Neueste Beiträge von Etege Menen Boarding School (@emgbss) auf Telegram

Etege Menen Boarding School Telegram-Beiträge

Etege Menen Boarding School
2,657 Abonnenten
376 Fotos
4 Videos
Zuletzt aktualisiert 25.02.2025 23:52

Der neueste Inhalt, der von Etege Menen Boarding School auf Telegram geteilt wurde.


THE TEACHING OF THE DONKEY

(worth reading)

One day a farmer’s donkey fell into a well. The animal cried loudly for hours, while the farmer tried to find something to do to get him out.

Finally, the farmer decided that the donkey was old and the well was already dry and needed to be covered anyway; that it really wasn't worth pulling the donkey out of the well..

He invited all his neighbors to come help him. They each grabbed a shovel and began to throw dirt into the well.

The donkey realized what was happening and cried horribly loud. Then, to everyone's surprise, he quieted down after a few shovelfuls of dirt.

The farmer finally looked down into the well and was amazed at what he saw... with each shovelful of dirt, the donkey was doing something incredible: It was shaking off the dirt and stepping on top of the dirt.

Very soon everyone saw surprised how the donkey reached the mouth of the well, went over the edge and trotted out...

Life is going to throw dirt at you, all kinds of dirt... the trick to getting out of the hole is to shake it off and use it to step up. Each of our problems is a step up. We can get out of the deepest holes if we don't give up...

Use the land they throw you to get ahead!!!

Remember the 5 rules to be happy:

1. Free your heart from hate.

2. Free your Mind of distractions.

3. Simplify your life.

4. Give more and expect less.

5. Love more and... shake the dirt, because in this life you have to be a solution, not the problem!

ወቅታዊ ጉንፋንና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመምን አሰመልክቶ የተሰጠ መግለጫ‼️

የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮንና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ሙከስ መምብሬን” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል። ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣ ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ2003 ዓ ም ጀምሮ የእንፍሉዌንዛ እና መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እየተሰራ ይገኛል። ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል1፡፡ በተጨማሪም የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን ከምንከላከልባቸው መንገዶች መካከልም የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግና በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት እና የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል የሚቻል መሆኑን እያስታወስን ሕብረተሰቡ ሊከተላቸው የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ እና መረጃዎችን በየጊዜው የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

መስማት ለተሳናቸው የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

(ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም) በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤትን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፤

👉 የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ  192

👉 የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና በላይ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

for 2017 EC Freshman Students