የእኛ ገፅ @yegna_getse Channel on Telegram

የእኛ ገፅ

@yegna_getse


#ከሁሉም ለሁሉም

የእኛ ገፅ (Amharic)

የእኛ ገፅ በአማርኛ የተዘረጋ መረጃና ቅዳሜን ከእኛ እንዲሰበስብ ለሁሉም ለአንተም ሆነ ከሁሉም ለሁሉም መረጃ አስተግቧል። ይህ የአማርኛ ቋንቋ በሚገኘው ሩጫ ፕሮግራም መረጃ ስለሆነ የተመደበበትን መልእክትና የሰው ቤት ደንብ ምንዝሮችን ይጠቀሙ። ለተጨማሪ መረጃ እና ወሬዎች የሚያግዙና መልሶቹን ስለምንጠቀሱበት ፔጅ ዋና መላኩን ለማስተላለፍ እኛ ለመዝናኛ ዋና መረጃዎች ለሁሉም ለለሁሉም ሴቶችና ወንዶች ማንነት ታዳጊ መረጃዎች በመሆን መረጃዎችን እንደአገልግሎት መስራት በዚህ ፕሮግራም አሜሪካ በተገኘው ቪዲዮ ፔድዎች ይመልከቱ።

የእኛ ገፅ

19 Sep, 10:36


አሰራሩ ላልገባችሁ linkun start ባለው መንገድ ክፈቱ

የእኛ ገፅ

19 Sep, 09:16


🌟 Get 5 Birr per referral!


🔗 Here’s your referral link: https://t.me/BirrBuddyBot?start=r06252992045


በዚህ ሊንክ በመግባት ቻናላቸውን join በማድረግ checkየሚለውን በመጫን የሚሰጠችሁን code መልሳችሁ text በማድረግ በመክፈት በመቀጠልም ለሌላ ሰው ሊንኩን በመላክ ለአንድ ሰው 5 ብር ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ።እውነተኛ እና የተረጋገገጠ ስለሆነ ይሞክሩት።

ብራችሁንም በባንክ አሊያም በቴሌብር አማራጭ ማውጣት ይችላሉ💸

የእኛ ገፅ

18 Sep, 15:17


https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startapp=ref_6311083435&startApp=ref_6311083435
Join the Moonbix Journey! Get 1000 Coins as a new player and stay tuned for exciting airdrops and special rewards from Binance!

የእኛ ገፅ

19 Jan, 12:40


"... ጅል የሚነቃው ሲዘንብ ነው። ያኔ ይበሰብሳል እንጂ መጠለያ አያገኝም። የሚወዱን ሰዎች በፍቅር እንደ ዣንጥላ ከበላያችን የሚዘረጉበት ዘመን አለ፤ ከብቸኝነት ዶፍ ከመልከስከስ ንዳድም ጠባቂዎቻችን የሚሆኑበት። ሁልጊዜ ግን እንደዚያ አይቀጥልም፣ አንድ ቀን ግፋችን ከብዷቸው ቸልተኝነታችን አድክሟቸው እንደ ዣንጥላ ይታጠፋሉ። ወይም አያያዛችንን አይቶ ጠንካራ ንፋስ ከእጃችን ይነጥቃቸዋል።..."

አልተዘዋወረችም

የእኛ ገፅ

12 Aug, 10:48


​​መ - መጽሐፍ

የቃላት ድርድር ፣ የዐረፍተ ነገሮች ጋጋታ ፣ የአንቀጾች ስብስብ አይሆን እናምናለን፡፡ ነፍስ ሽቶ ነፍስ ይዘራ ፣ ያድር ተማጽኖ በውስጥ ይሰፍን አይሆን ቢታመን ቅጥፈት ይሆን እናምናለን፡፡

ተ - ተደራሲ

በታቀፈው የቃላት ድርድር ፣ የዐረፍተ ነገሮች ጋጋታ ፣ የአንቀጾች ስብስብ ተጀቡኖ ሌላ አይመለከት መሆኑን እንነቅፋለን፡፡ በሸኚ ሀሳቦች ታጅቦ ፣ በተንጠልጣይ ሐረጋት ተንጠልጥሎ ካሰበበት አይደርስ ይታመን ቢሆን እውነት ይሆን እንነቅፋለን፡፡

