Birhan Nega

@birhan_nega


Senior Full-stack Software Engineer
Exelia technologies, Cyprus

Birhan Nega

21 Oct, 16:12


ጭራሽ ስዩም ተሾመ ነጻ ውይይት ላይ አቀረበው 😂
https://youtu.be/DLOztcbbl78?t=189&si=0U0KOZdXrNSNtqlo

Birhan Nega

21 Oct, 05:53


ስራ ፈላጊዎች ስራ የምታገኙበት
ስራ ያላችሁ productive የምትሆኑነት
ተማሪዎች የሚጠቅም የሆነን እውቀት የምትገበዩበት
አዳድስ ባለሙያዎችን የምትተዋወቁበት የሆነ የስራ ሳምንት ተመኘሁ።

#monday
#stayingmotivated
#backtobusiness

Birhan Nega

20 Oct, 03:21


ዛሬ የሰራኸው ስራ ነገ አንተን ይሰራሃል።

Garbage in garbage out አይደል

Birhan Nega

19 Oct, 17:58


Procrastination 😊

Birhan Nega

19 Oct, 08:12


To be absorbable is to be endlessly open to growth—taking in knowledge, adapting to change, and transforming challenges into opportunities for success.

Birhan Nega

19 Oct, 04:42


JavaScript is the language of the web.

The more JavaScript you learn, the more opportunities you will have.

Birhan Nega

18 Oct, 05:25


ሁሉም ሰው የራሱ ምሳሌ አለው።

Addisalem Tafere በመንግስት ቤት እየሰራሁ በነበረበት የስራ ባልደረባዬ ጋር አብረው ስለተማሩ ጠንካራ ጓደኛሞች ነበሩ። አመሻሽ 11 ሰዓት አካባቢ እና ቀን ምሳ ሰዓት እንገናኛለን ። በዛ አጋጣሚ ትውውቃችን እየተጠናከረ መጥቶ አማካሪያችን ሆነ።

አድስ የኔ mentor ብቻ አይደለም። ብዙ ልጆችን ረድቷል እኔም ምክሩን በደንብ ከሚሰሙት ነኝ።
ከተዋወቅን በኋላ ወደ ግል ድርጅት መሄድ እንዳለብኝ አስብኩ።

ከዛ በኋላ
Custor (Addis Ababa)
Taxiye (Addis Ababa )
Excellerent solutions (USA )
High tech systems (Romania)

አብረን የሰራንባቸው ድርጅቶች ናቸው።

ልምደን የማካፍልበት አንዱ ምክንያት mentor የማግኘት እድል ምን ያክል ጥቅም እንዳለው አይቸው ስላለፍኩ ነው። 1/2 of the credit goes to him.

በነገራችን ላይ እንደኔ የሌሊት ምሳ ይበላል 😊

Birhan Nega

18 Oct, 03:43


Bad writers make things complicated.

Great writers keep things simple

Good morning

Birhan Nega

17 Oct, 06:32


ለመጀመሪያ ጊዜ ቱርክ እንደሄድኩ እንግዳ ከሆኑብኝ ነገሮች አንዱ እጅግ ንጹህና ውብ ሱፍ የለበሱና ፍጹም ፕሮቶኮላቸውን የጠበቁ ሰዎች መንገድ ላይ የተለያዩ ጥቃቅን እቃዎችን ሲሽጡ መመልከቴ ነበር። በቆይታ የተረዳሁት በርካታ የባንክ ሰራተኞች፥ ሲቪል ሰርቫንቶች፥ መምህራን እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ቋሚ ሰራ ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በትርፍ ሰዐታቸው የመንገድ ላይ ሸያጭ ላይ መሰማራት የተለመደ መሆኑን ነበር።እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው ጎዳናዎች ላይ በመቆም የባንክ ሰራተኛው ካልሲ፥ መምህሩ ጌጣ ጌጥ፥ የመንግስት ሰራተኛው ውሃ ሊሸጡ ይችላሉ። የዚህ አይነት ትርፍ ሰራ ሀገራችን እምብዛም ስላልተለመደ ለረጅም ጊዜ እንግዳ ይሆንብኝ ነበር።

በሀገራችን ዛሬም ድረስ የተለመደው ማህበራዊ አመለካከት አንድን ሰው ከአንድ ሙያ ጋር ማሰተሳሰር ነው። መምህሩ ከማሰተማር፥ አሊሙ ከማቅራት፥ ዳዒው ከመሰበክ፥ ማህበረሰብ አንቂው ከአክቲቪዝም፥ ምሁሩ እውቀት ከማሰፋፋት ጋር ብቻ ይያያዛሉ። ከዚህ ማዕቀፍ የወጣ ሰራ ሲሰሩ ለብዙዎች እንግዳ ይሆናል፥ አንዳንዱም ተቃውሞውን ያሰማል። ይህ እሳቤ ብዙዎች ከሙያቸው ያለፈ ሌላ ሰራ ላይ በንቃትና በነጻነት እንዳይሳተፉ ማነቆ ሆኗል። ጊዜው፥ እውቀቱ፥ ፍላጎቱና እድሉ እያላቸው የማህበረሰቡን እሳቤ ላለመቃረን ሲሉ ብዙ የሚለወጡበትን እድል ያመክናሉ።

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ አይደለም የገንዘብ ነጻነት የሚሻ መደበኛ የሚባል ኑሮ ለመኖርም ሁለት፥ ሶሰትና አራት ገቢ የሚያሰገኙ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ግድ ይላል።
ለራሰ የሰጠነው ወይም ማህበረሰብ ያሸከመን ደረጃም ሆነ ማዕረግ ከመልፋትና ከመጣርና ከምንታወቅበት ሙያ ውጪ ከመስራት ሊያግደን አይገባም። እንዴት መምህር ሁኜ፥ ባንክ እየሰራሁ፥ ዶክትሬት ጭኜ፥ ዑስታዝና ሽኽ ተብዬ፥ ሲቪል ሰርቫንት ተደርጌ ይሄን እሰራለሁ እያልክ "ብራንድህን" የምትጠብቅበት ዘመን አልፏል። በሀላል መንገድ ለፍቶ አዳሪ ሁን፥ ሌላ ባታተርፍ የአላህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ ይሆንሃል።

ኢሰታንቡል የሚገኘው እድሜ ጠገቡና ትልቁ ገበያ Grand Bazaar መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል ጹሁፍ ተሰቅሏል:

" ለፍቶ አዳሪ የአላህ ወዳጅ ነው"

©️ኢብራሂም አብዱ

Birhan Nega

16 Oct, 17:56


ስለ ቴክኖሎጂ መስኮችና አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከምሁራን ጋር የምንወያይበት መድረክ በይፋ ተጀምሯል።

የቀጥታ ስርጭቱን ለመከታተል በዚህ ሊንክ ግቡ።

መጨረሻ ላይ ጥያቄዎች ካሏችሁ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://t.me/MuradTadesse?livestream

Birhan Nega

16 Oct, 12:00


የኳስ ነገር አይሆንልኝም በተለይ ብሄራዊ ቡድናችን ሲጫወት 😊

Birhan Nega

15 Oct, 05:51


Consistent effort 👌

Birhan Nega

15 Oct, 05:13


@EmmersiveLearning Python ኮርስ ጀምረዋል። እስካሁን የኮርሱ ክፍል 11 ድረስ ተለቋል። በተለይ programming fundamental ለጨረሳችሁ እንደ ቀጣይ step ብትወስዱት ይመከራል።

FYI ማስታወቂያ አይደለም። ጥቆማ ነው

Birhan Nega

14 Oct, 18:33


የሶሻል ሚድያ አካውንታችንን የሚገባውን ዋጋ እንስጠው።

ፓስወርድ ማስታወስ ባንችል ከአካውንቱ ጋር የተያያዙ ኢሜይልና ስልክ ቁጥር የምናውቀው መሆን አለበት።

የፌስቡክና ቴሌግራም አካውንታችሁን ተጠቀምው ወዳጆቻችሁን ገንዘብ በመጠየቅ ብዙ ኪሳራ የሚያደርሱ ዲጂታል ሌቦች ተበራክተዋል።

Birhan Nega

14 Oct, 11:46


Thank you

Birhan Nega

14 Oct, 04:35


The best learning happens when you try to solve a problem with code, not reading about how to write code

Birhan Nega

13 Oct, 16:14


Which one is best?

Birhan Nega

13 Oct, 03:27


ሶፍትዌር ማበልፀግ የቡድን ስራ ነው፡፡ በትንሹ ኮሜርሻል ሶፍትዌር ሲሰራ ቢዝነስ አናሊስት፤ ዲዛይን ፤ ኮዲንግ፤ ቴስተር ፤ ዳታቤዝ አድሚን ፤ ዴቮፕስ ኢንጂነር የሚባሉ ሮሎች ይፈለጋሉ፡፡

አንተ/አንቺ ሁሉንም መሆን መመኘት እንጂ መሳካት አይቀልህ/ሽም፡፡ ስለዚህ የቡድን ስራ መሆኑን መ-ገንዘብ ጥሩ ነው፡፡

ቢዝነስ አናሊስቱ የቢዝነስ ፕሮብሌሙን ይተነትናል፡፡ ዲዛይነሩ ያንን የቢዝነስ ችግር የሚፈታ የሶፍትዌር እልባት አርኪቴክቸር ይነድፋል፡፡ ኮደሩ አርኪቴክቱ የተለመውን ወደ ምድር ያወርዳል፡፡ ኮደሩ የሰራውን ቴስተሩ እክል ፍለጋ ይፈለፍላል፡፡ ዐላማው ተጠቃሚ ጋር ከመድረሱ በፊት የኛኑ ገመና ከቤት እንዳይወጣ በሚል መን-ፈስ ነው፡፡ ዴቮፕስ ኢንጂነሩ ያለቀለትን የፀደቀውን አዲስ ምርት ለተጠቃሚ ማድረስ ፤ ሶፍትዌሩ up and running መሆኑን ማረጋገጥ ስራው ነው፡፡

ስለዚህ ኮሜርሻል ሶፍትዌር ኢንጂነር ለመሆን የሚተልም ሰው አብሮ ለመስራት አመቺ ሰው መሆኑን ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡

ከፍ ሲልም በሶፍትዌር ቢዝነስ ውስጥ ጥልቅ ኢምፓክት መፍጠር የሚቻለውም አቅሞች ወደ አንድ ቋት ሲሰባሰቡ ነው፡፡

@anwarbilcha

Birhan Nega

13 Oct, 03:22


It won’t happen overnight. But if you quit, it won’t happen at all.

Good morning, everyone