ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ
ፀድቀሻል አለኝ..
ካለሁበት ሸለቆ
ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አ'ርጎኝ
አንቺ ብርቱ አለኝ...
እዩልኝ እዩልኝ..ደግነቱን እዩልኝ።
አስቱ 💙
22 Oct, 05:57
19 Oct, 18:46
18 Oct, 18:12
17 Oct, 15:14
15 Oct, 04:41
14 Oct, 04:06
12 Oct, 08:12
10 Oct, 13:56
07 Oct, 23:11
06 Oct, 05:05
04 Oct, 20:34
02 Oct, 19:52
02 Oct, 12:35
ለራሴ ከተውከኝማ እንደሸንበቆ እንኳ ረዘም ብዬ አልታይም። እንደተቀጠቀጠ ሸንበቆ እንኳን ሰው ላስደግፍ ለራሴም የማላስተማምን ድኩም ነኝና እንደሰው ስልቹ ብትሆን ሰብረህ ትጥለኝ ነበር ፤ አልጠቅምህምና።
ጧፍ ነዶ ነዶ እያለቀ ሲመጣ ይጤሳል። የዛኔ የሰሙ ክርፋት መከራ ነው ፤በዛ ላይ ብርሀንም አይኖረውም። ጌታዬ እንደሰው ብትሆን ጭላንጭሉን ብርሀን ታጠፋው ነበር።
የቃልህ መዶሻ ሲያደቀኝ የሀጥያቴን ሀያልነት ተመልክቼ ስለኔ የተሰቀለው ኢየሱስ ወንጌል ሲበራልኝ ድህነት በጭራሽ እንደማይገባኝ ተረድቼ ነበር። የተዘፈቅሁበትን ሀጥያት እያወቅሁት በየትኛው ፅድቄ እመካለሁ? በአመፅ የምቅበዘበዘዋን ፈልገህ ባዳንከኝ ሰሞን ላስደስትህ ታትር ነበር።
የሚያሳዝንህን ሀጥያት ተጸይፌ ላሸንፍ እታገል ነበር። ክቡር ቃልህን ማንበብ በፀሎት የልብ መሻትህን መፈለግ ስላንተ ማውራት አንተን ማዋራት ቀንበር አይመስለኝም ነበር ። ዛሬ የጉልበቴ መታሰርና የልቤ ዝለት ያኔ ከተፀየፍኩት ሀጥያት ጋር በድርድር የመወዳጀቴ ውጤት መሆኑንም አውቃለሁ።
ታድያ እኔ ራሴ ባለችኝ ትንሽዬ እውቀት መሳቴን ተረድቼ ድካሜን ከጠላሁ ነውርና እንከን ፈፅሞ የሌለብህ ቅዱሱ እግዚያብሄር ደግሞ ይብሱኑ እንዴት ሀጥያቴን ትጠላው ይሆን? ደክሜ ከስጋ ጋር እንደወትሮ መታገል ሲያቅተኝም የኔ ደግ መሲህ አትሰብረኝም ፤ አታጠፋኝም!
ከሀይማኖተኞቹ ፈሪሳውያን ይልቅ በሀጥያቱ ለሚሸማቀቀው ትራራለህ። የኔ መልካም! የኔ ብርቱ! ደካማውን ጥለህ ሀይልህን ከመግለጥ ይልቅ አፅንተኸኝ የምህረት ማሳያ ታደርገኛለህ። ሰላሜ ተናግቶ እምነቴ ሲላላ ከምንም በላይ የምወደው ቃልህን ለማንበብ ከእስትንፋሴ ይልቅ የምትቀርበኝን አባቴን ለማዋራት ተስኖኝ እንዲሁ ስምህን ስጠራ ታዝንልኛለህ።
በሀጥያት ደክሜ ፤ ንስሀ መግባት ሲያታክተኝ ማድረግ የምፈልገውን ፅድቅ ማድረግያ አቅም ያጣሁ ቀን አያጠፋኝም። የፀጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ እስከፍፃሜው ያፀናኛል። ሀያሉ ድካሜን ያግዛል።
አዲስ ፍጥረት መሆኔን እስክጠራጠር እንኳን ብደክም.. በበረቱ ሰዎች ምን ያህል ብቀና..በርትቼ እሮጥ የነበረበትን ጊዜ እያሰብኩ አሁን መንፏቀቅ እንኳን እንደተሳነኝ አይቼ ባነባ ድካሜን አይቶ የሚራራልኝ ደግ ካህን አለኝ።
ምህረቱ የበዛ! የሀጥያተኛውን ጥፋት የማይወድድ አባት አለኝ። ዘይቱን ሲጨምርልኝ ዳግም ብርሀኔ ይታደሳል። የደከሙትን ልጆቹን በፀጋው ደግፎ ያቆማል እንጂ እንደሰው ሸንበቆ አይሰብርም። እንደሰው ከብርቱዎቹ ጋር ወግኖ በሀጥያቴ ዝዬ ሳዝን አያጠፋኝም። ጠወልጋለች ብሎ አይሰብረኝም በፀጋው ባለጠግነት ያፀናኛል እንጂ!
ሸክሜ ሲከብድብኝ ወደኔ ነይ ይለኛል። አባት ነውና ሳይጠየፍ ቁስል ማከም እረፍትን መስጠት ያውቅበታል! ባርያህ ልሆን እንኳ አይገባኝም ብዬ እግሩ ስር ስደፋ ሙት የነበረች ልጄ መጣች ብሎ ቀለበቱን አድርጎልኝ ድግስ ያዘጋጃል።
30 Sep, 16:57
30 Sep, 14:14
26 Sep, 04:12
26 Sep, 04:12
21 Sep, 16:39