Christ and Him Crucified

@christisallsufficient


This channel is created to talk about nothing except Christ & Him Crucified.
We talk things in a reformed way.

Any comment & suggestion;
@reformed_1517

Christ and Him Crucified

20 Oct, 03:56


True poverty is not when people are without money, rather it's when people are without Christ.

-P. Roman

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

16 Oct, 16:05


ስለ ጆን ካልቪን ቀለል ያሉ 10 ነገሮች lol
1 የተወለደበት ዘመን ሚካኤል አንጄሎ የሲስቲን ቻፕልን paint ያደረገበት አመትና የሞተበት ዘመን ደግሞ ታላቁ ባለ ብእር ሼክስፒር የተወለደበት አመት ነው😲
2 ሉተር 95ቱን አናቅስት በውትንበርግ በር ላይ ሲለጥፍ ካልቪን የ8 አመት ጩጬ ነበር🥰
3 ጆን ካልቪን በ22 አመቱ የህግ ዶክትሬት ተቀብሏል 🤭
4 ቅስና ለመማር ገብቶ በዘመኑ ስነ ጽሁፍ በመማረኩ የላቲን፣ የግሪክና የ እብራይስጥ ቋንቋዎችን ጠንቅቆ የተማረ ባለ ብልህ አእምሮ አዳሽ ነበር🤔
5 በመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው መጸሃፍ ከስጦሶካዊያን ወገን የሆነው የሮሙ የሴኔካ መጸሃፍ ላይ የተሰራ ኮመንተሪ ነው። በዚህም ሂውማኒስት ምሁር ነበር 😑
6 ካልቪን ወደ አገልግሎቱ ጠልቆ እንዲገባ በተለይ መጋቢ እንዲሆን ያደረገው የጓደኛው የፋሬል እርግማን እንደነበር ይታመናል😨
7 ካልቪን ሉተርን በአካል ለማየት እንደጓጓ፣ እጅግ የምወደው አባቴ እያለ በፍሊፕ ሜላንክተን በኩል መጸሃፍና ሰላምታ ብዙ ጊዜ እየላከለት አንድም ቀን ከሉተር ጋር ሳይገናኙ ነው የሞተው😥
8 ካልቪን በጣም የሚጠየፈው ከመጸሃፍ ቅዱስ አሳብ ተሻግሮ ማሰብን (speculationን) ነው lol
9 ከአባቶች ታላቁ ጎርጎሪዮስና በርናንድ ክላርቮስ ከሁሉም በላይ የካልቪን የነፍስ ወዳጆቹ ናቸው 🤗
10 ካልቪን ለመጥበስ ያወጣው መስፈርት ይህ ብቻ ነው…. “እኔን የሚማርከኝ ብቸኛ ውበቷ _ ጭምትነቷ፣ ለመገዛት መሰጠቷ፣ ልታይ ልታይ ባይ አለመሆኗ፣ ስግብግብ ያለመሆኗ እና ለጤንነቴ አብዝታ የመጨነቋ ጉዳይ ነው!!"😁😁

Christ and Him Crucified

15 Oct, 11:46


ሽክሜን እና ጭንቀቴን
በፊትህ ይዤ እቀርባለሁ
ያለፈው ይበቃኛል
መለወጥ እኔ እሻለሁ

ጌታ ሆይ የልመናዬን ቃል ስማ
ፀሎቴንም መልስልኝ እጅህን ዘርግተህ ታደገኝ
በእራሴ ብዙ ደክሜያለሁ ስለፋ
የማላውቀውን በተስፋ ዕድሜዬን ሙሉ ስለፋ

Dawit Getachew

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

14 Oct, 18:51


አንድ ክርስቲያን እውነተኛ የሆነ ሕይወትንና በረከትን ሊካፈል የሚችለው ቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻ ነው።

በርግጥ ሕይወቴ ያለው ክርስቶስ ጋር ነው። በዚህ ምድር ደሞ መኖሬ ትርጉም የሚኖረው በእውነተኛ ወንጌል ጥሪ አምነው ክርስቶስን ከሚከተሉ ቅዱሳን ጋር በማሳልፈው የጸጋ መካፈል ውስጥ ነው። ክርስቲያን ሕይወትን ከዚህ ውጪ ቢያስብ ይጎሳቆላል።


@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

11 Oct, 17:39


በመከራና ፈተና ሁሉ የጸናችሁ ሁኑ፣ ለሰው አድልዎ አታድርጉ፣ በእምነት የበረታችሁ ሁኑ፣ ከእምነት የሆነ መልካም ሥራን ከመፈጸምም አትቦዝኑ፣ አንደበታችሁን ቆጥቡ፣ በጥበብና ማስተዋል ተመላለሱ፣ በነገር ሁሉ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፣ በምንም ሁኔታ ስለነገ አትመኩ፣ ጨካኝና ስግብግብ አትሁኑ፣ ከእምነት የሆነን ጸሎትም ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፣ የጌታንም መምጣት በናፍቆት እንጠብቅ።

አሜን!

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

07 Oct, 17:34


https://youtu.be/J1hzu_PaQe4?si=n6A1VHOADKXfv5Rg

Christ and Him Crucified

04 Oct, 13:42


የሰው ልጅ የነፍስ ርሃብ አለበት። እረፍትም ይሆናት ዘንድ ይለፋል በብዙ ይደክማል። ይኽም ለነፍሱ መመኪያ አለኝታ እንዲኖራት ጭምር ታስቦ ነው። ነፍስ ግን ሰው ለፍተው ባከማቸው በኃብት፣ በወርቅና እንቁ በሆኑ ነገሮች ከርሃቧ አትጠግብም። በእነዚህ ነገሮች መመካትም መጨረሻው ጥፋት ነው።

የነፍስ ጥያቄን በቃ ከዚህ ምድር ልናገኝ አንችልም። ክርስቶስ ብቻ ነው የነፍሳችንን ጥያቄ ልመልስ ምችል። ከእርሱ ጋር ተወዳጁ። ተገዙለት። እርሱ እውነተኛ የነፍስ መጋቢ ነው። ከዚህ ውጪ የሚገኝ የነፍስ እረፍት ሁሉ ጊዜያዊና ጠፊ ነው።

ነፍሳችን ድጋፍ በሚሆን በእግዚአብሔር ብቻ ትመካ!


@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

29 Sep, 14:35


ክርስቲያን

ሁሉ እንደተፈቀደለት በሚያምንም እንኳ ሁሉ ግን እንደማይጠቅመው ያውቃል። ለራስና ለሥጋ ስሜት ከመኖር ይልቅ ለእግዚአብሔር ክብር መኖርን ይመርጣል። ዓለም ከምትሰጠው ደስታና ተድላ ይልቅ በእግዚአብሔር ደጅ ተጥሎ መሰንበቱን የምወድ ነው። የቅድሚያ ቅድሚያ ለወንጌል የታመነ፤ በወንጌል የሚኖር፤ በወንጌል የሚቆም ነው።

የትም ቢሆን ምንም ቢሰራ፤ ምንም ዓይነት ፈተና ውስጥ ቢያልፍ በእግዚአብሔር ጸጋ የሚበረታ እንጂ ተስፋን የሚቆርጥ አይደለም። ጊዜያዊ የምድር ላይ ቆይታ አሳስቦት የሰማዩን ቤት 'ረስቶ ለዚህች ከንቱ ዓለም የሚወተውት አይደለም።

ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ነገር ሁሉ በአደራ የሚጠብቅ እንጂ በግድየለሽነት የሚተው አይደለም። ሰውን ሁሉ የሚወድ፤ ለሰው ልጅ ነፍስ መጥፋት ድምፁን የሚያሰማ፤ አድሎና ኢፍትሐዊ አሰራርን በግልጽ የሚቃወም ነው።

ዓለምን የከዳ፤ ከሰማይ የሚመጣን የማይናወጥ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጌታን ተግተው የሚጠብቅ ነው። ጥሪው ሰማያዊ ነውና ልቡም ሐሳቡም ያለው እሰማይ ነው።

ክርስቲያን በመሆኔ እደሰታለሁ፤ አሁን ካለኝ ወደፊትም ከምኖረኝ ከየትኛውም ሐብትና ዝና፤ ከዚህ ዓለም ስኬት ይልቅ የምኮራው ክርስቲያን በመሆኔ ብቻ ነው!!


@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

26 Sep, 17:42


@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

26 Sep, 15:24


ክርስቶስ በራስ ቅል ሥፍራ ተሰቀለ ማለት ከዚያ ዘመን ጀምረው እስከ ምጽአት ድረስ በሚነሡ ክርስቲያኖች ጭንቅላት ውስጥ ክርስቶስ ተሰቅሎ መኖር አለበት ማለት ነው። ፍቅሩ፣ መከራውና የመስቀሉ ነገር በጭንቅላታችን ተቋጥሮ እንዲኖር፣ እንዳንረሳው፣ ምንም ጊዜም ተቀርጾብን እንዲኖር ነው። አሁንም በጭንቅላታችን ውስጥ ክርስቶስ ተሰቅሎ ይኖራል! አይወርድም! አይወርድም!

ዛሬ የመስቀሉ ሥፍራ ቀራንዮ አይደለም፣ የእኛ ጭንቅላት ነው። ቀራንዮ ዛሬ ይተረካል እንጂ መስቀሉ የለም። መስቀሉ ያለው በምእመናን (አማኞች) ጭንቅላት (ልብ) ውስጥ ነው።
 
-አለቃ አያሌው ተምሩ


@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

24 Sep, 17:39


“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ

1 ቆሮንቶስ 15:58 NASV

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

24 Sep, 07:48


I'm a new Christian. Now what? 10 Steps:

1) Get baptized in the Triune Name of God.

2) Join a faithful local church with faithful word, sacrament, and discipline.

3) Read Scripture daily, at least a few verses.

