Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

@bonafideschools


School

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

21 Oct, 08:22


"አካላዊ ያልሆነው አብዛኛው ህመም የሚመነጨው ከግንኙነታችን ነው" ትዕግስት ዋልተንጉሥ ከቦናፋይድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ለተማሬ ወላጆች በተሰጠ ስልጠና ከተናገረችው የተወሰደ። ቀሪውን ሀሳብ በዚህ ቪድዮ ያገኙታል

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

16 Oct, 07:53


"ወደ ቦናፋይድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ስመጣ የመጀመርያየ አይደለም ። ወደ ቦናፋይድ ስመጣ ደስ ብሎኝ ነው የምመጣው። ኦርጋናይዝድ የሆነ ነገር አለ። ሥራ እንደሚሰራ በደንብ ያስታውቃል።"
ትዕግስት ዋልተንጉስ
የሥነ ልቦና ባለሙያና አማካሪ

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

14 Oct, 16:01


ሰንደቅ ዓላማችን

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

14 Oct, 06:43


ቦናፋይድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ለተማሪ ወላጆች ያዘጋጀው የሥልጠና ፕሮግራም መክፈቻ ዝግጅት

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

07 Oct, 05:58


ጉዞ "ምን ሆኛለሁ ? ፩ " በደማቅ ሁኔታ ባሳለፍነው ቅዳሜ በቦናፋይድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አዳራሽ ተከናወነ።

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

05 Oct, 10:46


ቦናፋይድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው የዛሬው መድረክ ጥቂት የ"ምን ሆኛለሁ?" መጻሕፍት ቅጂዎች ቀድመው ለሚገኙ ወላጆች ይሸጣል።

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

05 Oct, 06:40


እንግዶቻችን ትላንት ምሽት ሀዋሳ ገብተዋል

ለወላጆች እጅግ ጠቃሚ የሆነው መርሃግብራችን ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 25 ቀን 2017ዓ.ም. ከቀኑ 8 ሰዓት በቦናፋይድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት አዳራሽ ይከናወናል።

እንደተለመደው በመርሃግብሩ ላይ በሰዓቱ እንገናኝ።

8:00 መርሃግብሩ ይጀመራል።

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

03 Oct, 09:20


ስለቦናፋይድ ትምህርት ቤትና ትምህርታዊ ጉዳዮች  ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:-

  •    በፌስቡክ | https://www.facebook.com/profile.php?id=61557851047466

  •  በዩቲዩብ  | https://youtube.com/@Bonafideschool-yw4hv?si=T4wesJq5-NnC24f6

  • በቴሌግራም | https://t.me/bonafideschools

•  በቲክቶክ | http://tiktok.com/@bonafide.school

•  በዌብሳይት | www.bonafideschools.com

ገፆቻችን ይጎብኙን፣ ሼርና ላይክ በማድረግ ይከተሉን፡፡ አብረውን ስላሉ፣ ስለጎበኙን እናመሰግናለን! ጤና ይስጥልን!

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

02 Oct, 12:41


ዝም አላሉም፣ ያናገራሉ!
**
በልጅነታቸው ወራት በወላጆቻቸው ወይም በመምህራኖቻቸው "አትመልሱልኝ" ተብለው ያደጉ ልጆች ብዙውን ጊዜ አድገውም የመናገር አቅማቸውን የተነጠቁ ይሆናሉ። የሚናገሩት ጮክ ብለው ወደ ውጭ ሳይሆን በለሆሳስ ወደ ውስጥ ይሆናል። "ዝምተኛ " የምንላቸው ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች ዝም አላሉም። ይናገራሉ። የሚናገሩት ግን እንደ ብዙዎቻችን ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ ነው። በቃላት የሚናገሩትን ስላልሰማን "ዝምተኛ" እናደርጋቸዋለን።
***
ከመጽሐፉ ከገጽ 188 የተወሰደ።

ከደራሲያኑ ጋር ቅዳሜ 8 ሰዓት በቦናፋይድ ዓለም አቀፍ ትምህርት  ቤት አብረን እንወያያለን።

ለመሆኑ መጽሐፉን አግኝተዋል? ለቦናፋይድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መውሰድ ይችላሉ።

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

01 Oct, 16:35


ለልጆቻችን ብለን እየሰራን...
******
"...ወላጅነት ከኃላፊነት በላይ ነው። ከልብስ ማጠብ በላይ ነው። ወላጅነት ማለት ሰውና ሰው (ልጅና ወላጅ) የሚጣበቅበት ስሜት ነው። ጥያቄና መልስ አይደለም። ሀብቱ፣ እውቀቱ አይደለም አሁን የቸገረው። ግን ምን ያህል ወላጅ ነው ቤቱ ገብቶ ለግማሽ ሰዓት ከልጆቹ ጋር የሚያሳልፈው? ቤቱን ጥለን ውጭውን ስንባዝን የምንውለው ለልጆቻችን ስንል ነው። ይሁንና በመባዘናችን ምክንያት ልጆቻችንን እንተዋቸዋለን። ለእነርሱ ብለን እየሠራን ለእነርሱ አንሆንም። ስንቶቻችን ነን ልጆቻችንን "ውሎሽ/ህ እንዴት ነበር?" ብለን የምንጠይቀው?"
******
ከመጽሐፉ ከገጽ 150 የተወሰደ። ለመሆኑ መጽሐፉን አግኝተዋል? ለቦናፋይድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መውሰድ ይችላሉ።

Bonafide School ቦናፋይድ ትምህርት ቤት

30 Sep, 06:53


"እርግማኑ" እንዳይቀጥል...
******

"...በልጅነታችን ወራት በእኛና በወላጆቻችን መካከል ያለው ግንኙነት አድጎ ነው በእኛና በልጆቻችን መካከል የሚመጣው። ...አንድን ሰው የሚሰራው ቤተሰብ ብቻ ነው፣ ወላጅ ብቻ ነው እያልንም አይደለም። የወላጅ እና የቤተሰብ ሚና የጎላ ነው እያልን ነው። የወላጅ ሚና በጎረቤት አይተካም እያልን ነው። ...ቤተሰብ አበላሽቶ ጎረቤት የሚያስተካክለው እጅግ ጥቂት ነው።

...እኛ ጋ የታመመ ግንኙነት፣ የታመመ ፍቅርን፣ የታመመ ትዳርን ይዘው የሚመጡ ሰዎች እጅግ አብዛኛዎቹ የመታመም መነሻ የልጅነት ወቅት አስተዳደጋቸው ሆኖ ነው የሚገኘው። ወላጆች በልማድ ወይም ምንም አያመጣም ብለው እንደቀልድ ያደረጉት ነገር ነው አድጎና ቅርጽ አበጅቶ አሁን ላይ የሚደርሰው።

...ሰዎች መነሻ ችግራቸው 'ከታመመ ቤተሰብ የመጣ ነው' ካልን፣ ቤተሰባቸውስ ከማን ተቀበለው? እሱም ከታመመ ቤተሰቡ፣ የአያት ቤተሰብም ከቅድመ አያት ቤተሰብ። እያለ እያለ እርግማኑ እዚህ ደርሷል። 'እርግማኑ' እንዳይቀጥል፣ እዚህኛው ቤተሰብ ላይ እንዲቋረጥ ነው ይህንን መጽሐፍ [የጻፍነው]።

...መጽሐፉን የጻፍነው የነቃ ትውልድ ለመፍጠር ነው። ...'ልጅ በእድሉ ያድጋል' እንደምንለው፣ 'ቤተሰብም በእድሉ ይመሰረታል' እንዳንል ነው። ያለፈውን ስህተት ላለመድገም ነው። የምናውቀው በሽታ እንዳያመን ለማከም ነው። አመጣጡን የምናውቀው ጎርፍ ጠርጎ እንዳይወስደን ነው። ለደራሽ ጎርፍ ደግሞ ዝግጅት እንድናደርግ ነው።"

*******
ከመጽሐፉ ከገጽ 50-51 የተወሰደ። ለመሆኑ መጽሐፉን አግኝተዋል? ለቦናፋይድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መውሰድ ይችላሉ።