ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

@lihket_reading


እናንብብ እንለወጥ !! " ንባብ የአእምሮ ምግብ ነው "

📞 +25190 112 2031

https://t.me/Lihket_Reading

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

22 Oct, 08:28


ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም!!

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በቅን መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት!
መልካም ቀን

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

21 Oct, 14:38


የታሰረው እግሩ ሳይሆን ጭንቅላቱ ነው!
የአመለካከት ቁልፍ

የምንችለውንና የማንችለውን ነገር የሚወስንልን ማን ነው? ለምን ይህንን ብቻ በማድረግ ተገደብን?

እነዚህን ጥያቄዎች ለራሳችን ጠይቀን እውነተኛውን መልስ ብናገኝ ያቃተን ነገር እስካሁን ድረስ ያልሞከርነው ነገር እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡ ሰውነታችን አእምሮአችን የነገረውን ለመታዘዝና ለመፈጸም የተዘጋጀ ፍጥረት ነው፡፡ አእምሮዬ ትችላለህ ሲለው ሊሞክር፣ አትችልም ካለው ደግሞ ላይንቀሳቀስ ተገድቦ ይገኛል፡፡

በዚህ እውነታ ውስጥ የኦሎምፒክ ውድድሮች ክብረ-ወሰን የመስበራቸውንም ምስጢር እናገኘዋለን፡፡ የጨከነና ራሱን ያዘጋጀ ሰው ክብረ-ወሰንን እንደሰበረ ይኖራል - የራሱን ክብረ-ወሰን! ይህንን አትዘንጋ - የውስንነታችን የመኖሪያ ስፍራ አእምሮአችን ብቻ ነው!

አንድ ሰው የተለያዩ እንስሶች ለተመልካቾች ትእይንትን ወደሚያሳዩበት ስፍራ ገንዘቡን ከፍሎ ከገባ በኋላ ገና እንደተቀመጠ ያየው ነገር ግር አለው፡፡ ተራራ የሚያክለውን ዝሆን አንድ አጭር ሰው በትንሽ ሰንሰለት እግሩን አስሮ ወዲህና ወዲያ ያደርገዋል፡፡

“እንዴት አንዲት ቀጭን ገመድ ይህንን ግዙፍ እንስሳ ልታስረው ትችላለች?” አንድን ሰው ለመጠየቅ ወሰነ፡፡ ትእይንቱ አልቆ ሰው ሁሉ ሲበታተን ይህንኑ ጥያቄ በውስጡ እያጉላላ ወደ አሰልጣኙ እንደምንም ብሎ ደረሰ፡፡

በውስጡ የጠየቀውን ጥያቄ ለሰውየው በአንደበቱ ጠየቀው፣ “እንዴት አንዲት ቀጭን ሰንሰለት ይህንን ግዙፍ እንስሳ ልታስረው ትችላለች?”

መልሱ አጭርና ግልጽ ነበር፣ “ዝሆኑ ገና ሲወለድ ጀምሮ ነው ይህቺ ሰንሰለት በእግሩ ላይ የታሰረችው፡፡ ገና በለጋነቱ ሲታገላት አላሸነፋትም፡፡ የዝሆኑ ጥንካሬ ግን ይህችን ሰንሰለት መበጠስ ደረጃ ከደረሰ ቆይቷል፡፡

ዝሆኑ በውስጡ፣ “ይህችን ገመድ በፍጹም አልበጥሳትም” ብሎ ስለሚያስብ እንደታሰረ ይኖራል፡፡ የታሰረው እግሩ ሳይሆን ጭንቅላቱ ነው፡፡

“አይኖችህ አይተው የሚነግሩህን አትመን፡፡ የሚነግሩህ ውስንነትን ነው፡፡ መገንዘብ የምትችለውን ያህል ተገንዘብ፣ የምታውቀውንና የምትችለውን ለይተህ እወቅ፣ ወደከፍታ የምትወጣበትን መንገዱን ታየዋለህ” – Richard Batch

አንድ ሰው ካለበት ወጥቶ መሆን የሚገባውን ለመሆን ከፈለገ የግድ እስከዛሬ ያመነውን ነገር ለጥያቄ ማቅረብ አለበት፡፡ ካለማቋረጥ፣ “ለምን?” ብሎ ካልጠየቀ ባለበት ሁኔታና አመለካከት ታስሮና ሃውልት ሆኖ ይኖራል፡፡

“ሁኔታዬ ለምን እንደዚህ ሆነ?” “ይህንን ነገር ለምን አልችለውም?” “ይህንን ነገር ለምን አመንኩት?” የሚሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አለበት፡፡

ሰዎች የተለያዩ ገደቦችን በፊታችን ሊያስቀምጡብን ይችላሉ፣ ከማሰብና ከመጠየቅ ግን ሊከለክሉን አይችሉም፡፡ መልስ የምታገኘው ስትጠይቅ ነው፡፡

እውነታና ብልሃት ላይ የምትደርሰው ስታስብ ነው፡፡ ዝም ብለህ ሁኔታህን በመቀበልና ከአመታት በፊት የተነገረህን ገደብ አምነህ መኖር ይበቃሃል፡፡

የተሳሳትከውን፣ “ተሳስቼ ነበር” በማለት አዲስ ነገርን ለመሞከር ካልተነሳህ ሁኔታህ አይለወጥም፡፡ ይህንን አስታውስ፣ እስካሁን ያልቻልከው ነገር ያልሞከርከው ነገር ነው፡፡ የገደቡህን ነገሮች እወቃቸው፣ ነገር ግን በፍጹም አትቀበላቸው፡፡ ያመንካቸውን መልእክቶች ደግሞ ለማጣራት ምንጩን ለይተህ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

1.  ለራስህ የነገርከው

“ለራስህ የምትነግረው ነገርና የምታሰላስለው ነገር ባለጠጋ ወይም ደኃ፣ የተወደደህ ወይም የተጠላህ፣ ደስተኛ ወይም ኃዘንተኛ፣ ሰዎችን የምትስብ ወይም የምታርቅ፣ ኃይለኛ ወይም ደካማ የማድረግ አቅም አለው” - Ralph Charell

ከሌላ አካል ከምንሰማው ነገር የበለጠ ለራሳችን የምንነግረው ነገር ተጽእኖው እጅግ የላቀ ነው፡፡ ሰው ራሱን “ሊዘጋው” ወይም “አላናግርህም” ሊለው አይችልም - ሁሌ ከራሱ ጋር ነው፡፡ ሰው ሃሳብን ላለማሰብ የማይችል ፍጡር ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ የተስፋ መቁረጥ ወይም የተስፋ ጭላንጭል ምንጭ ሊሆን የሚችል እውነታ ነው፡፡ ተስፋ አስቆራጭ የሚሆንበት ምክንያት ለራሳችን የምንናገረውን መቆጣጠር ካቃተንና በጨለምተኝነት የተሞላን ሰዎች ከሆንን ነው፡፡

2.  ሰዎች የነገሩህ

“አንደበታችንን በፈለግነው ጊዜ መክፈትና መዝጋት እንደምንችል፣ ጆሯችንንም እንደዚያ ማድረግ ቢቻል እንዴት ግሩም ነበር?” – Chinese Proverb

ጆሮአችን ምንም እንዳይሰማ ማድረግ አንችልም፣ በጆሮአችን የገባውን መልእክት ግን የማጣራትና የማይጠቅመንን በመጣል ጠቃሚውን ብቻ ማሰላሰል መብቱ የእኛ ነው፡፡ አይናችንም እንዳያይ ማድረግ አንችልም፣ ለምናየው ነገር የምንሰጠውን ምላሽ ግን መቆጣጠር እንችላለን፡፡

3.  መገናኛ ብዙሃን የነገረህ

“ሁሉንም ስማ፣ የቱን እንደምታምን ግን በግልህ አመዛዝነህ ድረስበት” - George Eliot

እንደ እውነቱ ከሆነ የምታነብባቸው መጻሕፍትና የምታያቸው ፊልሞች የማንነትህ ነጸብራቆች ናቸው፡፡ ወይ ያንን ነህ፣ ወይም ደግሞ ወደ መሆን ትመጣለህ፡፡ ስለዚህ ወደ ማንነትህ የምታስገባቸውን መልእክቶች የምታጣራ ሰው ሁን!

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

18 Oct, 19:03


Live stream finished (1 hour)

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

18 Oct, 18:08


የእርሶ ሰብስክርብሽን ለሀገራችን የንባብ ባህል ማደግ  ያስፈልገናል ይልቁንም ለልህቀት ወሳኝነት አለው  ስለዚህም እርስዎ ፣  ጓደኛዎ ፣የስራ ባልደረባ እና ቤተሰብዎን በማጋራት ሰብስክራይብ ያድርጉ  ያስደርጉ
ስለቀና ትብብሮ እናመሰግናለን 🙏
https://youtu.be/-z4zG6PUwHc?si=yWQh4jEg-FhItwr3

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

18 Oct, 17:58


Live stream started

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

18 Oct, 06:15


እንደተለመደው ዛሬ አርብ ከምሽቱ ሦስት (3:00)ሰዓት ላይ በቀጥታ ቴሌግራም መስመራችን ላይ በቀጥታ ይጠብቁን !!ለሌሎች ወዳጆችዎ ሼር ያድርጉ !!

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

17 Oct, 08:14


• በአደባባይ ምላሽ ሰጥውበታል፤
• ደጋፊም፣ ተቃዋሚም ቀርቦ የልቡን ተናግሮበታል፡፡
እኔም ይህን እንደ ዕድል በመቁጠር የእግዚአብሔር የሆነውን ስራ በትህትና ለመግለጥ ጥረት አድርጌያለሁ፤ በሙገቱ መካከል በርካቶችን ምላሽ በመስጠት ለእውነቱ እንዲቆሙ እና አንዲተባበሩ ጠብቄያቸዋለሁ፤በተለይም፡-
• ዳግም የተወለደ ክርስትያን የዘላለም ዋስትና አለው፤
• ሰው ዳግም ከተወለድ አይጠፋም፤
• ONCE SAVED ALWAYS SAVE፤
የሚሉት በኢትዮጵያ ያሉ ባፕትሲቶች፡-
• ወይ አላነበቡትም ወይም
• እንዳለዬ አይተው ትተዋል፤
• አልያም እምነታቸው በአሉታዊ (በአፍራሽ) ትርክት ተሞልቶ ከሜዳው ውጭ ሆነው ጉስቁልናን ያስከተለ ምድራዊ ሕይወታቸውን እየመሩ ይሆናል፤
• ወይም በመንታ መንገድ ላይ ራሳቸውን አግኝተው እያነከሱይሁን አይሁን ባለውቅም ከ ከመኮንን ታደሰ እና ከዚክ ኑሩ በቀር ማንም መልስ አልሰጠም፡፡እርግጥ ታምሬ ፈቃዱ ‹‹መጥፋትን ያመላክታሉ ለተባሉት ክፍል ምንባቦች ግሩም ምላሽ ለማቀበል ዝግጅቱን በወጉ እያጠናቀቀ እንደሆነ ነግሮኛል፡፡
ወገኖቼ ከሶስት ቀናት በኋላ 2017 የምህረት አመትን እንቀበላለን፡፡በሚሰጡን 365 ቀናት መካከል፡-
• አገርን ሊያጎሳቅሉ የሚችሉትን፣
• ሕብረታችንን ሊያደፈርሱ የሚችሉትን፣
• ለግድያ ለመጠፋፋት ምክንያት በሆኑት አፍራሽ ትርክቶች ላይ ለመስራት ምን ያህል ዝግጁ ነን፡፡
• ታዲያ ራሳችሁንስ በአሉታዊ ተፅዕኖ አድራሽ ትርክቶች ተፅኖ ስር መሆን አለመሆናችሁን እንዴት አያችሁት?
--ይልቅኑ፡-
• ክርስትናችሁን በሚመለከት፣
• የክርሰቶስ መሆናቸሁን በሚመለከት፣
• መሰረታዊ የምትሉዋቸውን የአስተምህሮ ዘውግ በተመለከተ
• በጥቅሉ ቅዱስ ቃሉን በሚመለከት
• ልትኖሩ የወሰናችሁበት የእምነት አካሄድ በረከትን ወይስ መርግምን በሚያመጣው የኑሮ ዘይቤ ውስጥ አላችሁ?

‹‹…15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ፤ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።… እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤
28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
30 እኔና አብ አንድ ነን።(ዮሐንስ 10:15,26-30)

እንግዲህ ዳግም የተወለደ ሰው የተሰጠው የዘላለም ሕይወት የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በመሆን ራሱን የሚያኖር አማኝ ከማህበሩ በመለየት ስሙን ሊፍቅ ይገባል፤ እኒህ አይነት ሰዎች ከመነሻውም ክርስትን የሆኑ መስሏቸው የገቡ እንጂ ከጌታ የተወለዱ አይልነበሩም፤ ቁጥር 15 እኒህን አይነት ሰዎች በጎች እንዳልሆኑ ደምፁንም መለየትም ሆነ መስማት እንደማይችሉ ‹‹… እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።››በማለቱ ልንደመም ይገባል፡፡
ማጠቃልያ
ሊታወሱ የተገባቸው ሁነኛ ነጥቦች፡-
የሀሰተኛ ትርክቶች መለያ
• ከላቀው ጌታ ጋር ተካክሎ ተመሳስሎ ለመቆም ይጥራል፤
• በልዑል እግዚአብሔር ብቻ የሚከናወኑትን በራሱ በመፈፀም ሌላ አቻ ልዩ አግዚአብሔርን በሰው ውስጥ ለመፍጠር ይጥራል፡፡
• የሰውን ፍጥር መሆን እና በእንከን ውስጥ ያለ መሆኑን አስረስቶ አቅመኛ አድርጎ ያሳየዋል፡፡
• የኢየሱስን የትንሳኤውን ሐይል በእርሱ መንፈሰ ሙትነት ላይ ትንሳኤን በዳግም ልደት አማካኝነት ሊመጣ እንደሚችል አያምንም፡፡
• የእምነቱን እና የምግባሩን የመጨረሻ ባለስልጣን ቃሉ ነው ያለለትን በተግባር(በኑሮው) ይክዳል፡፡
• በሐጢያት የረከሰ ስብዕና ራስን በገዛ አቅም ሕያው ማድረግ አለማስቻሉን ለመረዳት ብርሀን ሰጪ ለሆነው ለመንፈስ ቅዱስ ራሱን አይሰጥም፡፡

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

17 Oct, 08:14


--የስሙንም ትርጉም ስንመለከት ‹‹ሩፋ›› ማለት ሐኪም ማለት ነው፡፡ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሩፋኤል ማለት ከእግዚአብሔር የሆነ ሐኪም ማለት ነው፡፡ ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለት መሆኑን በመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 10 ቁጥር 13 ላይ ‹‹በበሽታ ሁሉ ላይ፣ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ፤ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› ሲል እንዲሁም በዚሁ መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 6 ቁጥር 3 ላይ

‹‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መልአክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› በማለት እግዚአብሔር ለቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የወጣውን፤ ቁስል እና ደዌ፤ ይፈውስ ዘንድ ስልጣን እንደሰጠውና ሐኪም እንዳደረገው ነግሮናል፡፡

ሩፋኤል ፈታሄ ማሕፀንም ይባላል፡፡ በምጥ የተያዙትን ሴቶች እና እናቶች፤ ደግሞም እንስሳት እንኳን ምጥ ሲፀናባቸው፣ ስሙን ከጠሩላቸው ይፈታቸዋል፡፡ ይህ መልአክ በተለይ ለሴቶች እጅጉን ረዳታቸው ነው፡፡ ከፀነሱበት ጊዜ አንስቶ እስኪወልዱ አይለያቸውም፡፡በተለይ በእርግዝናቸው ጊዜ ስሙን እየጠሩ፣ መልኩን እየጸለዩ፣ ጸበሉን እየጠጡ እየተዳበሱ፣ ከተማጸኑት ጭንቀታቸውን ያቀላል፣ በሰላም ያዋልዳቸዋል፡፡የሚል ትርክት አለ፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ስለ ቅዱስ ሩፋኤል እንዲያሳውቃቸው፣ ክብሩን እንዲገልጽላቸው ጠየቁት፡፡ ጌታም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲመጡ አዘዛቸው፡፡ እነሱም መጥተው ሳሉ ሩፋኤል ስለማንነቱ ራሱ እንዲናገር አዘዘው፡፡

ለማንኛውም የቅዱስ ሩፋኤል ቀን የዘነበውን ዝናብ በዕቃ ቀድታችሁ አስቀምጡ፡፡ ያንንም ጸበል ቤታችሁን፣ ደጃችሁን፣ እንዲሁም የሥራ ቦታችሁን እርጩበት፣ እየቆጠባችሁ እህል ስታቦኩ አብኩበት ጠጡት ተጠመቁበት፡፡ ብዙ በረከት እና ፈውስ ታገኙበታላችሁ፡፡

ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገበ የሚከፍትበት ቀን ጳጉሜ ሦስት ስለሆነ የሰማይ መስኮቶች፤ ወይም ደጆች በሙሉ ተከፍተው፣ የምዕመናን ጸሎት በተለየ ሁኔታ የሚያርግበት ጊዜም ስለሆነ ይህን ቀን መጠቀም አግባብ መሆኑን ድርሳናቱ ከትበው ይዘዋል፤ወደ ሕዝብም አድርሰዋል፤ https://www.facebook.com/ethiopianorthdox
እንግዲህ አንድ ዘላላ ጉዳይ ወስጄ መጥኜ ያቀረብኩትን ትርክት በተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል መፈተሸ ተገቢ ነው፤የተሰጠኝን ዕድሜ በአግባቡ ከመጠቀምና ከተሰጠኝ አደራ ጋር ለማጣጣም ያስችለናል፤ ሁሉን እንምርምር እንደ ቃሉ መልካም የሆነውን እንያዝ፡፡

ለማንኛውም ክርስትና ተኮር ትርክቶች በሰዎች የግልና የቡድን ፍላጎቶች ላይ በመነሳትሊፃፉ እና ሊተረኩ እንደሚችሉ መጠርጠር ተገቢ ነው፤አባቶች ‹‹ጠርጥር ከገንፎውስጥ አለ ስንጥር››ይላ፡፡መዋ ብቻ ሳይሆን አለማጦ ወደ ሆድ መክተት ይበጃል፡፡
ክርስትና ከቅዱሳን መጻህፍት ጋር ያልተፋቱ ትርክቶችን አይቃወምም
በትዩዩ ክርስቶስንና የክርስቶስን ስራ ዝቅ የሚያደርጉትን የሚያደበዝዙትን ደግሞም ሊሽሩት የሚታገሉትን ሰው ሰራሽ ትርክቶችን ምንም አያመጡም በማለት ዝቅ አድርጎ ማየትም አግባብ አይደለም::
ትርክት ሁልግዜ መነሻ ሰበብ አለው፤ጥንት በብሉይ ኪዳን በዬሴፍ ላይ ተመስርቶ የተፈጠረው ትርክት እውነት ሆኖ የአባትየውን ማንነት እንዴት አፍዞት እንደነበር ልብ ማለት አለብን::
³⁴ ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ።
³⁵ ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፤ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ። አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።(ዘፍጥረት37፡34-5)
የዮሴፍ ሕልም በሁለቱም ግዜ ለእርሱ የመሰገዳቸው ምክንያት እረፍት አልሰጣቸውም፤በግዜ መፍትሔ ካልተሰጠው ነገ በእጁ ስር ወድቀው ታላላቆች የታናሻቸው ተገዢ ይሆናሉ::
-- ይህ ክብርን የሚነካ አካሔድ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ለወንድሞቹ ስጋት ሊሆንባቸው አይገባም፤ መፍትሔው ሕልመኛውን ማስወገድ ነው፡፡ እፍይ የሚያሰኝ ትርክት ፈጥረው መገላገል ነበር፡፡
ተሳካላቸውም::
በግዜው የቀረበው በደም የተነከረ ብጡቆ ተዘረጋግቶ ሲታይ በእርግጠኝነት የዬሴፍ መሆኑ ተረጋግጡዋል፡፡
ይህን ከእውነት ጥቂት ቆንጥሮ ግና ለእነርሱ ለዘለቄታው እንዳያስጠረጥር ተደርጎ የተፈጸመው ተጨማሪ ገለጣ እውነተኛ ትርክት ሆኖ በተከድኖ ይብሰል ለአመታት ዘለቀ፤
እግዚአብሔር የታሪክ ባለቤት ስለሆነግን ሁሉን በግዜው ወደ ብርሀን ሲያመጣው የሆነው የልዑሉን ወሳኔ እና ፈቃድ መገልበጥ አለመቻሉን ማፅናት ነው፡፡
በዳንኤል ክብረት መፅሐፍ ተመስጬ ባለበት ግዜ አገራዊው የኢትጵያዊነት ማንነት እንደተጠበቀ ሆኖ ግና በቀዳሚነት የታየኝ በክርስቶስ ነን የሚሉት የአማኞች ጉዳይ ነው፡፡ዘመናቸውን ከቃሉ ጋር በተጣጠሙ ትርክቶች እየመሩ ነው? ወይስ መተዳደሪያቸው በሰው ልክ በተሰሩ፣ ለገዛ ጥቅም ወይም ለገዛ የቤተ እምነት መለያነት ሲሉ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ባልተፈተሸ ግን እውነት በመሰሉ አሉታዊ ትርክቶች ተፅዕኖ ስር አሉ?፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ድምፁን ስለሚሰሙት ስለ ገዛ በጎቹ27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤
28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። ያለውን ሕያው ቃል ከግምት አስገብቼ በፌስ ቡክ ገፄ ነሐሴ 27 ይህን ለጠፍኩኝ፡፡

መንፈሳዊ ከመሰሉ
አፍራሽ ትርክቶች መካከል
አንዱ ‹‹ዳግም የተወለደ ይጠፋል!››
የሚለው ቀዳሚው ነው!!
ለአምስትሺዎቹ የፊት ገፅ ጉዋዶቼ(Face book Friends) ለጠፍኩላቸው፡፡አፍራሽ ማለቴ ‹‹ከእግዚአብሔር ተወልዶ ሳለ ይጠፋል›› የሚል ፅኑ እምነት ያለው ማንም፡-
• ዘመኑን ሁሉ ‹እጠፋ ይሆናል›በሚል ስጋት በሰበብ በአስባቡ ተሞልቶ ይኖራል፡፡
• ፀጋ በሙላት የለገሰውን ችርነት ሊጠቀምበት አልቻለም፤
• የውድቀቱን ጥልቀት ባለመረዳቱ ድርሸ አለኝ ለመዳኔ በማለት የገዛ ጉልበቱን ያዋጣል፤
• በስራ መፅደቅ መቻሉን ከማወጅ የተነሳ በክርስቶስ መስዋዕታዊ ሞት ላይ ጢቂ ይላል፤
• በነፃነት እንድንኖር ክርስቶስ ነፃ ባወጣን ተቃራኒ ራሱን ለባርነት በመስጠት ጉስቁላን መኖሪያው ያደርጋል፡፡
እርግጥ ይህን የድል ቃል ስለጥፍ ያለጣሁት ያልዘነጋሁት እውነትም አለ፡፡ ደንነት እንደሚታጣ የሚያስመስሉ ጥቂት ክፍለ ምንባቦች በሀያ ስባቱ የአደስ ኪዳን መፅሐፍት ውስጥ መኖራቸወን አውቃለሁ ግና ሁሉም በአውዳቸው ሲመነዘሩ፡-
ይህን የእግዚአብሔርን ባህሪይና ፈቃድ ተቃዋሚ መሆን አልቻሉም፤ ይልቅስ ስምም መሆን እንጂ፡፡
እርግጥ ሰዎች እነርሱን ተጠቀመው፡-
• ለጥቅማቸው የሚውል የየራሳቸውን ትርከት ፈጥረውባቸዋል፤
• በፈጠሩትም ዓለሙ በአብዛኛው አንዲከተላቸው አድርገዋል፤
• የቁጥር መብዛት፣ የቲፎዞ ማግሳት ደግሞም ይህን እውነት ለመቃወም በምድር ሊቃናት ነን ያሉት የፃፉትን መፅሐፍት አፅፎ ማስነበብ መፍትሔ አያመጣም ፡፡
• እግዚአብሔር ባለው የማይፀፀት፤በክርስቶስ የውጀት ስራም የረካ፣ በሀሳቡም ፀኑ ነው፤
• ዳግም የተወለደ አይጠፋም ከእጁም የሚነጥቅ ማንም የለም፡፡
በፌስ ቡክ ገፄ ነሐሴ 27 ለለጠፍኩት ‹‹መንፈሳዊ ከመሰሉ አፍራሽ ትርክቶች መካከል አንዱ ‹‹ዳግም የተወለደ ይጠፋል!›› የሚለው ቀዳሚው ነው!! ››ያልኩለትን ያነበቡት፡-

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

17 Oct, 08:14


ራሳቸውን ሳይፈትሹ ራሳቸውን ሰቅለው ይነሩ የነበሩ ሰዱቃውያን ሰባት ወንደማማቾችን በየተራ አግብታ በመጨረሻ እርሰዋም ስለሞተች እኒህ ሊቃውንት ሊጠይቁ ወደ እርሱ(ወደ ኢየሱስ) መጡ፤ከዚያም ከእነርሱ ያልተሸለ ትንታኔ ሲሰጥ እንሳለቅበታለን በሚል ወይም በሌላ ምክንያት በ‹‹ትንሳኤ ቀን ከየትኛው ባሉዋ ጋር ትሆናለች›› ብለው ጠየቁት፤ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ‹‹ የእግዚአብሔርን ቃልና ሀይሉን አታውቁመና ትስታለችሁ›› አላቸው አስከትሎም ያጠበቁትን መልስ ሰጣቸው በመልሱም በመካከላቸው ለዘመናት ሲነገር የነበረውን ሰው ተኮር ተረታ ተረት ወዲያ ጥሎ ‹‹በሰማይ ማግባት መጋባትም እንደሌለ ይለቁኑ ሁሉም እንደ መላዕክት እንደሚሆኑ›› ነገራቸው፡፡ከዚህም የተነሳ እንደ ዘላቂ እውነት ተቆጥሮ የነበረውን የእነርሱን ትንሳኤ አልባ ትምህርት በዜሮ አባዛው፡፡

የጳጉሜ ሦስት ማዕከላዊ የመልዕክቴ ተጠቃሽ ክፍል፡-
‹‹…15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ፤ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።… እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤
28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
30 እኔና አብ አንድ ነን።(ዮሐንስ 10:15,26-30) በሚለው መለኮታዊ ቃል ላይ እመላለሳለሁ፡፡
ካልተሳሳተኩ የ66 ቅዱሳት መፅሐፍት ማዕከላዊ ጭብጥ ምን ሊሆን ይችላል? የሚል ጠያቂ ከመጣብኝ የእኔ ምላሽ ይህን የተነበበውን ክፍል ፊትአውራሪ አድርጌ መተንተን ወይም ማስረዳት እጀምራለሁ፡፡ዛሬ ግን ይህን ክፍል በዚህ ቦታ ከማንሳትና በማጠቃልያዬ ላይ ከመድገም ውጭ ሌላ የትንተና መሰናዶ ለዚህ ክፍለ ምንባብ የለኝም፡፡በክፍል ሁለት መልዕክቴ ላይ ግን እመጣበታለሁ፡፡ዛሬ ግን አሉታዊ ተፅዕናን ባሳደሩብን ትርክቶች ላይ በማተኮር፡-
• አገሬን ኢትዮጵያን በወፍ በረር አይን አይቼ
• ክርስትናችንን ግን በወጉ ፈትሸን በደል ሕይወት ኖረን እንድንዘልቅ እና
• ዕደሜያችንን ለፍሬያማ ስራ አውለን እንድንወጣ መክሬ እጨርሳለሁ፡፡

የጭብጥ ማዳበሪያዬ የዳንኤል ክብረት በቅርቡ የታተመው መፅሐፍ ነው ፡፡

የትርክት ዕዳና በረከት (narriatives ) በዳንኤል ክብረት የተጻፈ ሠላሳ ስድስተኛው መፅሐፉ ነው፡፡ 575 ገፆችን ሸፍኑዋል፡፡ የወረቀት ዋጋውም አንድ ሺህ ብር ነው፡፡ፀሐፊው ትንታኔውን በተከታታይ ማስረጃዎች ላይ ተደግፎ እንደ ፃፈው ባቀረባቸው የግርጌ ማስታወሻዎችና ዋቢ መፅሐፍት አማካኝነት ግንዛቤ አግኛቻለሁ፡፡ እያነበብኩ ያስተዋልኳቸው በርካታ ቁም ነገሮች አሉኝ፡፡ቀዳሚው ራሱን ትርክትን በወጉ መረዳት ነው፡፡
"...ትርክት ሆን ተብሎም ይሁን በተለምዶ በዓላማ የሚዘጋጅ የቅብብል ገለጣ(ንግርት) ነው::ብዙ ጊዜ ታሪክን፣እምነትን፣ባህልን እና አመለካከትን ይይዛል::የሚነገርበትም በቂ ምክንያት አለው::
የሚዘጋጀውም ለዚያ ምክንያት ሲባል ነው፤ የሚካተቱ ገለጣዎች ከዚሁ ከተዘጋጀበት ዓላማ ጋር የሚሔዱ ሐሳቦች እና ታሪኮች ናቸው::ብዙ ግዜ የትርክቶች በጎነትና እኩይነት በትርክት ቀራጺዎቹ እጅና ፍቃድ ወይም ቁጥጥር ሥር ሲወድቅ ይታያል:(ትርክት ገፅ 13) ከዚህም የተነሳ
--በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊው ጉዳይ በተለይ በተሳሳተ ትርክት ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ በርከቶች ዛሬ የትንሳኤ ዕድል ቢያገኙ በእርግጠኝነት የሞቱለት ጉዳይ ሊያፀፅታቸው እንደሚችል መፅሐፉ በማጠቆም ያረዳል/በሕይወት ላሉቱ ደግሞ የማረም እድል ስላlaቸው ለእነርሱ ያበስራል፡፡እንግዲህ እኛ፡-
-- የሕይወቴ መመሪያ ነው ያልልነት እና ለልጆቼ አወርሰዋለሁ የምንለት ትርክት አዋጪ ነበር ወይ? በማለት በሕይወት ሳለን መፈተሻችን ግድ ነው
--ዳንኤል ክብረት፡-
• ሕውሐት በሕዝቡ መካከል ለበርካታ አመታት አስገብቶት የነበረው ሀይማኖት አከል ትርክት፣
• ኦነግ በስድሳ አመታት ውስጥ በግተርነት ይዞ ለነገም ያው ነኝ ያለለት ትርክት
• የሰው ልክ አማራ ነው በማለት እና ለኢትዮጵያ ህልውና በቀዳሚነት የመፈለጌ አስፈላጊነት ግድ ነው የሚለው ትርክት
• የትኛውም ለሕዝቤ አሳቢ ነኝ የሚል ነፃ አውጪ እጸናበታለሁ ያለለት የመገለጫውቹ ትርክቶች በሕዝብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በማምጣት ለጥፋት ውለው ከሆነ ለመፈተሽ ያለው የመጨረሻው መጨረሻ ዛሬ ነው፡፡
• ዕዳ አሸካሚ ትርክቶችን ከላያችን ላይ አስወግደን ለበረከት የሆኑትን ትርክቶች ለይተን መመልከት ተገቢያችን መሆኑን መፅሐፉን አንብቤ ስጨርስ ልብ ብያለሁ ያ ማለት መፅሐፉ ከእንከን የፀዳ ነው ማለቴ አይደለም፡፡፡፡
• ትርክት በየትኛውም የሰው ልጅ መንፈሳዊ፣ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ፣ስሜታዊ የሕይወት ዘርፎቹ ሁሉ ላይ ተገኝቶ ሥራውን ይሰራል፡፡

