Amhara Communications

@amharacommunications


This is the official Telegram channel of Amhara Regional State Government Communications Office.

Amhara Communications

22 Oct, 13:53


የአዊ ብሄ/አስ ብልፅግና ፓርቲ የስልጠና መርሃ -ግብር በእንጅባራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የስልጠና መርሃግብሩ " የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት " በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተሰጠ የሚገኘው።

በብልጽግና ፓርቲ የአዊ ብሄ/አስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ሰውነት፥ የስልጠናው ዓላማ የአመለካከት እና የተግባር አንድነትን በማጎልበት፣ የመሪዎችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በችግር ውስጥም ሆኖ ስኬቶችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ እንደሆነ አቶ አለሙ ተናግረዋል ።በ2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና የሚያጠናክር ለመዋቅሩ በተደራጀ ሁኔታ ስልጠና እየተሠጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተሰጡት ስልጠናዎችም ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል።ህልመኞች ሀገር ያሻግራሉ፣ ህልመኞች ስንሆን ያለንን ፀጋ እንረዳለን፣ሀገር ስለመገንባትና ህዝብ ስለመለወጥ እናስባለን ነው ያሉት ሀላፊው።አሁናዊው ትንቅንቅ የፖለቲካ አውድ ሳይበግረን ህልማችንን ለማሳካት የተስፋ ስንቅ የሚጨበጥበት መድረክም እንደሆነ አመላክተዋል።

ስልጠናው ሰላም እና መረጋጋት የምንፈጥርበት፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር የገጠመንን ስብራት የምንጠግንበት ትልቅ መድረክም እንደሆነ ተናግረዋል።

የአዊ ብሄ/አስ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው እንደገለፁት ስለነገ መዳረሻችን የምናስብ ከሆነ የጋራ የተግባባ ህልም ያስፈልገናል ብለዋል።ለዚህ ደግሞ ከአምና ዘንድሮ መሻሻል ያለው የትርክት እምርታ(ሪፎርም) እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል ።በስልጠናው የውስጣችንን ልዩነት በማጥበብ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል።

የስልጠናው ግብ ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር፣ የተጀመረውን ሪፎርም መሬት ማስነካት፣ የፓርቲውን እሳቤ እና ፍላጎት መረዳት እና መገንዘብ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡አያይዘውም ጠንካራ ተቋማት መገንባትእና መሪዎች በሥነ ምግባር ተምሳሌት ልንሆንም ይገባናልም ብለዋል፡:

የአማራ ክልል ምክር ቤት መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አየን ብርሃንአቶ አየን ብርሃን ባስተላለፍት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ በችግር ውስጥም ሆኖ የስኬቶች ባለቤት እንደሆነ ገልፀዋል። ሀገርን ለማሻገር የሚያስችሉ የተለያዩ ሴኬታማ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ስልጠናው አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመለካከት ጥራት ግንዛቤ የሚፈጥር እና አሁን ለገጠሙን የሰላም እጦት ችግሮቻችን መፍትሄ የሚቀመጥበት እንደሆነም ተናግረዋል። የገጠምንን የፖለቲካ እና የሰላም ስብራት የሚጠግን እና አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

የአሁኑ ስልጠና አምና ላይ" ከእዳ ወደ ምንዳ "በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ቀጣይ የስልጠና ክፍል ነው።

Awi communication

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

22 Oct, 13:49


ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ የጤፍ ክላስተር ከፊል ገጽታ በፎቶ::

ደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

22 Oct, 13:47


"የሕልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ የአመራር ስልጠና ጀመረ

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች "የሕልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት"በሚል መሪ ሃሳብ ከጥቅምት 12/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም የሚቆይ 3ኛ ዙር የአመራር ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በስልጠናው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ምክትል አስተዳደሪና የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት በሚል ሃሳብ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ወደ ውቢቷ ሰቆጣ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

አቶ ሹመት አያይዘውም በዚህ ስልጠና ሁለት አቢ አላማዎችን ያሉትና በጥቅብ ዲሲፕሊን የሚመራ ሲሆን አንደኛው አላማ ፓርቲያችን ብልጽግና በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና በውጨ ግንኙነት ሃገር ሊያሻገር የሚችል ጥልቅ ሃሳብ የያዘ ስልጠና ነው ሲለ ገልጸዋል።

ከእዳ ወደ ምንዳ ቀጣይ ምዕራፍ የሆነው ስለህልም ጉልበትና ልንደርስበት ስለምንፈልገው እድገት ከጽንስ ሃሳብ ጀምሮ ይህ አመራር ሊረዳቸው የሚገቡ ጉዳዮችና ባለፉት ስድስት አመታት ፓርቲው ሃገር እየመራባቸው የመጣባቸውና በፈተና ውስጥ ሆኖ ያሳካቸው የልማት፣ የፖለቲካና የውጭ ግንኙነት የዲፕሎማሲ ድሎችን በስፋት የምናይበት ስልጠና ነው ሲሉ አቶ ሹመት ገልጸዋል።

ሁለተኛ አላማው ርዕሰ በርሳችን የምንማርበትና ልምድ የምቀስምበት የስልጠና መድረክ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

Amhara Prosperity Party /APP/

Amhara Communications

22 Oct, 13:46


Amhara Communications pinned Deleted message