ባይራ |Bayra

@bayradigital


ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine)

ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት
ኢ-ሜይል [email protected]

ባይራ |Bayra

21 Oct, 05:31


ባይራ ግብዣ- 7
ወሪሳ

ወሪሳ የዓለማየሁ ገላጋይ ልብ ወለድ ድርሰት ነው፡፡ መቼቱን ወሪሳ እና እሪበከንቱ በሚባሉ ተጎራባች መንደሮች ላይ ያደረገው ይህ ልብወለድ ማህብረሰባዊ ማንነታችንን የሚፈትሽ ግሩም ስራ ነው፡፡ በወሪሳ ያልተፈተሸ ማህብራዊ ቅጥ የለም፡፡ ፖለቲካቸን፣ ነጣቂነታችን፣ ታሪካችን፣ የትምህርት ስርዓታችን ከፍ ሲልም ሰው የመሆን ትርክምክማችን ተፈክሮበታል፡፡ ቀልድን በሚፈጥሩ ተናዳፊ ምጸቶች፣ ፈገግና ቀጨም እያልን የደራሲውንም የቋንቋና የትረካ ብቃት እያደነቅን የምናነበው ስራ ነው፡፡

ዓለማየሁ ገላጋይ “አጥቢያ”፣ “ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር፡ ሕይወትና ክህሎት”፣ “ቅበላ”፣ “የፍልስፍና አፅናፍ”፣ “ኢህአዲግን እከሳለሁ”፣ “ኩርቢት”፣ “የብርሃን ፈለጎች”፣ “መልክአ ስብሐት”፣ “ወሪሳ”፣ “በፍቅር ስም”፣ “ታለ፤ በእውነት ስም”፣ “መለያየት ሞት ነው”፣ “ውልብታ”፣ እና “ሐሰተኛው፤ በእምነት ስም” ፣ “የተጠላው እንዳልተጠላ”፣ “ቤባንያ”፣ ማዕበል ጠሪ ወፍ፣ የተሰኙ መጻሕፍት ደራሲ እና ሐያሲ ነው።

ከደራሲው ብዙ ስራዎች ውስጥ በዚህ እትማችን ወሪሳን ታነብቡ ዘንድ ስንጋብዛችሁ ደስ እያለን ነው፡፡

ግብዣችን ይቀጥላል፡፡
ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

18 Oct, 07:03


ሙሉውን ከዚሁ ገጻችን፣ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9 ላይ ያገኙታል።

ባይራ |Bayra

18 Oct, 04:57


ባይራ ግብዣ- 6
ጥላሁን ገሠሠ፡ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር

ይህ መጽሐፍ በጋዜጠኛ ዘካሪያ መሐመድ የተዘጋጀ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በ2007 ዓ/ም ለህትመት በቅቷል፡፡ እንደገናም በ2013 ዓ/ም ታትሟል።

ጥላሁን ገሠሠ ከተወለደበት ዕለት አንስቶ የቤተሰቡንና የጥላሁንንም ታሪክ ሲመዘገብ ከነበረ ሰው ማስታዎሻ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ድንቅ መጽሐፍ ነው። የጥላሁንን የልጅነት ህይወትና በኋላም በሙያውና በጉልምስና እድሜው ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ ከሳይኮሎጂ (psycho analysis) አንጻር የሚተነትን ነው፡፡

ከጥላሁን ጀርባ ያሉ ሙዚቀኞችንና የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ታሪክ አብሮ በስፋት የዳሰሰበት ይህ መጽሐፍ በጥላሁን ገሠሠ ህይወት ዙሪያ ከተጻፉት መጻሕፍት የተለየ ታሪክና አቀራረብ ያለው ነው፡፡

ይሄን መጽሐፍ ብታነቡት ስለ ጥላሁን ገሠሠ ብሎም ስለ ሀገራችን የሙዚቃ አካሄድ ብዙ የምታገኙበት ነው ስንል ልንጋብዛችሁ ወደድን፡፡

ግብዣችን ይቀጥላል፡፡
ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]


ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

17 Oct, 11:13


በዚህ እትም የ "ባይራታ" አምዳችን ታላቁን ገጣሚ፣ መምህርና ፎክሎሪስት ጋሽ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬውን አስታውሰናል።

ከዚሁ ከቴሌግራም ገጻችን ላይ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ።

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

17 Oct, 07:54


ባይራ ግብዣ- 5

Siddhartha (ሲድሃርታ)

