Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

@drestif


ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን!
Inbox me via telegram @DrEstifanos

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

22 Oct, 07:54


ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው አረጋዊያን ነገሮችን ለማስታወስ መቸገር፣ የሚያውቋቸውን ቦታዎች ለማግኝት መቸገር፣ ልሂድ ልሂድ የማለት ባህሪ፣ ጥያቄዎችን መደጋገም፣ የቅርብ ሰዎችን መርሳት፣ ግራ መጋባት... የመሳሰሉት የጤና ለውጦች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ፡፡

12ኛው የስጦታ ወግ
▫️የመርሳት ችግር (Dementia) ምልክቶች
▫️አስቀድሞ መከላከላከያ ዘዴዎች
▫️የመርሳት ችግር የገጠማቸውን አረጋዊያን እንዴት እንርዳቸው?

በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ይሆናል

እንዳያመልጥዎ

📅 ቅዳሜ ጥቅምት 16 ከምሽቱ 1፡00
📍መድረክ፡ ስጦታ የቴሌግራም ቻናል

ለመሳተፍ ይህንን ይንኩ https://t.me/Sitotapsy?livestream

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

22 Oct, 05:55


ስለ ሰሞኑን ጉንፋን

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

21 Oct, 14:10


የሥራ ቦታ ለአዕምሮ ጤና(በ አሚኮ በኩር ጋዜጣ የወጣ)


ስለ አዕምሮ ጤና ይህ ነው ተብሎ ቁርጥ ያለ መገለጫ መስጠት ቢያስቸግርም የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚከተለው ይገልጸዋል፤ ከሌሎች ጋር ተስማምቶ መኖር ሲችል፣ ሥራ ሠርቶ ለራሱም ሆነ ለማህበረሰቡ ፍሬ ያለው ነገር መሥጠት እና ሕይወቱን በአግባብ መምራት ሲችል እንደሆነ ያብራራል፡፡

በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው ከበኩር ጋዜጣ ጋር የስልክ ቆይታ አድርገዋል። ባለሙያው የአዕምሮ ጤና ችግር በሦስት ነገሮች ሊገለፅ ይችላል ይላሉ፤ እነዚህም የአስተሳሰብ (Tought)፣ የስሜት (Feeling) እና የድርጊት ወይም የባህሪ ችግሮች (Behavioral disorder) መሆናቸውን ነው ያነሱት። እነዚህን ሦሰት ነገሮች ታሳቢ ያደረገ መዛነፍ ከማህበረሰቡ እሳቤ የወጡ፣ ውስጥንም የሚረብሹ ስሜቶች እንደሆነ ይገለፃል ብለዋል፡፡

እንደ የአሜሪካ ሳይካትሪክ አሶስየሽን ቅፅ (DSM) ከ360 በላይ የአዕምሮ ችግሮች ያሉ ሲሆን የድብርት፣ የጭንቀት፣ ... በሚል በተለያዩ ማዕቀፎች ይገለፃሉ፡፡

ከዓለማችን ሕዝብ 60 በመቶ ያህሉ ሥራ ላይ እንዳለ ይታመናል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ 15 በመቶ ገደማ ለተለያዩ የአዕምሮ ችግሮች የተጋለጡ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በየዓመቱ በመስከረም ወር መጨረሻ የአዕምሮ ጤና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። የዘንድሮ ዓአለም የአዕምሮ ጤና ቀንም በመስከረም ወር መጨረሻ ተከብሮ ውሏል። በሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና “IT’S TIME TO PRIORITISE MENTAL HELTH IN THE WORK PLACE” በሚል መሪ ሐሳብ ነው ተከብሮ የዋለው።

የሥራ ቦታ ለአዕምሮ ጤና፣ የአዕምሮ ጤና ደግሞ ለሥራ ቦታ ከፍተኛ ግንኙነት አለው የሚሉት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው የአዕምሮ መታወክ ሲኖር ምርታማነት ይቀንሳል ብለዋል። ከሥራ መቅረት በተጨማሪ በሥራ ቦታ መገኘት ቢቻልም በሙሉ አቅም ለመሥራት እንደማያስችል ነው ያስገነዘቡት።

