Yekatit 12 Hospital/ የካቲት ፩፪ ሆስፒታል

@yekatit12hospital


This is an official page of clients of Yekatit 12 Hospital Medical College.

Yekatit 12 Hospital/ የካቲት ፩፪ ሆስፒታል

31 Oct, 05:12


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 29 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

Yekatit 12 Hospital/ የካቲት ፩፪ ሆስፒታል

13 Dec, 18:54


ዜና የካቲት ቀን 26/3/12 ዓ.ም
ሆስፒታል ሜ/ኮሌጃችን በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ሬዝደንት ሀኪሞችን ተቀብሎ ማስተማር ጀመረ፡፡
ሆስፒታል ሜ/ኮሌጃችን የህክምና ዶክተሮችን ተቀብሎ ማስተማር ከጀመረበት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ አስካሁን ለ3ኛ ግዜ የህክምና ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወቃል፡፡ በያዝነው አመትም በማህ በረሰብ ጤና የትምህርት ክፍል በተለያዩ የትምህርት መስኮች የማስትሬት ድግሪ ፕሮግራም ከማስጀመሩም ባሻገር ለመጀመሪያ ግዜ የሬዝደንት ሀኪሞችን ተቀብሎ ለማስተማር አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ጨርሶ እነሆ የመጀመሪያ ባች ሬዝደንት ሀኪሞችን ተቀብሏል፡፡

በ25/3/11 ዓ.ም ለሀኪሞቹ በተደረገው የአቀባበል የምሳ ግብዣ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ በምሳ ግብዣው ላይም ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር አየለ ተሾመ ፣የመምህራን ተወካዮች፣ ዲፓርትመንት ሃላፊዎችና የጥራት ቁጥጥር ክፍልን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ክፍል ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር አየለና የማህፀንና ፅንስ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግገር አድርገዋል፤ ደ/ር አየለም ተማሪ ሀኪሞቹ በተቋሙ ቆይታቸው ስለሚጠበቅበባቸው ተግባራትና ስነምግባር ጨምሮ የተለያዩ የስራ መመሪያዎችን ለሀኪሞቹና ለዲፓርትመንት ሀላፊዎች ሰጥተዋል፡፡

በተላለፈው መልዕክት መሰረትም ሀኪሞቹ በቆይታቸው በተማሪነት መንፈስ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውን እንደሆስፒታል ሜ/ኮሌጁ ሙሉ ስታፍ በመቁጠር የህክምና አገልግሎት የመስጠት ስራዎችን በመስራት በሙሉ አቅማቸው ተቋሙን ማገዝ እንደሚገባቸውና ለዚህም ተቋሙ የበኩሉን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ተገልፃል፡፡ ዲፓርትመንቶችም የየስራ ክፍላቸውን Baseline ከፋፍሎ ለተማሪ ሀኪሞቹ በመስጠት ሀኪሞቹን ከወዲሁ ስራ ማስጀመር እንዳለባቸው ዶ/ር አየለ አሳስበዋል፡፡ የሬዚደንት ሀኪሞቹ በ ERMP ፕሮግራም የሚዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ወስደውና በሀገር አቀፍ ደረጃ በውጤታቸው ተወዳድረው በጤና ትበቃ ሚኒስቴር አማካኝተነት የሚመደቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ከኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Yekatit 12 Hospital/ የካቲት ፩፪ ሆስፒታል

13 Dec, 18:51


ዜና የካቲት ቀን 17/3/12 ዓ.ም
በላውንደሪ ክፍል የዕጣቢ መውረጃ ትቦ እድሳት እየተደረገ ነው፡፡
በሆስፒታላችን ላውንደሪ ክፍል እጥበት ከተደረገ በኃላ እጣቢው የሚፈስበት ትቦ ለረጅም ግዜ ተደፍኖ በመቆየቱና ከዚህ በፊትም የተደፈነውን ትቦ ለመክፈት የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ባለመሆናቸው ምክንያት ከማጠቢያ ማሽኖች የሚወጣው ደምና ሌሎች ከታካሚ የሚወጡ ፈሳሾችን በከፍተኛ ሆኔታ የያዘ እጅግ አደገኛ የሆነ የእጣቢ ፍሳሸ ላውንደሪው ከሚገኝበት ቦታ ጀምሮ እዛ አካባቢ ባሉ መንገዶችና የስራ ቦታዎች ላይ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሆኔታ ሲፈስ ተስተውሏል፡፡


ይህም በላውንደሪ ክፍል የሚሰሩ ሰራተኞችን፣ በአካባቢው በሚገኙ ዋርዶችና የስራ ክፍሎች ያሉ ሰራተኞችን ለከፍተኛ የጤና ችግር ሲያጋልጥ ቆይቷል፡፡ ፍሳሹም ሰራተኛውና ተገልጋይ በሚንቀሳቀስበት መንግድ ላይና የታጠቡ አንሶላዎችና ጨርቆች በሚሰጡበት ቦታዎች ጭምር እንደመፍሰሱ በእግር ስለሚረጋገጥ፤ የታጠቡ ልብሶችንም ስለሚነካካ መላውን የተቋሙን ማህበረሰብ ለከፍተኛ የጤና ችግር ተጋላጭ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡

የሆስፒታል ሜ/ኮሌጁ ማኔጅመንትም የችግሩን መጠንና አሳሳቢነት በመረዳት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት እጣቢው የሚፈስበትን ትቦ ቆፍሮ በማፍረስ አመቺ በሆነና የፍሳሹን መጠን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደአዲስ እየተሰራ እንደሆነ በተቋማችን የበሽታ መከላከል ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ፌቨን ከበደ ለስራ ክፍላችን ገልፀዋል፡፡ በእድሳት ስራውም የላውንደሪ ክፍል ሰራተኞችና የጉልበት ሰራተኞች በሰፊው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ወቅት ማሽኖቹን አቁሞ እድሳቱን ማከናወን ባይቻልም ሊከሰት የሚችለውን ብክለት ለመቀነስ ፍሳሹ የሚሄድበትን አካባቢ በረኪናና ሊሎች ኬሚካሎችን በመጠቀም የዲስኢንፌክሽን ስራ በሰፊው እንደሚሰራ ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