Siddhartha (ሲድሃርታ) በጀርመናዊው ደራሲና የስነ ጽሑፍ ኖቤል ሽልማት አሸናፊው በሆነው በገጣሚ፣ ሰዓሊና ደራሲ ሄርማን ሔሰ (Hermann Karl Hesse) የተጻፈች ልብ ወለድ ናት። የታተመችበት ዓመትም 1922 እ.አ.አ ነው፡፡

የሔሰ ዘጠነኛ ልብ ወለድ የሆነችው ሲድሃርታ መቼቷን ወደ ኋላ ትዘረጋለች፡፡ የቡድሂዝም መስራች በነበረው በሲድሃርታ (Siddhartha Gautama) ዘመንም ትደርሳለች፡፡

በዋናነት ውሰጣዊ መቃተትና ውስጣዊ ማንነትን ብሎም መንፈሳዊ መገለጥንም ለማግኘት የሚደረግ ጉዞ ተፈክሮባታል፡፡ በእኛ ሃገርም ሲድሃርታ በሚል ርዕስ በያሬድ ብርሃኑ ሳህሌ ተተርጉማ ቀርባለች፡፡ ይህቺን ልብ ወለድ ብታነብቧት አንዳች ነገር ታተርፋላችሁ በሚል ልንጋብዛችሁ ወደድን፡፡

ግብዣችን ይቀጥላል፡፡
ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

17 Oct, 04:46


እንኳን ተወለዱ ጋሽ ሀዲስ ዓለማየሁ

ከዚያ ኢትዮጵያ ትታየኛለች። ኢትዮጵያ ከስታ፥ ተንገላታ፤ ተጎሳቁላ፥ እያለቀሰች ትመጣና “እዩኝ እንዲህ ሆንሁ! አምሮብኝ፥ ተከብሬ፥ ታፍሬ፥ እኖር የነበርሁይቱ አሁን፥ በእናንተ ጊዜ እንዲህ ሆንሁ!” ብላ ልጆቿን ኢትዮጵያውያንን ስትወቅስ፥ ስትማጠን፥ ስትረግም ትታየኛለች፡፡

(ትዝታ ፥ በሀዲስ ዓለማየሁ ገጽ 161)


እነሆ ከዛሬ 115 ዓመት በፊት ጥቅምት 7፥ 1902 ዓ/ም ፥ በጎጃም፥ በጎዛምን ወረዳ፥ በእንዶዳም ኪዳነምህረት ቀበሌ ተወለዱ።

ታላቁ መምህር
አርበኛ
ዲፕሎማት
ጸሐፌ ተውኔት
ደራሲ
ሀዲስ ዓለማየሁ።

በጽሑፍ ዘርፍ እነዚህን አበርክተውልናል፡፡
ያበሻና የወደኋላ ጋብቻ -ተውኔት
ፍቅር እስከ መቃብር- ልብወለድ
ወንጀለኛው ዳኛ- ልብ ወለድ
የእልም ዣት- ልብ ወለድ
ተረት ተረት የመሰረት- ተረቶች
ኢትዮጵያ ምን አይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል- ስነ መንግስት
ትዝታ- በጣሊያንና በኢትዮጵያ መካከል በነበረው የ5 ዓመት ጦርነት ያሳለፉትን የአርበኝነት ተግባርና የህይወት ትዝታዎቻቸውን የሚያወሱበት፡፡

በዲፕሎማሲው ያበረከቱት እልፍ ነው፡፡ ለዚህም በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት አዳራሽ ህያው ምስክር ነው፡፡ በአርበኝነቱ ህይወታቸውን አስይዘው ከጎጃም እስከ ትግራይ፥ ከትግራይ እስከ ሱዳን፥ ከሱዳን እስከ ጎሬ፥ ከዚያም እስከ እስር ተዋድቀዋል፡፡ በስነጽሑፉ ያበረከቱትን መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡

እናም እኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ በመወለዳቸው ሀገር ብሎም ዓለም ብዙ አትርፋለችና በእሱ ደስ ይለናል፡፡

እንኳን ተወለዱ ጋሼ!
(ነፍስ ኄር)

(ፎቶ በአዘጋጁ፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኘው የደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ ሀውልት)

ባይራ |Bayra

16 Oct, 11:54


አንዳንዴ
በደብተራው

አንዳንዴ፦
ተራራው እንኳን ብታይው፣ በነፋስ ሞገድ ይናጣል
ፀሐይ ፊት መቆም የቻለም፣ በሻማ ሙቀት ይቀልጣል
ካሰሙት እልልታ ይልቅ፣ ጉድ ያሉት ከጉድ ያወጣል
ካልደመቁበት ወርቅ አልማዝ፣ ያጌጡበት አምባር ይበልጣል፤