4) Pray daily, at least for a few minutes.

5) Honor and care for your parents.

6) Become truly excellent at your vocation.

7) Marry a faithful Christian man or woman.

8) Have as many children as possible.

9) Baptize your children in the Triune Name.

10) Give your children a Christian education.

https://t.me/protestantpost/1278

Christ and Him Crucified

23 Sep, 14:03


People who do not like children are swine, dunces, and blockheads, not worthy to be called men and women, because they despise the blessing of God, the Creator and Author of marriage.

St. Luther

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

21 Sep, 18:49


አወዳደቄ አጅግ አስፈሪ፣ የሚያቆስል፣ እንዲሁም አስደንጋጭ ቢሆንም እንኳ ከኢየሱስ ውጪ ከድካሜ ልያነሳኝ የምችል ማንም የለም።

ደክመን ኃጢአት ውስጥ መገኘታችንን ግን ኖርማል ለማድረግ፤ የሌለ ሥነ-መለኮት ከሰራን፣ አጓል መፈላሰፍ ከጀመርን፡ ያኔ ከባድ አደጋ ውስጥ እንገባለን። ኃጢአት ላደከማት ነፍስ መሰበር እንጂ ካለ ንሰሐ ሰላም የእርሷ አይደለም። በድካም ውስጥ ሁና፣ ሰላም የሚሰማት ነፍስ እርሷ ክርስቶስን አታውቅም።

ኃጢአትን አብዝቶ የሚጸየፍ፣ ብንወድቅ እንኳ ቶሎ ወደ ጌታ የሚያሮጠን ልብ ልኖረን ይገባል። ጸጋው ይርዳን!

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

20 Sep, 04:11


ጌታን ሲጠብቅ ታምኖ የኖረ፥
ብርሃንን ሳያይ ማነው የቀረ?
የነፍስህ ጥማት ናፍቆትህም ሁሉ፥
ጸንተህ ብትቆይ መልስ ያገኛሉ።

Pastor Tesfaye Gabiso

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

17 Sep, 05:34


ኃጢአቴ በደሌ ገብቶኝ ተጸጽቻለሁ
አምላኬ ደግ ነህና ምሕረት እሻለሁ
ቀድሰኝ እቀደሳለሁ

- Daniel Amdemichael

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

16 Sep, 17:04


In the absence of Christ, a man finds no hope.

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

10 Sep, 20:05


መልካም ኣዲስ ዓመት ይሁንላችሁ!

እግዚአብሔር በዚህም ዓመት በምሕረቱ፣ በመግቦቱ፣ በታማኝነቱ፣ በጸጋው ኃይል ያስደንቀን።

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

07 Sep, 14:11


አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”

1 ቆሮንቶስ 15:33 NASV

@Christisallsufficient

Christ and Him Crucified

06 Sep, 15:03


አቤቱ የማዳንኽን ደስታ ስጠን!

ብዙ ጊዜ ተደስተን እናውቃለን። ምናልባት ያሰብናቸው ነገሮች ተሳክተውልን፣ የምንፈልገውን ነገር አግኝተን፣ ጥሩ ምግብ በልተን ጠግበን፣ ቱር ወ'ተን ምናምን...። ይኽ ደስታ ለሰው ልጅ ሁሉ የተቸረ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ በመግቦቱ ፍጥረተ ዓለምን ሁሉ ይመግባልና።

ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ከፍ ያለ ምናልባትም አንዳንዴ ልንገልጸው ማንችለው ደስታ ይሰማል። ስንጸልይ ሸክማችን ስቀለን፣ ቃሉን ስንሰማ፣ የወንጌሉ ስብከት ባዶነታችንን ስያሳየን፤ በመንፈስ ቅዱስ ረድኤት በዚህም በዚያኛውም ዓለም ያለንን መታመናችንን በክርስቶስ ላይ ስንጥል፣ በዚህ ምድር ላይ ከመዳናችን ውጪ አንዳች ደስታን ልሰጥ የሚችል ነገር እንደሌለ ስንረዳና ነፍሳችን ሐሴት ስታደርግ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ባለን እውነተኛ ሕብረት ውስጥ መንገዳችንና አካሄዳችን ስንፈትሽ፤ አንዱ በሌለው ስታነጽ ያለው ስሜትና ሚሰጠን ደስታ እጅጉን ልዩ ነው። ...

እንግዲኽ ይኽ ለክርስቶስ ምርጦች ብቻ የተተው ጸጋ ነው። በመዳን ውስጥ ያለ ደስታ ይለያል። በምንም ሁኔታ ከምንም ዓይነት ነገር ጋር ልናነጻጽረው አንችልም።

“የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።”

— መዝሙር 51፥12)

እግዚአብሔር ሁሉ ጊዜ በምንም ዓይነት ውስጥ ሁኔታ ሆነን በክርስቶስ የማዳን ሥራ ውስጥ ባለው ደስታ ሁሉ እንድንደሰት ዘንዳ ይርዳን!

@Christisallsufficient