ግጻዌ

@gitsawe


የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።

ግጻዌ

30 Sep, 21:41


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም ብዙኃን ማርያም
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ስቡህ ከተባለ በኃላ
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ንባርኮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን፤ ስብኩ በዓለ ማርያም ወበዓለ መስቀል ዘዮም።
@EOTCmahlet
መልክአ ማርይም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ፍጽመነ ንዕትብ በዕፀ መስቀሉ፤ ነግሀ ነቂሐነ እምንዋም በከመ ይቤሉ አዕማደ ሰላም፤ ዘዮም መስቀል አሠነየ ዓለመ እንተ በልየ፤ በስነ ማርያም አዋከየ፤ ለክርስቲያን ኮኖሙ ዕበየ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ዮም መስቀል አሠነየ እንተ በልየ ዓለመ አሠነየ/፪/
በስነ ማርያም አዋከየ በስነ ማርያም/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ ዘግምጃ ቤት
ወይቤልዋ እምነ ጽዮን በሐ ወይቤልዋ ደብተራ ፍጽምት በሐ ወይቤልዋ ብርሃነ አህዛብ በሐ ወሪዶ እመስቀሉ ሙቁሐነ ፈትሐ

መልክአ ማርያም
ሰላም ለጒርዔኪ ሠናይ እምወይን፤ በከመ ይቤ ሰሎሞን፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ብርሃን፤ ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ኢያዕጽበኒ ዕርቃን፤ ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን።
@EOTCmahlet
ዚቅ
በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም፤ ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና፤ መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም፤ ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን፤ ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን፤ አጽገዩ ሕዝበ ወመሐይምናን፤ በቤተ መርዓ ተመልዑ ክርስቲያን።
@EOTCmahlet
ወረብ
ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን/፪/
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ማርያም፦
ሰላም ለሐቌኪ በትረ ሌዋዊ ሣውዕ፤ዘኢሐፀነኪ ጠል ወዘኢሰቀየኪ ነቅዕ፤ማርያም ድንግል እግዝእተ መላዕክት ወሰብዕ፤ሰድኒ ብሔረ ፍግዕ በትንባሌኪ ባቍዕ፤ምስለ ኅሩያንኪ ደርገ አሀሉ በስንዕ።

ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አሕዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ

መልክአ ማርያም
ሰላም ለመልክዕኪ ዘተሠርገወ አሚረ፤ ዘያበርሕ ወትረ፤ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ፤ አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ
@EOTCmahlet
ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ማርያም አብርሂ፤ መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ፤ ጽዮን ዮም ተፍሥሒ።
@EOTCmahlet
ወረብ
አብርሂ አብርሂ ማርያም አብርሂ አብርሂ/፪/
መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ ጽዮን ዮም ተፈሥሒ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ ዘግምጃ ቤት-
ፍጽመነ ንዕትብ...

መልክዐ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ: ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ: ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ: ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ: ዘጸገየ ማሕጸንኪ አፈወ ነባቤ።

ዚቅ
ሐፁር የዓውዳ ወጽጌረዳ ግብተ በርሃ ገጻ እምጸሐይ በትእምርተ መስቀል ክቡራት ዕንቊ መሠረታ

ወረብ፦
ግብተ በርሃ ገጻ እምጸሐይ በርሐ ገጻ ግብተ እምፀሐይ/፪/
ክቡራት ዕንቍ መሠረታ ሐፁር የዓውዳ ወጽጌ ረዳ በትምህርተ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ማህሌተ ጽጌ
ብሩካን አርጋብ...
ዚቅ፦
ወበእንተዝ አዘዙነ መምህራነ ቅዱስ ወንጌል፤ አምሳለ ፈጣሪ ልዑል፤ ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል።

ወረብ፦
ወበእንተዝ አዘዙነ መምህራነ ቅዱስ ወንጌል ወንጌል አምሳለ ፈጣሪ ልዑል /፪/
ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል  ማርያም ድንግል/፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት፤ እንተ ኃሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት፤ ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ፤ ግበር ታቦተ በዘትድኅን፤ እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፤ አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ።
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
አክሊለ ተቀጺላ/፪/
አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ/፬/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል፤ ይእቲኬ ቤተ ምስአል፤ ዘአስተዓጸቡ ታቀልል፤ ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል፤ በአክናፈ መላእክት ትትኬለል፤ ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፤ መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል፤ ጽሕፍት ውስተ ወንጌል፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
@EOTCmahlet
አመላለስ
ጽሕፍት ውስተ ወንጌል/፪/
ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ እስመ ለዓለም
ጸሎትክሙ ጽንዕት ሃይማኖትክሙ ርትዕት፤እንተ በኵሉ ትረድዕ፤ሠናያን ወውርዝዋን በምግባረ ጽድቅ አግዓዝያነ አንትሙ፤እለ መነንክምዎ ለዝንቱ ዓለም ኃላፊ፤ከመ ነግድ ፈላሲ ሀልዉ አኃውየ ፍቁራንየ፤ምንት ይበቁዓነ ንብረቱ ለዝንቱ ዓለም፤ኢትርሲቶ ለዝንቱ ዓለም፤ኢወርቅ ሤጡ ለነፍስክሙ፤ሀቡ ናጥብዕ ወንንሣእ መስቀለ ሞቱ ለፍጹም መድኃኒነ፤ኢየሱስሃ ክርስቶስሃ ሰብሕዎ፤ሀቡ አኰቴተ ለስብሐቲሁ፤እንዘ አልብነ ኵሉ ብነ፤እንዘ አልቦ ዘየአምረነ ብዙኃነ የአምሩነ፤ንልበስ ልብሰነ ዘድልው ለነ በኃቤሁ፤ማኅደርነ ዘበሰማያት።

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share #

ግጻዌ

13 Sep, 21:57


“በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቆረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።”
  — ገላትያ 6፥9

"ምንም እንኳ መረዳት ቢከብድህ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ማንበብ አታቋርጥ፣ ምንም የመንፈስ ቅዱስ ሙቀት ባይሰማህ ጸሎት ማድረግን እንዳታቆም፣ ምንም ከልብ የሆነ ጸጸት ባይሰማህም ኃጢያትህን ለካህን መናዘዝ አትተው። ምንአልባትም ስለትዕግስትህ እና ስለጽናትህ ብላ የእግዚአብሔር ጸጋ ወደአንተ ቀርባ መረዳትን፣ የነፍስ ሙቀትን እና ጸጸትን ትሰጥህ ይሆናል።"
— ቅዱስ አባታችን ሺኖዳ ሣልሣዊ

በመንፈስ ቅዱስ ተስፋ በርትተን፥ የሕይወትን ፍሬ የምንሰበስብበት መልካም ዓመት ያድርግልን።

ዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ

ግጻዌ

06 Sep, 10:10


የማታ ተማሪ!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/nicodemus_night_school

ግጻዌ

04 Sep, 17:30


እኔም ተደንቄ የቆሰሉ ሐኪሞቼን እየቆጠርኩ ወደ ቤቴ ተመለስኩ። እንግዲህ ምን እላለሁ? እግዚአብሔር አምላክ እኛ ከምንወዳቸው በላይ ወደውን የእኛን ደስታ ከራሳቸው ኃዘን በላይ የሚያስቀድሙ ራሱ የሰጠን ስጦታዎቻችንን እርሱ ራሱ በቸርነቱ ይጠብቅልን።

ይህን ጽሑፍ ስታነቡ በሃሳባችሁ ሲመላለሱ ለነበሩት ለቆሰሉት ሐኪሞቻችሁ ላኩላቸው።

..................................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ነሐሴ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆

ግጻዌ

04 Sep, 17:29


+ የቆሰሉ ሐኪሞች +
..............................................................

አንድ ወዳጄ ከትንሽ ሳምንታት በፊት አጋጠመኝ ብሎ የነገረኝን ላጫውታችሁማ። ቀኑ የመድኃኔዓለም ዕለት ነበር። በጣም ልቡ የሚቆስልበት እና ለዓመታት እግዚአብሔርን በጸሎት ሲጠይቅበት የነበረ ከባድ የሚያስጨንቅ ችግር አለበት። ይህን ችግር እንዲፈታለት ለመድኃኔዓለም ስዕለት ሳይቀር ተስሎ እንዲሠምርለት እየጠበቀ ነው። በወርኃዊ ክብረ በዓሉ ዕለት የሚታመምበትና ኅሊናው የሚቆስልበት ችግር  አለበትና የዓለም መድኃኒት መድኃኔዓለም ጋር እንደለመደው ሊያለቃቅስ ከመሸ 2:00 አካባቢ ነጠላውን አጣፍቶ ወደ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መሄድ ጀመረ።

  ከሌላው ቀን በተለየ ደግሞ ያቺን ቀን ችግሩንና በሽታውን እያሰበ ሲረበሽና ሲያዝን ነበር የዋለው። ማታ የሄደበትም ምክንያት ከአባቱ ከመድኃኔዓለም ጋር በነፃነት እንዲነጋገርና እንደፈለገ ማልቀስ እንዲችል ነበር። ገና ከቤቱ ሲወጣ ኃዘኑ ተጫጭኖት ዕንባው እያነቀው ነበር። ከቤቱ ሲወጣ ከባድ ዝናብ ዘንቦ ስለነበር ባለ ኮፍያ ሹራቡን አጥልቆ ባጠለቀው ኮፍያ ውስጥ ያሉ ዓይኖች ትኩስ ዕንባን በጉንጮቹ ላይ እያፈሰሱ መንገዱን ጀመረ። ወደ ቤተ ክርስቲያን በእግሩ እየሄደ ሳለ ግን አንዲት ወጣት እናት ሕፃን ልጇን ከጀርባዋ አዝላ፣ በዚያ ከባድ ብርድ ውስጥ ልጇን ባዘለችበት ነጠላ ብቻ ብርዱን እየተከላከለች፣ ጭቃ መሬት ላይ ብጣሽ ፌስታል አንጥፋ ተቀምጣበት በጨለማ ክፉኛ እያለቀሰች ያገኛታል። ተቀምጣ የምታለቅስበት ቦታ መኪናዎች የሚተላለፉበት አደባባይ አካባቢ ስለነበር ሰዎች ብዙም አላዩዋትም። ያዩዋትም ሰዎች ስለመሸባቸው ወደ ቤታቸው በሰላም ለመግባት ስለሚሯሯጡ ቁጭ ብሎ አዋርቶ የሚረዳት ሰው ልታገኝ አልቻለችም። ይህ ወዳጄ ግን ከሩቅ አያት።

  አስቡት እናንተ መሯችሁ፣ አዝናችሁ እያለቀሳችሁ የሚያራራ ለቅሶ የምታለቅስ ልጇን ያዘለች እናት ስታጋጥማችሁ? እንዴት ሊከብድ ይችላል? ወዳጄ ግን ሊያልፋት አልቻለም። "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና የጩኸቴን ቃል ከመስማት ርቀሃልና" የሚለውን የዳዊት መዝሙር ከዕንባ ጋር ሊዘምረው እየሄደ "አምላኬማ ፍጹም ትቶኛል" ብላ የደመደመች መንገድ ላይ የምታለቅስ እናት አጋጠመችው። ራሳችን እያዘንን ክፉኛ የሚያዝንን ሰው ማጽናናት ምንኛ ይከብድ ይሆን? ራሳችን እያለቀስን የሰውን ዕንባ ለማበስ የሚያስገድደን ቦታ ላይ እንደመገኘት ምን የሚከብድ ነገር ይኖር ይሆን?... ወዳጄ ያጋጠመው ይህ ነበር።

  ይህ ወዳጄ ግን ትኩስ ዕንባውን ከዓይኑ ላይ ጠርጎ ኃዘኑን እንደምንም ቻል አድርጎት ወደ እናቲቱ ቀረበ። "እናት ምን ሆነሽ ነው?" ... ቀና ብላ አይታው የመረረ ለቅሶዋን ቀጠለች። ቁጢጥ ብሎ ደግሞ በእጁ ራሷን ቀና እያደረገ "እናት ምን ሆነሽ ነው?.. በጣም መሽቷል እኮ" ይላታል። የሚያዝን ሰው ኃዘኑ notice ሲደረግበት የበለጠ ሆድ እንደሚብሰው ሁሉ እርሷም ጥያቄውን መመለስ ትታ የመረረ ለቅሶዋ ላይ ጩኸት ጨምራበት ማልቀሱን ቀጠለች። ወዳጄም በጣም ራርቶላትና አዝኖላት ቅድም በራሱ ችግር ምክንያት ከዓይኖቹ ላይ ፈሰው የጠረጋቸው ዕንባዎች ደግመው ስለእናቲቱ በመራራት ዓይኖቹ ላይ ቀረሩ። "እንዴ የኔ እናት ኧረ እባክሽን በቃ አታልቅሺ፣ ምን እንደሆንሽ ንገሪኝና ልርዳሽ? በማርያም በቃ አታልቅሺ" ብሎ ይለምናት ጀመር።

እናቲቱም በመረረ ለቅሶዋ እየተንተባተበች "ከበደኝ ፣ አልቻልኩኩም ፣ በቃ ደክሞሞኛልልል" አለችው። "ምኑ ከበደሽ?" ብሎ ጥያቄውን ቀጠለ እያዘነላት። ወዳጄ የራሱ ሸክም ከብዶት "ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ" ብሎ ወደሚጣራው ክርስቶስ እየሄደ የእናቲቱን ሸክም ግን ሊያቀል ክርስቶስ በእርሱ ተሰየመ። እናቲቱም መለሰች "አልቻልኩም፣ ልጄን ማሳደግ ከበደኝ፣ ልጄን የምመግበው የለኝም፣ የምቀይርለት ልብስ የለኝም" አለችው። "እናቴ ባለቤትሽ የት ነው? የልጁ አባት?" .... "የልጁ አባት ወታደር ነው። የት እንዳለም አላውቅም" አለችው በምሬት ድምጽ።

  ቀና አድርጓት ከዓይኖቿ ላይ ዕንባዋን እየጠረገ "እናቴ በእግዚአብሔር ታምኛለሽ አይደለ?" ..."አዎ" ...... "እና ታዲያ እግዚአብሔር የሚተውሽ፣ የሚረሳሽ ይመስልሻል?.... እንኳን እኔና አንቺን ይቅርና ትንኝን እንኳን ሳይዘነጋ የሚመግብ አምላክ እኮ ነው ያለን እናቴ።... አንቺንም የፈጠረሽ፣ ልጅሽንም የሰጠሽ እኮ እግዚአብሔር ነው። ተይ በቃ አታልቅሺ የኔ እናት እባክሽን። እግዚአብሔር ፍጥረቱን መቼም አይረሳምኮ። እንድንጠነክርለት፣ እርሱን ጥለነው እንዳንሄድ ነው በጥቂቱ የሚፈትነን እናቴ። የኔ እናት ወደ እግዚአብሔር ተጠግተሽ አንቺም መበርታት ነው ያለብሽ እሺ፤ መቼም ቢሆን ደግመሽ እንዳታማርሪ እሺ እናቴ፤ እግዚአብሔርን ስታመሰግኚው እኮ የሚያስፈልግሽን ሁሉ ጨምሮ ይሰጥሻል። አይዞሽ በቃ የኔ እናት እሺ" ብሎ በየዋህ አንደበቱ እስካሁን ሰምቶ ካጠራቀማቸው ስብከቶች እያጽናና ብዙ የሚጠግኑ ቃላትን ነገራት። ይህን ሁሉ ሲናገራት ለቅሶዋ ቀስ በቀስ ይበርድና ፊቷም ይፈካ ነበር። "በይ በቃ የኔ እናት ከዚህ በኋላ እንዳታለቅሺ" ብሎ ዕንባዋን ሙሉ አበሰላት። እሺ ብላ አንገቷን ነቀነቀችለት። "የት ነው ቤትሽ?" ብሎ ጠየቃት ለመሸኘት እየተዘጋጀ። እናቲቱም "ቅርብ ነው ቤቴ አትጨነቅ በቃ ራሴ እሄዳለሁ" ብላው ልጇን እንዳዘለች አቅፋው አመሰገነችው። ወዳጄም ኪሱ ውስጥ ለታክሲ ብሎ ከያዘው 50 ብር ሠላሳ ብሩን ለግሷት በቃለ እግዚአብሔር አጽናንቶ ወደ ቤቷ ሸኝቶ እርሱም በተራው ሊያለቅስ ወደ አባቱ መድኃኔዓለም ጉዞውን ቀጠለ።

  ወዳጄም ለእኔ መንገሩን ቀጠለ፤ "አየህ ጆዬ አንተ ምንም ደካማ ብትሆን እግዚአብሔር ለሌሎች ሰዎች ግን ብርታት ያደርግሃል። እንደ መጻጒዕ የአልጋ ቁራኛ የሚያደርግ በሽታ ውስጥ ብትሆን እንኳን ለሌሎች መድኃኒት ሊያደርግህ የታመነ አምላክ ነው። ከእርሱ ሥዕል ፊት ቆመህ የምታነባበት ሺህ የልብ ኃዘናት ቢኖርብህ እንኳን ለሌሎች ግን የደስታቸው ምክንያት ያደርግሃል።እግዚአብሔር የሰውን ቁስል ባንተ ለማከም ግዴታ የአንተ ቁስል እንዲድን አይጠብቅም። አየህ እግዚአብሔር እኮ በጣም ቸር ነው።እንደዚያ ከፍቶኝ በማለቅስበት ሰዓት የሰውን ዕንባ እንዳብስ አደረገኝ። ለምን ረሳኸኝ ብዬ ልጮህበት እየሄድኩ በሰው የተረሳችን ነፍስ በአንደበቴ አጽናንቶ መቼም እንደማይረሳኝ ነገረኝ።

  አየሃ ጆ፤ ሁላችንምኮ በአጠገባችን ያሉ የራሳቸው ብዙ በሽታ እያለባቸው ለእኛ ግን መድኃኒት የሆኑን፤  የሚያለቅሱበት ብዙ ሺህ የልብ ስብራት እያለባቸው የእኛን ዕንባ ግን ከማበስ የማያርፉ፣ እግዚአብሔርን ደጅ የሚጠኑበት ብዙ ጥያቄ እያለባቸው ለእኛ ግን የጸሎታችን መልስ የሆኑን፣ ብዙ ልባቸው የሚቆስልበትና ፊት የሚያጠቁር ኃዘን እያለባቸው እኛ እንዳናዝን ግን ከእኛ ፊት የሚስቁ፣ ፋታ የማይሰጥ የሕይወት ፈተና ውስጥ ሆነው ለእኛ ግን የዕረፍታችን መስክ የሆኑልን፣ በበሽታ እየተሰቃዩ እኛን ግን የሚያክሙ አነዚያ እግዚአብሔር የሰጠን የቆሰሉ ሐኪሞቻችን አሉ። አዎ እነዚያ የማይተኩ ከአምላክ የተሰጡን የታረዙ አልባሾቻችን፣ የተራቡ መጋቢዎቻችን፣ የደከሙ ብርታቶቻችን፣ የሚያለቅሱ ፈገግታዎቻችን፣ የሚያዝኑ ደስታዎቻችን አሉን። አንዳንዴ እግዚአብሔር መቼም እንደማይረሳን የምናውቀው በእነዚህ ወዳጆቻችን ነው። ዘወትር ስለእነርሱ እግዚአብሔርን ማመስገን እና በሕይወት ሳሉ ዕለት ዕለት ፍቅራችንን ልንገልጥላቸው ይገባናል።" ብሎ ወዳጄ ንግግሩን ጨረሰ።

ግጻዌ

04 Sep, 08:01


ብዙዎቻችሁ በጠየቃችሁን መሠረት ምዝገባ መጀመራችንን በደስታ እናበስራለን!

እስከ ጳጕሜን 5 ቀን የ 20% ቅናሽ ማድረጋችንንም ስናሳውቅ በደስታ ነው።

ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ:-
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://register.nicodemusnightschool.com

እናመሰግናለን!

ግጻዌ

02 Sep, 08:42


ኒቆዲሞስን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3፣ 7 እና 19 ላይ ታሪኩን ያገኙታል።

https://t.me/nicodemus_night_school

ግጻዌ

01 Sep, 11:06


የኒቆዲሞስ የማታ ትምህርት መለያ ወይም ሎጎ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/nicodemus_night_school

9,164

subscribers

213

photos

4

videos