አንዳንዴ፦
መናን ከሰማይ ከምሻ፣ ይሻላል ያገር ባቄላ
እድሜ ቀጥል ነው ዝምታም፣ ፈገግታ ከማይሰጥ መላ፤

አንዳንዴ፦
ከብዙ ስርሚዜ ይልቅ፣ የገዛ ጥላህ ይበቃል
አስር ክንዶችን ከመደገፍ፣ ያቀፉት አንዱ ይሞቃል፣

አንዳንዴ፦
እንደ እራፊ ተጥሎ፣ በተፀየፉት በረካ
ቋጥኙ ሀመልማል ሁኖ፣ ሜዳ ገደሉ ሲፈካ
የተለሙት ጭማድ በልቶት፣ ወንዝ አፈራሹ ይፀድቃል
ንቀው የጣሉት ከደጃፍ፤ ፀባኦት ድረስ ይመጥቃል።
አ ን ዳ ን ዴ .... ።


————————————————-
————————————————-


(ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቅጽ 1 ቁጥር 9)


ኑኒ ባይራክ!
ታላለቆች ነን!

ባይራ |Bayra

16 Oct, 07:08


ዮ ማስቃላ- መስቀልና ዶርዜ

ወልደሐዋርያት ዘነበ ስለ መስቀልና ዶርዜ ቆንጆ ጽሑፍ አስነብቦናል።

እዚሁ የቴሌግራም ገጻችን ላይ በነጻ ማንበብ ትችላላችሁ።

ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9።

አብሮነታችሁ አይለየን።

ኑኒ ባይራክ!
ታላለቆች ነን!

ባይራ |Bayra

16 Oct, 04:20


ባይራ ግብዣ - 4
የማለዳ ድባብ

የማለዳ ድባብ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2009 ዓ/ም የታተመች የግጥም መድብል ናት፡፡ ደራሲውም በዕውቀቱ ስዩም ነው፡፡

የማለዳ ድባብ በግጥማዊ ውበቷ ምሉዕ የምትባል መድብ ናት፡፡ በግጥም መልክ የሚነሱ ሃሳቦችም ከቋንቋ ቀረጻ ጋር ተዳምረው ለልብ ይደርሳሉ፡፡

በዕውቀቱ ስዩም ከማለዳ ድባብ በፊት ኗሪ አልባ ጎጆዎች ሚል የግጥም መድብል 1995 ዓ/ም፣ በራሪ ቅጠሎች የሚሰኝ ልብ ወለድ በ1996 ዓ/ም፣ እንቅልፍና እድሜ የሚል ልብወለድ በ1999 ዓ/ም፣ የሣት ዳር ሃሳቦች የሚል የግጥም መድብል በ2000 ዓ/ም፣ ስብስብ ግጥሞች በሚል ርዕስ በ2001 ዓ/ም፣ መግባትና መውጣት የሚል ልብ ወለድ በ2002 ዓ/ም እንዲሁም ከአሜን ባሻገር የሚሰኝ ታሪካዊ ወግ በ2008 ዓ/ም ለአንባቢ አቅርቧል፡፡ ከማለዳ ድባብ በኋላም አዳምኤል የሚሰኝ የመጨረሻ የግጥም ስራውን ለአንባቢ አድርሷል፡፡

ይህችን መድብል ታነቧት ዘንድ ለጊዜው ጋበዝን።

ግብዣችን ይቀጥላል፡፡
ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

15 Oct, 11:27


አንዳንዴ---

ውብ ግጥም በገጣሚ ደብተራው!

ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9 ላይ የተወሰደ።

ያንብቡን!
ቤተሰብ ይሁኑ!
ስትፈቅዱ ለሌሎች ይደርስ ዘንድ አጋሩልን።

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

15 Oct, 05:03


ቡድናዊነት!

ከመቼውም ጊዜ በላይ ግለሰባዊነት (individualism) በሚቀነቀንበት በዚህ ዘመን ለዓለም ህዝቦች መለያቸው ቡድናዊ አስተሳሰብ ነው። ሆ ብሎ መውገር፣ ሆ ብሎ መስቀል፣ ሆ ብሎ ማውረድ የጋራ መልካችን ነው።

የዓለምን መልክ የቀሩት ጥቂት ግለሰቦች የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ። ብዙዎቹ በቡድኖች ተገፍተዋል። እንደኔ ካላሰብህ በሚል የመጀመል እሳብ አግልለዋቸዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቆንጆ ጽሑፍ ያጋራን ወንድማችን ብርሃን ደርበው ነው። በባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9 እትም "ቡድናዊነት በድናዊነት?" በሚል መጠይቃዊ ርዕስ አጠር መጠን ያለች ተናዳፊ መጣጥፍ አስኮምኩሞናል።

እዚሁ የቴሌግራም ገጻችን ላይ ታገኙታላችሁ። በነጻ ይኮምኩሙ!

