❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

@yefikr_gitmoch_debdabewoch


የፍቅር ግጥሞች እና ደብዳቤወች ይቀርባሉ።
ይህን ቻናል ሲቀላቀሉ
📖 ግጥሞች
💌 ደብዳቤወች
🗣 አጫጭር ገለፃወች
🗣 አጫጭር ትረካወች
🎬 ታሪኮች
🔍ወጎች ሰለ ፍቅር የተባሉ
🎻🎹🎧 ሙዝቃ
ይቀርቡላችሆል።
መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ🤣😁😆
ለማንኛውም አሰተያየት @Montecristo01 ይጠቀሙ።

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

15 May, 20:10


🗣T

@yefiker_gitmoch_debdabewoch
@yefiker_gitmoch_debdabewoch

Open Open US

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

10 May, 20:34


ማን ይሆን

አይኑ ተመልክቶ ልቦናው ያልቃኘ
……… የያዘውን ትቶ ሌላ ያልተመኘ
……… አካዊ ወረት ያረገጠ ወዳጁን
አለ ወይ ከሰዎች ያልጎዳ ወዳጁን
ውድ ፍቅረኛውን ልቡን እንዳፈቀረ😏
……በሷ ተወስኖ ዘላለም የኖረ
እስከመጨረሻው መንፈሱ ሳይላላ
ከሚወዳው በቀር ያልተመኘ ሌላ
ማናው ይህንን የሰራ በቃሉ የሚገኝ ባስቀመጡት ስፍራ ያልተለዋወጠ
ማን ይሆን ወዳጁን በሌላ ያልሸጠ🤷‍♀

#Tsenu


🌷🌺🌹🌸🌷🌺🌹🌸🌷🌺🌹
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀

@ponem_channal☔️
@ponem_channal☔️

For any comment
@Lovepoem1_bot

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

07 May, 20:26


​​💌

🕊🍃🌹🍃..............
#Tsenu Kal

አንች ማለት የመኖሬ ተስፋ ነሽ.. አንዳንዴ ምን እላለሁ መሰለሽ አንች ባትኖሪ ኑሮ ማንን
አፈቅር ነበር......? እና . . . . . . . . . . . . . . . . .
. . ባንች ፍቅር ተይዤ መግቢያዉ እና መዉጫዉ ጠፍቶብኝ እንገላታለሁ:: እባክሽን ፍቅርዬ በህይወት መኖሬን ትርጉም አልባ አታድርጊዉ...ላንች ያለኝ ቦታ ከምታስቢዉ በላይ ነዉ::
ብቻ የኔ ቆንጆ እሽ በይኝና ፍቅሬን ላሳይሽ..ትንሽ እንኳን በልብሽ አኑሪኝ... አውቃለሁ የኔ አለም"ትወጂኛለሽ " ግን ማመን አትፈልጊም....እስከመቼ የኔ ውድ ሞትና ህይወት...ተስፋና ህልም ከገነት ወደሲኦል ያመላልሱኝ....ነፍሴ በቋፍ ነው ያለችው እባክሽን በፍቅር አምላክ
ይሁንብሽ ልብሽን አዳምጪው...ፍቅሬን ተጋሪኝና ከገደል አፋፍ የተንጠለጠለች ነፍሴን ታደጊያት....።።።።።።

@ፅኑ

👒.........🍃🌹🍃..............👒

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

05 May, 10:44


የእትየ መናሹ ሬሰቶራንት
ተራኪ፥ ሞንቴ
ድርሰት ፥ በእውቀቱ ሰዩም

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

04 May, 15:06


የእትየ መናሹ ሬሰቶራንት

ይህ የሬሰቶራንት ዳሰሳ እቲየ መናሹን ለማሰደሰት ወይም ለማበሳጨት የተፃፈ አይደለም። እኛ ሰፈር ቱሪሰቶች ሳት ብሎቸው ብቅ ቢሉ ወይም እህል ውሃ ቢያምራቸው በምን አኳሆን ሊሰተናገዱ እንደሚችሉ ለማሳሰብ የቀረበ ነው።እትየ መናሹ የግቢ አጥር ላይ ምግብ በአዲሰ መልክ ጀምረናል የሚል ፅሁፍ ይታያል ፅሁፉ የተለጠፈው ጃንሆይ የታህሳሱን ግርግር ባበረዱ በሶሰተኛው ቀን መሆኑን በህይወት ያሉ የሀገር ሺማግሌወች ይናገራሉ።
እትየ መናሹ ይሄንን ማሰታወቂያ በተመለከተ አውርተው አይጠግቡም
"ትዝ ይለኛል ይህንን ፅሁፍ የፃፈልኝ ከቤታችን ዝቅ ብሎ ይኖር የነበረ አንድ አይና ሰአሊ ነው።" ይላሉ በትልቅ ጭልፋ ሺሮ እያወጡ "እንግዲህ ይህ ሰአሊ ግማሽ ቀን ሙሉ ቀለም ሲቀባ ውሎ አንድ ቃል ብቻ ፅፎ ምሳውን ትሪ ሙሉ እህል ዝቆ ይሄዳል በማግሰቱ አመሻሺ ላይ መጥቶ አንድ ቃል ይጨምርና እራቱን ወፍራም ምንቸት አብሽ ከነ አይቡ ጠርጎ ቦርጩን እየዳበሰ ይሄዳል። እንደገና በማግሰቱ ይመለሰና ሌላ ጎረድ ጎረድ በአዋዜ ጥርቅም አርጎ አንድ ቃል ፅፎ ውልቅ ይላል።እንግዲህ ይሄን ሁሉ የሚበላው በነፃ ነው።በነፃ ታዳ ይሄን ሁሉ በልቶ የፃፈው ምግብ በአዲሰ መልክ የሚለውን ብቻ ነው።ሞሰቤን ሳያራግፈው አንድ ልበለው ብየ በቃህ አልኩት ከዚያም የቀረውን ፅሁፍ መሰረተ ትምህርት ተምሬ እኔው እራሴ ጨረሰኩት።ቀለም ከየት አመጣሽ አትለኝም። በቀይ ወጥ ፃፍኩት አሁን በቀይ ወጥ የተፃፈ ይመሰላል ? ይመሰላል ወይ? "
ተመጋቢ ነህ እንበል ዋናውን በር አልፈህ ወደ ውሰጥ ትገባለህ ከፊት ለፊት ባለው ሰንጥቅጥቅ ግርግዳ ላይ ጥቅሰ ቢጤ ተፅፎ ታያላህ እንዲህ ይላል።
"ልጄ ሆይ ይጠቅመሃል እና እህልን ብላ ገዝተህ ብላ ትን እንዳይልህ እህል እያላመጥክ ባታወራ ጥሩ ነው።የለም ማውራት አለብኝ ካልክ ግን ሰለ ምግብ ጣት አሰቆርጣሚነት ብቻ አውራ።ልጄ ሆይ እንዳያንቅህ እንጥልህም እንዳይጨፈለቅ ጉርሻህን መጥነህ ትጎርሰ ዘንድ እለምንሃለሁ። የቀረበልህ እህል በረከት እንዲኖረው።አውሎ ነፋሰ የመታው ጭድ እንዳይመሰል ከፈለክ የእጅህን አሰነዛዘር በልክ አድርገው።" መፅሃፈ ሲራክ ቁጥር 50
ከዚህ ጥቅሰ ፈንጠር ብሎ "ከመብላቶ በፊት ይህን ያንብቡ የሚል ማሥታወቂያ ታያለህ።"
እንዲህ ይላል "ይህ ምግብ ቤት የታህሳስ ግርግር ሰሞን ጃንሆይ በሌሉበት ተመርቆ ተከፈተ ምግብ ቤቱ ሲቆቆም በሁለት መለሰተኛ ሰታቲወችና በአንድ ጠማማ ጭልፋ ቢሆንም እድገቱን በማፋጠን በአሁኑ ጊዜ እግዜር ይመሰገን አራት መቀቀያ ቱፋወች ፣ አሰራሁለት ማማሰያወችና ሶሰት መክተፊያወችን ይዞ በመንቀሳቀሰ ላይ ይገኛል። ከዚህ በላይ በልምድና በእድሜ የበሰሉ ሁለት ወጥ ቤቶችም አሉት እነሱም እትየ መናሹና የልጅ ልጃቸው ወርቅነሺ መሆናቸውን ሰንገልፅ ኩራት ይሰማናል።"
"በቅርቡ በልተው ለሚጠጡ ደንበኞች የውሃ ሺንት አገልግሎት እንደምንሰጥ ይፋ አድርገናል። ጉድጎድ ቁፋሮውም ከአሁኑ ተጀምሮል።" የሚል ማሰታወቂያም አለ ይህንን ካነበብክ በሆላ ታጨበጭባለህ የእትየ መናሹ የልጅ ልጅ ወርቅነሺ እርጥብ መዳፎን በቀሚሶ ጠርዝ እያደረቀች "ምን ልታዘዝ?" ትላሃለች። "ምን ምን አላችሁ?" ትላታለህ።
"በየአይነቱ"
"ሌላሰ"
"ቃሪያ እና ጎመን የሌለው በየአይነቱ"
"ሌላ የለም?"
"እሱማ ቀይ ወጥም አለ"
"ቀይ ወጡን አምጭልኝ።"
"ማምጣትሰ አመጣልሃለሁ ግን"
"ግን ምን?"
"የትናንት ወዲያ ነው።"
"የትናንት ወዲያ?"
"ለነገሩ አሞቀዋለሁ በርበሬም እጨምርበታለሁ።"
"በይ የኔ እህት በያይነቱ አምጭልኝ።"
"ሂሳብ ቅድሚያ ነው።"
"ሰንት ነው?"
"ብር ተሰሙኒ"
ብር ተሰሙኒህን ትከፍልና በያይነቱ ይመጣልሃል እየበላህ እንዳለ ከድመት ከፍ ከነበር ዝቅ የሚል ድመት ከጎዳ እየሮጠ መጥቶ እግርህ ሰር ገብቶ እርይ ይላል አቧራ የጎረሰ ጫማህን አንሰተህ ሆዱ ላይ ልትረግጠው ሰትቃጣ እትየ መናሹ ከጎዳ ብቅ ብለው "አንድ ጉርሻ ጣልለትማ ሰሞኑን አይጦች ሱባኤ ገብቶል መሰል።" ይላሉ
አንተ ከእንጀራው ቆርሰህ ለድመቱ ሰትወረውርለት በአየር ላይ ቀልቦ ይሰለቅጠውና እንደገና "ሚያው" ይላል
"ድገመው ካልደገምከው አይሄድልህም።" ይላሉ እትየ መናሹ።
እየበላህም እንዳለ አንድ ጠብደል ለማኝ በሩን ሞልቶ "እምየ እራበኝ" ብሎ ይጮሃል እትየ መናሹም ከንፈራቸውን እየመጠጡ "አፈር ልብላ መሶቤ ሲራቆት ትመጣለህ።" ብለው ወደ አንተ ይዞሩና "እሰቲ ትንሽ ቆርሰህ ሰጠው ያፀድቅሃል።" በልተህ ጨርሰህ እጅህን እየታጠብክ ሶፍት ቢጤ ፍለጋ ሰትገላመጥ ካዩህ እትየ መናሹ ወደ ልጅ ልጃቸው መጮሃቸው አይቀርም "አንቺ ወርቅነሺ እሰኪ አሮጌ ሻሸን አምጭለት።" ይሉሃል
"መፀዳጃ ቤት አለ?" ብትላቸው "የለም" አይሉህም በሹል አገጫቸው ወደ በሩ እየጠቆሙህ እንዲህ ይሉሃል።
"አንድ ሃምሳ ሜትር ያክል በእግርህ ቆም ብለህ ሂድ ከዛ አውቶብሰ ያዝና አንድ ፌርማታ ያክል ሂድ ከዚያ ትወርድና በግራ በኩል ያለውን አሰፓልት ይዘህ ተራመድ የአንድ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ያህል ቢያሰኬድህ ነው። የወደቀ የሰልክ እንጨት ታያለህ የሰልክ እንጨቱ ላይ ቁጭ ብለው ሎተሪ የሚሸጡ ሺማግሌ ታያለህ እዚያ አካባቢ የህዝብ ሽንት ቤት አለ ብለህ ጠይቃቸው። በአካባቢው ካለ ይጠቁሙሃል።

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

04 May, 08:57


ተራኪ ፥ ሞንቴ
ድርሰት ፥ በእውቀቱ ሰዩም

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

03 May, 17:22


ጉባኤው
በእውቀቱ ሰዩም

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

01 May, 20:33


ተጓዥ ወድጃለው ቢሄድ የማይደክመው
እንደ ወራጅ ውሃ መድረሻ የለለው
እንዴት ልከተልህ የትስ ልጠብቅህ
ልብህን እደኮከብ ሰማይ ላይ በትነህ
ስከተልህ ላልደርስ እንደመሪት ገዝፈህ
ንገረኝ ፍቅርየ መውደድህን መያዝ
ፍቅርህን መሸከም ስላቃተኝ መያዝ
አታዝንልኝ ሞይ ስባዝን ስዋትት
እደጥጥ አባዝቶ እንደ ጨርቅ መሳሳት
እኔም ስከተልህ አተም ስትርቀኝ
እኔ ብቻ እማውቅህ አንተ የማታውቀኝ
ስንቶችን ገለሀል ሱንቱን አድንሀል
በኔ ቢጤ ልቦች በስንቱ ነግሰሀል
ባንተ ፍቅር ነደው ስንቶቹን ገለሀል



❤️❤️❤️❤️

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

01 May, 11:31


ተራኪ፥ ሞንቴ
ደራሲ፥ በእውቀቱ ሰዩም

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

01 May, 06:05


በእውቀቱ ሰዩም
ሰሌዳ እና ጠመኔ

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

28 Apr, 16:14


በእውቀቱ ሰዩም
የእትየ መናሹ ፔንሲዮን

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

28 Apr, 15:58


በእውቀቱ ሰዩም
የእትየ መናሹ ሬሰቶራንት

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

22 Apr, 18:07


🎶 Tedros Tadese_Asaw Tekemachto cover by johanis🎧 @fetashow

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

21 Apr, 14:34


ቢሮክራሲ እና ሰልጣኔ
ድርሰት: በእውቀቱ ሰዩም
ተራኪ: ሞንቴ ክሪሰቶ

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

19 Apr, 17:32


ፍቅር የተጠማሁ

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

19 Apr, 17:30


አልኖርም

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

17 Apr, 18:43


የሀረብ ሀገሯ ሴት😔😭

❤️ ግጥሞች ❤️ እና ❤️ደብዳቤወች❤️

15 Apr, 18:09


@Montecristo01