሸት ነው።
16- ሒጃብና ኒቃብ እየለበሱ መጥፎ መሥራት የኢስላምን ንጽሕት ሙስሊምን ሥም ጭምር ማጠልሸት ነው።
17- ሆነብለሽ ወንዶችን አትፈታተኚ።
18- በሐራም መንገድ ገንዘብም ሆነ ትዳር ባገኙት አትቅኚ።
19- ያለ ኒካሕ የተወለደ ልጅ አባት የለዉም ።
20- ደረትሽን አትክፈቺ አታሳብጪም።
21- ቀሚስሽን ከኋላም ሆነ ከፊት አትቅደጂ።
22- ፀጉርሽን አትጎዝጉዢ አትቀጥይ።
23- ሽቶም ሆነ ዶድራንት አትቀቢ።
24- ሊፍት ስትገቢ ከወንድ ጋር ብቻሽን አትግቢ።
25- ብቻሽን ባዶ ቤት ዉስጥ አትደሪ።
26- ተሰተሪ በሁሉም ነገር አላህ ይሰትርሻል።
27- ስትስቂ በስሱ፤ ሰታወሪ ድምጽሽ ዝቅ ይበል ።
28- በሥራ ቦታ ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነት ቀይ መስመር ይኑርሽ።
29- ተግባቢ እና ትህትና ያለሽ ሁኚ ።
30- በተቻለሽ መጠን አላህን ፍሪ።
አላህ ይሠትረን።
=

ye allah baroche

21 Oct, 16:59


🦋❝ጀነት ስንገባ አንድም ሰው ከመካከላችን እንዲጎድል አንፈልግም..በሉ ተነሱ ልጆቼ❞ እያለች ልጆቿን ለሱብሒ ሶላት የምትቀሰቅስ አንዲት እናት ነበረች🥰🥰

አሏህ ለልጆቻቹህ ምርጥ ዓርዐያ የምትሆኑ ያድርጋቹህ ያድርገን🤲🦋

ye allah baroche

21 Oct, 16:56


ከእውቀት አንድ ሰው ሊወገድ የሚችለው

🎙ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ

ሁዳ መልቲሚዲያ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
----------------------

ye allah baroche

21 Oct, 07:50


"በሜዳው አሏህ አለ!"
ይላል በፈራረሰችው የሊባኖስ ከተማ በአቧራ የተሸፈነችው መኪና

ye allah baroche

20 Oct, 18:39


አንዳንዴ እቀድመዋለሁ ብላቹህ ያሰባችሁት ነገር
ቀድሞቹህ ስታገኙት በቃ ደስ ባይልም
ጀሊሉ ያስቀደመዉ ለጥበብ ነዉና አልሀምዱሊላህ

ye allah baroche

20 Oct, 17:49


አንድ ባለ ትዳር ወደ አንድ ጥበበኛ ሰው ጋር መጣና ልጄን እንዴት በተርቢያ ላሳድግ? ብሎ ይጠይቃል
ጥበበኛውም:_እድሜው ስንት ነው?
ሰውየው:_7ወር
ጥበበኛውም: _ዘግይተሀል ልጅህን በተርቢያ የምታሳድገው እናቱን በትክክል ስትመርጥ ነው!!አለው


፠ ትውልድን ነው የምታመርተው! !በደምብ እሰብ