ደ - ደራሲ

የቃላት ድርድር ፣ የዐረፍተ ነገሮች ጋጋታ ፣ የአንቀጾች ስብስብ ሰዳሪ አይሆን እናውቃለን፡፡ ነፍስ ሽቶ ነፍስ ይዘራ ይሆን በሚሆነው መጽሐፍ የጌትነት ቦታ አይኖረው እናውቃለን፡፡ በገጾች ተጀቡኖ ሌላ አይመለከት መሆኑን ይነቅፍ በሆነው ተደራሲ ዘንድ ፋና ወጊ ይሆን አይችል እንደሆን እናውቃለን፡፡

አምነን ፣ ነቅፈን ፣ አውቀን “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም”ን እነሆ እንላለን፡፡

የእኛ ገፅ

10 Aug, 20:15


ነገም ሌላ ቀን ነው
👍

የእኛ ገፅ

10 Aug, 20:08


​​#ነገም ሌላ ቀን ነው
ይህ መፅሐፍ በማርጋሬት ሚሼል "GONE WITH THE WIND " በሚል ተፅፎ በገጣሚና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን "ነገም ሌላ ቀን ነው " ተብሎ ተተርጉሟል፡፡
#ደራሲዋ ማርጋሬት ሚሼል መፅሀፉ ሲታተም ሰላሳ ስድስት ዓመቷ ነበር ። "ጎን ዊዝ ዘ ዊንድ"ን ፅፎ ለመጨረስ አስር ዓመት ፈጅቶባታል። በሃያ ስድስት ዓመቷ ባጋጠማት የቁርጭምጭሚት ጉዳት ከአልጋ በዋለችበት ወቅት ነው ይህንን መፅሀፍ የጀመረችው ፤ ስለ አሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ሲተረት ፣ሲወሳ ፣ ሲነገራት ከአትላንታና ጦርነቱ ጋር ጥርሷን ነቅላ ያደገች ናት ። መፅሀፉም በመጀመሪያ እትም ከአንድ ሚሊዮን ኮፒ በላይ የተሸጠ ፣ እስከ 1965 በአርባ ሀገሮች በሰላሳ የተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። እያንዳንዱ አሜሪካ ጠንቅቆ ያውቀዋል ።
#ተርጓሚው ገጣሚና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ ሳለ "ነገም ሌላ ቀን ነው” ሲል ይህን መፅሀፍ የተረጎመው በሲጋራ ወረቀት ላይ በመፃፍ ነው፡፡ በዚያ አስቸጋሪ ጊዜ ይህንን ትልቅ መፅሀፍ በአስቸጋሪና ለመመኮር እንኳን ከባድ በሆነ መልኩ ተርጉሞ ለንባብ ያበቃው መጋቢት 1982 ዓ/ም በ670 ገፆች ተሰናድቶ ነው፡፡
እናም ደራሲዋም ፣ ተርጓሚውም ፣ የመፅሀፉም ታሪክ በአስቸጋሪና ከባድ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም በጥንካሬ ማለፍን ይነግሩናል ፤ ያስተምሩናል ። ስለዚህ አሁን በዓለማችን የተፈጠረው ሁሉ ያልፋል ፣ ይነጋል። ምክንያቱም #ነገም ሌላ ቀን ነው!!

#ነገ ሲሰራ
ወንድሜ! ጨንቆUል? ቀፎሀል? ፈርተሀል? ሰግተሀል? በል አንሳ 'ጽዋህን - ሀዘንህ እስኪጨንቀው ፤ የቀረህን ፍሬ በወኔ ጭመቀው ።
ታዲያ ዋ! የጭማቂህ ሙሌት እንዳይበዛው አረፋ ፤ ትዝታ የወለደው ነስንስበት ተስፋ ።

#መፅሐፋን በpdf ለምትፈልጉ እነሆ በረከት ብለናል!

የእኛ ገፅ

05 Aug, 08:47


ሞጆ በአለማየሁ ገላጋይ አይን🥰

የእኛ ገፅ

05 Aug, 08:07


#ይስማዕከ 
#አዲስ  መፅሀፍ  እነሆ
#ግፋዓን
ጦርነት  ሲጀምር  ፓለቲከኞች  ጥይት  ያቀብላሉ።ባለፀጎች  ምግብ  ያቀርባሉ  ድሆች  ልጆቻቸውን  ይለግሳሉ  ጦርነቱ  ሲይበቃ  ፓለቲከኞች  ቀሪ  ጥይቱን  ይሰበስባሉ።ባለፀጎች  ከጦርነት  በተረፈው  ሀብታቸው  ማደግ  ይጀምራል።ድሆች  ግን  ልጆቻቸውን  በመቃብር  ስፍራ  ይፈልጋሉ።

