Latest Posts from ETV NEWS (@etv_zena_official) on Telegram

ETV NEWS Telegram Posts

ETV NEWS
Ethiopian Broadcasting Corporation | Etv
1,966 Subscribers
16 Photos
1 Videos
Last Updated 26.02.2025 09:57

The latest content shared by ETV NEWS on Telegram


የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ እስካልወጣ ድረስ ህወሓት ትጥቅ እንደማይፈታ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ!

የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ እስካልወጣ ድረስ ህወሓት ትጥቅ እንደማይፈታ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።በደቡብ አፍሪካ እና በኬንያ ከተደረገው ስምምነት በኋላ “የኤርትራ ሰራዊት ንብረት እየዘረፈ፣ እያወደመ እና ንጹሃን ዜጎች እየገደለ” እንደሆነ የገለጹት አቶ ጌታቸው፣ የተደረሰው ስምምነት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውጪ ያሉት የውጭ ሃይሎች እንዲወጡ የሚያስገድድ ነው ብለዋል።

“ከጅምሩም የህዝባችን ደህንነት ለማስጠበቅ ነው ስንዋጋ ይነበርነው” ያሉት አቶ ጌታቸው “ህዝባችን በአንድም በሌላም መንገድ ደህንነቱ ከተጠበቀ ከባድ መሳርያዎች እና ታንኮች ተሸክመን የምንቀጥልበት ምክንያት የለንም”ብሏል።በስምምነቱ መሰረት ለ6 ሚልዮን ዜጎች የሚደርስ ሰብአዊ እርዳታ እየጠበቁ መሆናቸውንም አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል።

[Addis Zeybe]

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አዛዦች ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ‼️

በናይሮቢ ሳምንት ያህል የፈጀውን ውይይት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አዛዦች ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

አሁን የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ለሰብአዊ ርዳታ "ያልተገደበ እንቅስቃሴን ለማመቻቸት" መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮአቸው ተመለሱ‼️

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መንግሥት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮአቸው ተመልሰዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከውጊያ ኮማንድ ፖስት ወደ መደበኛ ማዘዣ ቢሮአቸው ከተመለሱ በኋላም በመንግሥት እና በህወሓት በተደረገው ስምምነት መሠረት በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#AddisAbaba

አዲስ አበባን የሚወክል መለያ ሎጎ ይፋ በዛሬው  ዕለት ይፋ መደረጉን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል። መሪ ቃሉም #አፍሪቃዊቷ_መልኀቅ (The Vibrant of Africa) በሚል ቀርቧል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል‼️

ይህንን ሲያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የእርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ እየሠራ ይገኛል።

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ ነው።

ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ ይሆናል።

አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል።

በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር አድርጎ ይወስደዋል።

በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ‼️

በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓም 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና  መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ  በሁለት ዙር ሲሰጥ በነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ከ 900ሺህ በላይ ተማሪዎች በ130 የፈተና ጣቢያዎች መፈተናቸው ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፈተናው  በመጀመሪያዉ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት ካጋጠሙና በመጀመሪያዉ ዙር ማጠቃለያ ከተገለጹ  ችግሮች ዉጪ በታቀደው መሰረት  በስኬት መጠናቀቁን ገልጾ፤  የሁለተኛ  ዙር ተፈታኞችም ከዛሬ ጀምሮ ወደ አካባቢያቸው መመለስ መጀመራቸውን አስታውቋል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ የነበሩትን የወ/ሮ ሀቢባ ዑመርን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።

የግለሰቧ ያለመከሰስ መብት የተነሳው በክ/ከተማው በአርሶ አደርና አርሶአደር ልጅ ሰበብ በተፈፀመ የመሬት ምዝበራ ወንጀል ተጠርጥረው በመሆኑ ነው።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ
********************************

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን መኪና ዛሬ ተረክቧል።

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ብቸኛው የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱን ተከትሎ ከመንግስት የመኪና ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል።

ሽልማቱ በተለያየ ምክንያት ለሰለሞን እንዳልተሰጠው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን የመኪና ሽልማቱን ተረክቧል።

ጠፈርተኛ ነኝ ወደ ምድር የምመጣበትን ገንዘብ ከላክሽልኝ አገባሻለሁ በማለት 30ሺ ዶላር የተጭበረበረችዉ ጃፓናዊት መነጋገሪያ ሆናለች

በጃፓን ሺጋ ግዛት ነዋሪ የሆነች የ65 ዓመቷ ሴት አንድ ሩሲያዊ የጠፈር ተመራማሪ ነኝ ከሚል ሰው ጋር በፍቅር ወድቃ ከአለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ወደ ምድር እንዲመለስ 30,000 ዶላር መላኳ ተሰምቷል፡፡ ፍቅረኛሞቹ የተዋወቁት በማህበራዊ ድህረ ገጽ አማካይነት ሲሆን ይህንኑ "የጠፈር ተጓዥ" በጣም እንደወደደች ትናገራለች፡፡

የጽሑፍ መልእክት መላላክ እንጀመሩ ብዙም ሳይቆይ ሰውየው ፍቅሩን በመግለጽ ወደ ጃፓን በመምጣት እንደሚያገባት ቃል ይገባላታል። ነገር ግን አንድ ችግር እንዳለበት ይነግራታል፡፡ በአለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ተሳፍሮ ወደ ምድር ለመመለስ አቅም እንደሌለዉ ይገልጽላታል፡፡

ጠፈርተኛ እንደሆነ በሚያሳዩ ፎቶዎች እና በንግግራቸዉ በፍቅር የተማረከችዉ ይህችዉ ጃፓናዊት ሴት ለራሺያዊዉ ፍቅረኛዋ ወደ ምድር መምጫ ሮኬት እና በጃፓን ለማረፊያ ክፍያ በሚል ገንዘብ ትልከለታለች፡፡በአምስት የተለያዩ አጋጣሚዎች በድምሩ 4.4 ሚሊዮን ዶላር ወይም 30,000 ዶላር ትልክለታለች፡፡ነገር ግን ይህዉ ፍቅረኛዋ የዉሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል፡፡

Via ዳጉ ጆርናል

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆና እንድትቀጥል በትኩረት ይሰራል- ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ
***************************************

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆና እንድትቀጥል በትኩረት እንደሚሰራፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር በምጣኔ ሀብቱ ዘርፍ የተስተዋሉ ስኬቶችን እና ችግሮችን አንስተዋል፡፡

ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በሐዋላና እና በመሳሰሉ መንገዶች የሚላከው የውጭ ምንዛሬ በአማካይ 10 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን በዚህም ባሰለፍነው የበጀት ዓመት በዘርፉ ከ5.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

ይህም በ2013 ዓ.ም ከተመዘገበው 4.9 ቢሊዮን ዶላር በ14 ነጥብ 5 በመቶ በማደግ ባለፉት 10 ዓመታት ተደርሶበት የማይታወቀውን መጠን ማግኘት መቻሉን ነው ያለከቱት።

የፌደራል ታክሲ ገቢ ባለፉት አራት ዓመታት የተሻለ እድገት ያስመዘገበ ሲሆን በ2014 ዓ.ም የነበረው 93.5 በመቶ አፈፃፀም አስመዝገቧል።

በሀገራችን እያደገ የመጣው የህዝብ ብዛት መሰረት በማድረግ መንግስት ለዜጎች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልጸዋል።