Ethiopia 24 @ethiopia_24 Channel on Telegram

Ethiopia 24

@ethiopia_24


Ethiopia 24 (English)

Are you looking for the latest news, updates, and information about Ethiopia? Look no further than Ethiopia 24 - your one-stop destination for all things related to this beautiful country in the Horn of Africa. As the name suggests, Ethiopia 24 brings you news 24 hours a day, 7 days a week, ensuring that you never miss out on important developments. From politics to culture, sports to entertainment, Ethiopia 24 covers it all, providing you with comprehensive coverage of all aspects of Ethiopian life. Whether you are a resident of Ethiopia, a diaspora member, or simply someone interested in learning more about this fascinating country, Ethiopia 24 has something for everyone. Join us today and stay informed about everything happening in Ethiopia and beyond!

Ethiopia 24

09 Jan, 15:37


Maths Mid Exam

https://youtu.be/41OdE4YVkYg

Ethiopia 24

07 Jan, 16:07


የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንድታጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

አገልግሎቱ የ2017 ዓ.ም ፈተናዎች ይዘትን በተመለከተ ባስተላለፈው መልዕክት፤ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ 9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው ሊዘጋጁ እንደሚገባ አገልግሎቱ ጠቁሟል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24

Ethiopia 24

07 Jan, 06:08


Logic Mid Exam

https://youtu.be/opzW730_Jqk

Ethiopia 24

29 Dec, 18:26


Communicative English Mid Exam Questions 👇

https://youtu.be/sTUoY86xS8Q

Ethiopia 24

15 Dec, 18:55


Physics mid exam
Questions with Answers

https://youtu.be/TRjxZ1OpqkA

Ethiopia 24

13 Dec, 16:11


#MealMenu   ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል

ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ያስተላለፈው የተማሪዎች የምግብ ሜኑ መግለጫ

<በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሸፍን ባለመቻሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ጥናት በማካሄድ በጀቱ እንዲሻሻል ለመንግስት ጥያቄ በማቅረብ የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ በጀት ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በቁጥር መከ/0-721/1 በቀን 25/03/2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አሳውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ሚኒስቴር መስሪ ቤታችን ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት 3 ገጽ አባሪ በማድረግ የላክን መሆኑን እየገለጽን ይህ የምግብ ሜኑ ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል ያለበት መሆኑን አሳስባለሁ፡፡> (ሚንስትር ዴኤታው)

የምግብ ሜኑውን ከምስሉ ይመልከቱ

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24

Ethiopia 24

11 Dec, 19:31


5 commen interview Questions
በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ የሚጠየቁ 5 ጥያቄዎች

https://youtu.be/ovTRja_gOHI

Ethiopia 24

27 Nov, 18:21


Entrepreneurship Chapter 1 Mid Exam Questions 👇

https://youtu.be/Mp8XEzLaj8o

Ethiopia 24

08 Nov, 18:42


የዩኒቨርሲቲዎች መግብያ በር👇

https://youtu.be/yerS2HtOCfI

Ethiopia 24

30 Oct, 18:50


አዲስ ተመርቃችሁ ስራ ለምትፈልጉ 9 ጠቃሚ ምክሮች👇
https://youtu.be/fdFQgptcKDE

Ethiopia 24

28 Oct, 15:23


የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ | General Knowledge Questions 👇
https://youtu.be/_s1VHqo9q5I

Ethiopia 24

24 Oct, 16:57


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24

Ethiopia 24

16 Oct, 04:08


#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች በፖርታል የማመልከቻ ጊዜ ሐሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ብቻ የሚከፈት መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም የዶክመንታችሁን Hard Copy በተመሳሳይ ቀን ሐሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት 6 ኪሎ በሚገኘው ሬጅስትራር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 እንድታስገቡ ተብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24

Ethiopia 24

14 Oct, 04:06


የዩኒቨርሲቲዎች መግብያ በር👇

https://youtu.be/yerS2HtOCfI

Ethiopia 24

10 Oct, 14:39


#ተራዝሟል ይሁን እንጂ "አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻቸውን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ መሙላት በመቸገራቸው" የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫ መሙያ ጊዜው እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24

Ethiopia 24

09 Oct, 10:02


#Remedial_Program #መቁረጫ_ነጥብ #ምደባ
በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

#placement  በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24

Ethiopia 24

30 Sep, 06:13


የመውጫ ፈተና ለወደቁ ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ተገለጿል።

የመውጫ ፈተና ወድቀው በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች፣ ትምህርት ሚኒስቴር ዘንድሮው መፍትሔ እንደሚያስቀምጥ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የመውጫ ፈተና ወድቀው በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች የተማሩትን የሚገልፅ ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።

የመውጫ ፈተና የወደቀ ተማሪ እንዴት ዓይነት ቴምፖራሪ እንደሚሰጠው እና ሥራ እየሠራ እንደገና መፈተን እንዲችል ሁኔታዎች ይመቻቻል ብለዋል።

Ethiopia 24

Ethiopia 24

28 Sep, 08:55


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻ ግዜን እስከ መስከረም 25/2017 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

ለ GAT ፈተና ለማመልከት 👇
https://youtu.be/ySKPc452sak

Ethiopia 24

26 Sep, 06:48


የ 2017 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት 4

@ethiopia_24

Ethiopia 24

18 Sep, 16:52


የ 2017 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት 3

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24