Bulbula GSS Since 2000 E.C student

@bulbulagss


ውድ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰብ በዚህ ቻናል የሚለቀቁት ጉዳዪች በዋናነት ትምህርትቤቱ ለተማሪዎቹ የሚያስተላልፈው ማስታወቂዎች፤ትኩስናወቅታዊ ትምህርታዊ መረጃዎች እንዲሁም በክፍል ደረጃችሁ ለምትማሩት ትምህርት አጋዥ በሚሆናችሁ ትምህርት መሆኑን እንገልፃለን።

Bulbula GSS Since 2000 E.C student

20 Oct, 19:35


ውድ ተማሪዎቻችን!!!
ጠንካራ ተማሪ ለትምህርት ቤቱ እና ለሀገሩ ከራሱ በላይ ዋስትና ነው።
መልካም እድል ለእናንተ!!

Kabajamtoota barattoota keenyaa!!!
Barataa cimaan/ttuun mata isaarra / isheera darbee (darbitee) mana barnootaa isaaf/isheef akkasumas biyya isaaf/ isheef wabiidha.
Carraa gaarii isiniif hawwina!!

Dear our students!!!
A strong student is a guarantee beyond himself/herself for his/her school and for his/her country.
Good luck to you!!

Bulbula GSS Since 2000 E.C student

17 Oct, 20:00


ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም

በትምህርት ቤታችን በቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሂደናል።

ሽልማት የተሰጣቸው ተማሪዎች ከ500 በላይ ያስመዘገቡ አምስት ተማሪዎች ሲሆኑ ተማሪ ያስሚን ከድር፣ ተማሪ ኤፍሬም ካሳ፣ ተማሪ ሥምረተ መድኅን ሲሳይ፣ ተማሪ መአሩፍ በድሩ እና ተማሪ ቤተልሔም ጨርቆስ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች በከተማ ደረጃም ተሸላሚ የነበሩ ሲሆኑ ተማሪ ያስሚን ከድር በክብርት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የውጭ ሀገር የትምህርት እድል የተሰጣት ተማሪያችን ናት።

በዛሬው ዕለት እነዚህ አምስት ተማሪዎች በሰንደቅ አላማ ሥነ ሥርዓት ላይ ተጠርተው  የምስክር ወረቀት፣ ሜዳሊያ፣ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የጽሕፈት መሳሪያዎች ከት/ቤቱ ተበርክቶላቸዋል።  ተማሪዎቹም ለት/ቤቱ ተማሪዎች ተሞክሯቸውንና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Bulbula GSS Since 2000 E.C student

13 Oct, 11:27


#AAU

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የማደሪያ አገልግሎት ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በመርካቶ፣ በላምበረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡
©tikvahuni

Bulbula GSS Since 2000 E.C student

08 Oct, 17:48


መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የሬሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆ

በ2016 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ለተፈተኑ ተማሪዎች በሬሚዲያል (ማካካሻ) ፕሮግራም ለመማር የሚያበቃው የመግቢያ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

በዚህም በመንግሥት ወጪ ለሬሜዲያል መግቢያ ነጥብ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 204 ሲሆን ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ሴቶች ደግሞ 192 መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በግል ለመማር ደግሞ 31% ከመቶ ውጤት ሆኖ መወሰኑ ተገልጿል።

የትምህርት ቤታችን የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን!!

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ (300 እና በላይ) እና በሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ በየትምህርት ቤታቸው መሙላት እንደሚችሉም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

2,235

subscribers

263

photos

17

videos