🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸 @doctorethiopia Channel on Telegram

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

@doctorethiopia


√ Help us by Sharing our posts to your friends & relatives
√ Contact admin @Drethiopiafam

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸 (English)

Are you interested in learning more about health and wellness practices in Ethiopia? Look no further than Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸 Telegram channel! This channel is dedicated to providing valuable information on various health topics specifically tailored to the Ethiopian community. From traditional remedies to modern medical practices, Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ covers it all. Join our community and help us by sharing our posts with your friends and relatives. We believe that sharing knowledge is key to promoting better health outcomes for everyone. You can also reach out to our admin @Drethiopiafam for any questions or inquiries. Stay informed, stay healthy with Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸 on Telegram!

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

28 Apr, 06:29


Nelson Textbook 22nd Edition
Volume I and II
!!!

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

13 Mar, 18:59


KDIGO 2024 Clinical Practice Guideline for the Evaluation and Management of Chronic Kidney Disease

https://t.me/ClinicalPharmGuideline

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

11 Mar, 15:34


Tinea capitis -ቆረቆር /የራስ ቅል ፈንገስ ኢንፌክሽን
👉 Join Here

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

11 Mar, 13:51


ቆሮቆር/Tinea capitis

መግቢያ
• ቆሮቆር በራስ ቅል ቆዳ በሚገኙ የጸጉር እንቡጦች ላይ የሚከሰት የፈንገስ ኢንፌክሽን ነው።
Join Here

ስርጭት
• እድሜቸው ከ 3-14 አመት ክልል ውስጥ ባሉ ህጻናት ላይ በብዛት ይከሰታል።
• አዋቂዎች ላይ የተለመደ ባይሆንም ከበሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ ሊከሰት ይችላል።
      
መተላለፊያ መንገድ
• ከሰው ወደ ሰው
• በአብዛኛውን ፈንገሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ
• በተበከሉ እቃዎች (ማበጠሪያ ፣ ኮፍያ ፣ ፎጣ ፣ የጸጉር መቁረጫ ማሽን...)
• ከእንስሳት ወደ ሰው
• ፈንገሱ ካለባቸው እንስሳት ጋር በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ
       
ምልክቶች
• በአብዛኛው ህመም ወይም ማሳከክ የሌለው
• በራስ ቅል አንድ ቦታ ላይ ወይም የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተበታተኑ ቅርፊቶች/ብናኞች
• የፀጉር መመለጥ
• መግል የያዙ እብጠቶች
• አንገት አካባቢ የሚገኙ እጢዎች መቆጣት (ንፍፊት)
• የፊት ወይም የሌላ አካል ክፍል ላይ የሚወጡ ሽፍታዎች 
ምርመራ
• በአብዛኛው በአካል ምርመራ ይታወቃል
• አጠራጣሪ ሁኔታዎች ካሉ ህመሙ ከተከሰተበት ቦታ ላይ ናሙና በመውሰድ የፈንገስ ምርመራ

ህክምና
• የሚዋጥ መድኃኒት
• ፈንገሱ በታችኛው የቆዳ ክፍል ላይ በሚገኙ የጸጉር እንቡጦች/ስር ላይ ስለሚከሰት የሚቀቡ መድኃኒቶች ውጤታማ አይደሉም።
• በመሆኑም አፍ በሚወሰዱ ፀረ-ፈንገስ መድሀኒቶች ነው መታከም ያለበት።
• እነዚህም መድሀኒቶች በልጆቹ እድሜ ወይም የሰውነት ክብደት መሰረት ይሰጣቸዋል
• የሚዋጡ መድኃኒቶች አይነት
• ግሪስሆፉልፊን
• ተርቢናፊን
• ፍሉኮናዞል

