ቀን 26/6/2017
ሰላም እንዴት ናችሁ የተወደዳችሁ የማራናታ ቻናል ቤተሰቦቻችን ውድ ቅዱሳን የክርስቶስ ፀጋ በያላቹበት ይድረስ ዛሬም ምህረት ጥበቃው በዝቶልን በቀን ላይ ቀን ተጨምሮልን ዛሬን አይተናል በቤቱ ያኖረን አምላክ ይመስገን!!
ትናንት ምርጫችን እንለይ በሚል ርዕስ ተምረን ነበር እናም መልካም ነገርን መምረጥ ህይወትን መዳንን ያስገኘናል ምክንያቱም የመረጥነው ኢየሱስን ነውና ዛሬም ከዛ በመቀጠል የመረጥነውን መዳን በትጋት እንጠብቅ በሚል እንማራለን
ርዕስ:መዳናችንን በትጋት እንጠብቅ
ሮሜ 13:11 ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
በቃሉ የተነገሩ ትንቢቶች እየተፈፀሙ ነው እግዚአብሔር ወደ እኛ የእቀረበ ነው እናም የመዳናችንን ፍፃሜ በትጋት መፈፀም አለብን ዘመኑ አልቋል በእግዚአብሔር አሰራል የመንግስቱ ፍፃሜ የተወሰነለት ጊዜ አለ እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል በዛ ሰዓት ሲመጣ እንዳያጣን ዛሬ ቀን ሳለ ለመዳናችን ዋጋ እንስጥ
በቤታችሁ አንድ የከበረ እንግዳ ሊመጣ እንደሆነ ቢነግራችሁ ምን ያክል እንደምትዘጋጁ አስቡት ያለ የሌለ ነገራቹን ፍስስ አድርጋቹ አዘጋጅታችሁ ነው ምጠብቁት አይደል ለሰው እንደዚህ ከሆናችሁ ይልቁንስ የመዳናችሁ ዋስትና የሆነ የዘላለም ህይወትን ያገኛችሁበት የልጅነት ስልጣን የሰጣችሁ ከእርሱ ጋር ልትነግሱ ውቢቷን ኢየሩሳሌምን ሊያወርሳችሁ ቃል ኪዳን የገባላችሁን አምላክስ በምን መልኩ ነው ተዘጋጅታችሁ ምጠብቁት??
ሌሎች እንደሚኖሩት እንደሚመላለሱት መመላለስ የለብንም በዋጋ ነው የተገዛነው እርሱ ሞቶ ነው እኛ ህይወትን ያገኘነው ስለዚህ መዳናችንን አጥብቀን መያዝ አለብን መዳናችንን ማቃለል የለብንም
ዕብራውያን 6:11-12 በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።
ዳተኛ መሆን ከእኛ ይራቅ በህወታቸው የእግዚአብሔርን ስም የሚያስነቅፉ ለቤተክርስቲያን ስራዎች እንቅፋት የሆኑ ሰዎች ይኖራሉ መዳናቸውን ችላ ብለው በአለማዊነት በስጋዊነት ተግባር የተጠመዱ ይኖራሉ እውነት ኢየሱስ እንደሆነ አውቀው ብርሀን በርቶላቸው ነገር ግን ያገኙትን ድንቅ መዳን ችላ ይላሉ እግዚአብሔርን በነገር ሁሉ ያዋርዳሉ ከዚህ ነገር እራሳችንን እንጠብቅ
ዕብራውያን 6:4 አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን
5 መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን
6 በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።
እናም ዛሬ በህይወታችን በኑሮአችን ላይ የሚፈታተነን ነገር ይኖራል ለመዳናችን እንቅፋት የሚሆኑ ብዙ ፈተናዎች ሊፈራረቁብን ይችላሉ ማጣት መታረዝ እስከ ሞትም የሚያደርስ ፈተና ልገጥመን ይችላል ነገር ግን የሞተልንን ክርስቶስን ብቻ እንመልከት በትዕግሥት እና በእምነት ወደ ፊት እንሂድ እንጅ ለመዳናችን እንቅፋት እንዲሆኑብን እጅ አንስጥ አንሸነፍ እንደ ወርቅ የነጠረ ክርስቲያን እንሁን እንደዛ ሲሆን ነው መዳናችንን በትጋት መጨረስ የምንችለው
የተስፋውን ቃል ለመጨረስ መዳናችንን መፈፀም አለብን በራሳችን ምኞት እና ሀሳብ ተታለን ከመንግሥቱ እንዳንጎል
ኢየሱስ ሁላችንንም ይርዳን መዳናችንን በትጋት የምንጠብቅበት ሀይል ይስጠን አሜን!!
🤷♀🤷♂በፀሎት ወጣችሁ በምስጋና ግቡ🤷♀🤷♂
🌻የእለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸
🌼ብሩህ ቀን🌼
@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
Any comments@maranathawoch
Inbox @Fasikaa