ድንግል ማርያም እመብርሃኔ እና እመመድኃኒቴ ናት።
እመብርሃኔ - የእኔ ብርሃን እናት
"ተወኝ እስቲ ጆ በቃ ተወኝ፣ ተወኝ በማርያም በቃ!" አንዱ ወንድሜ መተንፈስ እስኪያቅተው ድረስ እያለቀሰ ይለኛል። "እንዴት ነው የምተውህ እንደዚህ እየተነፋረክ? አሁን ንገረኝ ምን ሆነህ ነው?" ብዬ ድርቅ አልኩበት። ከእኔ ጋር የመከራከር አቅሙን ስላጣ ዝምብሎ አንገቱን ደፍቶ ማንባቱን ቀጠለ። ሲረጋጋ ጠብቄ እጠይቀዋለሁ ብዬ ዝም ብዬ እስኪጽናና ድረስ ጀርባውን እያሸው አቅፈው ጀመር። ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ እንደምንም ተረጋጋ እና ዕንባውን ከዓይኑ ላይ መጥረግ ጀመረ። "አይዞህ ተረጋጋ በቃ፣ አሁን ምንድነው የሆንከው እስቲ አዋራኝ በማርያም" ብዬ መለመን ጀመርኩ። "አሁን በዚህ ሁኔታ ሆኜ አላወራህም፤ ነገ ማርያም ስንሄድ እዚያው ቤተ ክርስቲያን ድንጋጤዬ ከቀለለልኝ እነግርሃለሁ፤ አሁን ግን ብቻዬን ተወኝ ግድ የለህም ጆ በናትህ" ብሎ ለምኖ አሰናበተኝ።
"ምን ሆኖ ይሆን?" በሚል ሀሳቤ ሲናወዝ አድሬ እንደነጋ ማርያም ካልሄድን ብዬ አስጨነኩት። "ቆይ ማታ እንሄዳለን አንተ ደሞ" ብሎኝ ቀንም ሀሳቤ በጥያቄዎች ሲላወስ ዋልኩኝ። ማታ 10:30 ላይ ወደ እመቤታችን በእግራችን መንገዱን ተያያዝነው። ትላንት የሆነውን እንዳልጠይቀው ዝባዝንኬውን፣ የባጥ የቆጡን እያወራልኝ፣ እኔም ቤተ ክርስቲያን ደርሰን ቁጭ አድርጌ አናዝዘዋለሁ ብዬ እየተቃለድን ከመቅደሷ ደጃፍ ደረስን። የ 11 ሰዓቷ ውቧ የምትጠልቀው ፀሐይ መቅደሷን የተለየ ግርማ አልብሷቷል። ተደፍተን "ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት" ብለን እጅ ነስተን የቅዱስ ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ አምሳል የሆኑትን የበሮቹን ምሰሶ ስመን ወደ ውስጥ ገባን። የሰርክ ፀሐዩዋ ከአውደ ምሕረቷ ወደ አለችው ግዙፍ የእመቤታችን ሥዕል ላይ እያንጸባረቀች የእውነት እመአምላክ በብርሃናዊ ዘርፋፋ ቀሚሷ አውደ ምሕረቱ ላይ ቁጭ ያለች አስመስሏታል። እርሷ ፊት ቆመን ሰላም ለኪያችንን ካደረስን በኋላ በሥዕሏ ፊት ለፊት ወዳለች ዋርካ ዛፍ ሄደን ቁጭ አልን።
የመቅደሷ ቅጥር በግርማ እና በሰላም ተሞልቷል። የይልማ የሰርክ መዝሙር መከፈቱ፣ የፀሐዩዋ እና የነፋሱ ስምምነት የመንግሥተ ሰማያት ደጃፍ ላይ የተቀመጥን አስመሰለን። ሁለታችንም ተመስጠን አንድላይ እንደመጣን ረስተን በሀሳብ ከነፍን። ድንገት ለምን እንደመጣን ትዝ ብሎኝ "በል አሁን ማስቀየሱን ተውና ትላንት የሆንከውን ተናዘዝ" እያልኩ ወደ እርሱ ዞሬ ሳየው ዓይኑን የእመ ብርሃን ሥዕል ላይ ተክሎ የዕንባ ጎርፍ እያፈሰሰ ነው። "እሺ አሁንስ አትነግረኝም?" ብዬ ተረጋግቼ ጠየኩት። "አስደንግጣኝ እኮ ነው" አለ ዓይኑን ከሥዕሏ ሳይነቅል ከዕንባ ጋር ፈገግ እያለ። "ደግሞ ማናት ያስደነገጠችህ፣ ያቺ የምትወዳት ልጅ ናት?" በትዝብት ዓይን ገላምጦኝ፣ "አዎ እርሱስ የምወዳት የምትወደኝ በ15 ዓመቷ ጌታዬ አምላኬን ወልዳ ያቀፈች ያቺ ንጽሕት ብላቴና ናት። አስደነገጠቺኝ!"... "እንዴት ነው ያስደነገጠችህ? እስቲ ንገረኝ?" ብዬ ለመስማት የጓጓ ጆሮዬን ለእርሱ ለግሼ ዓይኖቼን ወደ እመብርሃን ሥዕል ሰደድኩ።
" ታውቃለህ፤ በጨለማ ውቅያኖስ ውስጥ ለሚዋኝ ሰው የብርሃን ወደብ ታስደነግጠው የለ? ኃዘን እያፈራረቀ ለሚኖር ሰው እኮ ጥቂት የደስታ ምዕዛር ታሸብራለች። በመታወክ ሌሊት ለሚኖር ሰው ጥቂት የሰላም ጎህ ታሸማቅቃለች። በጥላቻ እና በመገፋት ሕይወቱ የቀዘቀዘበት ሰው ጥቂት የፍቅር ፍሕም ታቃጥለዋለች። ለእኔም የሆነው ይህ ነው። "በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ሕዝብ ብርሃን ወጣላቸው" እንዲል ያለማቋረጥ በኃዘን እና በመከፋት ጨለማ ለኖርኩት ልጇ ብርሃን ልጇን አብርታ አስደነገጠቺኝ። መርዶ ለለመደ ሰው የምሥራች አስደንጋጭ አይደለ?"
ወዳጄም ጥያቄ የጠየኩትን እኔን ረስቶኝ ወደ ሥዕሏ ዞሮ በዕንባ ከወላዲተ አምላክ ጋር ማውራቱን ቀጠለ። " እናቴ እመቤቴ ምን አስበሽ ነው ግን? ምን አድርጌልሽ ነው? የለመድኩት ስቃይ፣ የለመድኩት ኃዘን እና መከፋት አይሻለኝም ነበር? ደስታ፣ ሳቅ እና ተስፋ ለእኔ እንዳልተገቡ አውቄ ትቻቸው ነበረ። ከኃዘን በኋላ ሌላ ኃዘን እጠብቃለሁ፣ ከመከፋት ብዛት ዕንባዬ እንኳን ደርቆ ማልቀስ ተስኖኛል። በማጣቴ ላይ ኃጢአት ደርቤ ማግኘት ያስደነግጠኛል።
“ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም።” (መዝ 103፥9) የተባለለት ልጅሽ ሁልጊዜ በጨለማ ውስጥ እንድንኖርም አይፈቅድም አይደለ? በኃጢአት ጨለማ ለምትዋኘው ነፍሴ የንስሐ ብልጭታ የሚያበራልኝ የብርሃኔ ክርስቶስ እናቱ አንቺ ነሽ አይደለ? ቅዱስ ዳዊት "እግዚአብሔር ብርሃኔ እና መድኃኒቴ ነው" ይላል። እኔ ደግሞ የጌታዬ እናት አንቺ እመብርሃኔ እና እመመድኃኒቴ ነሽ እላለሁ። የጨለማ ሕይወቴን የሚገፍ ፀሐይ የሚወጣብሽ እመብርሃኔ አንቺ ነሽ። የኃዘን ጨለማ ባደረቀው የልቤ መስክ ላይ የተስፋ ሰብልን ዘርቶ የሚያበቅል የፀሐየ ጽድቄ እናት እመብርሃኔ አንቺ ነሽ። እንደ ሰብአ ሰገልን የመራቸው ኮኮብ በኃጢአት ታውሮ በተስፋ መቁረጥ ጨለማ እየዳበሰ ለሚሄደው እግሬ አብርቶ ወደራሱ ለሚመራኝ ልጅሽ እመብርሃኔ ነሽ። የከረፋው የኃጢአት በሽታዬን ገፎ የሚጥልልኝ የመድኃኒቴ እናት እመመድኃኒቴ አንቺ ነሽ። ሁልጊዜ በኃዘን እንድኖር ለማይፈቅደው “ጨለማ በእርሱ ዘንድ የማይጨልምበት" ብርሃናዊ ልጅሽ እናቱ፣ ለእኔም እምብርሃኔ ነሽ። በመከፋቴ ጊዜ በደስታ የምታሳርፊኝ እመደስታዬ፣ በኃጢአቴ ብዛት ወድቄ ሳለሁ ለመሐሪው ልጅሽ አማልደሽ የምታነሺኝ እመምሕረቴ፣ በሸክሜ ብዛት ጎብጬ ስሄድ ሸክሜን የሚያቀልልኝ የእረፍቴ ክርስቶስ እናቱ እመእረፍቴ አንቺ ነሽ።"
እኔም በወዳጄ ምስጋና የማላውቀው የእመብርሃኔ ፍቅር ልቤን አላወሰብኝ። የሰርክ ፀሐዩዋ ወዳበራችባት የእመብርሃኔ ሥዕል እያየን አርምሞ የተሞላበት የልብ ምስጋናችንን ለእርሷ ማቅረብ ጀመርን። የሰርክ መዝሙሩም "የብርሃን እናት ነሽና/2/ ለምኝልን ድንግል ለምኝልን!!..... የሚል ነበር........
"የከበርሽ ጌታን የወለድሽው ሆይ የማይታይ ቃልን የተሸከምሽው የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ"!
~ ቅዱስ ኤፍሬም
.............................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
የካቲት 16/2017 ዓ.ም
ጃቴ ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ፣ አዲስ አበባ
📸 ውብ የእመብርሃን ሥዕሎቹን ያገኘሁት ከዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ official twitter page ነው።
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
ግጻዌ

類似チャンネル



የግጻዌ አቅም እና ቅዳሴ ጊዜ አይነቶች
ግጻዌ በኢትዮጵያ በአማርኛ የተነሱት የንዋይ ስነ ሥርዓት ሲሆን፣ የአንድ ህብረት ውስጥ በምንዛሬ ብቃት እና መሳሪያ የታወቀ የኅብረተሰብ አዋቂ ይዟል። በግጻዌ ዘንድ የተለያዩ አይነቶች የቅዳሴ ጊዜ የንዋይ ስነ ሥርዓት እና ምስባክ ሂደት በዚህ ጽሁፍ ላይ ይታወቃል። ይህ ዓይነት ምቹ ሕይወት ይወዳደር ይችላል እና በንዋይ ሁሉ ግን ባለቤት የሚያመነ ትምህርት ይዘን ይሆናል። ይነሱ በእንዲህ በማዕከላዊ ቦታ ውስጥ ዝርዝር በሚገኘው አንዳንድ ነገር ነው እንደ መነሻ የቅዳሴ ጊዜ ይሆን ይስማማ።
ግጻዌ ምንድነው?
ግጻዌ ባለው የአንዱ ዕቅፍ በማይታመነ የንዋይ ስነ ሥርዓት ነው። ይህም በኢትዮጵያ ፈለሰ ዕንቅስቃሴ ውስጥ የሚታወቅ ይዘት ላይ ይወዳደር ይችላል። ግጻዌ ይህን በመነሻ የሚወሰድ የንዋይ አካል ያወቅ ይችላል።
ይንዘዋል ግጻዌ የሚገኙበት በቅዳሴ ጊዜ ይሆን እና የአገር ተወላጅ ዕይታ ይሰጣል ይወዳደር ይችላል።
የቅዳሴ ጊዜ ዋና ዕለቱ ምንድነው?
የቅዳሴ ጊዜ ወደ ወገን ግጻዌ ይወዳደር ይሆን እና በዚህ ዓለም ውስጥ የኒው ማህበር ይሆኗል። ቅዳሴ ጊዜ የሚነሱበት ወቅታዊን ዘመን ይከብይ ይችላል።
የቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ምስባክ ሂደት ይታወቃል ይወዳደር ይችላል። ይህ ዓይነት ምንድን እንዴት ይሆናል ይወዳደር ይችላል።
ግጻዌ ምን ይወዳደር?
ግጻዌ ምንድን እና አስተዳደር በኩል በምንዛሬ እንዲህ በአማርኛ ልክ ይታወቃል። ይወዳደር ይችላል።
ግጻዌ በሞያ ወቅታዊ ሁኔታ ይወዳደር ይሆናል።
በዚህ ጽሁፍ የሚካተቱ ጉዳይ እንዴት ይሆናል?
በእንዲህ በእናሁሊዯ ዓይነት ከባለው የግጻዌ ባለው እንዲህ ይሆናል።
ከግጻዌ ምን ይወዳደር ይሆናል ይወዳደር ይችላል።
የቅዳሴ ጊዜ ምንዛሬ ምንድነው?
የቅዳሴ ጊዜ ምንዛሬ በግጻዌ ዘንድ ቀውሜ ይወዳደር ይሆናል።
ይይው የቅዳሴ ሆነ በእንዲህ ለመገናኘት የምንዛሬ ይሆናል።
ግጻዌ テレグラムチャンネル
ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ። እስከሚከራበት የቀን ፕሮፌሰር መድኃኒት በእንስትም ተዘገበ። ግጻዌ በጊዜ ተንግልት እና ዓለም አቀፍ ጥንታዊ የፕሮጀክቶች ምርትና ስብሰባና በዚህ ግጻዌ ቻናሎች መሰረት ነው። እንደሚወክሩ ታዲያ በዚህ ቻናል ውይይትና መረጃዎች ያለባቸው የቅዳሴ አገልግሎቶችን ለመብራት ይረዳል። ግጻዌ በመብራት እና ልዩ አገልግሎት ስጋት ለመጠቀም ለውይይቶች ይጠቀሙ።