• አጋዥ ህክምና
• ጸረ-ፈንገስ ሻምፖዎች (2% ኬቶኮናዞል ሻምፖ) 
• እንደ ማበጠሪያ ፣ ኮፍያ ፣ ሻሽ የመሳሰሉ ከራስ ቅል ቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው መጠቀሚያዎች በፈላ ውሀ መታጠብ/በጸረ-ተህዋሲያን ኬሚካል መጽዳት ይኖርባቸዋል  እንዲሁም ህመሙ ካለባቸው ጋር በጋራ አለመጠቀም።
• ሌሎች የቆዳ ክፍሎች ላይ የሚወጡ የፈንገስ ህመሞች (ጭርት ፣ ጮቅ/Tinea pedis ፣ ጥፍረ-መጥምጥ) ለቆሮቆር መንስኤ ሊሆኑ ስለሚችሉ እነዚህ ህመሞች ያሉባቸው የቤተሰብ አባላት ህክምና መውሰድ ይኖርባቸዋል
👉 Join Here

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

02 Mar, 13:20


👉 ቻናሉን ይቀላቀሉ @Doctorethiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

02 Mar, 13:18


የቆዳ አስም (Atopic dermatitis, Atopic eczema)

መግቢያ
የቆዳ አስም በቆዳ ላይ የሚከሰት መቆጣት ወይም  መብገን ነው::

የጤነኛ ቆዳ ቁልፍ ተግባራትን
1. በመጀመርያ ደረጃ ኢንፌክሽን መከላከል
2. ከውጪ የሚመጡ ባእድ ነገሮችን ወደ ሰውነታችን እንዳይገቡ መከላከል
3. ዉሃ ከሰውነት በብዛት እንዳይወጣ በማድረግ የሠውነት እርጥበትና ወዘናን መጠበቅ

ለቆዳ አስም  አጋላጭ ሁኔታዎች
1. ከዘረመል ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ተጋላጭነት
2. አካባቢያዊ ተጋላጭነት (ውርጭ፣ ብርድ፣ ብናኝ)
3. የቆዳ ላይ ባክቴሪያ መራባት

ተያያዥ በሽታዎች
1. የሳንባ አስም
2. ሳይንሳይተስ
3. የአፍንጫ አለርጂ
4. የምግብ አለርጂ

ስርጭት

አለም አቀፍ
• የቆዳ አስም በሁሉም ሃገራት፣ የቆዳ አይነቶች፣  የኑሮ ደረጃ የሚከሰት ነው
• ከ15-20% (ከመቶ  ከ15-20 የሚደርሱ) ህፃናት ላይ ይከሰታል።

ኢትዮጵያ
• የበሽታውን ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አገርአቀፍ ጥናት ባይኖርም በሽታው በሁሉም የጤና ተቋማት ላይ ከሚታዩ የቆዳ በሽታዎች መካከል ዋንኛው ነዉ።

ፆታ
• አይለይም

እድሜ
• አብዛኛውን ጊዜ በመጀመሪያው አንድ አመት እድሜ ውስጥ ይጀምራል።

ምልክቶች
• ማሣከክ
• የቆዳ መቅላት
• የቆዳ መቁሰልና ውሀ መቋጠር
• የቆዳ ድርቀት
• የቆዳ መሰነጣጠቅ
• የቆዳ መሻከር
• ሽፍታዎች
• አጓጎት

እድሜያቸው እስከ 2 አመት ላይ ያሉ ህፃናት
• በጭንቅላት ቆዳ ላይ
• በፊታቸው ላይ
• በአይበሉባቸው በኩል ባለ ክርናቸው ላይ

እድሜያቸው እስከ 2 እስከ 12 አመት ላይ ያሉ ልጆች

• ክንዳቸው መታጠፊያ ላይ
• ጉልበት መታጠፊያ ላይ
• ከንፈር ላይ
• አንገት ላይ

እድሜያቸው ከ 12 አመት በላይ ያሉ አዋቂዎቹ 
• ክንዳቸው መታጠፊያ ላይ
• ጉልበት መታጠፊያ ላይ
• የጡት ጫፍ ላይ
• የአይን ክዳን ዙርያ
• የእጅ መዳፍ ላይ
• አንገት ላይ
• የጣት ጫፍ ላይ

