Afri ፈጣን መረጃ

@afritoday


እንኳን ደህና መጡ። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎች በፍጥነት የሚያገኙበት ትክክለኛው የAfri today (Afri ፈጣን መረጃ )
የቴሌግራም ቻናል ነው ። እናመሰግናለን።
📢 ፈጣን ሀገራዊ መረጃዎች
📢 ዓለም ዓቀፍ መረጃዎች
📢 አዝናኝ እና አስተማሪ መረጃዎች
📢 ወቅታዊ ጉዳዮች
📢 ሁሉንም በአንድ የሚያገኙበት ቻናል ነው ።

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 14:48


አልሀምዱሊላህ!
በውሳኔህ ተሳስተህ አታውቅም !
ብዙ ሰተኸኝ ነበር ጥቂት ወስደህብኛል ክብርና ልቅና ላንተ የተገባ ይሁን!

አሁንም ቢሆን የጉዳት መጠናችን በውል አልታወቀም ቢሆንም የብዙዎች ወንድሞቼ ንብረት በአጠቃላይ በሚባል መልኩ ወድሟል አላህ ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን የተሻለውን አላህ ይተካልን!!

ሲቀጥል ብዙዎቻችሁ CBE account እየተቀባበላችሁ ልታግዙኝ እየሞከራችሁ ነው!!! በጣም አመሰግናለው!! ግን እኔ ከብዙ አላህ ከሰጠኝ ፀጋ በጥቂቱ ስለሆነ የነካኝ ለኔ የምታረጉትን ገቢ ለወንድሞቼ እንድታረጉ በትህትና እጠይቃለው!!! እንዲሁም የኔን የለጠፋችሁትን እንድትሰርዙት በአክብሮት እጠይቃለው!!!!

Via: ሐሩን_ሰዒድ

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 11:48


መንገድ ለምን መስፋት እንደሚያስፈልግ ትላንት ምሽት ተረዳሁ!

መንገድ የሌለው እና አንድ መግቢያ ብቻ ያለው በመሆኑ ትላንት አደጋው ከፍቷል። ጥረቱ ባይሳካ ከበባው ባይፋጠን ከዚህም ይከፋ ነበር። ግን ፈጣሪ ረድቶናል፣ ተመስገን እንበል! መንገድ ግን ለምን መስፋት እንደሚያስፈልግ ትልቅ ትምህርት ሰጥቶናል። መንገድ አለመኖር አማራጭ አሳጥቶ ስንመለከት በጣም አዝነናል። በጉልበት መንገድ እያበጁ ነበር አስተባባሪዎች እሳቱን ለመቆጣጠር ሲጥሩ የነበሩት።

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 11:42


የእሳት አደጋው በከፊል 🔥

Afri ፈጣን መረጃ

22 Oct, 05:10


" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።

ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።

በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።

ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።

አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።

አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።

ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።

ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (መርካቶ)

Afri ፈጣን መረጃ

21 Oct, 18:07


መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው መድረሳቸውንና እሳቱን ለማጥፋት በጥረት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Afri ፈጣን መረጃ

21 Oct, 07:24


ኢራን የአሜሪካን ደህንነት ሰብራ የሞነቸፈቺው መረጃ በጣም ጨዋታ ቀያሪ ነው።

👉ይህ የደህንነት መረጃ እስራኤል ኢራንን እንደት ማጥቃት እንዳለባት ፤ ምን አይነት ጥቃት መፈፀም እንዳለባት ፤ የትኞቹን የኢራን ኢላማዎች መምታት እንዳለባት ፤ ኢራንን ለማጥቃት ኑክሌየር መጠቀም አለመጠቀሟን ፤ አሜሪካና አጋሮቿ ምን አይነት የማጥቃትና የመከላከል እገዛ ለእስራኤል ማድረግ እንዳለባቸው የሚያትት ሰፊ የስለላ መረጃ ነው የኢራን ሀከሮች ሰብረው በመግባት የሞነቸፉት።

👉ይህ መረጃ የሚቀመጠው አምስት አይኖች " Five eyes" በሚል ጥምረት በሚታወቁት በአሜሪካ ፤ እንግሊዝ ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ብቻ ቢሆንም ኢራን በርብራ ሰብራው ገብታለች። የጠላቶቿን እቅድም በሙሉ አግኝታዋለች።

