«ሁል ጊዜም በዚህ ዓለም ሕይወትህ ያለ ዛሬ በስተቀር ሌላ ቀን እንደሌለ አስብ እንዲህ ብታደርግ ኃጢአትን አትሠራም።» (የዕለቱ መና)
«እግዚአብሔርን በመከራህም በተድላህም ሁልጊዜም አስበው መከራ በደረሰብህ ጊዜ ያስብህ ዘንድ።» (ማር ይስሐቅ)
«በሰው ስህተት ውስጥ ለመደበቅና እፎይታ ለማግኘት አትሞክር። በእርሱና ባንተ መካከል ያለው ልዩነት እርሱ መናገሩ አንተ ዝም ማለትህ ወይም አንተ ድራማውን ችለህ በድብቅ ማድረግህ ነው።»