በአግባቡ ካልታከመ ሊያስከትል የሚችሉ መዘዞች
• በማሳከኩ የተነሳ ለከፍተኛ የእንቅልፍ ችግር፣ ጭንቀትና በራስ የመተማመን ችግር
• የቆዳ ላይ ወይም የውስጥ ባክቴሪያ፣ ቫይረስ፣ ፈንገስ ኢንፌክሽን
• የአይን መቆጣት
• ለተባይና ኬሚካል አለርጂ መጋለጥ

ምርመራ
• የቆዳ አስም ታካሚው በሚሰጠው ታሪክ እና ሐኪሙ በእይታ በመለየት ማወቅ ይቻላል። እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምርመራዎች ሊታዘዙ ይችላል።

ህክምና

ምክር አገልግሎት/ትምህርት
በቆዳ አስም የሚጠቁ ሰዎች ስለ በሽታው ምንነት፣ እንዳይባባስ ማድረጊያ ዘዴዎች እና የስነልቦና እገዛ በቂ ጊዜ ወስደው ከሐኪሙ በቃል፣ በፅሁፍ ወይም በኢንተርኔት መረጃ ማግኘት አለባቸው
• ይህ የቆዳ ህመም በቀላሉ የማይድንና ሄድ መጣ የሚል ዘላቂ ህመም መሆኑን ሊረዱት ይገባል።
• በሽታው ለስንት አመት እንደሚቆይ በትክክል መተንበይ ቢያዳግትም አብዛኞቹ በጉርምስና እድሜ ይሻሻላል።

እጥበት
• ገላቸውን በየቀኑ አለማጠብ
• በሳምንት 1 ወይም 2 ቀን መታጠብ
• በረኪና (በክዳኑ ያህል ተመጥኖ) በ 5 ሊትር ውሃ ውሰጥ ጨምሮ ማጠብ የባክቴሪያ መጠን እንዲቀንስ ይረዳል

ሳሙና
• ደረቅ (የልብስ፣ አጃክስ) ሳሙናዎችን አለመጠቀም
• የሚያለሰልሱ ሳሙናዎችን  መጠቀም

ቅባቶች
• የቆዳ ድርቀትን ለመከላከል በየእለቱ ፓራፊን ወይም  ቫስሊን የወይራ ዘይት ሙሉ ሰውነታቸውን መቀባት

ልብስ
• ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መጠቀም
• በሚተኙበት ጊዜ ልብስ ባለመደራረብ ሙቀትን መቀነስ

ምግብ
• አንዳንድ ምግቦችን መመገብ ሁኔታውን ሊያባብሱ ይችላሉ:: እንደ እንቁላል፣የላም ወተት ፣ ለውዝ ፣ አኩሪ አተር ፣ ስንዴ የመሳሰሉት ከሚያባብሱ ነገሮች ተጠቃሾች ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ምግቦች ለልጆች እድገት ወሳኝ በመሆናቸው ወላጆች በምርመራ ካልተረጋገጠ በስተቀር  ሙሉለሙሉ ማቋረጥ የለባቸውም።

መድኃኒት
• ስቴሮይድ (በሚቀባ ወይም በሚዋጥ እድሜ፣ ስፋት፣ ማሳከኩ ያለበት ቦታ ከግምት ያስገባ) በዋናነት የቆዳ አስም ህክምና ነው።
• የባክቴሪያ ወይም የቫይረስ ኢንፌክሽን ካለ በሚቀባ ወይም በሚዋጥ መድኃኒት መታከም አለበት።

👉ቤተሰብ ይሁኑ @Doctorethiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

07 Oct, 11:41


👨‍⚕ የመገጣጠሚያ ህመም ሁሉ ሪህ አይደለም !
----------------------------------------------
በተለምዶ ሪህ የምንለው በህክምናው ዓለም Gouty arthritis የሚባለው ሲሆን ህመሙ የሚከሰተውም በሰውነታችን የUric acid ከመብዛት የተነሳ  በመገጣተሚያዎቻችን ላይ  Urate crystalls ሲለሚጠራቀሙ ነው።