የሥራ ቦታ ጤናማ ካልሆነ ለተለያየ አዕምሮ ችግሮች ያጋልጣሉ። ሥራችን ተጨማሪ ጉልበት (አቅም) የሚጠይቅ ሲሆን በቀኑ ለማድረስ የሚደረግ ሩጫ እና የሥራ መደራረብ ሲኖር ውጥረት ውስጥ ያስገባል። ይህ የሥራ መደራረብ እና በቀኑ ለማድረስ የሚደረግ ሩጫ ጤናማ ላይሆን ይችላል።

በሌላ በኩል የተመጠነ ውጥረት ጥሩ ጎን እንዳለው የጤና ባለሙያው ይናገራሉ። ይህም የበለጠ ለመሥራት ያተጋል የሚሉት ባለሙያው በጣም ውጥረት የሚያበዙ ከሆነ ግን ወደ ጭንቀት ወይም ዲስትረስ ያድጋል። ይህ ማለት የሚያስጨንቀን ነገር እንኳን ቢያልፍ ልንቋቋመው የማንችለው የሰውነትን ሥርዓትን የሚያዛባ ዓይነት ውጥረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

ከዚህ ችግር ለመውጣት ባለመቻላችንም ችግሩ ወደ መታከት(Burnout) ያድጋል። ይህ ደግሞ እንደ አንድ የአዕምሮ ሕመም ይታያል፡፡
ምልክቶቹ ደግሞ ሥራ ቦታ ገና ስንገባ ኃይል ማጣት (መድከም)፣ የሥራ ቦታ ማስጠላት፣ መሰላቸት፣ የሥራ አፈፃፀም መቀነስ፣ ... የመሳሰሉት ናቸው።
እነዚህ ምልክቶች ከሥራ ውጪ በሆነ ሰዓት ላይኖሩ ይችላሉ፤ ከሥራ ውጭ ከቀጠሉ ግን ተስፋ መቁረጥ እየተሰማ ወደ ድብርት ስሜት እና ሌሎች የአዕምሮ ሕመሞች ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ቀደም ሲል የአዕምሮ ሕመም ካለባቸው ሰዎች ላይ ይህ ችግር ከተከሰተ ደግሞ ከባድ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡

በሥራ ላይ የሚከሰተውን የአዕምሮ ችግር ለመከላከል ዋናው መፍትሔ የሚሆነው በሥራ ቦታ አካባቢ ያሉ አመራሮች በተቻለ መጠን የሠራተኞቻቸውን አዕምሮ ጤና መከታተል፣ የሥራ አካባቢውን ጤናማ ማድረግ (ጤና መሆኑን ማረጋገጥ)፣ ሠራተኞች ችግር ካጋጠማቸው ቀድሞ ለይቶ አስፈላጊ እገዛ ማድረግ እና ለዚህ ደግሞ ጥሩ ግንኙነት መመሥረት እንደሚገባ ዶ/ር እስጢፋኖስ አስገንዝበዋል፡፡
ጥሩ ቀረቤታ ከሌለ እና አምባገነናዊ አመራሩም አምባገነን ከሆነ ለሠራተኞቹ ጭንቀትን ሊፈጥር ይችላል፡፡

ሠራተኞች ከሥራ ውጭ በሻይ ሰዓት፣ ከሥራ ሊወጡ ሲሉ ወይም በሥራ ሰዓት ራሳቸውን ዘና የሚያደርጉበትን ቦታ (ሻይ፣ ቡና፣ … ማዕከላት)፣ ማመቻቸት እና የእንቅስቃሴ ማዕከል (wellness corner) ማድረግ ያስፈልጋል፤ በተጨማሪም ማሕበራዊ ሕይወትን የሚያጠናክሩበት የመጽሐፍ ዳሰሳ ዓይነት ዝግጅት ማድረግ የሠራተኛውን ተግባቦት በመጨመር ችግሮቻቸውን ተነጋግረው የሚፈቱበትን መንገድ ሊፈጥር ይችላል፡፡

ባለሙያው እንደሚያነሱት ከነዚህ በተጨማሪ የጭንቀት አስተዳደር (Stress management) ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ችግሮች ቢገጥሟቸው እንዴት መውጣት ይችላሉ የሚለውን እንዲገነዘቡ ማድረግ ይገባል፡፡

ተቋማቱ የአዕምሮ ሕመም ያለባቸው ሠራተኞች ካላቸው ደግሞ ሕክምና እንዲያገኙ ማድረግ ይባል፤ ይህም ሕመሙ ከታከመ ከመሥራት የማይከለክል በመሆኑ ሕክምናውን ማመቻቸት፣ ሕመም ላይ ሲሆኑ ደግሞ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ሥራቸውን ቤታቸው ወስደው እንዲሠሩ ማድረግ፣ የሠዓት ቁጥጥር አለማድረግ፣ ተመካክሮ ረፍት እንዲወጡ መስጠት፣ አግላይ ቃላትን ባለመጠቀም ሥራቸውን እንዲሠሩ ማድረግ ይገባል፡፡

በኛ ሀገር ውስጣዊ ችግሮቻችንን የምንገልፅበት የራሳችን መንገድ አለ የሚሉት ዶ/ር እስጢፋኖስ ጭንቀት የሚገለፀው በአካላዊ ምልክቶች መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አዕምሮ ውጥረት ውስጥ ሲሆን እና ችግሩ ካልተፈታ ወደ አካላዊ ምልክት ይቀየራል፤ ለምሳሌ ራስ ምታት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የልብ ምት መዛባት፣ የደረት እና የሆድ ሕመም፣ ምንም ሳይሰሩ መዛል፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ መነጫነጭ፣ የተግባቦት ችግር፣ ሥራ መጥላት፣ … የመሳሰሉ ምልክቶች ከታዩ የውጥረት እና የመታከት ስሜት ውስጥ እየገባሁ ነው ብሎ መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡

እነዚህ ስሜቶች ሲፈጠሩ የሥራ ባልደረባን ማማከር፣ ከተቻለ ደግሞ በአቅራቢያ ካለ የሥነ ልቦና ባለሙያ ጋር በመመካከር መድኃኒት ሳይወሰድ በምክክር መፍትሔ ማምጣት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም በቤት ውስጥ የተለያዩ ዘና የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን (ዮጋ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ) ማድረግ፣ ራስን መንከባከብ፣ ከቤተሰብ ጋር ማሳለፍ፣ ረፍት ወስዶ ከራስ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ እንደሚገባ ነው የጤና ባለሙያው ዶ/ር እስጢፋኖስ የሚመክሩት፡፡

(ማራኪ ሰውነት)
በኲር ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp:// www.ameco.et/Bekur
በቴሌግራም - https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

20 Oct, 14:29


የተዘጋ የአንጎል ደም-ስርን በመክፈት እስትሮክን ለማከም የሚውለው  በመርፌ የሚሰጥ መድሐኒት :rTPA 

በደም ስር በሚሰጥ መድሐኒት እስትሮክን በማከም ፈር ቀዳጁ የሀገራችን ሆስፒታል ጥቁር አንበሳ ህክምናውን በነፃ እየሰጠ ይገኛል ፤ በብዙ መቶ ሺ የሚሰጥ ህክምና መሆኑን አይዘንጉ ፤

ደም ስር ለአንጎል የኤልክትሪክ ገመድ ለቴሌቢዥን እንደ ማለት ነው ። የደም ስር ምግብና መጠጥ ከልብ ወደ ልዩ ልዩ ክፍለ አካሎች ወስዶ በምላሹ  ከነሱ ዳግም ወደ ልብ የሚመላለስበት ማጓጓዣ መስመር ነው ። ክፍትና አስተማማኝ መሆን አለበት ። የኤሌክትሪክ ገመዱ የተቆረጠበት TV   መስራት እንደማይችል ሁሉ የደም ስር ያላገኘ አንጎል ክፍልም አይሰራም ።  አንጎል የደም ዝውውር መቋረጥን መቋቋም የማይችል የአካል ክፍል ነው ።

