Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት) (@diresabian2011) Kanalının Son Gönderileri

Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት) Telegram Gönderileri

Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት)
Wel Come To Our School.
3,463 Abone
3,524 Fotoğraf
126 Video
Son Güncelleme 01.03.2025 04:22

Sabian Secondary School (ሳ\ሁ\ደ\ት\ቤት) tarafından Telegram'da paylaşılan en son içerikler


ከጥር 19/05/2017.ዓ.ም እስከ ጥር 23/05/2017.ዓ.ም ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የቆየው የአንደኛው ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ1ኛው ወሰነ ትምህርት የማጠቃልያ ፈተና በገጠር ና በከተማ በሚገኙ በሁሉም የግልና የመንግስት ት/ቤቶች መስጠት ተጀምሯል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን ር/መምህር እና ሱፐርቫይዘር ልማት ኋላፊ የሆኑት አቶ ሀሩን አብዱረማን በት/ቤቶቹ በመገኘት ተዘዋውረው ባያቸው የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች ፈተናው በስአቱና የፈተናን ህግና ደንብ ተከትሎ ከኩረጃ ነጻ በሆነ የፈተና ስርዓት እየተሰጠ በመሆኑ ይህ የምዘና ስርአት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አቶ ሀሩን ገልፀዋል።

ስለሆነም ፈተናው ከትላንት ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ ሲሆን ለሚቀጥሉት 4 ቀናትም የሚሰጥ ይሆናል።

ጥምቀት ነው ደስ ይበላችሁ !!!


ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ/ም የከተራ በዓል እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በሰላም አደረሳችሁ! ። በዓሉ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር በደስታ የምታሳልፉበት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!! በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንላችሁ!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የበይነ መረብ (የኦንላይን) ምዝገባ ተጠናቀቀ!!

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የምዝገባው ሂደት በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰልጣን አሊይ በመልዕክታቸው እዳስታወቁት ለአለፉት ጊዜያት ሲከናወን የነበረው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ በስኬት ተጠናቋል፡፡

ምዝገባውም አምና ታይተው የነበሩ መጠነኛ ክፍተቶችን ባረመ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የመንግስትና የግል ባለድርሻዎችን አመስግነዋል ።

ቢሮው የጀመረውን የለውጥ ስራ ከዳር ለማድረስ በተጀመረው ግለት ሁሉም በከፍተኛ ኃላፊነትና ቁርጠኝነት በመስራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትብብራችንን ማጠናከር ይኖርብናል በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
«ትጋት ለትምህርት ጥራት»

ሰላም እንዴት አመሻቹ በድጋሚ ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳቹ እያልን ፎርም የሞላቹ ተማሪዎች ነገ በ30/04/2017 በመደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜአቹ በየክፍላቹ ትፈርማላቹ :: ፎርም ያልሞሉ ተማሪዎች ነገ ጠዋት እስከ 4:00 ድረስ ይሞሉና የመፈረሚያው ስም ዝርዝር ተካተው ለከሰአት ፊርማ ይዝጋጃል:: በዚህም መሰረት ፎርም ያልሞላቹ ተማሪዎች ነገ ጠዋት የመጨረሻ በመሆኑ ላልሞሉ ተማሪዎች ይህንን መልእክት ያልሞሉ ካሉ እባካቹ ንገሩልንን በነሱ ምክንያት ነው ሰኞ የነበረው ፊርማ የቀረው :: አደራ ነገ ሁሉም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዳትቀሩ አደራ አደራ:: መልካም ምሽት!!!

ይህ ሳምንት የከሰአት ፈረቃ እንደሆናቹ አስታውሱ::

ለሳ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ለክርስትና እምነት ተከታዮች መምህራን ፤ የአስተዳደር ሰራተኞች፤ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን !! መልካም በአል!!

ፎቶ ተስተካክሎ ያለቀ

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

የ2017 ዓ.ም ፈተናዎች ይዘትን በተመለከተ ባስተላለፈው መልዕክት፤ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ 9-12ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ገልጿል።