አጋላጭ /ቀስቃሽ ምክንያቶች የምንላቸው

- አልኮል መጠጥ(ከወይን በስተቀር)
- ቀይ ስጋ አዘውትሮ መመገብ
- ጉዳት/trauma
- ቀዶ ጥገና
- አንዳንድ መድሃኒቶች (Hydrochlorothiazide , lastix , anti -TB esp Ethambutol , pyrazinamide)
- ኢንፌክሽን
- የባህር እንስሳት /ዕፅዋት ምርቶች/seafoods

አጋላጭ ያልሆኑ ምግቦች
     - የወተት ምርቶች
     - ቡና

የሪህ ምልክቶች እና መገለጫዎች

     -በአብዛኛው መካከለኛ የዕድሜ ክልል ላይ ያሉትን ያጠቃል
    -በአብዛኛው ወንዶችን ያጠቃል
   - ከፍተኛ ህመም እና የመገጣጠሚያ መቅላት፡ማበጥ፡ሲነካ ህመም መሰማት
  - ብዙ ጊዜ የእግራችንን አውራ ጣት ሲያጠቃ እንደ ጉልበት(ሎሚ)፡ቁርጭምጭሚት እና የእጅና የእግራችን ጣቶችን መገጣጠሚያዎችንም ያጠቃል

ህክምናው
1.ድንገተኛ ከሆነ/Acute attack
💊-Asprin
💊-prednisolone
💊-Colchicine
2. የቆየ ከሆነ/chronic attack
-አጋላጭ/ቀስቃሽ ያልናቸውን ምግቦች መተው
💊-መድሃኒት Eg:Allupurinol

@Doctorethiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

07 Oct, 11:40


ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis)

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ የብግነት በሽታ ሲሆን መገለጫውም በአንድ ጎን የሚከሰት የእጅና የእግር አንጓ ብግነት ነው ቀስ በቀስም አንጓዎችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው።

ከመገጣጠሚያ በተጨማሪ ሳንባን ፣ደምን፣ ቆዳንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ነው። በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚፈጠር ነው።

የሚያሳየው ምልክቶች
ከአምስት በላይ በአንድ ጎን ያሉ አንጓዎች ህመም
👉 የአንጓ እብጠት
👉 ጠዋት ሲነሱ ሰውነትን ማጠፍ አለመቻል
👉 የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴ መቀነስ
የድካም ስሜት
አጠቃላይ የጡንቻ ህመም
የክብደት መቀነስ

🍏 ከመገጣጠሚያ ውጪ ሲከሰት

👉 ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም
👉 የአይን እንባ መድረቅ፣ የዓይን ህመምና መቅላት
👉 ቆዳ ላይ እብጠት፣ መጥቆርና መቅላት
👉 የእግርና እጅ መደንዘዝ

🍏🍏🍎 የሚታዩ ምልክቶች🍏🍎🍏

👉 እብጠት
👉 ሲነካ ምንም
👉 የመገጣጠሚያ ጉዳት

🍏🍎🍏የሚሰጡ ምርመራዎች🍎🍏🍎

ምርመራው በአብዛኛው ከታካሚው በሚወሰደው ተረክ እና ሀኪሙ በሚያየው ምልክቶች ይለያል በተለይ ከሌሎች የአንጓ ብግነት የሚለየው የጣቶቻችን የመጨረሻውን አንጓ ባለማጥቃቱ ነው።
የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ (rheumatoid factor, anti -CCP , ESR/CRP, CBC)
ራጅ ምርመራ

🍏🍎🍏 የሚሰጡ መድኃኒቶች 🍎🍏🍎

የህመም ማስታገሻ
የሪማቶይድ መድኃኒቶች (methotrexate, chloroquine phosphate, steroid) ፈጽሞ ያለሀኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለባቸሁም ምክንያቱም የጎንዮሽ ጉዳታቸው የከፋ ስለሆነ ከዛም ባሻገር ክትትል በየጊዜው መደረግ አለበት።

