አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መነካካት፣ መብላት እና መጠጣት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ትነካካ፣ ትበላ እና ትጠጣ ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 4
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” እኔ የወር አበባ ላይ እያለሁኝ ጭኔ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር"*። أَنَّ عَائِشَةَ حَدَّثَتْهَا أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَّكِئُ فِي حَجْرِي وَأَنَا حَائِضٌ، ثُمَّ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ.
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 3, ሐዲስ 10
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አጥብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْسِلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 279
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አበጥር ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 686
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ በወር አበባ ጊዜ አጥንት እግጥ ነበር፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስጋውን ከእኔ ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸው በማሳረፍ ይግጡ ነበር። እንደዚሁም የወር አበባ ላይ እያለሁ በእቃ ስጠጣ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እቃውን ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸውን በማሳረፍ ይጠጡ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَتَعَرَّقُ الْعَظْمَ وَأَنَا حَائِضٌ، فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَشْرَبُ مِنَ الإِنَاءِ فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَنَا حَائِضٌ .
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 675
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ለእኔ፦ *"ከመሥጂድ ሰሌኑን አምጪልኝ" አሉኝ፥ እርሷም፦ "በወር አበባ ላይ ነኝ" አልኩኝ" አለች። እርሳቸውም፦ "የወር አበባሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ አይደለም" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ " نَاوِلِينِي الْخُمْرَةَ مِنَ الْمَسْجِدِ " . فَقُلْتُ إِنِّي حَائِضٌ . فَقَالَ " لَيْسَتْ حَيْضَتُكِ فِي يَدِكِ
አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በፆም ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር መነካካት፣ መሳሳም እና አብሮ መተኛት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በፆም ጊዜ ትነካካ፣ ትሳሳም ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 89
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በፆም ወር ውስጥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ይስሟት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ فِي شَهْرِ الصَّوْمِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 79
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ከሚስታቸውን አንዷን(ዓኢሻህን) ይስሙ ነበር፥ ከዚያም ደስ ይላት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ إِحْدَى نِسَائِهِ وَهُوَ صَائِمٌ . ثُمَّ تَضْحَكُ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 83
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ሚስታቸውን ይስሙ ነበር፥ ከእናንተ ይልቅ እሳቸው ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يُقَبِّلُ وَهُوَ صَائِمٌ وَكَانَ أَمْلَكَكُمْ لإِرْبِهِ
"ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር" የሚለው ኃይለ-ቃል በፆም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ክልክል መሆኑን ለማሳየት ነው። አንዲት እንስት ከባሏ ጋር የጨዋታ ጊዜ ሊኖራት እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የጨዋታ ጊዜ እንደነበራት ትናገራለች፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 102
አቢ ሠለማህ ከዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደዘገበው፦ "ዓኢሻህ ከነቢዩ"ﷺ" ጋር በጉዞ ላይ ሳለች እንዲህም አለች፦ *"ከነቢዩ"ﷺ" ጋር ሩጫ ተወዳደሩኝ እኔም አሸነፍኳቸው፥ ያሸነፍኳቸው ሳልወፍር በፊት ነበር፡፡ ከወፈርኩ በኃላ ግን ተወዳደርኳቸው አሸነፉኝ። እንዲህም አሉኝ፦ "ብድር መለስኩኝ"*። وَعَنْ أَبِي سَلَمَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا كَانَتْ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي سَفَرٍ قَالَتْ فَسَابَقْتُهُ فَسَبَقْتُهُ عَلَى رِجْلَىَّ فَلَمَّا حَمَلْتُ اللَّحْمَ سَابَقْتُهُ فَسَبَقَنِي فَقَالَ " هَذِهِ بِتِلْكَ السَّبْقَةِ " .
እውነት ሚሽነሪዎች እንደሚሉት ዓኢሻህ በነቢያችን"ﷺ" የሥነ-ልቦና እና የተክለ-ሰውነት ጥቃት ደርሶባት ቢሆን ከላይ ያለውን የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመግባባት ጊዜ ለአማንያን ይጠቅማል ብላ ትተርክ ነበርን? ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የነበሩ የኢሥላም ጠላት ነቢያችንን"ﷺ"፦ "ጠንቋይ፣ ደጋሚ፣ መተተኛ፣ ዕብድ" ወዘተ ሲሉ በዓኢሻህ እና በእሳቸው መካከል የነበረውን ጋብቻ ለምን አልተቹም? እርሷ ስለ ጋብቻዋ በአሉታዊ መልኩ አንድም ቀን አምርራና አማራ የማታውቀውን ሚሽነሪዎች ዙሪያ ገቡን ሳያዩ ኢሥላምን ለማጠልሸት እና ሙሥሊሙን ለማብሸቅ "አስገድዶ መድፈር" የሚሉት የአእምሮ ስንኩላን ስለሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ነገር ግን አላህም ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ
✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም