ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም (አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ)
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እያስለማ ያለውን የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አስተዳደር ስርዓት (eTAS) ፕሮጀክት የሙከራ ትግበራ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት፤ የፕሮጀክት ቡድኑ፤ የያያ ክፍያ ስርዓት አ.ማ፣ የባንክ ተወካዮች፣ የዞን እና ከተማ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊዎች እና ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል፡፡
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረት ማህሙድ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለፁት ያለው የታክስ አስተዳደር ስርዓት ኋላ ቀር እና ከወረቀት አሰራር ያልወጣ በመሆኑ ለታክስ መጭበርበር እና ስወራ የመዳርግ እድሉ ከፍተኛ ነበር ብለዋል፡፡
ይህ ቴልኖሎች ግብር ከፋዮች ከእንግልት እንዲወጡ፤ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እና የሚሰበሰበው ገቢ በትክክትል ለመንግስት እንዲደርስ በማድረግ የገቢ አሰባሰቡን የሚያሳድግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ሶስት ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ሲጠናቀቅ ከከፍተኛ ግብር ከፋይ እስከ እርሻ ግብር ከፋያችን የሚያስተናግድ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ የሙከራ ትግበራው በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በሚገኙ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ላይ ነው ብለዋል፡፡
“ዘመኑ የቴክኖሎጅ እና የተሻለ መረጃ ያለው ጌትነትን የሚያገኝበት ጊዜ በመሆኑ ተቋማት አሰራሮችን በቴክኖሎጅ በማስተሳሰር አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳነት መንገሻ አየነ (ዶ.ር) ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲያችን ከሚሰራቸው ዋና ዋና ስራዎች ውስጥ የማህበረሰብ አገልግሎት በመሆኑ የክልሉን ገቢ የሚሰበስበውን የክልሉን ገቢዎች ቢሮ በቴክኖሎጅ ማዘመን መልካም ተግባር እንደሆነ ተናግረው ሌሎችም ተቋማት በሀገር ውስጥ ባለሙያ የሚበለፅግን ቴክኖሎጅ መጠቀም እንዲጀምሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የያያ ክፍያ ስርዓት አ.ማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ አምደፅዮን ጋሻው እንደገለፁት ግብር ከፋዮች ግብራቸውን ለመክፈል ወረፋ እና እንግልት በመቀነስ ቤታቸው ሆነው በማንኛው ሰዓት እንዲፈሉ በማድረግ ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ማበርከት እና የክፍያ ሂደቶችን ለማቅለል ድርጅታቸው እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የሙከራ ትግበራዎን ተግባራዊ ለሚያደርጉ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ እና ለክፍለ-ከተማ ባለሙያዎች ስለ ቴክኖሎጅው አጠቃቀም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ሲሳይ አስማማው
ካሜራ ባለሙያ፡- ማስተዋል ሁነኛው
መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ይከታተሉ፡-
ፌስ ቡክ፡-https://www.facebook.com/AmraNews
https://www.facebook.com/profile.
በቴሌግራም:- https://t.me/bureauof
በዩትዩብ:- https://www.youtube.com/ ገቢያችን
በገቢያችን ተቴሌቪዥን ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 5:30 እስከ 6:00 እና
ሳምንታዊ የገቢዎች ቢሮ የሬድዮ ፕሮግራም ዘወትር እሁድ ከቀኑ 10:10 እስከ 10:40 በአማራ ራዲዮ እና ኤፍኤም 96.9 ይከታተሉን።
እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በ 9504 ይደውሉ