እንግዲያስ ዛሬን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ከሚቀርበው ትርክት ለምን አልጀምርም፡- ጳጉሜ ሦስትን በተመለከተ፡፡ከዛሬ ከቅርቡ ስጀምር ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አመካኝንት በተደለደለው የየቀኑ አመላካች ጭብጥ መካከል ጳጉሜ ሦስት‹‹ የሉዓላዊነት ቀን ነው‹ሕብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት›› በመበላ ተጠርቱዋል፡፡ወደ ሩቅ አመታት ወደ ኋላ ስንመለስ ደግሞ ብዙ ሰዎች ወርኃ ጳጉሜ ላይ ይጠመቃሉ፡፡
--ሰዎች በጳጉሜ ሲጠመቁ ያለ ምክንየት አይደለም; ቀድመው የተረዱት፣ የሰሙት፣ የተማሩት እና ያመኑት የራሳቸው ትርክት ስላላቸው ነው፡፡
--ዛሬ በኢትዮጵያ አቀፍ ዕለቱ ለሚመለከታቸው የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል የተሰጠው ቀን ነው፡፡ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ስለሆነ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡
--በጳጉሜ ሦስት በዓለም ላይ ያሉ ውቅያኖሶች፣ ባህሮች፣ ወንዞች፣ ኩሬዎች በአጠቃላይ ውሃዎች ተከፍተው የሚባረኩበት ቀን ነው፤
-- ከዚህም የተነሳ ይህን ትርክት የሚያውቁ አብዛኞቹ ከተቻለ ጸበል ቦታ በመሔድ፣ መሄድ ባይመች፣ ቤታቸው ውስጥ ባለው ውኃ ቢጠመቁ ይባረኩበታል፤ ከበሽታቸውም ይድንበታል፡፡

በዮሐንስ ወንጌል በምዕራ 5 ቁጥር 4 ላይ ‹‹አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ፣ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኃላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር›› ይላል፡፡

--ዛሬም እንደ ቀድሞ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል፤ በዓለም ላይ ያሉትን ውሃዎች ስለሚያናውጣቸው ፣ ስለሚባርካቸው፤ ብንጠመቅባቸው እንፈወሳለን፡፡

--በልጅነታችን ጳጉሜ ሦስትን ‹‹ሩፋኤል አሳድገኝ›› እያልን እንጠመቅ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡
-- ጳጉሜ ሦስት በዘነበው ውኃ መጠመቅ ትልቅ መታደል እና ፈውስ ነው፡፡ በደዌ ይሰቃይ የነበረው ኢዮብም በዚህ ቀን ነው ተጠምቆ ነው የዳነው፡፡

--ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በመጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15 ላይ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› በማለት ተናግሯል፡፡