🍏🍎 ሪማቶይድ አንጓ ብግነት ያለበት ሰው ምን መመገብ የለበትም 🍎🍏
👉 አልኮል መጠጣት የለበትም
👉 ቀይ ስጋ
👉 ቅባት የበዛበት ምግብ
👉 ለስላሳ
👉 የእንስሳት ተዋጽኦ ( ወተት ፣ እርጎ ፣አይብ)
👉 ጨው የበዛበት ምግብ
👉 ስንዴ ገብስ እና
👉 በፋብሪካ የተቀናበረ ምግብ መውሰድ የለበትም።
@Doctorethiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

23 Sep, 12:50


የጡት ህመም | Breast Pain

🔬🦠የጡት ህመም የሚያስከትሉ 09 ምክንያቶች

1. ሆርሞኖች

የወር አበባ ከመጀመሩ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ህመም ይሰማዎታል፧ ከጀመሩ በኋላ ያቆማል።

ይህ የሆነበት ምክንያት የወር አበባዎ ከመጀመሩ በፊት የኢስትሮጅንና ፕሮጄስትሮን መጨመር ነው።

ነፍሰ ጡር ከሆናችሁ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ የሆርሞን ምርት እየጨመረ በመምጣቱ ጡቶዎን ይታመማሉ።

ህመሙን ለመቀነስ መውሰድ ያለቦት እርምጃዎች፦
- ካፌይን ያስወግዱ
- የጨው መጠን ይቀንሱ
- ስጋራ ማጨስን መተው
- የህመም ማስታገሻ ይውሰዱ
- የወሊድ መከላከያ ክኒኖችን ወይም
የሆርሞን ምትክ ሕክምናን መቀየር
ሊረዳህ እንደሚችል ሐኪሞን ይጠየቁ።

2. የጡት ጉዳት

ይህ በአደጋ ምክንያት, ስፖርት በሚጫወቱበት ጊዜ ወይም በጡት ቀዶ ጥገና ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

ህመሙ ካልተሻሻለ ወይም ከእነዚህ ምልክቶች አንዱን ካዩ ሐኪምዎን ይምክሩ፦
- ከባድ እብጠት
- በጡት ውስጥ እብጠት ካለ
- መቅላት እና ሙቀት
- የማይጠፋ ቁስል ካለ

3. በማይደገፍ ብራ ምክንያት

ተገቢው ድጋፍ ከሌለ ጡቶችን ከደረት ግድግዳ ጋር የሚያገናኙት ጅማቶች ከመጠን በላይ ይወጠሩ እና ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሰለዚ ብራዎ ትክክለኛ ሳይዝ መሆኑን ያረጋግጡ።

4. የጡት ህመም ከደረት ግድግዳዎ የመጣ ሊሆን ይችላል

5. ጡት ማጥባት

ጡት ማጥባት አንዳንድ ጊዜ የጡት ህመም ምንጭ ሊሆን ይችላል።

- በመነካከስ ወይም በደረቁ፣ በተሰነጠቀ ቆዳ ወይም በበሽታ ምክንያት የጡት ጫፍ ህመም ይፈጠራል

- ተገቢ ባልሆነ መልኩ ጡት ማስያዝ በጡት ማጥባት ግዜ የጡት ህመም የሚያስከትሉ ናቸው።

6. የጡት ኢንፌክሽን

ጡት የሚያጠቡ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ በጡት ኢንፌክሽን ይያዛሉ። የጡት ኢንፌክሽን ካለብዎ ትኩሳት ሊኖርብዎት ይችላል። በተጨማሪም የጡት መቅላት ፤ እብጠትና ህመም ይኖራል። የጡት ኢንፌክሽን ካለቦት ዶክተር ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው።

