ካንቺጋማ
አብረን በላን አብረን ጠጣን
አብረን ገባን አብረን ወጣን
ካንቺጋማ
ተደባደብን ተቃቀፍን
አንዴ ዳበስ አንዴ እፍን
አንዴ ቦረሽ አንዴ ምጥጥ
አንዴ ፈገግ አንዴ ፍጥጥ
ካንቺጋማ
ተለያየን ተራራቅን
ተኮራረፍን ተታረቅን
ተፋቀርን ተዋደድን
ጅራፍ ፈታን ሳር ገመድን
እንደ አዲስ ተኮራረፈን
እንደገና ልንታረቅ
አንቺ ከኔ ስታነቢ
እኔ ካንቺ ስነፋረቅ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ስንታደል ሁሉን ባንዴ
ከዛን ሁሉን ስንቀማ
ካንቺጋማ
ብርሃን ላይ ስንቴ አበራን
ጠሃዩዋ ላይ አንፀባረቅን
ጨረቃ ላይ መንገድ ሰራን
ልታጎርሺኝ ስትዘረጊ
ስትመልሺ ልጎርስ ስል
ተደብቄሽ ስታነቢ
አይንሽ እሳት እስኪመስል
አንዴ አብረን ስንጨፍር
አንዴ አብረን ስንመለኩስ
በፀሎት ጧፍ እንደችቦ
ደማቅ ፍቅር ስንለኩስ
ስንመፀውት ከሰው ዘርፈን
እኔ እና አንቺ አብረን ሆነን
አንዴ ፊቱ ስንፀድቅ
አንዴ ደግሞ ስንኮነን
ተኳረፍን ተታረቅን
ተፋቀርን ካንቺጋማ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ሁሉም ጣዕም አጣጣምነው
ተጋራነው ሁሉን ስልጣን
ዳግም መሬት ልንለጠፍ
ከጠፈር ላይ እየወጣን
ካንቺጋማ😍....
https://t.me/sadstorye