እስትሮክን በአመርቂ ሁንታ  ማከም ካስቻሉ የህክምና ውጤቶች አንዱ በደም ስር የሚሰጥ ህክምና ነው ። መ'ዳኒቱን  በደም ስር ሰጥቶ በአንጎል ውስጥ የተዘጉ ደም ስሮችን መክፈት የሚያስችል የህክምና አይነት ነው ። ከልብ ተነስቶ አለያም በአንጎል ደም ስር ውስጥ በተፈጠረ ደም መርጋት አማካኝነት የተዘጉ ደም ስሮችን መክፈት የሚችለው  የጓጎሉና የረጉ ደም ውህዶችን በማሟሟት ነው ። መድሐኒቱ በረመጥ ላይ እንደተጣደ ሞራ እነዚያን የረጉ ደም ውህዶችን ያቀልጣል ፤ በዚህም የደም ስሮቹ ለደም ዝውውር ምቹና አስተማማኝ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ።

መድሐኒቱ ውድ በመሆኑ እና  ስለ ገናናነቱ ወይም ፈዋሽነቱ ብዙም ባለመነገሩ (በቅርብ መታወቁ እና የህክምና ጉዟችን በማደግ ላይ በመሆኑም ጭምር ) በሀገራችን በደንብ የሚታወቅ አይደለም ። በሀገራችን ለመጀመሪያ ግዜ በመንግስት ሆስፒታል ይኸንን መድሐኒት ለእስትሮክ ታካሚዎች መስጠት የጀመረው ጥቁር -አንበሳ ሆስፒታል ነው ። ሆስፒታሉ  ድንገተኛ የእስትሮክ መታከሚያ ማዕከል በማቋቋም ህክምናውን መስጠት ከጀመረ ሁለት አመታት ተቆጥረዋል ።

የማዕከሉ መከፈት የህክምናውን አመርቂ ውጤት በተግባር ማሳየት በመቻሉ ህክምናውን ማስፋፋት እንደሚገባ አሳይቷል ። እስትሮክ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ችግር ነው ።አስቸኳይ ህክምና መፈለጉ ህክምናው በግዜ የተገደበ መሆኑን ያሳያል ። አንጎል በግዜ የተገደበ ነው ። ያለ ምግብና መጠጥ የአንጎል  ህዋሳት በሒወት ሊቆዩ የሚችሉት ለደቂቃዎችና ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው ። <ግዜ አንጎል ነው >  በሚል መፈክር ነው እስትሮክ የሚታከመው ።

አሁንም እስትሮክ የማይታከም ህመም ፤ የሰይጣን ምት ተደርጎ ይታሰባል ። እስትሮክን ማከምም መከላከልም እንደሚቻል ሳይንስ አረጋግጧል ። ከዚያ በላይ ታክመው የዳኑ የአይን እማኞች በብዙዎቻችን አጠገብ ይገኛሉ ። ያንን ያላደረኩ ከኛ መራቃቸውን እናስታውሳለን ። ችግሩ የግንዛቤ አለፍ ሲልም የአገልግሎት ውስንነት መኖሩ ነው ። ተገቢውን የነቃና የተቀላጠፈ የድንገተኛ ህክምና አሰጣጥ ስረዓት በሁሉም ሆስፒታሎች በመዘርጋት ፤እያንዳንዱን ማህበረሰብ ስለ ህመሙ አስከፊነት እና አስቸኳይነት ግንዛቤ በማስረፅ ተጎጂዎችን በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል እንዲመጡ በማድረግ  እስትሮክን በመርፌ በሚሰጥ መድሐኒት ማከም እንደሚቻል እናሳውቅ ።

መድሐኒቱ የሚሰጥበት የግዜ ገደብ አጭር በመሆኑ ተጎጂዎች ቀድመው መድረስ አለባቸው ። እስትሮክ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚከሰት የእጅና እግር መስነፍ ፣ ፊት መጣመም አለያም የመገዳገድና እረፍት የለሽ ትውከት የሚያስከትል ድንገተኛ አካላዊ የአንጎል ችግር ነው ፤ችግሩ የደም ዝውውር መቋረጥ ነው ።

መድሐኒቱ ውድ በመሆኑ በቀላሉ የሚቀመስ አይደለም ። የጥቁር አንበሳ የነርቭ ህክምና ትት ክፍል ባደረገው ጥረት መድሐኒቱን ከለጋሾች በነፃ ለታካሚዎች እያደረሰ ይገኛል ። ምንም እንኳ ከለጋሽ የሚገኝ ልገሳ ቋሚ ይሆናል ባይባልም ለግዜው ግን ብዙዎችን መታደግ አስችሏል ።ቀጣይ ዘላቂ መፍትሔ በሆስፒታሎች በኩል ከሚመለከተው አካል ጋር ተመካክሮ እንዲቀርብ ግንዛቤውን ለመንግስትም ማስረዳት የባለሙያ ሐላፊነት ነው ።

እስከዚያው ሁሉም ሰው እስትሮክ ታማሚን በአፋጥኝ ህክምና ወዳለበት መሔድ እንደሚገባው ይኸን መልእክት ያሰራጭ፤ ያሳውቅ!

References
Jankovic J, Mazziotta JC, Pomeroy SL, Newman NJ, Bradley WG (Walter G. Bradley and Daroff’s neurology in clinical practice, eight's edition P 1393-94.

ዶር መስፍን በኃይሉ ፤ ጥቁር አንበሳ

@HakimEthio

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

10 Oct, 15:05


October 10 is world mental health day!

According to the report 1 in 6 people suffer from mental illness. Celebrating mental health day can have huge contribution by creating awareness, tackling stigma and enhancing mental health advocacy.

This year's them is about prioritizing mental health day at work place. It has been said 60% of world population is at work. Among those, 15% of them will have mental illess at least at a time. This marks the need of prioritizing mental health at work place which has bidirectional relation.

As Sigmund Freud said, there are two main needs for human being, Love/sex and Work. Hence, able to work has huge implication to our mental health.

At the same time, our work can be source of problem, especially when it gets stressful. It is just like food, which is vital to us, and when it gets unhealthy, it results morbidity.

Stressful work can lead to Sress, distress, burnout and many other mental illnesses. On the other side, mental illness can impact our productive by resulting Absenteeism and presentism.

It is a privilege for me to be panelist at the event organized by JSI at USAID office today.

Let's give priority for mental health at work place!

አሻም!

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

09 Oct, 11:35


የአእምሮ ጤና እና አርት ቴራፒ

ቀን፡ ቅዳሜ ጥቅምት 02
ሰዓት፡ ከ9፡00-11፡00
መግቢያ፡ በነጻ
ቦታ፡ ስጦታ ሴንተር፣ 4ኛ ፎቅ፤ ከጦር ሀይሎች እና ቶታል (3ቁጥር ማዞሪያ) መካከል

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

አሁኑኑ ይመዝገቡ https://forms.gle/8pAeB55ymM7iBEUV7

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

08 Oct, 13:37


በየአመቱ October 10 የአለም የአዕምሮ ጤና ቀን ተከብሮ ይውላል::

ዘንድሮም በዓሉ በሃገር ደረጃ 'በስራ ቦታ ለአዕምሮ ጤና ቅድምያ የምንሰጥበት ጊዜ አሁን ነው' በሚል መሪ ቃል በወራቤ ኮምፕርኼንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፓናል ውይይት፣ በጥናታዊ ጽሁፍ ዳሰሳ እና በመሳሰሉ ፕሮግራሞች በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል::

በፕሮግራሙም ላይ የፌድራል እና የክልል ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸው ከተለያዩ ክልሎች እና መስሪያቤቶች የተውጣጡ እንግዶች ተገኝተዋል::

እንደ ሆስፒታልም በአዕምሮ ህክምና ዘርፍ ያለንን በጎ ተሞክሮ ለታዳምያን አስጎብኝተናል::

በስራ ቦታችን ለአዕምሮ ጤናችን ቅድምያ እንስጥ!

አሻም!

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

30 Sep, 08:03


ቪርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?

👉🏽 ቪርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።

👉🏽 ከሶስት አመት በታች የሆኑ ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት የሚጠቀሙ ልጆች የተለያዩ የባህርይ እክሎች እና የተግባቦት እክሎች ያጋጥማቸዋል።

የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች

🧩 ከፍተኛ እንቅስቃሴ (እረፍት የለሽ መሆን)
🧩ትኩረት ማድረግ አለመቻል
🧩 ጨዋታዎች ላይ ፍላጎት መቀነስ
🧩ማህበራዊ መስተጋብር ወይም ተግባቦት አለመኖር
🧩ተለዋዋጭ ስሜት
🧩 የመረዳት እክል
🧩 የንግግር እና ቋንቋ መዘግየት
🧩 የተገደበ የአይን ግንኙነት እና ማህበራዊ መስተጋብር
🧩ተደጋጋሚ ባህሪያት ወይም የተገደበ ፍላጎት
🧩ስሜትን የማቋቋም እክል
🧩ለነገሮች ስሜታዊነት (sensitive)

የቪርቹዋል ኦቲዝም መንስኤ

👉🏽ቪርቹዋል ኦቲዝም ህፃናት በሞባይሎች፣ በታብሌት፣ በቴሌቭዥን፣ በኮምፒውተሮች እና በላፕቶፕ ስክሪን ላይ የረዘመ ጊዜ ሲያሳልፉ የሚፈጠር ሁኔታ ነው።

የቪርቹዋል ኦቲዝም ቴራፒዎች

👉🏽በዋነኛነት የባህርይ ቴራፒ እና የስፒች ቴራፒ
👉🏽የስክሪን ጊዜን ማቆም ወይም መገደብ
👉🏽የአካል እንቅስቃሴዎችን መጨመር
👉🏽ፊት ለፊት የሚናገሩበትን መንገድ መፍጠርና ማስተዋወቅ
👉🏽 ምቹና ደጋፊ አካባቢ መፍጠር

በማህሌት አዘነ
ስፒች ላንጉጅ ቴራፒስት

ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic

አድራሻ :- መገናኛ -ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ

☎️ 0940103047

Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy

Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

26 Sep, 17:30


ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ እህት ወንድሞቼ፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ::

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

26 Sep, 09:26


በየአመቱ October 10 የአለም የአዕምሮ ጤና ቀን መሪ ቃል ተሰጥቶት በአለም ደረጃ ይከበራል:: የዚህ አመቱ መሪ ቃል 'በስራ ቦታችን ለአዕምሮ ጤናችንን ቅድሚያ እንስጥ' የሚል ነው::

በስራ ቦታዎት ውጥረት፣ ጭንቀት ፣ መታከት፣ ድብርት እና መሰል ችግሮች አጋጥሞዎት ያውቃል?

ለመሆኑ በስራ ቦታዎት የአዕምሮ ጤናዎትን ለመጠበቅ ምን እያደረጉ ነው?

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

26 Sep, 08:18


Join us for the 11th round of the 'Sitota Weg' event hosted by the Sitota Center for Mental Health Care!

This week, we will explore the vital topic of workplace and mental health.

Our guest speaker, Mr. Alemayehu Gabisa, a counseling psychologist, will share valuable insights and strategies to enhance mental well-being in professional environments.

Date: Saturday Oct 28
JOIN US: https://t.me/Sitotapsy?livestream
Time: @19:00

Don't miss this opportunity to engage in meaningful discussions and improve your workplace mental health!

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

21 Sep, 18:57


🔵 CALL FOR ABSTRACT 🔵

🔸EVENT:- World mental health day.

🔸HOST:- Worabe Comprehensive Specialized Hospital Collaborating with Ministry of Health

🔸DATE: October 10, 2024

🔸THEME:  "It is time to prioritise mental health in the workplace"

Subthemes:

Workplace stress, distress and burnout

➡️ Impact of mental health problems on workplace productivity

➡️ Workplaces mental health interventions

➡️ Others related to main theme

🔶 Important dates

▪️Abstract submission deadline: September 30, 2024

▪️Notification of acceptance date: October 3, 2024

▪️Full paper submission deadline: October 6, 2024

🔸Submit abstract to:

[email protected]
[email protected]

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

20 Sep, 15:30


📍እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ በሚበዛባቸው አገራት ጾታዊ ጉዳዮችን በግልጽ ማውራት እንደነውር ይቆጠራል፡፡ እርሶስ በዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?