👉በዚህ የተደናገጡት አሜሪካና እስራኤል በከፍተኛ ሁኔታ አደገኛ ክስተት ነው የተከሰተው ያሉ ሲሆን ጉዳዩን እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል።

👉የሆነው ሆኖ የጠላትን እቅዶች ማግኘት እጅግ ትልቅ ድል ነውና ኢራን አሳክታዋለች።

Afri ፈጣን መረጃ

19 Oct, 18:39


4ኛው የብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች ስብሰባ በካዛን ሩስያ መካሄድ ጀመረ


አራተኛው የብሪክስ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ ካዛን ከተማ ሩስያ እየተካሄደ ነው።

በሩስያ የወቅቱ ሊቀመንበርነት እየተመራ ባለው ስብሰባ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉዳይ ምክትል አስተባባሪ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል።

የካዛን ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት፣የብሪክስ አጋር አገራት አሠራር ማዘጋጀት ላይ አተኩረው ይሠራሉ።

16ኛው የብሪክስ አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቅምት 12 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በካዛን ከተማ ሩስያ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል

Afri ፈጣን መረጃ

19 Oct, 18:14


በሶማሌ ክልል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም በተንቀሳቀሱ 60 የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ የፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

በሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 60 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው በ10 የምርመራ መዝገብ ተከሰው እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በ60 የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ በቂ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃ በማቅረብ በሽብር ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለፍትህ ሚኒስቴር በመላክ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ተዘዋዋሪ ችሎት ሁለት የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በዕድሜ ልክ እስራት፣ 56 ተከሳሾች እንደወንጀል ተሳትፎአቸው ከ6 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአልሸባብ የሽብር ቡድን አባልነት የተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲፈረድባቸው ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

Afri ፈጣን መረጃ

18 Oct, 18:37


የኢትዮጵያ መንግሥት ራስ ገዟ ሶማሌላንድ አዲስ አበባ ላይ ኢምባሲ እንድትገነባ በነጻ ቦታ ሰጥቷል

👉የሶማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢሳ ካይድ፣ ለግዛቲቷ በተሰጣት ቦታ ላይ ትናንት የኢምባሲውን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

👉መንግሥት ለኢምባሲ መገንቢያ ቦታ መስጠቱቱ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ያለውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናክረው የግዛቲቷ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጧል።

Afri ፈጣን መረጃ

18 Oct, 05:26


ሽንፈቱን የአለም ፍፃሜ አታድርጉ ገኒን የገጠምነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይዘን ነው ብለዋል አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ

"ምን እንደሚያስጨንቃችሁ አላውቅም ውሌ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ጥቅምት 23 ነው አትጨነቁ እለቅላቹሀለው''

" በ2 ጨዋታ 4ለ1 እና 3ለ0 ተሸነፍን እንጂ ለማጋነን ተብሎ 7ለ1 መባል የለበትም ልክ አይደለም"

"7ለ1 ተሸነፍን ተብሎ መጋነን የለበትም ክሬዲት ለማሳጣት እንዳይህንባችሁ እሰጋለሁ 8 ለ0 ተሸንፈንም እናውቃለን''

"ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይዘን ነው " ( ዮሴፍ ከፈለኝ )

Afri ፈጣን መረጃ

17 Oct, 19:44


በሞቃደሾ ጥቃት ተፈፀመ

በሶማሊያ ሞቃደሾ በሚገኘው የፓሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙ ታወቀ።

እንደዘገባው ከሆነ ግብፅ ወደ ስማሊያ ካስገባችው መሳሪያ መካዘን አካባቢ መሆኑ ተነግሯል። በጥቃቱ እስካሁን ሰባት ሰዎች ሞተዋል ሲል inside Africa ዘግቧል።

Afri ፈጣን መረጃ

17 Oct, 11:18


ጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ጆን ዳንኤል ላይ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የዋስትና ብይን አጸና

ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአውሮፕላን አንወርድም በማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው የተከሰሱት ስድስት ግለሰቦች ላይ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገባቸውን የዋስትና ጥያቄን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አፀና።