የእኛ ገፅ

02 Aug, 15:09


እነሆ  ደግሞ  አንብቤ  ከተደመምኩበት  እና  ከወደድኩት  መፅሐፍ  ውስጥ
​​በናሁሰናይ  ጸዳሉ  አበራ  የተደረሰው  '  ሜሎሪና  '  የተሰኘውን መፅሐፍ   ታነቡት  ዘንድ  ጠቆም  አድርጌ  ለማለፍ  ወደድኩ


መጽሐፉ  ታሪካዊ  ይዘት  ያለው  ስነ-ልቦናዊ  ልቦለድ  ሲሆን  የሰው  ልጅ  ሞትን  ለማሸነፍ  በሚያረገው  ትግል  ውስጥ  የኢትዮጵያውያንን  ቀደምት  ጥበባዊ  ሚና  የሚተርክና  ከፍተኛ  የአስተሳሰብ  ልዕልናችንን  የሚያሳይ  መጽሐፍ  ነው  ፡፡ 

አቀራረቡም  አዝናኝና  የሥነልቦና  ምክሮችንና  ሀሳቦችን  ከታሪካዊ  ክስተቶች  ጋር  ደምሮ  የያዘ  ነው፡፡

የታሪኩ  መቼት  1960  -  1994   ሲሆን 
መተማ  ፣  ጎንደር  ፣  ዐዲስ  አበባ  ፣  ትግራይ  (ደብረዳሞ  ገዳም  ፣  አል  ነጃሽ  መስጂድ  )  ፣  አሜሪካ  (  ዋሽንግተን  ፣  ኒውዮርክ  ፣  ኮሎራዶ)  ፣  እንዲሁም  እግረመንገድ  እስራኤል  ድረስ  ይዘልቃል  ::


"ሜሎሪና"  መጽሀፍ  የውስጥ  ገጽ  እንዲሀ  ይለናል  !!

‹‹አንዳንዴ  ሰው  የመዘዘው  ሁሉ  መከራ፣  የተጠጋው  ሁሉ  እሾህ  የኾነበት  ሲመስለው  ሕይወትን  በጤናማ  አእምሮው  መጋፈጥ  ይፈራል፡፡  ››
         ገጽ  155

‹‹  የሰው  ልጅ  በሕይወት  ዘመኑ  ሁሉ  መጠኑና  ስፋቱ  ቢለያይም፣  ራሱ  በሠራው  አሊያም  ሌሎች  ባጠሩለት  እስር  ቤት  ይኖራል፡፡  እንደ  ራሱ  አሳብና  አመለካከት  ግን  ትልቅ  እስር  ቤት  የሚኾንበት  አንዳች  ነገር  የለም፡፡  ለካስ  እስር  ቤት  ቦታ  ሳይኾን  አስተሳሰብ  ነው፡፡  በዚህች  ምድር  እጅግ  ብዙ  ሰው  በአእምሮው  እስር  ቤት  ውስጥ  በአሉታዊ  አስተሳሰብ  ታስሮ፣  በከንቱና  እንቶ  ፈንቶ  ፍርሀት  ተይዞ  ማንም  እንዳይረዳው  ኾኖ  የእስር  ቤት  ቊልፉን  ራሱ  ደብቆ  ይኖራል፡፡  ››

‹‹...አብዛኞቻችን  ሕይወታችንን  የምንመራው  ነገን  በመፍራት  ነው፡፡  በተለይም  በማይመች  አካባቢ  ስንኖር  ሕይወታችን  እንዲሁ  የሚያልቅ  ስለሚመስለን  ሐዘናችን  ይጨምራል፡፡  ሕይወት  ትጨልምብናለች፡፡  የሕይወት  ጥያቄዎችም  መነሣት  የሚጀምሩት  በዚህ  ጊዜ  ነው፡፡  አኹን  ለመሥራት  እስከተነሣን  ድረስ  በሕይወታችን  ረፈደ  የሚባል  ጊዜ  ባይኖርም፣  የሰው  ልጅ  ግን  ከሕይወት  ይልቅ  ለሞት፣  ከደስታ  ይልቅ  ለሐዘን፣  ከመቀጠል  ይልቅ  ለማቆም  የቀረበ  ፍጡር  ነው፡፡  ለዚህ  ነው  በሕይወት  ዘመኑ  ሲለፋ፣  ሲዳክርና  ሲባዝን  የሚታየው፡፡   ››