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

15 Oct, 04:25


ባይራ ግብዣ - 3
ማስታዎሻ

ማስታዎሻ በደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን በደራሲ ዘነበ ወላ የተጻፈ መጽሐፍ ነው።

ደራሲ ዘነበ ወላና ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር አብረው በነበሩባቸው ዓመታት ያሳለፏቸውን ጊዜያት፣ የጋሽ ስብሃትን ህይወት፣ የንባብ ባህል እንዲሁም ስለ ተለያዩ ጉዳዮች በሰፊው የተተነተነበት መጽሐፍ ነው። ማንኛም የጋሽ ስብሃትን ህይወት ማዎቅ ለሚሻ፣ በጋሽ ስብሃት ዙሪያም ጥናት ማድረግ ለሚፈልግ ይሄ መጽሐፍ ተመራጭ ነው።

ባይራ ዲጂታል መጽሔትም ማስታዎሻን ስትጋብዝ አንዳች ነገር እንደሚገኝበት በመተማመን ነው።

ግብዣችን ይቀጥላል፡፡

ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 7 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

14 Oct, 08:21


ኑኒ ባይራክ!

ባይራ |Bayra

14 Oct, 05:01


ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ በባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 9 እትማችን "ብርሃን ጨልጦ መስከር (የእሳቱ ሥላሶች)" በሚል ርዕስ ድንቅ ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ እዚሁ የቴሌግራም ገጻችን ላይ በነጻ መኮምኮም ትችላላችሁ፡፡

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]


ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

11 Oct, 14:05


እነሆ!

ባይራ ዲጂታል መጽሔት

ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 9

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]


ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

11 Oct, 04:19


ባይራ ዲጂታል መጽሔት

ቅጽ 1 ቁጥር 9

ዛሬ ማታ በቴሌግራም ገጻችን ይጠብቁን! ገጹን በመቀላቀል ቤቴሰባችን ይሁኑ።
ቅንነቱ ያላችሁ ለሌሎችም አጋሩልን።

Stay tuned!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

10 Oct, 13:51


ባይራ ዲጂታል መጽሔት

ቅጽ 1 ቁጥር 9

ነገ ዓርብ ማታ ይጠብቁን!

Stay tuned!


በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!

ባይራ |Bayra

10 Oct, 04:20


ባይራ ግብዣ - 2
ኦቶባዮግራፊ

ኦቶባዮግራፊ ከስሙ እንደሚያመለክተው የፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያምን ህይወት የሚያትት መጽሐፍ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የህይወት ታሪኬ በሚል ርዕስ በ1946 ዓ/ም እንደታተመ ይነገራል። በድጋሜም ኦቶባዮግራፊ በሚል ርዕስ በ1998 ታትሟል፡፡ ጸሐፊው ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት በታላቁ የአድዋ ጦርነት ወቅት የ12 ዓመት ልጅ ሆነው ተሳትፈዋል፡፡ ከድል በኋላ በራስ መኮንን ጥያቄና በአጼ ምኒልክ ይሁንታ ወደ ሩሲያ ሄደው ለ11 ዓመታት ተምረው በልጅ እያሱ ዘመን ተመልሰዋል፡፡ ከልጅ እያሱም ሆነ አጼ ኃይለስላሴ ጋር ሆነው ሀገራቸውን ለመለወጥ ደፋ ቀና ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስምና አስተዋጽኦ ያላቸው ሰው ናቸው፡፡ በንጉሱ ዘመን የተዘጋጀውን የመጀመሪያውን ህገ መንግስት ያረቀቁት እሳቸው ናቸው፡፡ የአሰበ ተፈሪ ወይም ጭሮ ከተማም መስራች ናቸው፡፡በዚህ መጽሐፋቸውም ህይወታቸውን፣ ለሃገራቸው ያላቸውን ቀናኢነትና ቁጭታቸውን ከትበዋል፡፡ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ መሆኑን ለመመስከርም እንወዳለን፡፡

ግብዣችን ይቀጥላል፡፡
ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8 የተወሰደ

በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ!
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!