📍ጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቭዥን በጉዳዩ ዙሪያ ከአዕምሮ ህክምና ባለሙያ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ልጆች እድሜአቸውንና የማገናዘብ ደረጃቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ጾታዊ ትምህርት ማግኘት እንዳለባቸው ሰምተናል፡፡

📍ዝርዝር መረጃውን በምሽቱ የ1፡30 የአዲስ ነገር ዜና መጽሔት በቴሌቭዥን ስለምናቀርብ በተለይ ወላጆች እና ልጅ አሳዳጊዎች እዳያመልጣችሁ እንጠይቃለን፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#Shortcode_SMS_7696_WN
https://t.me/ebstvnews

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

20 Sep, 15:30


Check out my interview with EBS today @1:30 local time in the evening

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

15 Sep, 08:10


#የመርሳት ችግር/dementia
***
ሰዎች በጊዜ ሂደት በፊት የነበሯቸው የማሰብ፣የማስታወስና የማገናዘብ ብቃት(Cognitive capacity) እየቀነሰ ሲመጣና በህይወታቸው ላይ ችግር መፍጠር ሲጀምር የመርሳት ችግር ተከሰተ እንላለን::

ይህ ህመም: በተለይም እድሜያቸው ከ65 አመት በሆናቸው ሰዎች ላይ በብዛት ቢስተዋልም: በወጣትና ጎልማሶች ላይ ሊከሰት ይችላል::

ምክንያቶቹም:-

▪️አልዛይመር እና ሌሎች የአዕምር ሴሎችን የሚያጃጁ ችግሮች
▪️የጭንቅላት ደም ስር ችግሮች(ስትሮክ..)፣
▪️የጭንቅላት እጢዎች: ጭንቅላት ላይ የሚደርስ አደጋ: ኢንፌክሽኖች( HIV እና የመሳሰሉ)፣
▪️የንጥረ ነገሮች መዛባት(ቪታሚን እና የመሳሰሉ)

🔹ምልክቶቹም በሚከተሉት የCognitive domain(የግንዛቤ/ማስመሰል ማእቀፍ) እክሎች ሊገለጡ ይችላሉ::

▪️ትውስታ/memory (ብዙ ጊዜ የቅርቡን ጊዜ ትውስታዎችን በመርሳት ይጀምርና ቀስ በቀስ የድሮዎቹን መርሳት ይከተላል)

▪️Language: እንደ ልብ ቃላትን አማርጦ ለመጠቀም ይቸገራሉ

▪️ Complex attention- ሃሳባቸውን ሰብስበው ነገሮችን ለመከወን ይሳናቸዋል

▪️Perceptual-motor- በፊት በቀላሉ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸውን ነገሮች(ምሳሌ: መኪና መንዳት) ሲያቅታቸው ይስተዋላል: ቅልጥፍናቸው ይቀንሳል::

- Executive function- ነገሮችን በትክክል አቅዶ መፈጸም ያቅታቸዋል:: ስራ ቦታ ያልለመደባቸውን ስህተት መስራት ሊጀምሩ ይችላሉ::

- Social cognition- የሰዎችን ሃሳብና ስሜት አንብቦ መረዳት ያቅታቸዋል:: እንግዳ አይነት ባህርይ(ተሳዳቢነት: የብልግና ቃላትን እንደመጠቀም..) ሊያሳዩ ይችላሉ::

🔸 ህክምናው

▪️ችግሩን እንዳመጣው መንስኤ ይለያያል::

በጥቅሉ:

▪️ከላይ የተጠቀሱትን ዋንኛ መንስኤዎችን ማከም:
▪️ህመሙ እየተባባሰ እንዳይሄድ የሚያደርጉ መድሃኒቶችን መስጠት
▪️ተጓዳኝ ችግሮችን ማከም- እንደ ድባቴ: የባህርይ መለወጥና ሳይኮሲስ ያሉትን ማከም
▪️ የስነ ልቦና ህክምናዎች( እንደ ትውስታን የሚቀሰቅሱ ክዋኔዎች ያሉ..)
▪️ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ችግር ፈቺ ስራዎች መስራት (የውርስ:ሃብት ማስተዳደርና መሰል ጉዳዮች)

***
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን የሚያሳዩ ሰዎች ካጋጠሙን ወደ ህክምና ተቋማት በመውሰድ ህክምናን ማግኘት ይቻላል::

አሻም!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ

https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif