FDRE Government Communication Service

@gcsfdregovernment


Use This Link For More Information

https://www.facebook.com/FDRECommunicationService?mibextid=ZbWKwL

https://twitter.com/fdreservice?lang=en

https://www.youtube.com/@gcsInfo-yj2pd

FDRE Government Communication Service

22 Oct, 07:20


የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሊወሰዱ የሚገቡ መፍትሔዎች፦

*ሰላምን ማፅናት
*አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ በአካባቢ ባለው የውሃ አማራጭ በመጠቀም በጥምረት የመስኖ ስራን መስራት
*የተጀመረውን የስንዴ ኢኒሼቲቭ ምርትን ክረምት ከበጋ አጠናክሮ መቀጠል
*በከተማ እና ገጠር ተግባራዊ እየሆነ ያለው የሌማት ትሩፋት ስራን አጠናክሮ መቀጠል
*ዘላቂቅ እና ዘመን ተሻጋሪ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራን እንደየ አካባቢው መስራት
*በየጊዜው በምርምርና አዳዲስ ፖሊሲ ስራውን መደገፍና ማጠናከር
*በጉዳዩ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን በሁሉም አማራጮች መስራት
*የስራ እድል አማራጮችን ማስፋፋትና አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት ጥቅም ላይ ማዋል
*የገበያ አማራጭ እና የቁጠባ ዘዴዎችን መዘርጋት
*ተቋማዊ ጥረት ማጠናከር
*በዘርፉ የሀገር በቀል እውቀቶችን ማዘመን እና ጥቅም ላይ ማዋል
*ለጉዳዩ ተገቢውን ምላሽ መሰጠቱን መፈተሽ

FDRE Government Communication Service

20 Oct, 08:05


"በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ በ620 ሄክታር ላይ የለማው ስንዴ አመርቂ ውጤት አሳይቷል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓም

FDRE Government Communication Service

18 Oct, 11:12


የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?
***************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል። በዛሬው ዕለት የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?

ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ የእንግሊዘኛ መምህር በመሆን አገልግለዋል።

በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽንን (ኢቢሲ) በመቀላቀል በተለያዩ ሀገራት ተዘዋውረው በጋዜጠኝነት አገልግለዋል።

በባልደረቦቻቸው ዘንድ ጠንካራ፣ ሥራ ወደድና የእቅድ ሰው ናቸው የሚባልላቸው የአሁኗ የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፣ቀጠናዊ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ትንተና በመስጠትም ይታወቁ ነበር።

በ2009 ዓ.ም ፋና ብሮድካስትን በመቀላቀል በጣቢያው የራሳቸውን አሻራ ስለማኖራቸውም ይነገራል።

የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሰላማዊት ካሳ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በቆዩባቸው ከአሥርት ዓመት በላይ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በመንቀሳቀስ አገልግለዋል።

በ2013 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ ለአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡት ሚኒስትሯ፤ ቀጥሎም ለመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሚኒስትር ዲኤታነት በመስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም ተሹመዋል።

ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ እስከዛሬ በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሚኒስትር ዴኤታነት ያገለገሉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስተር በመሆን ተሹመዋል።
#EBC

FDRE Government Communication Service

18 Oct, 10:56


ጥቅምት 8፣ 2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡

1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር

FDRE Government Communication Service

18 Oct, 07:49


አሁን ያለው ትውልድ በትብብር መወሰን ያለበት አንድ ነገር ቢኖር ልጆቻችን ላይ አብዝተን በመስራት የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል እንዳለብን ነው።

@AbiyAhmedAliofficial

FDRE Government Communication Service

16 Oct, 18:15


📷
የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች የተለያዩ ተቋማት ጉብኝት

1,412

subscribers

2,933

photos

165

videos