ገጽ  186

‹‹የብራናው  ጥቅልል  ሦስት  ታላላቅ  ምስጢሮች  ዐቅፏል፡፡  የመጀመሪያው  ስለ  ሰው  ልጅ  ታሪክና  የሕይወቱ  ዐላማ  ያትታል፡፡  ኹለተኛው፣  በምድር  ላይ  መጥፎ  የሚባሉና  ብዙ  ችግር  የሚያስከትሉ  ቀናትን  ማወቂያ  ምስጢራዊ  ቃሎችን  ይዘረዝራል፡፡  እነዚህ  የአባቱ  አስተማሪ  ከረገሟቸው  ቀናት  ጋር  ተመሳሳይነት  ያላቸው  ናቸው፡፡  ሦስተኛውና  የመጨረሻው....››

ገጽ  176


“ለካ  ነገሮች  የሚመዘኑት  በብዛታቸው  ብቻ  ሳይኾን  በጥራታቸው  ነው  “ 
ገጽ  117

‹‹...  የሰው  ልጅ  በሕይወት  ዘመኑ  ሁሉ  መጠኑና  ስፋቱ  ቢለያይም፣  ራሱ  በሠራው  አሊያም  ሌሎች  ባጠሩለት  እስር  ቤት  ይኖራል፡፡  እንደ  ራሱ  አሳብና  አመለካከት  ግን  ትልቅ  እስር  ቤት  የሚኾንበት  አንዳች  ነገር  የለም፡፡  ለካስ  እስር  ቤት  ቦታ  ብቻ  ሳይኾን  አስተሳሰብ  ጭምር  ነው፡፡  በዚህች  ምድር  እጅግ  ብዙ  ሰው  በአእምሮው  እስር  ቤት  ውስጥ  በአሉታዊ  አስተሳሰብ  ታስሮ፣  በከንቱና  እንቶ  ፈንቶ  ፍርሀት  ተይዞ  ማንም  እንዳይረዳው  ኾኖ  የእስር  ቤት  ቊልፉን  ራሱ  ደብቆ  ይኖራል፡፡  ›› 
ገጽ  179

"...  በምድር  ላይ  የሚወዱትን  ሰው  በሞት  እንደመቀማትና  ተስፋ  ያደረጉትን  እንደማጣት  ትልቅ  ህመም  የለም፡፡  ሲደጋገም  ደግሞ  ሐዘን፣  ሥቃይ፣  ችግርና  መከራ  እንደመጫሚያና  ልብስ  አጥልቀዋቸው  የሚዞሩ  ያህል  ይሰማል፡፡"
ገጽ  106

ከ"ሜሎሪና"  መጽሐፍ  የተወሰዱ  ጠቃሚ  የሕይወት  ምክሮችን  በጥቂቱ  እነሆ✍️


ያለፍክበት  የሕይወት  መንገድ  አስሮ  ሊይዝህ  አይገባም  ፤  ነገህን  መወሰን  የራሳህ  ምርጫ  ነው፡፡

በሕይወትህ  የደስታ  ምንጭ  መኾን  ባትችል  ለሌሎች  የሐዘን  ምክንያት  አትኹን፡፡

በምድር  ላይ  ምንም  ፍጹም  ነገር  የለምና  አንተም  ፍጹም  ለመሆን  አትሞክር።  ሰዎችም  ፍጹም  እንዲሆኑ  አትጠብቅ።  ነገር  ግን  ኹሉን  በመልካምነትና  በቅን  ልቦና  አከናውን  ፡፡ 

ያለህን  ችሎታ  ፣  አቅም  ፣  ዕውቀት  አንተ  ካላከበርከውና  ካላወጣኸው  ማንም  መጥቶ  ሊያከብርልህና  ሊያወጣልህ  አይችልም  ፡፡  ስለዚህ  ከተቀምጥክበት  ተነሳና  ከምኞት  ወጥተህ  ወደ  ተግባር  ተሻገር  ፡፡

ዝምታ  ፣  በውስጡ  ትልቅ  ጩኸት  የያዘ  የማይጠየቅ  ጠያቂ  ፣  የማይመረመር  መርማሪ  ነውና  ከዙሪያህ  ካለ  የሰዎች  ጫጫታ  በላይ  በላይ  የውስጥ  ዝምታህን  አድምጥ  ፡፡ 

በሕይወትህ  ትልቅ  መከራ  ፣  ችግር  ፣  ሀዘን  ደርሶ  ሊሆን  ይችላል  ፤  "ሰው  እንዴት  በዚህ  ውስጥ  ያልፋል?"  ብለህ  አዝነህ  ፣  ተክዘህ  ሊሆንም  ይችላል  ፡፡  ግን  በሕይወት  ዘመንህ  መዘንጋት  የሌለብህ  ነገር  "ተስፋ"  የሚባል  ነገር  መኖሩን  ነው።

#ሜሎሪና
#ናሁሰናይ  ፀዳሉ  አበራ
#ታሪካዊ_የሳይኮሎጂ_ልብወለድ

መፅሐፉን  ማግኘት  ላልቻላችሁ  እነሆ  በPdf  ከስር  ታገኙታላችሁ

┄┄┉┉✽‌✿✽‌✿»‌✽‌┉┉┄┄

የእኛ ገፅ

27 Jul, 22:37


ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ
ደራሲ - እሱባለው አበራ

የእኛ ገፅ

27 Jul, 22:36


​​መከፋት በውብ ቋንቋ ሲፃፍ አይተው ያውቃሉ?  መከፋት የሚወደድ ነገር ሆኖ አያውቅም ማለት እሱቤ እስከሚፅፈው ድረስ .....

ዝም ያሉ ገፀ ባህርያትስ በጭጭታቸው ውስጥ ብዙ ሲናገሩ አድምጠዋል ? እዚህ ግን ኩልል ብሎ በሚወርድ ትረካ ዝምታቸው ፊደል ሰርቶ ይተረካል ።

ስለ ባይተዋርነት ያለዎት ግንዛቤስ ምን ድረስ ነው ? ለሌላ ሰው ባይተዋር በመሆን እና ለራስ ባይተዋር በመሆን መካከል ስላለው ልዩነትስ? ባይተዋሩን እርሶነቶን ባገኙበት ቅፅበት ቢለዩትስ? በአንድ ጊዜ ራስን ማግኘትን ፣ ራስን ማወቅን ፣ ከራስ መሸሽን፣ ከራስ ማምለጥ ፣ ራስን አለማዳን ፣  በራስ ላይ መጨከን ራስ ላይ ቸል ማለትስ ምን ምን እንደሚል ማወቅ ይፈልጋሉ ?  ማወቅ ከፈለጉ "ህይወት ወደ ግራ ሲያነቡት ሞት ነው " የሚለው የገብረክርስቶስ ግጥም ስንኝ መግቢያ ያደረገ "ግራ እና ቀኝ" የሚል የመፅሃፉ ክፍል ላይ ያገኙታል ።

በህይወት እያሉ እስትንፋስ ሳይቋረጥ ሞትን ተዋውቀው ለምደውትስ ያውቃሉ?  ሞት ሳይመጣ ቀድመን የተቀበልነው ተናፋቂ እንግዳችን ሲሆን መድረሱን በፈገግታችን የምናጅብበት ክስተት ልብ ያማል ።

ሞት የሁሉ አለቃ ነው ብለው ቀን ከሌት በጥበቃው ሲተጉ ፤ ሁሉን ከበስተኋላዎ ጥለው የተስፋ መቁረጥ የመጨረሻ ፅንፍ ላይ ተገኝተው ያውቃሉ? እና ታዲያ ከዛ የተስፋ መቁረጥ ጫፍ ላይ ምን መለሶት? ማንስ ዳግመኛ ህይወትና ተስፋን ይዘራል ? ከፍቅር በላይ ሞትን የሚያሸንፍስ ማን አለ? ይሄን አለመሆን ( ተስፋ መቁረጥ ) በመሆን ( በፍቅር ተስፋ በማድረግ ) ማየት ከፈለጉ የመፅሃፉን " መሆን አለመሆን" በሚለው የመፅሃፉ ክፍል ያገኙታል ።

በታሪክ ፍሰት እና በገፀ ባህሪ አወቃቀር አስገራሚ የሆነው ይህ የእሱቤ መፅሃፍ  ደራሲው በፈጠረው የ 'እንጀራ እና  ማባያ' ቅርፅ በ Adam Reta  ህፅናዊነት እና በነ ሰልማን ሩሽዲ ማጂክ ሪያሊዝም ተሰናስኖ ውብ ሆኗል ።

የድርሰቱን ጊዜና ቦታ ( መቼት እንዲሉ የስነፅሁፍ ሰዎች ) በእኔ ግምት ጊዜው አሁን ያለንበት ዘመን ይወክላል ( አሁን ያለንበትን ጊዜ የሚወክል ከሆነ ለምን 'ትዝታሽን ለእኔ - ትዝታሽን ለአንቺ ' የሚል የትዝታ ርዕስ ተሰጠው የሚል ካለም  ፣ ለእኔ እስከሚገባኝ ትዝታ ወይንም ትውስታ የጊዜ ጉዳይ ቢሆንም የርዝመትና እና እጥረት ግን አይደለም ። ማለት 'አሁን' ከምንለው ጊዜ ተነስተን ያለፉ ክስተቶችን የምንዳስስበት ሁኔታ ሲሆን እኒህ ክስተቶች 'አሁን ' ከሚባለው ጊዜ በሰከንድም በአመታትም ቢርቁ 'ትዝታ' የሚባለው መጠሪያ የሚቀያየርባቸው አይሆንም ።

ቦታን በተመለከተ ፤  በመፅሃፉ ላይ በግልፅ የተቀመጠ ወይንም የተገለፀ  የተለመደ የሚታወቅ የሰፈር ፣ የሃገር ፣ የቀበሌ ወይንም የክልል ስሞች ስለሌሉ ታሪኩን ሁሉም የራሱ ሊያደርገው የሚችል ነው ፣ የታሪኩ ቦታ ሊጠቀስ ከሚችል ሰፈር እና ሃገር ይልቅ ተመሳሳይ ስሜት እና ህመም የሚጋሩ የሰው ልጆች ልብ ነው ። 

ይህ የቦታ 'የትምነት' የገፀ ባህርያቱ ስም ላይም በሌላ አይነት ቅርፅ ተከስቷል ። የእሱቤ ገፀ ባህርያት ስማቸው በመጀመሪያ ፊደላት ብቻ የተገለፁ ስለሆነ ( 'ገ' 'ደ' ወ.ዘ. ተብለው )ገፀ ባህርያቱን እኛ የፈለግነውን 'ማንም'ልናደርጋቸው እንደምንችል ተሰምቶኛል ። ለምሳሌ ' ገ' ተብሎ የተቀመጠውን ገፀ ባህሪ ገዛኸኝ ወይንም ገብሬ በማለት 'ማንምነት' ን ማላበስ እንችላለን ። በዚህ ማንምነት ውስጥ ደግሞ የረቀቀ ሁሉን መሆን አለ ብዬ አምናለሁ ።

ይህቺ በጣም ትንሽ መሳይ ግን ትልቅ የሆነች መፅሃፍ ይሄ የኛ ትውልድም ስነ ፅሁፍን በተመለከተ የራሱን መንገድ ተከትሎ በራሱ ዘዬ አዲስ ነገርን መፍጠር እንደሚያስችል እና ይህ ዘመንም የራሳቸውን አዲስ መንገድ እና የስነፅሁፍ ቅርፅ የሚፈጥሩ የምንኮራባቸው ጎበዛዝት እንዳሉን የምናሳይበት ምስክር ነው ።

   አንዳንዴ መፅሀፍት በጣም ተጋኖ ይወራላቸዋል። ነገር ግን ገዝተን ወይም ተውሰን ስናነባቸው እንደጠበቅነው ሳይሆኑ ይቀራሉ። የእሱባለው አበራ ንጉሴ "ትዝታሽ ፡ ለእኔ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ"  የተሰኘው መፅሀፍ ከነዚህ መፅሀፍት ፍፁም ይለያል። ይህ መፅሀፍ ተጀምሮ እስኪያልቅ በእያንዳነዱ ገፅ ብዙ ነገሮችን ይዳስሳል።
 የመፅሀፉ ደራሲ እሱባለው አፃፃፉ እፁብ ድንቅ የሚያስል ነው ። አንዴ የሚነበብ መፅሀፍ ብቻ ሳይሆን ተደግሞ እንዲነበብ አድርጎ ነው የፃፈው ።
  ግን እንደ ማኪያቶ ባያንስ ደስ ይል ነበር ። ለነገሩ ማኪያቶ ስላነሰ አይደል የጣፈጠው እረ እንደውም መፅሀፉ እንኳንም አነሰ ።
 ለአንበብያን እንዲያነቡ ከሚጋብዛቸው መፅሀፍ አንዱ ሆኖ  አግኝቼዋለው
መፅሐፉን ማግኘት ለማችሉ ከስር በpdf ለቅቄዋለው
መልካም ንባብ!

የእኛ ገፅ

03 Jan, 12:36


Channel created