7. የጡት ህመም የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ሊሆን ይችላል።

8. የጡት እጢ/ሲይስት ሲይስትን ለመመርመር ሐኪምዎ ማሞግራም/ አልትራሳውንድ ሊያዝሎዎ ይችላል።

9. የጡት ህመም አንዳንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

በጡት ላይ ያለው ቆዳም ሊወፍር ወይም ወደ ውስጥ ሰርጎድ ሊል ይችላል። ስለ የጡት ካንሰር ካሳሰበዎት ወዲያውኑ ዶክተርዎን ያነጋግሩ።

@Doctorethiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

14 Aug, 17:46


የእግር ሽታ ለመቀነስ👇👇
💧እግር አብዛኛውን ግዜ ሽታ የሚያመጣው ላብ ነክቶት ያልደረቀ ካልሲ ወይም ጫማ ካደረግን ነው ስለዚህ

💧አንድ ጫማ ከሁለት ቀን በላይ አከታትሎ አለማድረግ

💧ጫማችን እንዲደርቅ በትንሹ 24ሰአት ንፋስ ላይ ማቆየት

💧ካልሲ በየቀኑ መቀየር የካልሲው አይነት ኮተን ቢሆን ጥሩ ነው

💧እግራችንን በ አንቲ ባክቴሪያል ሳሙና (ላይፍ ቦይ መታጠብ)

💧ከታጠብን በኋላ እግራችንን በአግባቡ ማድረቅ

💧ጥፍራችንን መቆረጥ እና ማጽዳት

💧ጠንካራ ቦታዎችን ሞቅ ባለ ውሀ ዘፍዝፎ በእግር መፈቅፈቂያ ማስወገድ አነዚህ ቦታዎች ላብ ሲነካቸው ይሞቀሙቃሉ ለሽታም ያጋልጣሉ።
ከእነዚህ ጥንቃቄዎች አልፎ ካስቸገረ ግን የህክምና ባለሙያ ጋር ቀርበን መታየት ያስፈልጋል።
@Doctorethiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

14 Aug, 17:44


መጥፎ የእግር ጠረንን ይገላገሉ!
======
በአብዛኛዉ ጊዜ መጥፎ የእግር ሽታ የሚያመጡ ነገሮች በቀላሉ ሊታከሙ/ሊወገዱ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ላይ የእግር ሽታዉ በቀላሉ የማይጠፋና ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል የህክምና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዉ የሽታዉን መንስኤ ካረጋገጠ በኃላ አስፈላጊዉን ህክምና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

መጥፎ የእግር ጠረን መንስኤዎች
--ባክቴሪያ
ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚደርሱ መጥፎ የእግር ሽታ እንዲከሰት የሚያደርጉት በስኒከር መጫሚያዎች ዉስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ናቸዉ፡፡ ባክቴሪያዎቹ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን የሚመገቡ ሲሆን እርጥበታማና ላብ እንዲከሰት የሚያደርጉ የእግር ጫማዎች ባክቴሪያዎቹን የመሳብና ምቹ መራቢያ ቦታዎች ይፈጥርላቸዋል፡፡

እነዚህ ባክቴሪያዎች ኦርጋኒክ አሲድና ሰልፈር ዉሁድ ስለሚያመርቱ እግር የተበላሸ እንቁላል ጠረን እንዲኖረዉ ያደርጋሉ፡፡

--ፈንገስ እንፌክሽን
መጥፎ የእገር ሽታ በብዛት ከሚያመጡ መንስኤዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ የፈንገስ እንፌክሽን ሲሆን ፈንገስ በተጨማሪም በእግር መርገጫ/ተረከዝ ቆዳ ላይ የመድረቅና በእግር ጣቶች መሃል የቆዳ መላላጥ እንዲመጣም ያደርጋል፡፡ይህ አትሌትስ ፉት ወይም ቲንያ ፔዲስ ይባላል፡፡ ቲንያ ፔዲስ ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚተላለፍ ሲሆን በእርጥበት አዘል አካባቢዎች ለምሳሌ የልብስ መቀየሪያ ስፍራዎች( ፈንገሱ ሌላ ያለተሸፈነ ሰዉ ቆዳ ጋር የሚገናኝበት ስፍራ) ፈንገሱ በብዛት ሊገኝ ስለሚችል መተላለፉን ሊጨምር ይችላል፡፡