ከ15 ቀናት በፊት በስር ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ የተባሉ ተከሳሾች ግን በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር።

ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የይግባኝ ባዮችን አቤቱታን እና የከሳሽ ዐቃቤ ሕግ መልስ፣ የግራ ቀኝ ክርክርን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ከህግ አንጻር ተገቢ ነው በማለት ብይኑን በማጽናቱ ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ይከታተላሉ።

ዘገባው የፋና ነው።

Afri ፈጣን መረጃ

16 Oct, 19:30


የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ (ፐርሰንት) 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አሳወቀ


ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ዛሬ በይፋ የተበሰረ ሲሆን፤ ዝቅተኛው የሼር ወይም የአክሲዮን መጠን 33 እንዲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

ከፍተኛው የክሲዮን ወይንም የሼር መጠን 3 ሺህ 333፤ የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንደሆነ ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ገልፀዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌ ብር የሚፈፀም ሲሆን፤ ሽያጩ ከጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ይቆያል ተብሏል።

Afri ፈጣን መረጃ

16 Oct, 17:40


ልዩ መረጃ፡ የመንግሥታዊው ባንክ የዶላር መሸጫ ዋጋ መቀነስ

በመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዶላር ከብር አንጻር ያለው ምንዛሬ በመሸጫው ቅናሽ አስመዝግቧል። ባንኩ በመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ሲያደርግ በመግዣው ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርጓል። ባንኩ የባለፈውን ሳምንት ቀናት እንዲሁም ትናንት ጥቅምት 4/2017 ድረስ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ112.39 ሲገዛ የነበረ ሲሆን፣ መሸጫው 123.63 ነበር።

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 5/2017 ባወጣው አዲስ ዋጋ የመግዣ ዋጋው ላይ መጠነኛ ጭማሪ በማድረግ አንድ ዶላር 113.13 እንደሚገዛ አሳውቋል። በአንጻሩ ባንኩ በመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ በማድረግ ለአንድ ዶላር 115.39 ዋጋ አስቀምጧል። በመሸጫ ዋጋ ላይ የተመዘገበው ቅናሽ 8.24 ብር ነው።

Afri ፈጣን መረጃ

14 Oct, 18:44


በዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ሊያደርግ የነበረ ተጠርጣሪ ተያዘ

የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ካሊፎርኒያ ግዛት ያልተመዘገበ እና የተቀባበለ መሳሪያ የያዘ ሰው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ኮቸላ በተባለች የካሊፎርኒያ ከተማ ውስጥ የተያዘው ተጠርጣሪ በተለያየ ስም የተለያዩ ፓስፖርቶች፣ የሀሰት ታርጋ የተለጠፈበት መኪናና የተቀባበለ መሳሪያ ይዞ መገኘቱን የከተማዋ ፖሊስ ኃላፊ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

የፖሊስ ኃላፊው ጨምረውም በእጩ ፕሬዝዳንቱ ላይ የተቃጣ ሶስተኛ የግድያ ሙከራ እንዳከሸፍን ነው የምረዳው ብሏል።

ተጠርጣሪው ቪም ሚለር የተባለ የ49 ዓመት ጎልማሳ መሆኑንና የኔቫዳ ግዛት ነዋሪ ስለመሆኑ ፖሊስ ጠቅሶ ሁለት ሕገ ወጥ መሳሪያ እና ከፍተኛ የመምታት ኃይል ያላቸው ጥይቶችን ይዞ በመገኘት ወንጀል እንደሚከሰስ መግለጹን አልጄዚራ ዘግቧል።

ሆኖም ተጠርጣሪው በዋስ የተለቀቀ ሲሆን ለሚዲያ በሰጠው መረጃ ክሱ ፍጹም ሀሰት እንደሆነና የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ መሆኑን ተናግሯል። “እኔ አርቲስት ነኝ፤ በፍጹም በማንም ላይ አደጋ የማደርስ ሰው አይደለሁም” ሲል አስተባብሏል።

ካሁን በፊት በዶናልድ ትራምፕ ላይ ሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራዎች መደረጋቸው ይታወሳል።