ቀን 08/01/2016.ም
ማስታወቂያ
******
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙ ሉ
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመጀመሪያ ድግሪና በPGDT በማታ እና ቅዳሜና እሁድ (Evening & Weekend) ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ከመስከረም 14 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ዋናው ሬጅስትራር በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለማመልከት የሚያስፈልጉ መረጃዎች
ሀ. ለመጀመሪያ ዲግሪ
1. ተዛማጅ በሆነ ትምህርት መስክ በመምህርነት ዲፕሎማ የተመረቀ/ች
ዋና ዲፕሎማውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር
ትራንስክሪፕት ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር
በትምህርት ቢሮ እስፖነሰርነት የተማረና የአገልግሎት ጊዜውን ያላጠናቀቀ ከሆነ ከትምህርት ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ
2. ተዛማጅ በሆነ ትምህርት መስክ በደረጃ 4 የተመረቀ ከሆነ የብቃት ማረጋገጫ እና የ 2 ዓመት የስራ ልምድ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. ባለፉት 2 አመታት በትምህርት ሚኒስተር የተቆረጠውን ከ12ኛ ክፍል የመግቢያ ነጥብ የሚያሞላ
የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር
የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክርፒት ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር
12ኛ ክፍል ስርተፍኬት ከማይመለስ ኮፒ ጋር ይዞ መቀረረብ ይጠበቅበታል፡፡
ለ. ለPGDT
ዋናውን ዲግሪ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር
ትራነስክሪፕ ከማይመለስ ፎቶኮፒ ጋር
ማሳሰቢያ
1. ከላይ ከተጠቀሱት የትምህርት ማስረጃዎች በተጨማሪ አመልካቾች አንድ ክላሴር ፣ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የ100 ብር ደረሰኝ በ ኢትዮያ ንግድ ባንክ Acc No 1000449424658 የተከፈለ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. አመልካቾች ቀድመው ከተመረቁበት ኮሌጅ/ዪኒቨርሲቲ ከምዝገባ በፊት Official Transcript ማስመጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
List of First Degree Programs
*******
BEd Civics and Ethics Education
BEd Social Studies (Geography and Environmental Education)
BEd in Social Studies (History)
BEd in Mathematics
BEd in General Science (Biology)
BEd in General Science (Chemistry)
BEd in General Science (Physics)
BEd in Information Technology
BEd in Amharic Language and Literature
BEd in Oromo Language and Literature
BEd in English Language and Literature
BEd in Special Needs and Inclusive Education
BEd in Early Childhood Development and Education
BEd in Educational Leadership and Management
BEd in Educational Psychology
BEd in Physical Education and Sport
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማናጅመንት ዳሬክቶሬት