የተሰነጣጠቀ የእግር ቆዳ ለፈንገሱ በቀላሉ መያዝ ምቹ እድል ሊፈጥር ይችላል፡፡

--ከመጠን በላይ ላብ( Hyperhidrosis)
የላብ እጢዎች ከመጠን ያለፈ ላብ የሚያመርቱ ከሆነ መጥፎ ጠረን እንዲከሰት ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በብብታቸዉና በእግር/እጅ መዳፍ ዉስጥ ከመጠን ያለፈ ላብ ሊያልባቸዉ ይችላል፡፡ ይህ ከመጠን ያለፈ ላብ መጥፎ የብብትና እግር ጠረን እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዳንድ ሰዎች ላይ ይህ ከመጠን ያለፈ ላብ የመሸማቀቅ ወይም የማፈር ስሜት ሊፈጥርባቸዉ ስለሚችል እራሳቸዉን ከማህበራዊ መስተጋብር ሊያገሉ ይችላሉ፡፡

--ሊደረግ የሚችል ሕክምና
የእግርን ንፅህና በአግባቡ በጠበቅ ባክቴሪያዉን ማጥፋት ይቻላል፡፡ እግርን በየቀኑ በመታጠብ፣የእግር ካልሲዎችን/ሹራቦችን ቶሎ ቶሎ በመቀየርና እንዲሁም ጫማን በመቀያየር የእግር ላይ ባክቴሪያ እድገትን መቀነስ ይቻላል፡፡

የችግሩ መንሳኤ ፈንገስ ከሆነ ፓውደር ወይም መድሃኒቶችን በመጠቀም ሊታከም ይችላል።

የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች መዳኒቶችን ሊያዙ ይችላሉ።
@Doctorerhiopia

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

02 Jul, 21:03


ከምግብ በኋላ ፈፅሞ የማይመከሩ ነገሮች

1. ሻይ አይጠጡ
ሻይ በሰውነታችን ከፍተኛ መጠን ያለው አሲድ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ አሲድም በተመገብነው ምግብ ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች እንዲጠነክሩ አልፈጭ እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡

2. አያጭሱ
ምግብ ከተመገቡ በኋላ ወዲያው ሲጋራ ማጨስ አደገኛ ነው ከምግብ በኋላ የሚያጨሱ ሰዎች በሣንባ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነወ፡፡

3. ፍራፍሬ አይመገቡ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ፍራፍሬ መመገብ አንጀታችን ወዲያውኑ በአየር እንዲወጣጠር ያደርገዋል፡፡ፍራፍሬ መብላት ከፈለጉ፤ምግብ ከመመግብዎ ከአንድ ሰአት በፊት ወይም ከተመገብዎ ከአንድ ሰአት ተኩል በኋላ ቢሆን ይመረጣል፡፡

4. ገላዎን አይታጠቡ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ወዲያውኑ ገላን መታጠብ በእግርና በጃችን አካባቢ የደም ፍሰት (ዝውውር) መጠኑ እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን በሆዳችን ያለው አካባቢ የደም ፍሰት ይቀንሰዋል፡፡በዚም ምክንያት የምግብ ስልቀጣ ይዳከማል፡፡

5. ቀዝቃዛ ውሃ አይጠጡ ከምግብ በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ከበላነው ምግብ ውሰጥ የሚገኙት ዘይት ነክ ነገሮች ወደ ጠጣርነት ይቀየራቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የምግብ መፍጨት ከመጓተቱም በላይ ወደ ጠጣርነት የቀየረውን ዘይት እና ቅባት ጨጓራ ውስጥ የሚገኝ አሲድ ጋር በማገናኘት በፍጥነት ተሰባብሮ ወደ አንጀት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡ይህም ወደ ስብነት ተቀይሮ ለካንሰር ሰበብ መጋለጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ከምግብ በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ከመጠጣት ይቆጠቡ፡፡ በምትኩ ለብ ያለ ውኃ መጠጣት የምግብ ልመት ስርአጡ የተሳካ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

6.የእግር ጉዞ አያድርጉ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ የእግር ጉውዞ ማድረግ የምግብ ስልጠቃ ሂደት በአግባቡ እንዳይከናወን ያደርገዋል፡፡

7. ወዲያውኑ አይተኙ በልተን ወዲያውኑ ከተኛን የተመገብነው ምግብ በአግባቡ አይፈጭም፡፡ ይህ ደግሞ ለጨጓራ ህመምን ለአንጀት ቁስለት ይዳርጋል፡፡

#ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያጋሩ 🙏

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

25 Jun, 16:10


ብጉር ( ACNE)

ብጉር እጅግ የተለመደ እና አብዛኞቻችንን የሚያጠቃ የቆዳ ችግር ነው። የሚከሰተውም በቆዳችን የሚመነጭ ቅባት ወይንም የሞቱ ሴሎች የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎቻችን ሲደፍኑ ነው።

በአብዛኛው በጉርምስና ጊዜ የሚመጣው ብጉር የሆርሞን መለወጥን ተከትሎ ነው።

የብጉር ምልክቶች እንደ አይነቶቻችው ይለያያሉ።

1, ቀዳዳዎቻቸው የተደፈኑ ( ነጭ የሚሆኑ ብጉሮች)

2,ቀዳዳዎቻቸው የተከፋቱ (ጥቁር ብጉሮች)

3,ቁስለት ያለው ብጉር ( የተቆጣ ብጉሮች)

4,መግል የያዙ ብጉሮች ( የባክቴርያ ኢንፌክሽን ያለው ብጉሮች)

5,ጠጣር ብጉር ( ትልቅና የህመም ስሜት ያላቸው ብጉሮች) ናቸው።

ብጉርን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

* የሆርሞኖች በሰውነታችን መለዋወጥ

*መድሃኒቶች በተለይም ሆርሞኖችን የያዙ ከሆኑ

*ቅባትነት ያላቸውን መዋቢያዎችን መጠቀም

*ጭንቀት

*የወር አበባ መምጣት ናቸው።

ለብጉር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

*እድሜ
ሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች የሚጠቁ ቢሆንም የጉርምስና እድሜ ላይ ግን በብዛት ይስተዋላል።

*በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።

*ቅባቶች
ቅባቶችን መጠቀም ይህን ሊያስከትል ይችላል።

*ጭንቀት
ጭንቀት ብጉር እንዲባባስ ስለሚያደርግ ማስወገድ ተገቢ ነው።

ብጉር እንዳይባባስ ለመቆጣጠር ምን ማድረግ እንችላለን

*ብጉር የወጣበትን ቦታ በሰሱ ማጽዳት በውሃና በሳሙና መታጠብ (በቀን ሁለት ጊዜ)።

*ቅባታማ የሆኑ የመዋቢያ ውጤቶችን መጠቀምን ያስውግዱ።

*በብጉር የተጎዳ ቆዳዎን በእጅዎ አይነካኩ።

*ከባድ የጉልበት ስራ ከሰሩ በሗላ ገላዎን እና ፊትዎን ይታጠቡ።

ብጉር ቆዳዎን እያጠቃ የሚያስቸግርዎ ከሆነ እና ከላይ በተጠቀሱት መከላከያ መንገዶች የማይሻሻል ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ብጉርን ለማከም የተዘጋጁ መድሀኒቶችን በትክክሉ መጠቀም ተገቢ ነው።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ።

ጤና ይስጥልኝ!

🩺 Doctor ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀ - ዶክተር ኢትዮጵያ 🩸

25 Jun, 16:10


ብጉር እና ህክምናው

2,138

subscribers

219

photos

27

videos