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

17 Oct, 08:14


መነሻ ሀሳብ ከ‹‹የትርክት እዳ እና በረከት››መፅሐፍ
‹‹ዳግም የተወለደ ይጠፋል›› ለሚሉ የተሰበከ ደግሞም የተጻፈ
ጳጉሜ ሦስት ያቀረብኩት ስብከተ ቃል ነው፡፡
ስሜ ታደሰ
ጉዝጉዋዝ ብጤ
የክርስትና መለያው ትንሳኤው ነው፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ከሞት በመነሳት ሕያው መሆኑ ክርስትናን ልዩ ያደርገዋል፡፡ የእርሱ ከሞት ሕያው ሆኖ መነሳትን ግን ከክርስትና ጅማሮ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ትንሳኤውን ላለመቀበል ትውልዱ በየገዛ ዘመኑ ‹‹ሞተ እንደቀረ›› የሚያመላክት ገለጣ በመስጠት ላለፉት 2000 አመታት ሲፅፍ ሲሰብክ ሲመራር ከርምዋል፡፡ዘልቁል፡፡(የዚህን እውነተኝነት በአውሮፓውያኑ የሁለት ሺህ አመተመህረት የሚሊኒየሙ የመግቢያ አመት የተሰናዳውን መፅሐፍ 2K የተሰኘውን መፅሐፍ ማንበብ ብቻ በቂ ይሆናል)፡፡
የራሳቸው የሆነውን ትርክት ለማደርጀት የየራሳቸውን መስፈንጠሪያ በመያዝ ፈላስፋውም፣ሳይንቲስቱም፣ አዋቂ ነኝ ያለው ሁሉ የየድርሻውን አፍራሽ ታሪክ ወግ እየፈጠረ በሰው ልክ አሰናድቶ አስነብቧል፡፡
ከጥንት ከጠዋቱ እንዲህ ሆነ፡-‹‹… የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና ‹‹ጌታ ሆይ ያ አሳች በሕይወቱ ሳለ ከሦስት ቀን በኋላ እነሳለሁ እንዳለ ትዝ አለን፤እንግዲህደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም ከሙታን ተነሳ እንዳይሉ የኋለኛይቱ ስህተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ…››(ማቴ 27፡6304)ብለውት ነበር፡፡
ጥበቃው ቢጠናከርም የኢየሱስን ሕያው መሆን እና ትንሳኤውን ማገድ ወይም ማስቆም አላስቻለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልክ እንዳለው በሦስተኛው ቀን ተነሳ፡፡
ፀሐፊው ማትዮስ በወንጌሉ ሴረኞቹ መነሳቱን እንዳረጋገጡ እንደገና ተሰብስበው ‹‹…ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ፤›› አላቹዋ አፋቸውንም ለማዘጋት ሀሰቱን እንድ ትክክለኛ ቃል እንዲናገሩ በረከት ያላ ገንዘብ ሰጡዋቸው፡፡‹‹…አንርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩዋቸው አደረጉ፤ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ሲወራ ይኖራል፡፡…››(ማቴ 28፡ 13-5) በማት ፃፈልን፡፡
የክርስትናን የወህ ልክ ለማዛባት ጥረት ማድረግ የተጀመረው ከዚህ ግዜ ጀምሮ ነበር፡፡
በመሪዎች አማካኝነት(ፈሪሳውያ፣ካህናት እና ሰዱቃውያን) ሕዝብ አንዲሳሳት የሚያደርግ ትርክት ፈጥረው ያኔ የነበረው ትውልደ ‹‹በድኑ ተሰርቁዋል›› ሲል ከረመ፡፡
ይኸው ገለጣ ‹‹በድኑ ተሰርቆ እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ማናችንም ሰዎች ሞቱዋል፤ አልተነሳምም›› የሚለውን ትርክት በተመሳሳይ መንገድ በዚሁ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጭምር ፅሐፍት አሳማኝ የመሰለ አሳች ድርሳን እያወጡ መሆኑን ከግምት እንድናስገባ እፈልጋለሁ፡፡

የትርክት ዕዳና በረከት!!
በዚህ ምድር ላይ የምኖረው የተሰፈርልኝን እድሜ ብቻ ነው፡፡ለመወለዴ(ወደዚህ አለም ለመግባቴ) ግዜ እንዳለው ሁሉ ለሞቴም ቀን (ለመውጣቴም) ግዜ ተወስናሎታል፤(መክብብ3፡3)
ይህ የተሰፈረልኝ እድሜ ካበቃ በኋላ ተመልሶ ለማግኘትም ሆነ ለማምጣት አይቻልም፡ ከሞት ቀጥሎ ተለጣቂው በተለወጠ የኑሮ ዘይቤ ውስጥ ራስን ማገኘት ነው፡፡
ከዚህም የተነሳ ዛሬ በምድር እንድኖር በተፈቀደልኝ መንገድ በቀጣይ ለመኖር አይቻልምና ግዜ ሰጥቼ የተሰጠኝን አመት ተጠቅሜበታለሁ ወይስ አብክቼዋለሁ? የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ በወጉ መመለስ እፈልጋለሁ፡፡
ከተጠቀምኩበት፡-
• በአግባቡ እንድጠቀመበት የረዳኝን የአስተሳሰብ፣የዕውቀት የአመለካከት፣ የእምነት እና የኑሮ ዘይቤን አጥርቼ የበለጠ ፍሬያማ እንዲሆንልኝ በእርሱ ላይ እሰራለሁ፡፡
• አብክቼው ከሆነም ለመብከቱ ምክንያቱን ከራሴ ጀምሬ በዙሪያዬ ያሉትን ነባራዊ ሁኔታዎችን ሁሉ እፈትሻለሁ፡፡ እምነቴን፣አመላካከቴን ፣አስተሳሰቤን እውቀቴንም ጭምር፡፡
በነገራችን ላይ መብከት ከራስ ብቻ አይመጣም፤ አብካቾች በላያችን ላይ ከሰሩት አካሔድ የተነሳ ብዙ ነጎሮቻችን በብክነት ሊጠቃ ይችላል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳለሁ ያስተማረኝ ደበበ ሰይፉ በ1962 አመተ ምህረት ላይ ተገኝቶ በግጥም ስለ ‹‹መምህሩ›› የፃፈውን ከ‹‹የብርሀን ፍቅር›› ከተሰኘው ስብስቡ መዝዤ ላነብላችሁ እፈልጋለሁ፡፡
ሳነብላችሁ‹‹ድንቄም…›› የተባለ›› አስተማሪ ወይም መምህር ብቻ አይታያችሁ፣
• ያነበባችሁት መፅሐፍ;-ለውጤታማነት ያላበቃችሁ
• ያመናችሁት ስብከት፡-የቕዠት ሕይወት ያኖራችሁ
• ያደማጣችሁት ተረታ ተረት፡-እያዋዛ እያዝናና ያባከናችሁ፡፡
• እና ምንም ጥቅም ያላገኛችባቸውን ምናምንቴና የሆኑትን ሁሉ አስቡበት፡፡
ድንቄም መምህር
ራሱን ሲከሽን
ሲያንቆለጳጳሰው
ማር-ወተት ሲያረገው
ከንፈሩን ሲስመው
ሊያስተምረኝ መጥቶ
ብሽቅ አደረገኝ
የተረብ ጋዘና መሆኑ ሰቀቀኝ
ለጋ ጊዜዬ ላይ መሽናቱ ነደደኝ
እንዳይሰማው ፈርቶ
ልቤ አንሾካሾከ
‹‹አስተምረኝ ባለ
ስንት ነገር አለ››
(1962 ተገጠመ፤ የብርሀን ፍቅር፤ በደበበ ሠይፉ 1980 ታተመ)

መምህሩ አደራ አለበት፡-
• እውቀትን የማሻገር፣
• ትውልድን የመቅረፅ፣
• ልኩን የመግለጥ፣
• በምሳሌነት የመኖር
• ይህን ለማድረግ የተሰፈረለት ግዜ ላይበቃውም ይችል ይሆናል፤
እርሱ ግን ለጋ ዕድሜ ባላቸው ልጆች ላይ(ማደግ በሚችሉት ላይ)፡-
• ትያትር ሠራባቸው፣
• ራሱን አገዘፈባቸው፣
• በማይመለስ ግዜያቸው ላይ ፈቅ የማደርገውንና የትም የማያደርሰ ወሬ አቀበላቸው፡፡
እርግጥ ይህ እየሆነ ባለበት ሊናገሩ እየፈለጉ ከእስር ቤታቸው ያልተፈቱት በልባቸው የማይጠቅም ስራ እየሰራ መሆኑን ተረድተው ያንሾካሸኩ አሉ፡፡
ሽከሽካታው ማን ያውቃል ‹‹ማወቁንስ እናውቃለን ብናገር እናልቃለን ወይም ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም››ን ምርጫቸው አድርገው ›› ይሆናል፡፡ ንቁ ልጆች ሰሚ ብቻ አይደሉም፤ አድምጥው ይለያሉ፤ ይታዘባሉ፡፡
እኔ ግን ይህን በተመለከተ ለመመለስ ዛሬ እድል አግኝቻለሁ፡፡ እድሎች በተፈጥሯቸው ሳይታሰቡ ተገኝተው ሳይታሰቡ ይለያሉ፤ ከዚህም የተነሳ የገጠመኝን እድል በወጉ ለበጎ ስራ ልጠቀምበት እፈልጋለሁ፡፡ራስን ለመፈተሸ፡፡
እንደ ሰው ልማድ የተቀመረው የአመታት አቆጣጠር 365 ቀናት ሲጠናቀቅ አመቱ ላይ አንድ ቁጥር በመጨሩ ያነቃኛል፡፡ እናም ይህ ቁጥር ከ2016 ወደ 2017 የሚቀየርበት ግዜ ላይ ስለደረስኩ የቀደሙትን ወራት እና ቀናት እንዴት እንዴት አሳለፍኩ? እለላሁ፡፡

ጳጉሜ ሦስት ዛሬ ነው 2016 ን ልሰናበተው ሰባ ሁለት ሰዐታትት ብቻ ቀርተዋል፡፡ከሦስት ቀን በኋላ 2017 ይገባል፡፡መስከረም አንድም በዕለተ ረቡዕ ይውላል፡፡
ከዚህም የተነሳ ዳግም ከተወለዱኩቡት ግዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ባሉት አመታት መካከል 2016ንም ጨምሮ ለውጤታማነት ብቃትን ሊሰጡ የቻሉና ያልቻሉ ትርክቶችን መፈተሸ ተገቢ መሆኑን መናገር እፈልጋለሁ፤ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት በመመላለስ በ2017 የ365 ቀናት የኑሮ አካሔዳችንን እኔም እናንተም በመመርመር ከጌታ የተሰጡንን በጎ ነገሮች እንፈትሻለን፡፡

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

16 Oct, 08:22


የእርሶ ሰብስክርብሽን ለሀገራችን የንባብ ባህል ማደግ  ያስፈልገናል ይልቁንም ለልህቀት ወሳኝነት አለው  ስለዚህም እርስዎ ፣  ጓደኛዎ ፣የስራ ባልደረባ እና ቤተሰብዎን በማጋራት ሰብስክራይብ ያድርጉ  ያስደርጉ
ስለቀና ትብብሮ እናመሰግናለን 🙏
https://youtu.be/-z4zG6PUwHc?si=yWQh4jEg-FhItwr3

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

14 Oct, 11:01


ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል:
https://youtu.be/9mro02PtlLc?si=3MPsFOFDnicgmR6t

ንባብን በተመለከተ በዚህ YouTube ይዘን ስለምንቀርብ ሰብስክራይብ በማድረግ አብራችሁን እንድትቆሙ በፍቅር እንጠይቃለን !!
https://youtu.be/9mro02PtlLc?si=3MPsFOFDnicgmR6t

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

13 Oct, 05:19


ቤተሰብ እና ንባብ
****
በቅርቡ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ምንም እንኳን 70 በመቶ ወላጆች ማታ ማታ ለልጆች ጣፋጭ ታሪኮችን ማንበብ አስፈላጊነቱን ቢያምኑም ግማሽ ያህሉ ብቻ ይተገብራሉ፡፡

ከአምስት ቤተሰቦች አንዱ ደግሞ በስራ ብዛት የተነሳ ለልጆች የማንበብ ልማድ የለውም ፡፡

በእኛ ሀገር የተካሄደ ጥናት ማግኘት ባልችልም የማንበብ ባህላችን አነስተኛ መሆኑ ያስማማናል ብዬ አስባለሁ።

👉 የህፃናት አእምሮ በአምስት አመታት ውስጥ 90 %  እድገት ያከናውናል ።በዚህ ፈጣን የእድገት ወቅት የቤተሰብ ድርሻ በተለይም መጽሐፍት በማንበብ የታገዘ ከሆነ ፍሬያማ ትውልድ ለማፍራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

👉በጋራ የቤተሰብ ጊዜ (Quality Time) ከሚከናወኑት መካከል መጽሐፍ ማንበብ አንዱ ነው።

👉 መጽሐፍ ለማንበብ ትሁት መሆን ይጠይቃል። ለማወቅና ለመማር ዝግጁነትና ፍላጎት ይሻል። የንባብ ረሃብ ትርጉም ያለውና ዓላማ መር ሕይወት እንዲኖር ይረዳል።

ወላጅ ለልጁ መጽሐፍ የማንበብ ጥቅሙ ምንድነው ?

👉  በወላጅና በልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል

👉የልጆችን የማንበብ ክህሎት ያዳብራል

👉የልጆችን የፈጠራ አቅም ያጎለብታል

👉የልጆችን የቃላት ችሎታ ያሳድጋል

👉ማህበራዊ መስተጋብርን ያሳድጋል

👉የልጆችን የስሜት ብስለት ያዳብራል

👉የልጆችን የአእምሮ ጤና ያበለፅጋል

አንባቢ ትውልድ ለማፍራት እየተጋ የሚገኘውን ወንድማችንን ጥልሽ ከጎኑ በመቆም ልናበረታታው ይገባል።