በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

@aafarmersandurbanagriculture


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

21 Jan, 00:26


ጥራት ያለው የወተትና የእንቁላል ምርት ከገበያ ባነሰ ዋጋ ከእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል እያገኙ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)

የእንስሳት ልማት የልህቀት ማዕከል ጥራት ያለው የእንቁላልና የወተት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች እያቀረበ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ማዕከሉ ጥራት ያለው የእንቁላልና የወተት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ በማቅረብ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ረገድ አወንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን የማዕከሉ ኃላፊ ዶ/ር ፀጋ ለማ ገልፀዋል።

በማዕከሉ የከብት ማድለብ፣ የእንቁላል ዶሮ እርባታ እና የወተት ላም እርባታ እያከናወነ ሲሆን እንቁላል በ8 ብር፣ አንድ ሊትር ወተት በ75 ብር እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች እያቀረበ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በማዕከሉ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን እየሸመቱ ያሉ ተጠቃሚዎች የእንቁላልና የወተት ምርት በገበያ ላይ ካለው ዋጋ ባነሰ እያገኙ መሆኑን የገለፁለት መሆኑን ማዕከሉ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ፔጃችን ላይ ገልፃል፡፡

የማዕከሉ ኃላፊ የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል ምርት ለገበያ በማቅረብ ገበያ ከማረጋጋት ባሻገር የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው በ104 ማህበራት ተደራጅተው እየሰሩ እንደሚገኙና በሌሎች የስራ ዘርፎችም ለበርካታ ነዋሪዎች የስራ እድል መፈጠሩን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ተጨማሪ ማዕከላትን በሌሎች ክፍለ ከተሞች ለማስፋፋት በከተማ አስተዳደሩ እቅድ እንደተያዘ የተናገሩት ዶ/ር ፀጋ ምርት ለነጋዴ እንዳይደርስ አሰራር ተዘርግቷል ሲሉ አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

21 Jan, 00:26


ተጠያቂነትን ለማስፈን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጥንቃቄ መለየት ይገባል፡፡

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ

በከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር፣ የቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል አድርጓል፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ አባላት (አቶ ቴዎድሮስ ሙሉጌታ፣ አቶ ሙሉጌታ አለሙ እና አቶ ዘውዴ ተፈራ) የመልካም አስተዳደር ችግሮች በየደረጃው በጥንቃቄ ስለመለየታቸው፣ ውይይት የተደረገባቸው እና የዕቅድ አካል ሆነው ችግሮቹ እየተፈቱ ያሉበትን ሁኔታ የማረጋገጥ ስራ ሰርተዋል፡፡

የኮሚሽኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በአግባቡ ተለይተው፣ ለአመራሩና ለባለሙያዎች ግንዛቤ በማስጨበጥ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ችግሮቹ መፍትሔ እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ድጋፍና ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ወርቅነህ በበኩላቸው የኮሚሽኑ አገልግሎት አሰጣጥን ቅሬታና አቤቱታ በማይፈጥር መልኩ ለማስኬድ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቴክኒክ አማካሪ የሆኑት አቶ በፍቃዱ ሰለሞን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የህግ ማዕቀፍ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተለይተው አሰራር እየተበጀላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቅሬታና አቤቱታ ህግ ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ በዳዳ በበኩላቸው እንደ ኮሚሽን በርካታ ቅሬታዎች የሚነሱት ከመብት ፈጠራ ጋር በተያያዘ ሲሆን ከመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ጋር በመሆን ችግሩን ለመፍታት ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ለድጋፍና ክትትል ቡድኑ አንስተዋል፡፡

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ከመልካም አስተዳደር አንፃር፣ ከቅሬታና አቤቱታ አቀባበልና አፈታት ጋር በተያያዘና ተጠያቂነትን እያረጋገጡ ከመሄድ አኳያ በሰነድና በቃለመጠይቅ ያገኛቸውን ነጥቦች መነሻ በማድረግ አቅም መሆን የሚችል አስተያየትና የቃል ግብረ-መልስ ሰጥቷል፡፡

የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታሁን አበበም የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ያነሳቸውን ነጥቦች ለቀጣይ የዕቅዳችን አካል በማድረግ ለተገልጋዮቻችን ከባለፈው የበለጠ የተሳለጠ አገልግሎት የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

21 Jan, 00:20


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡
1. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ - የቱርዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ- የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

21 Jan, 00:17


ዕቅድ ከሪፖርት ጋር ተናባቢ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም
የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ ፋሩቅ ጀማል የከተማ ግብርና ዘርፍ እና የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ከዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ገምግመዋል፡፡
ዕቅድ ከሪፖርት ጋር ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ተናባቢ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑም በውይይቱ ወቅት ትኩረት ተሰጥቶ ተነስቷል፡፡
በሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ወቅት የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ክፍተቶችን ደግሞ ለቅሞ በመለየት በጋራ ማስተካከል እንደሚገባ አቶ ፋሩቅ ጀማል አንስተዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም መሬት ላይ ተግባር አለ፤ ነገር ግን የባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ውስንነት ስላለበት ለባለሙያዎች ስምሪት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
የማዕከልና የክፍለ ከተማ የእንስሳት ሃብት ልማት፣ የእጽዋት ሃብት ልማት፣ የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት እንዲሁም የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች በስራቸው ያሉ ባለሙያዎችን ስራ ቆጥሮ በመስጠት ወደ ስራ ማስገባትን ተገቢውን አገልግሎት በስታንዳርዱ መሰረት መስጠት እንደሚገባ አጽህኖት በመስጠት በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

21 Jan, 00:14


የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)

በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ሥርዓትን መገንባት አማራጭ የሌለው የዘመኑ አሰራር ሥርዓት ነው፡፡

የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሳ ባይሳ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን አጠቃላይ መረጃ አዲስ ሶፍትዌር በማበልፀግ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮሚሽኑ የICT ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጌቱ በቀለ የበለፀገውን ሶፍትዌር መነሻ በማድረግ ለማዕከል፣ ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የመረጃ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ወደ ሥራ እንዲገቡ የተደረገ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡

በምልከታችንም አዲሱን ሶፍትዌር በመጠቀም የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በወረዳው ያሉ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን እና ቤተሰቦቻቸውን አጠቃላይ መረጃ እያስገቡ መሆኑን ተመልክተናል፡፡

ሶፍትዌሩ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ልጆች፣ የተወሰደ ይዞታ፣ ቀሪ ይዞታ፣ የተደራጁ ማህበራት አጠቃላይ መረጃ እና ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮቹ የተደረገ ድጋፍ በዓይነት የያዘ መሆኑን አቶ ረጋሳ ባይሳ ገልፀዋል፡፡

አቶ ረጋሳ አያይዘውም በ6ቱም ማስፋፊያ ክፍለ ከተሞች ቀደም ብሎ በማንዋል ተይዞ የነበረው መረጃ በአዲስ መልኩ በቴክኖሎጂ እንዲደራጅ አቅጣጫ ስለተቀመጠ ሁሉም ወደስራ በመግባት የጠራ መረጃ እያደራጁ ነው ብለዋል፡፡

1,795

subscribers

3,894

photos

225

videos