በሚቀጥለው ዓመት ትምህርት ቤት ከሚመዘገቡ ዕድሜያቸው መታወቂያ ለማውጣት የደረሱ ተማሪዎች ከልደት ካርድ ውጭ የፋይዳ መታወቂያ እንደሚጠየቁ ሰምተናል።
የሲቪል ምዝገባ እና አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ተከትሎ በሚቀጥለው አመት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኤጀንሲው ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ገልፀዋል።
ኤጀንሲው ከአገልግሎቱ ጋር መስራት ከጀመረበት 2 ወር ጊዜ አንስቶ በአዲስ አበባ 1.8 ሚሊየን የሚሆኑ ነዋሪዎች የፋይዳ መታወቂያ መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።
ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን የምዝገባው ሂደት የሚከናወን ሲሆን፤ 40 በመቶ የሚሆነው ምዝገባ በኤጀንሲው መከናወኑን ገልፀዋል።
የተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን ከመንግስት ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ ወደ ግል ትምህርት ቤቶች ለማስፋፋት ዕቅድ መያዙንም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
በሚቀጥለው 6 ወራት ጊዜ ውስጥ የነዋሪነት መታወቂያ የሆነ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የያዘ፣ የመንጃ ፍቃድ ቁጥር ያለው እንዲሁም እንደ ኤቲ ኤም ካርድ የሚያገለግል ሁሉንም በአንድ የያዘ ስማርት ካርድ ወደ ስራ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ETHIO FM 107.8
ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
https://t.me/Ethio_educations